3 months ago
የአንጋፋው ፖለቲከኛና ምሁር አቶ ሌንጮ ለታ የላቀ የክብር አገልግሎት በሽልማት ተገለጠ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አዲሱን ዘመናዊ መሠረተ ልማት በይፋ ባስመረቀበት በዚሁ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ለቀድሞው የተቋሙ ከፍተኛ መሐንዲስ፣ ታዋቂው ፖለቲከኛ፣ ጸሐፊና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ ሌንጮ ለታ ልዩ የምስጋናና የእውቅና ሽልማት ሰጥተዋል።
አቶ ሌንጮ ለታ ተቋሙ ከ1963 እስከ 1966 ዓ.ም በተመሠረተበት መጀመሪያ ዘመን ጠንካራ መሠረት ከጣሉ ቁልፍ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
ከአሜሪካ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ያገኙትን ከፍተኛ ዕውቀት በተግባር ላይ በማዋል በተቋሙ ውስጥ በከፍተኛ መሐንዲስነት ሀገራቸውን በታማኝነትና በቅንነት አገልግለዋል።
ይህ የተበረከተው ታላቅ ዕውቅና ዘላቂና ጠንካራ ተቋማዊ ግንባታ ሊረጋገጥ የሚችለው በትናንትናው ጥራት ባለው መሠረት ላይ የዛሬውን ዘመናዊ አሠራር በመገንባትና በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን በተግባር ያሳየ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
መርሐ ግብሩ ለአንጋፋው መሪና ምሁር የተገባ የክብር መግለጫ ከመሆኑም ባለፈ ለሀገር በታማኝነትና በዕውቀት ማገልገል የትውልድ ምስጋናና ክብር እንደሚያሰጥ ማሳያ ሆኖ አልፏል።
#lencholeta #ethiopianstandardsinstitute #recognitionaward #ethiopianpolitics #hornof Africa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments