3 days ago
ከታላቁ የለሚ ስሚንቶ እስከ ጎርጎራ በአማራ ክልል የተመዘገቡት ግዙፍ የኢንዱስትሪና የቱሪዝም እመርታዎች
**************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳብራሩት በለውጡ ዓመታት በአማራ ክልል ከፍተኛ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የፈጠሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል።
ከእነዚህም መካከል በኢትዮጵያ ትልቁ የሆነው የለሚ ስሚንቶ ፋብሪካ በከፍተኛ የመንግሥት ድጋፍ ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል።
ከዚህም ባሻገር በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን እና አረርቲ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተገነቡ ሲሆን፣ የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው ግዙፉ የሴራሚክ ፋብሪካ በደብረ ብርሃን መገንባቱ እንዲሁም በርካታ የዘይትና ሌሎች የግል ኢንዱስትሪዎች በስፋት መሠራታቸው ክልሉን ወደ አዲስ የኢንዱስትሪ ማዕከልነት እያሸጋገረው ይገኛል።
በቱሪዝሙ ዘርፍም ቢሆን ከዚህ ቀደም የነበረውን የመዳረሻ እና የማረፊያ ችግር በመፍታት ታሪካዊ ዐሻራዎች እየተቀመጡ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ለትውልድ የሚሻገረው የጎርጎራ ፕሮጀክት፣ በመፍረስ ላይ የነበረው የፋሲለደስ ቤተመንግሥት አስደናቂ ዕድሳት እና ከኤርፖርት እስከ ፒያሳ የተሠሩት የመሠረተ ልማት ሥራዎች የጎንደርን ውበት ይበልጥ አጉልተውታል።
ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በመተባበር የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የማደስ ሰፊ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ እጅግ ማራኪ የሆነው የሎጎ ሀይቅ ሪዞርትም የውጭ ዜጎችን ጭምር ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች እየሳበ ይገኛል።
ወደ ደባርቅ የሚወስዱ መንገዶችን ጨምሮ በቱሪዝም መሠረተ ልማት ላይ የተሠሩት እነዚህ የማይናቁ ሥራዎች የክልሉን ገጽታ በብዙ እጥፍ የቀየሩ ታላላቅ ስኬቶች ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #amhararegion #lemicement #tourismethiopia #industrialdevelopment

Comments