6 months ago
ጦርነቱ በነዳጅ ብቻ ሳይሆን በኮንዶም ዋጋ ላይ ጭምር ተጽኖ አሳድሯል ተባለ
#ethiopia | በዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች የሆነው የማሌዥያው ካሬክስ (Karex) ኩባንያ፣ በኢራን ጦርነት ሳቢያ እያጋጠመው ባለው የጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የምርት ዋጋን ለመጨመር እየተገደደ መሆኑን አስታውቋል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጎህ ሚያ ኪያት ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ የጦርነቱ መፋፋም በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ በማስተጓጎሉ፣ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ከ20% እስከ 30% የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ይችላል።
ዋነኛ ምክንያቶች፡
-ከየካቲት ወር ጀምሮ በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ለምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እጥረት አጋጥሟል።
-ምርቶች በባህር ላይ ለረጅም ጊዜ ተከማችተው መቆየታቸውና የትራንስፖርት መስመሮች መለዋወጥ ወጪውን አናርቶታል።
_ለማሸጊያና ለምርት ሂደት የሚወጡ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል።
መቀመጫውን ማሌዥያ ያደረገው ይህ ግዙፍ ኩባንያ፤ ONE, Trustex, Carex እና Pasante የተሰኙ ታዋቂ የኮንዶም ብራንዶችን የሚያመርት ሲሆን፣ በዓመት ከ5 ቢሊዮን በላይ ኮንዶሞችን ለዓለም ገበያ ያቀርባል።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ለጥቂት ወራት የሚበቃ ክምችት ቢኖረውም፣ ጦርነቱ በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ ግን የዋጋ ጭማሪው የማይቀር መሆኑን ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#karex #globaleconomy #iranwar #supplychain #businessnews #condomprice #safesex #ethiopia #newsupdate

በ40 ቀኑ ጦርነት ኢራን 145 ቢሊዮን ዶላር አጣች
#ethiopia | በኢራን፣ በአሜሪካና በእስራኤል መካከል ለ40 ቀናት የዘለቀው አስከፊ ጦርነት በኢራን ላይ ታሪክ የማይረሳው ውድመት ጥሎ አልፏል።
የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ ሀገሪቱ ከአስርተ ዓመታት በኋላ ወደማታውቀው የኢኮኖሚና የወታደራዊ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
ከ140 እስከ 145 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት ወድሟል።
የመኖሪያ ቤቶች፦ 100,000 ቤቶች ፈርሰዋል።
857 ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም 339 የህክምና ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
23,500 የንግድ ድርጅቶች በመውደማቸው ከፍተኛ የሥራ አጥነት ስጋት ተፈጥሯል።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) እንደገለጸው፣ የኢራን ሚሳይል ማምረቻዎችና ወታደራዊ መሠረቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመዋል።
በተለይ 4 ዋና ዋና የባሊስቲክ ሚሳይል ማምረቻዎች በመውደማቸው፣ ኢራን ያላትን የመከላከል አቅም ለጊዜው አጥታለች ተብሏል።
"ከዚህ ግዙፍ ውድመት ለማገገም ኢራን ረጅም ዓመታት ይፈጅባታል!" — የፖለቲካ ተንታኞች
#getu #iranwar #middleeastcrisis #economicloss #breakingnews #militaryupdate #globalpolitics #usa #israel #iran #peacetalks #ኢራን #ጦርነት #ኢኮኖሚ #መካከለኛውምስራቅ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments