20 days ago
ከጃዝ ባር ባለቤትነት እስከ ዓለም አቀፍ ተደናቂ ደራሲነት!
#ethiopia | በ1949 በቶኪዮ ጃፓን የተወለደው ሃሩኪ ሙራካሚ በስነ ጽሑፍ እና በሙዚቃ ዘርፍ ውስጥ ስማቸውን የተከሉ ስመጥር ሰው ናቸው።
ሃሩኪ የዓለማችን ታዋቂ ደራሲ እሆናለሁ ብሎ አንድም ቀን አስቦ አያውቅም ነበር።
ከዩኒቨርሲቲ ምረቃ በኋላ ከባለቤቱ ጋር በቶኪዮ ትንሽ የጃዝ ባር ከፍቶ ለዓመታት በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ቢሆንም በ1978 የቤዝቦል ጨዋታ እየተከታተለ በነበረበት ወቅት ሕይወቱን የቀየረ አዲስ አጋጣሚ ተፈጠረ።
አንድ ተጫዋች ኳሷን አርቆ ሲመታ የተመለከተው ሙራካሚ ድንገት ልብወለድ መጻፍ እንደሚችል በውስጡ ተሰማው።
ከዚያ በፊት ምንም ዓይነት ልብወለድ ጽፎ ባያውቅም በዚያው ምሽት የጽሕፈት መሳሪያዎችን በመግዛት መጽሐፉን አንድ ብሎ ጀመረ።
የመጀመሪያው መጽሐፉም ከአንድ ዓመት በኋላ ለንባብ ያበቃ ሲሆን ሙሉ ጊዜውን ለጽሕፈት ለመስጠትና ስኬታማ ደራሲ ለመሆን በሕይወቱ ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ እንዳለበት ተገነዘበ።
ሙራካሚ ከተማራቸው ከባድ የህይወት ትምህርቶች መካከል ትርጉም ያለው ስራ ለመስራት የተለየ የሕይወት ዘይቤ ለመከተል ፈቃደኛ መሆን እንደሚገባ ይናገራል።
የጃዝ ባሩን በመዝጋት ሙሉ ጊዜውን ለጽሕፈት የሰጠ ሲሆን ጠዋት ጠዋት መጽሐፉን ተያያዘው።
ሃሩኪ አንድ ብሎ የጀመረው የድርሰት ስራው አሁን ላይ አስራ ሦስት እጅግ ተወዳጅና ተደናቂ የሆኑ የድርሰት ውጤቶች ለአንባቢያን ማድረስ ችሏል።
መሮጥ ወይም ዋና መዋኘትን ያካተተ ጥብቅ የዕለት ተዕለት ልምድ በህይወቱ አዳበረ።
ሃሩኪ ስኬቱ የመጣው ስራውን ለዓመታት በተከታታይና በጽናት በመደጋገም ነበር።
ይህን ፍልስፍናውን የሚያንጸባርቀው ታዋቂ አባባሉ “ሕመም አይቀሬ ነው መሰቃየት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው” ይላል።
የሙራካሚ ሕይወት አዲስ የሕይወት ምዕራፍ አንዳንድ ጊዜ በጣም ትንሽ በሆነ ውሳኔ እንደሚጀምር አሳይቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #japan #jazzbar #book #harukimurakami #motivation

Comments