1 month ago
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ወርቃማው ጫማ
*******************
የፖርቹጋል የቡድኑ መሪ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በልምምድ ሜዳ ላይ በታየበት ሜርኩሪያል ሱፐርፍላይ 11 ወርቃማው ጫማ (Gold Scorpion) የተሰኘ ልዩ ጫማ የአድናቂዎችን ቀልብ በከፍተኛ ሁኔታ ስቧል።
ይህ ልዩ ዲዛይን የተዘጋጀው ሮናልዶ በስድስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ላይ ግብ በማስቆጠር በዓለም እግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ላስመዘገበው ድንቅ ስኬት እውቅና ለመስጠት ነው። ጫማው የፊት አጥቂውን ታሪካዊ የሙያ ጉዞ የሚዘክር እና ለስኬቱ የተበረከተ ክብር ነው።
ከኡዝቤኪስታን ጋር በነበረው ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የዓለም ዋንጫ ግቦቹን ወደ 10 ከፍ ያደረገው ሮናልዶ የኤውሴቢዮን የረዥም ጊዜ ክብረ ወሰን በመስበር የፖርቹጋል የዓለም ዋንጫ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።
ፖርቹጋል ከኮሎምቢያ ጋር የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ የምታደርግ ሲሆን የሮናልዶ ወርቃማ ጫማ እና አዲስ ታሪክ የጻፈው የግብ ማስቆጠር ብቃት በደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ተስፋን ፈጥሯል።
በሃና ምንዳሁን
#ebcsports #cr7 #portugal #worldcup2026 #goldscorpion #cristianoronaldo #footballnews #recordbreaker

Comments