7 months ago
የዓለም የነዳጅ ዋጋ የ2008ቱን ታሪካዊ ከፍተኛ የዋጋ ጣሪያ ሊሰብር እንደሚችል ተጠቆመ
#ethiopia | ታዋቂው የኢንቨስትመንት ባንክ ጎልድማን ሳክስ ባወጣው አዲስ መግለጫ፤ በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በኢራን አካባቢ እየተባባሰ የመጣው ግጭት በነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፍጠሩን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ እ.ኤ.አ በ2008 ተመዝግቦ የነበረውን ከፍተኛ ዋጋ ሊበልጥ እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ባንኩ እንዳመለከተው፥ በተለይ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ያለው የነዳጅ ዝውውር መገታት በገበያው ላይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በቅርቡ በተደረገ የንግድ ውሎ እስከ 119 ዶላር ደርሶ ነበር። ምንም እንኳን ዋጋው ረገብ ብሎ በ108.65 ዶላር ቢዘጋም የአቅርቦት እጥረቱ ስጋት ግን አሁንም ዓለም አቀፍ የዋጋ ግሽበትን እያባባሰው ይገኛል።
እንደ ጎልድማን ሳክስ ትንበያ ከሆነ፦
* መስተጓጎሉ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ እስከ 2027 ድረስ የነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ ሆኖ ሊቆይ ይችላል።
* ምንም እንኳን የነዳጅ ፍሰቱ በሚያዝያ ወር ወደ መደበኛ ሁኔታው ይመለሳል ተብሎ ቢታሰም፤ በምርት መሰረተ ልማቶች ላይ የደረሰው ጉዳት ግን ጥርጣሬን ፈጥሯል።
* የኦፔክ (OPEC) አባል ሀገራት ያሏቸው ትርፍ የማምረት አቅሞች ክፍተቱን በከፊል ሊሞሉ እንደሚችሉ ቢታመንም፤ አሁን ያለው የኃይል አቅርቦት ቀውስ ግን ከነዳጅ ገበያ ባለፈ በዓለም አቀፍ የቦንድ፣ የውጭ ምንዛሬ እና የአክሲዮን ገበያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #globalnews #fuelprice #goldmansachs #economy #oilmarket #energycrisis #internationaltrade #opec

Comments