1 month ago
በምክክር እና በምርጫ የጸናች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ
*************
ኢትዮጵያ ሁለት ታሪካዊና ወሳኝ ኩነቶችን - የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ እና 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ - በአንድ ዓመት ውስጥ በስኬት ማከናወኗ የሕዝቧን እየጎለበተ የመጣ የዴሞክራሲ ባህልና የሀገሪቱን የታላቅነት አዲስ ምዕራፍ ያበሰረ ድል ሆኗል።
ይህ ስኬት ሂደቱን በጥርጣሬ ሲከታተል የነበረው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው የጋራ ውሳኔ የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር ለማጽናት ያደረጉትን አርዓያነት ያለው ሽግግር በአድናቆት እንዲመለከተው አስችሏል።
ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ የመዋቅር ክፍተቶችና የፖለቲካ ውዝግቦችን በኃይል ለመፍታት ይደረግ የነበረውን አፍራሽ አካሄድ በዘላቂነት በመተካት፣ ዜጎች በነፃነት የሚወያዩበትና የጋራ ሀገር የሚገነቡበትን ዕድል ፈጥሯል።
ዜጎች ለሰዓታት በጽናት በመሰለፍ ድምፃቸውን በሰላም የሰጡበት 7ኛ ጠቅላላ ምርጫም በሀገራችን ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማት መገንባታቸውን እንዲሁም ግጭትና ትርምስ ምንም ተቀባይነት እንደሌለው በማረጋገጥ ለምስራቅ አፍሪካና ለመላው አህጉራችን ተግባራዊ ትምህርት የሰጠ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።
ሀገራችን ምክክርና ምርጫን አጣጥማ መሄድ መቻሏ እንደ ሕዝብ የፖለቲካ ትኩረታችንን ከዕለት ተለት ውዝግብ ወደ ረጅም ጊዜ የልማት ዕቅዶች እንድናዞር በር ከፍቷል።
ይህም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት፣ ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያችን ስኬት አዲስ ተስፋን ፈንጥቋል።
ኢትዮጵያ በምክክር ታሪካዊ ቁስሎቿን እያከመች፣ በምርጫ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ተቋማቷን እያጸናች የወደፊት ታላቅነቷን በራሷ እጅ እየጻፈች ትቀጥላለች።
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #democracy #nationaldialogue #generalelections #ebc #ebcdotstream

5 months ago
ከፍተኛ የመራጮች ቁጥር የተመዘገበበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ
********************
በኢትዮጵያ እስካሁን ከተደረጉት ስድስት ጠቅላላ ምርጫዎች በተለየ መልኩ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ 50.5 ሚሊዮን ዜጎች ይበጀናል የሚሉትን ለመምረጥ የምርጫ ካርዳቸውን ወስደዋል።
ይህ ከፍተኛ ቁጥር የህዝብን የልብ መሻት፣ የተቋማትን ጥንካሬ እና የሀገርን ቀጣይ አቅጣጫ የሚወስን ታላቅ ሁነት ከፊታችን መኖሩን ያመላከተ ነው።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሚሊዮኖች የተሳተፉበትን የ1987ቱን ጠቅላላ ምርጫ ጨምሮ ካለፉት 6 ጠቅላላ ምርጫዎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ልዩነት የታየበት ነው።
የ1992ቱ ጠቅላላ ምርጫ 21.6 ሚሊዮን ዜጎችን ያሳተፈ ሲሆን፣ ለ1997ቱ ጠቅላላ ምርጫ መንደርደሪያ የሆኑ አበይት ጉዳዮች የተስተዋሉበት ነበር።
የ1997ቱ ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ቁጥር ከ1992ቱ ጠቅላላ ምርጫ በ26 በመቶ ከፍ ያለ ነበር።
በ2002 እና በ2007 የተካሔዱት ጠቅላላ ምርጫዎችም ከፍተኛ የመራጮች ቁጥር ዕድገት የታየባቸው ሲሆኑ፣ ለ2013ቱ ጠቅላላ ምርጫ ደግሞ 38.4 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበው ነበር።
በዘመናት ውስጥ እያደገ የመጣው የመራጮች ቁጥር በዘንድሮው የ2018 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ደግሞ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት 50.5 ሚሊዮን ደርሷል።
የዘንድሮውን የመራጮች ምዝገባ ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲጂታል አማራጭ 5.5 ሚሊዮን መራጮች ለምርጫው መመዝገባቸው ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #generalelections #voterregistration #ebc

Comments