Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያችን ደርሰናል !
#ethiopia | በአዉሮፓ አለምአቀፍ ፌስቲቫል ቱርክ ትራባዞን አክሻባት አለምአቀፍ የባህል ፌስቲቫል የኢትዮጵያን ባህል፣ ኪነ-ጥበብና እሴቶች በማስተዋወቅ የባህል ዲፕሎማሲ ስራ ሲሰራ የቆየዉ የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ልዑክ ቆይታቸዉን አገባደዉ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ።

ከተለያዩ የአዉሮፓ ሀገራትና ከኢሲያ ሀገራት ሀገራቸዉን ወክለዉ የተለያዩ የልዑካን ቡድኖች በተገኙበት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትንም በዓለም አደባባይ ሲያስተዋውቁ የሰነበቱት ልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸዉ መድረሳቸውን የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ይርጋ አሳዉቀዋል ።

የኪነ ጥበብ ልዑኩ በቆይታቸው ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሥራዎች አድናቆት እና የሜዳልያ ሽልማት የተሰጣቸዉ ሲሆን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ የተደረገበት፣እሴቶቻችንና ሀብቶቻችንን ያስተዋወቅንበት መድረክ መሆኑን የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ይርጋ ገልጸዋል።

የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ከዚህ በፊት በህንድና ሩሲያ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገራት ጋር በባህልና ኪነ ጥበቡ ዘርፍ ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ የባህል ዲፕሎማሲ ስራዎችን እየፈጸመ የመጣ ሲሆን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳዉቀዋል ።

ለዚህ ጉዞ መሳካት አስተዋጽኦ ለነበራቸው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ክላስተር ፣ መሬት ቢሮ ፣ ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ባቱ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እናመሰግናለን ።

ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪካችን ነው !
Gebremaryam Yirga ገብረማርያም ይርጋ
የአብክመ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.