4 months ago
ከአካባቢ ጥበቃ ወደ ዘላቂ ገቢ፤ “የሚበላና የሚሸጥ የአረንጓዴ ዐሻራ”
****************
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከተተከሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች መካከል ለሥነ-ምህዳር ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ እና ለህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ከፍተኛ ጠቀሜታ ላላቸው ዕፅዋት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል።
የደን ሽፋንን መጨመር ትኩረቱን አድርጎ የጀመረው ይህ መርሐ ግብር ወደ የሚበላና የሚሸጥ አረንጓዴ ዐሻራ መርህ በመሸጋገር የሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የወጪ ንግድን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በቅርብ ዓመታት በተደረጉት ዘመቻዎች የአርሶ አደሩንና የከተማ ነዋሪውን ገቢ በቀጥታ ሊቀይሩ የሚችሉ፣ የ“ከተማ ግብርና” እና የ“ትውልድ ዐሻራ” አካል የሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል።
ከእነዚህም መካከል አቮካዶ ለላኪ ድርጅቶችና ለውጭ ገበያ የሚቀርብ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ የቻለ ሲሆን፣ በተለይም በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎች ላይ የተሰራው ሥራ ለአግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፉ ሰፊ የምርታማነት አቅም ፈጥሯል።
በተጨማሪም ማንጎ እና ፓፓያ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ለጭማቂ ምርትና ለቀጥታ ፍጆታ በስፋት እየዋሉ ሲሆን፣ ሙዝ፣ ብርቱካን እና ሎሚ በየጓሮው በቀላሉ የሚጸድቁና ፈጣን የገቢ ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አርሶ አደሩ ውስን ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ፋይዳ ባለው ባህር ዛፍ ላይ ለረጅም ዘመናት ጥገኛ ሆኖ የቆየ ቢሆንም፣ በተሰጠው ሰፊ የግንዛቤ ትምህርት ከባሕር ዛፍ የላቀ ጥቅም በሚሰጡ ተክሎች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ሆኗል።
በተለይም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ዛፎች በመንቀል፣ በምትካቸው የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬዎችን እንደ ሙዝ፣ እንሰት እና ጃክ ፍሩት ያሉ ተክሎችን በመተካት ረገድ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።
ባሕር ዛፍ ምንም እንኳን የውሃ ፍጆታው ጥንቃቄ የሚሻ ቢሆንም፣ ለግንባታ ማገርና ምሰሶ፣ ለቤት ማገዶ እና ለስልክ እንጨት ያለውን ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት ለማሟላት በተመረጡና ምቹ በሆኑ ቦታዎች ላይ ብቻ ተተክሏል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ አስገኝ በሆነው ቡና ላይ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአሮጌ ቡና ተክሎችን በመተካትና በአዳዲስ መሬት ላይ ምርጥ የቡና ዝርያዎችን የመትከል ስራ በሰፊው ተከናውኗል።
እነዚህ ተክሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ፍሬያማነት በመሸጋገር አመርቂ ውጤት እያስገኙ ሲሆን፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ለሻይ ልማት የሚሆኑ ችግኞች በስፋት መሰራጨታቸው የአርሶ አደሩን የገቢ አማራጭ ዘርፈ-ብዙ በማድረግ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳየ ይገኛል።
ከዚህም ባሻገር ለኢንዱስትሪ እና ለግንባታ ግብዓት የሚሆኑ የደን ዕፅዋት ልማት ላይ ሰፊ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን፣ ለአፈርና ውኃ ጥበቃ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር ለቤት መስሪያ፣ ለቤት ዕቃዎች ፋብሪካዎችና ለወረቀት ምርት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እምቅ አቅም ያለው ቀርከሃ (አረንጓዴው ወርቅ) በስፋት ተተክሏል።
እንዲሁም ግራርና የደጋ ጥድ ለከፍተኛ ጥራት ጣውላ ምርትና ለደንን መሰረት ላደረጉ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት እያገለገሉ ይገኛሉ።
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተተከሉት እንደ ሰስባኒያና ሉሲና ያሉ የመኖ እጽዋት የእንስሳት ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ የአፈርን ለምነት በተፈጥሯዊ መንገድ እያሳደጉ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ ይህ መርሃ ግብር አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ፣ የወጪ ንግድን የሚያሳድግና የህብረተሰቡን ኑሮ የሚያሻሽል እውነተኛ የኢኮኖሚ ምሶሶ ሆኗል።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ethiopianbroadcastingcorporation #greenlegacy #greeneconomy #ecofriendly #fruitexport

Comments