21 days ago
ገዳ ባንክ "ፉርቱ" የተሰኘ ያለንብረት ዋስትና አገልግሎት የሚሰጥ የዲጂታል ብድር አገልግሎት ይፋ አደረገ
ገዳ ባንክ ከኳንተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያለምንም ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይንቀሳቀስ የንብረት ዋስትና በሞባይል ስልክ ብቻ የሚሰጥ "ፉርቱ" የተሰኘ አዲስ ዲጂታል የማይክሮና አነስተኛ ብድር አገልግሎት ይፋ አድርጓል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው ይፋዊ የማስጀመር ስነ-ስርዓት ላይ፤ አገልግሎቱ አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን፣ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን፣ ሴቶችን እና በመደበኛ የባንክ አሰራር የዋስትና እጥረት ምክንያት የብድር እድል ማግኘት ያልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታልሞ የተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
የገዳ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንዴ ቡልቶ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር እና በሰጡት ማብራሪያ፤ ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ አሳታፊ እና ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ለማቅረብ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። "ፉርቱ" የተሰኘው የኦሮምኛ ቃል "መክፈቻ" ወይም "ቁልፍ" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ አገልግሎቱ በተለይም የፋይናንስ አካታችነትን ለማሻሻል እና የአነስተኛ ስራ ፈጣሪዎችን የስራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት ለመቅረፍ ትልቅ መፍትሔ እንደሚሆን አብራርተዋል።
ስርዓቱ አርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ (AI) ቴክኖሎጂን በመጠቀም ደንበኞች በባንኩ ያላቸውን የሂሳብ እንቅስቃሴ እና የተለያዩ መረጃዎችን በመተንተን ያለ ሰው ንክኪ የብድር አቅማቸውንና ብቃታቸውን በራሱ የሚወስን መሆኑ ተመላክቷል። በተጨማሪም ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የተጣመረ በመሆኑ ደንበኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ እና ባልተወሳሰበ ሂደት በሞባይል መተግበሪያቸው አማካኝነት የብድር ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ ያስችላቸዋል።
ስለብድር ወለድ እና የክፍያ ጊዜ በተሰጠው ማብራሪያ፤ እንደደንበኛው የባንክ እንቅስቃሴ እና የግብይት መጠን (Transaction) የወለድ መጠኑ እና የመክፈያ ጊዜው የሚወሰን ይሆናል። ከፍተኛ የግብይት እንቅስቃሴ ያላቸው ደንበኞች ዝቅተኛ የወለድ መጠን የሚያገኙ ሲሆን፣ የክፍያ ጊዜውም ከደንበኛው ፍላጎት አንጻር (ለምሳሌ ከአንድ ወር ጀምሮ) ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። ደንበኞች ብድሩን በትክክል ከፍለው በጨረሱ ቁጥር ከፍተኛ የብድር መጠን ማግኘት የሚያስችላቸው እድል ይከፈትላቸዋል።
ከስጋት (Risk) እና ማታለል (Fraud) ቁጥጥር ጋር ተያይዞ፣ ስርዓቱ ለረጅም ጊዜ በቴክኖሎጂ እና በደህንነት ጥናት (Security Audit) ሲፈተሽ መቆየቱ ተገልጿል። የዲጂታል መታወቂያ እና የደህንነት ማረጋገጫዎች መተግበራቸውም ፍጹም አמיናዊ እና ህጋዊ አሰራርን እንደሚያረጋግጥ ተመላክቷል።
የኳንተም ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሶፎንያስ እምቢበል በበኩላቸው፤ ቴክኖሎጂው የሰዎችን ህይወት የመቀየር እና አዳዲስ እድሎችን የመክፈት አቅም እንዳለው ገልጸዋል። «ፉርቱ» በባንኩ እና በደንበኞች መካከል ያለውን ርቀት የሚያጠበብ፣ ፍጥነት እና ቀላልነትን ያካተተ ዲጂታል ድልድይ መሆኑን አብራርተዋል።
አገልግሎቱ በተለይም አዳዲስ ጀማሪ ቢዝነሶች፣ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች፣ የመንግስት እና የግል ተቀጣሪዎች እንዲሁም ሴቶች የፋይናንስ ተዳራሽነት አግኝተው ስራቸውን የሚያስፋፉበት አዲስ እድል ይዞ መጣሉ ተጠቅሷል።

2 months ago
ud83dudea8 u1230u1260u122d - u12a0u1276 u12f3u12cau1275 u1265u122du1203u1291 u1260u1356u120au1235 u1273u1235u1228u12cd u12cbu1209 | u1260u12c8u122d 3.3 u121au120au12eeu1295 u1265u122d u12f0u1218u12c8u12dd u1208u1263u120du1293 u121au1235u1275?! u12e851 u121au120au12eeu1295 u1265u1229 u12e8u12ccu1265u1235u1355u122au12adu1235 (Websprix) u1245u120cu1275! ud83dude31 #ethiopia #websprix #ethiopiannews #fraud #ethiopianbusiness ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
🚨 ሰበር - አቶ ዳዊት ብርሃኑ በፖሊስ ታስረው ዋሉ | በወር 3.3 ሚሊዮን ብር ደመወዝ ለባልና ሚስት?! የ51 ሚሊዮን ብሩ የዌብስፕሪክስ (Websprix) ቅሌት! 😱 #ethiopia #websprix #ethiopiannews #fraud #ethiopianbusiness
4 months ago
ኩባንያችን የቴሌኮም እና ዲጂታል ደኅንነትን ለማረጋገጥ ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ለፍትሕ ተቋማት ሰጠ!
ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቱን የዲጂታል ደኅንነት ለማስጠበቅ እና የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል እንዲቻል፣ ከተለያዩ የፍትሕ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በተለያዩ ከተሞች ሰጥቷል።
“የኢትዮ ቴሌኮም እና የፍትሕ ተቋማት ጥምረት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ደኅንነት” በሚል መሪ-ቃል በድሬደዋ፣ በሐዋሳ እና በአዳማ ከተሞች በተካሄዱት በእነዚህ የሥልጠና መድረኮች ላይ፤ ከፌዴራልና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ በአጠቃላይ 171 ዳኞች፣ አቃቤያነ ሕግ እና የፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናው ኩባንያችን የሦስት ዓመት ስትራቴጂውንና የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማፋጠን ከሚያደርገው ግዙፍ የ4ጂ እና 5ጂ ኔትወርክ መሠረተ ልማቶች ማስፋፊያ ባሻገር የእነዚህን መሠረተ ልማቶች ዘላቂነት ለማስቀጠልና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከፍትሕ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ወሳኝ በመሆኑ የተዘጋጀ ነው።
ሥልጠናው በዋናነት በዲጂታል ፋይናንስና በቴሌኮም ዘርፍ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን (Telecom & Financial Fraud) ለመከላከል እንዲሁም በቴሌኮም መሠረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን በሕግ አግባብ ለመቆጣጠር በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው መድረክ ላይ የተሳተፉ የፍትሕ ተቋማት ሀላፊዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፤ መድረኩ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመረዳትና ተገቢውን የሕግ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ግንዛቤ የፈጠረላቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን የቴሌኮም መሠረተ ልማትን እንደ ሀገር ሀብት በመጠበቅና ወንጀሎችን በብቃት በመከላከል ረገድ ከኩባንያችን ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኩባንያችን ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን በሌሎች ከተሞችም አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህ መድረክ ኩባንያችን ለሀገራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት መስፋፋት ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር፣ ከቁልፍ የፍትሕ ባለድርሻ አካላት ጋር የላቀ አጋርነት በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚው ደኅንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ይታመናል።

5 months ago
የሳፋሪኮም ማስጠንቀቂያ
#fastmereja I ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞቹ በማያውቋቸው ዓለም አቀፍ ስልኮች አማካኝነት ለከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና ለማጭበርበር ድርጊት እንዳይጋለጡ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላለፈ። አጭበርባሪዎቹ ደንበኞች ተመልሰው እንዲደውሉ በማድረግ ከፍተኛ የውጭ አገር ጥሪ ክፍያ (International Tariff) እንዲቆረጥባቸው የሚያደርግ ስልት እየተጠቀሙ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ተዋናዩ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ግለሰቦች በማያውቋቸው የውጭ አገር ስልክ ቁጥሮች አማካኝነት "Missed Call" ወይም የጥሪ ምልክት በማድረግ ደንበኞች ተመልሰው እንዲደውሉ የማሳሳት ስራ እየተሰሩ ይገኛሉ።
እንደ ተቋሙ ገለጻ፣ በተለይም በ +601፣ +993፣ +371፣ +370፣ +255፣ +375፣ እና +381 መሪ ኮዶች የሚጀምሩ ስልኮች ለማጭበርበሪያነት በስፋት እየተዋሉ መሆኑ ተለይቷል። ደንበኞች ለእነዚህ ጥሪዎች ምላሽ በሚሰጡበት ወይም ተመልሰው በሚደውሉበት ወቅት፣ ጥሪው የሚታሰበው በዓለም አቀፍ ከፍተኛ ታሪፍ በመሆኑ በሂሳባቸው ላይ ያለውን የገንዘብ መጠን ወይም የአየር ሰዓት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይበላል።
ይህ አይነቱ ማጭበርበር በዓለም አቀፍ ደረጃ "Wangiri Fraud" በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ አጭበርባሪዎቹ ከቴሌኮም ኦፕሬተሮች ጋር በሚኖራቸው የገቢ ክፍፍል ስምምነት ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ ነው። በመሆኑም ህብረተሰቡ ለማያውቃቸው የውጭ አገር ጥሪዎች ተመልሶ በመደወል አላስፈላጊ ለሆነ ኪሳራ እንዳይጋለጥ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

6 months ago
በፍቅር ስም የተፈጸመው የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ማጭበርበር፡ ናይጄሪያዊው በ15 ዓመት እስራት ተቀጣ
#fastmereja I በፍቅር ግንኙነት ስም ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ያጭበረበረው ናይጄሪያዊው ሳሂድ ሰንዴይ ኦዎላቢ በአሜሪካ ፍርድ ቤት የ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት። ግለሰቡ በሴት ስም የተከፈቱ የሀሰት ማህበራዊ ገጾችን በመጠቀም ተጎጂዎችን ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ መዳረጉ ተረጋግጧል።
እንደ አሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ፣ ኦዎላቢ በገመድ አልባ የግንኙነት መረብ ማጭበርበር (Wire Fraud) እና ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ግለሰቡ እና ግብረ-አበሮቹ የተጠናከረ የማጭበርበር ሴራ በመዘርጋት የሚከተሉትን ወንጀሎች መፈጸማቸው በምርመራ ጋዜጠኝነት የተረጋገጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፦
ኦዎላቢ በኢንተርኔት አማካኝነት በተለይም የሴትነትን ማንነት በመላበስ ከተጎጂዎች ጋር የፍቅር ግንኙነት በመመሥረት ጥልቅ እምነት እንዲጥሉበት ያደርጋል።
ተጎጂዎቹ እምነት ከጣሉ በኋላ የተለያዩ የፈጠራ ሰበቦችን በመጠቀም ገንዘብ እና ሚስጥራዊ የግል መረጃዎቻቸውን እንዲልኩለት ሲያደርግ ቆይቷል።
የተሰረቀውን ገንዘብ ለመደበቅ የተጎጂዎችን የባንክ ሂሳብ ለሌሎች የማጭበርበሪያ ተግባራት እንደ Laundering ሲጠቀምበት እንደነበር አቃቤ ህግ አስረድቷል።
በሰሜን ካሮላይና ግዛት ብቻ አንዲት ግለሰብ ከ120,000 ዶላር በላይ እንዲዘረፉ ማድረጉ ለተወሰነበት የከባድ እስራት ቅጣት በምክንያትነት ቀርቧል። ይህ የፍርድ ውሳኔ በዲጂታል ዓለም ውስጥ የሚፈጸሙ መሰል የፍቅር ግንኙነት ማጭበርበሮች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ እና በህግ እንደሚያስጠይቁ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

Comments