2 months ago
ስመጥሮቹ የእግርኳስ ከዋክብት ከ "ሌጎ" ማስታወቂያ ስንት ተከፈላቸው?
#ethiopia | ግዙፍ የመጫወቻ አምራች ኩባንያ የሆነው "ሌጎ" (LEGO) የአለም ዋንጫን በማስመልከት በሰራው እና ከፍተኛ ተመልካችን ባገኘው ማስታወቂያ ላይ ለተሳተፉት ስመጥር የእግርኳስ ከዋክብት የከፈለው የገንዘብ መጠን ይፋ ተደረገ።
በማስታወቂያው ላይ ሊዮኔል ሜሲ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ኪሊያን ምባፔ እና ቪንሰስ ጁኒየር በአንድ ክፍል ውስጥ ሆነው ይታያሉ።
በተለይም ሊዮኔል ሜሲ በራሱ የኢንስታግራም ማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ያጋራው ይሄው የቪዲዮ ማስታወቂያ ከ 19 ሚሊዮን በላይ 'ላይክ' (Like) በማግኘት ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቷል።
ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ ተቋሙ ለነዚህ ከዋክብት በድምሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ክፍያን የፈፀመ ሲሆን፣ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡
* ክርስቲያኖ ሮናልዶ፡- 3.43 ሚሊዮን ዶላር
* ሊዮኔል ሜሲ፡- 2.59 ሚሊዮን ዶላር
* ኪሊያን ምባፔ፡- 852,000 ዶላር
* ቪንሰስ ጁኒየር፡- 325,000 ዶላር
አንድ አስገራሚ እውነታ ደግሞ ማስታወቂያው በሚቀረፅበት ጊዜ አራቱም ከዋክብት በአካል በአንድ ቦታ ላይ አለመገናኘታቸው ነው። የማስታወቂያው ፕሮዳክሽን ቡድን ቪዲዮውን የበለጠ ተፈጥሯዊ እና እውነተኛ ለማስመሰል ለከዋክብቱ አምሳያ ሰዎችን (stand-ins) በመጠቀም ቀረፃውን እንዳጠናቀቀ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #lego #footballstars #cristianoronaldo #lionelmessi #mbappe #viniciusjr #sportsnews #footballads #sportbusiness