5 months ago
⚽️ የፊፋ ማች ኤጀንቱ ኢንጂነር ፍፁም ለዳዊት እስጢፋኖስ አካዳሚ የሜዳ እና የትጥቅ ድጋፍ አደረጉ! 🙌
#ethiopia | "ለነገዋ ኢትዮጵያ የእግር ኳስ ተስፋዎች የሚሆን አጋርነት ተፈጥሯል"
የፊፋ ማች ኤጀንት የሆኑት ኢንጅነር ፍፁም አድነው፤ ዛሬ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በሰሚት በሚገኘው የዳዊት እስጢፋኖስ የእግር ኳስ አካዳሚ በመገኘት ወሳኝ ድጋፍ አድርገዋል።
የድጋፉ ዝርዝር:
✅ ትጥቅ: 130 ፒፕስ (Bibs) እና 10 እግር ኳሶች ለአካዳሚው ተበርክቷል።
✅ የሜዳ ዕድል: ከትጥቅ በተጨማሪ ከ"Soccer Space" ጋር በመተባበር ለፕሮጀክቱ ነፃ የሜዳ ድጋፍ እንዲያገኙ ተመቻችቷል።
ኢንጂነር ፍፁም ማናቸው?
ኢንጂነሩ ከዚህ ቀደም ሸገር ደርቢን በዱባይ እንዲሁም የሀዲያ ሆሳዕናን ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ በማሰናዳት የሚታወቁ ሲሆን፤ የመካኒሳ፣ ኮልፌ እና ፋሲል ከነማ ታዳጊዎችንም ሲደግፉ ቆይተዋል። በቀጣይም ከዳዊት እስጢፋኖስ አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት የሁለትዮሽ ስምምነት ይፈፅማሉ ተብሏል።
የአሰልጣኝ ዳዊት ምላሽ:
"ይህ ድጋፍ አካዳሚው አንድ እርምጃ መጓዝ መጀመሩን ያሳያል፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ የታሰበውን ራዕይ ስለደገፉን እናመሰግናለን" ሲል አሰልጣኝ ዳዊት እስጢፋኖስ ተናግሯል።
ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ለሚተጉት አካላት ምስጋና ይገባል!
👏
#dawitestifanosacademy #grassrootsfootball #fifaagent #fitsumadnew #support #ethiopianfootball #soccerspace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments