3 days ago
የዓለም ሻምፒዮኑ ጀግናው ክብሮም ንጉሴKebrom muaythia and kickboxing champion . ደማቅ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ሊደረግለት ነው!
የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ ላደረጉ፣ የኢትዮጵያን ስም በኩራት ላስጠሩ ጀግኖች እውቅና መስጠትና ማበረታታት የሁላችንም ታሪካዊ ድርሻ ነው!
ኢትዮጵያውስጥ Ethio Fight Night አሸናፊ እንዲሁም
በታኅሣሥ ወር 2023 ዓ.ም (December 2023) በጣሊያን ሀገር በታዋቂው Fight Clubbing አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም የሞይታይ ሻምፒዮና (Muay Thai World Championship) ላይ በ67 ኪሎ ግራም ክብደት ሙሉ ኢትዮጵያን ወክሎ በመወዳደር፣ የዓለም ሻምፒዮን (World Champion) በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘውና የሀገር ኩራት የሆነው የሳሪስ አዲሱ ሰፈር ልጅ ክብሮም ንጉሴ (The King) ታላቅ የክብር እና የምስጋና መርሃ ግብር ተዘጋጅቶለታል።
ክብሮም ንጉሴ በዓለም አቀፍ የማርሻል አርት መድረኮች (እንደ Bellator እና WPG Combat ያሉ) የብራዚልና የሌሎች ሀገራት ጠንካራ ተፎካካሪዎችን በበላይነት በመርታት የሚታወቅ፣ የሁለት ጊዜ የጣሊያን K1 ሻምፒዮን እና የኢንተርኮንቲኔንታል ሻምፒዮን በመሆን በፅናትና በደምና በላቡ የተጓዘ እውነተኛ የኢትዮጵያ አልማዝ ነው።
ይህንን ታላቅ ድል እና የሀገር ባለውለታ በደማቅ ሁኔታ ለመዘከር፣ መላው የሳሪስ ወጣቶች ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ደማቅ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር (Appreciation & Recognition Ceremony) አዘጋጅተዋል።
ይህ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ከ 500 በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ የኢትዮፋይት (EthioFight)night )&etfc አዘጋጆች ፡ተወዳዳሪዎች እና አዘጋጆች፣ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የሳሪስ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የክብር እንግዶችና አጋር ድርጅቶች በነቂስ የሚገኙበት ይሆናል።
የሰፈራችንን፣ የከተማችንንና የሀገራችንን ጀግና በጋራ ሆነን እንቀበለው፤ እናበረታታው! ሁላችሁም ሚዲያዎችና ስፖርት አፍቃሪዎች በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ እንድትታደሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

1 month ago
በዓመት ሁለት ጊዜ ዐለም አቀፍ የቦክስ ውድድር ይካሄዳል
በኢትዮጵያ የፕሮፌሽናል ቦክስ ስፖርትን ለማሳደግና በዘርፉ ያሉ ስፖርተኞችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢቲኤፍሲ (ETFC) መስራችና ባለቤት አቶ ጌታቸው መለሰ ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው በቅርቡ የተካሄደው የቦክስ ውድድር በስኬት መጠናቀቁንና በርካታ የስፖርቱ አድናቂዎች የተከታተሉት እንደነበር ተናግረው፤ በዕለቱ በተካሄዱት 11 የቦክስ ፍልሚያዎች ላይ 22 ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸውን እና እንደየደረጃቸው ክፍያ መፈጸሙን ገልጸዋል።
በአዳራሽ ውስጥ ከ2,500 እስከ 3,000 የሚደርሱ ተመልካቾች በግንባር ተገኝተው ውድድሩን የተከታተሉ ሲሆን፣ በዲጂታልና በኦንላይን የቀጥታ ስርጭት ደግሞ በርካታ ሚሊዮን አድናቂዎች እንዲሁም ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ተመልካቾች ውድድሩን መከታተላቸውንም አቶ ጌታቸው አብራርተዋል።
ድርጅቱ በቀጣይም የቦክስ ስፖርቱን የበለጠ ለማስፋፋት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ፣ በየሦስት ወሩ ትላልቅ ውድድሮችን፣ በየወሩ ደግሞ ከፊል የማጣሪያ ውድድሮችን ለማካሄድ ማቀዱን እና በዓመት ሁለት ጊዜ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበትን ውድድር ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
አዘጋጆቹ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ውድድሮች ያገኟቸውን ልምዶች በመጠቀም በቀጣይ የሚካሄዱ ፕሮግራሞችን ይበልጥ ጠንካራ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ውድድሮቹን ወደ 11 ፍልሚያዎች ዝቅ ለማድረግ መወሰናቸውን አብራርተዋል፤ ይህም አሰራር የሀገር ውስጥ ስፖርተኞች ወደ ውጭ ሀገር ሄደው እንዲወዳደሩና የውጭ ሀገር ተፋላሚዎችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሳተፉ በማድረግ ረገድ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
Seledadotio

የሽሮሜዳ እግር ኳስ ቡድን ባለድሎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው
#ethiopia | የቤላ ፉትሳል ውድድር የ2018 ዓ.ም አሸናፊ የሆነው የሽሮሜዳ እግር ኳስ ቡድን በሜዳ ላይ ላሳየው ድንቅ የቡድን ስራ እና የማይበገር መንፈስ የእራት ግብዣ እና የማበረታቻ ሽልማት ተደረገለት።
የሮሚና ባለቤት አቶ ሚካኤል ግርማ ያዘጋጁት ይህ የምስጋና እና የእውቅና ምሽት ለተጫዋቾቹ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ ነበር።
በስነ ስርዓቱ ላይ በውድድሩ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቡድኑ ተጫዋቾች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።
በዚህም መሰረት፡
* በሃይሉ ግርማ (አመለ ሸጋው)፡
የቡድኑ የተከላካይ አማካይ እና ዋና ምሰሶ በመሆን ላሳየው አስደናቂ ብቃት የ100,000 ብር ሽልማት እና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች እውቅና አግኝቷል።
* ልባርጌ ስዩም፡
በሜዳ ላይ ባሳየው ከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ትጋት እና ድንቅ እንቅስቃሴ የ50,000 ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።
* ቶማስ ቶይቶ (ሮዛ)፡
በማራኪ አጨዋወቱ እና በስፖርታዊ ጥበቡ የ30,000 ብር ሽልማት በተወካዩ በኩል ተረክቧል።
በተጨማሪም በምሽቱ ልዩ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት በETFC 02 በ63 ኪሎ ግራም ምድብ የቦክስ ሻምፒዮኑ አትሌት አብርሃም አለም የ100,000 ብር የድል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የቡድኑ አባላት እና ደጋፊዎች ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል፣ ክብር እና ድጋፍ ለሮሚና ባለቤት አቶ ሚካኤል ግርማ ያላቸውን የከበረ ምስጋና እና መልካም ምኞት ገልጸዋል።
#shiromeda #bellafutsal #romina #boxing #ethiopiansport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የማርሻል አርት አሰልጣኙ ማስተር ሀሰን ሞሚን ከጆኒ ጋር ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ
በሀገር ውስጥ የኤምኤምኤ (MMA) ስፖርት ዘርፍ አዲስ ውጥረት የሚያነሳስ መረጃ ወጥቷል። የአፋር ክልል ተወላጅ እና የዳካይቶ ሪዩ (Dakayto Ryu) ማርሻል አርት አሰልጣኝ ማስተር ሀሰን ሞሚን፡ በቅርቡ ትልቅ ትኩረት ከሳበው ተፎካካሪ ጆኒ (Johnny) ጋር በሪንግ ውስጥ ለመጋጠም ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል።
ማስተር ሀሰን የሀገር በቀል የትግል ስፖርት እና የባህል ማርሻል አርት ጥንካሬን በኦክታጎን ውስጥ ለማሳየት ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የገለፁ ሲሆን፡ አሁን ላይ የግጥሚያው መካሄድ በETFC አዘጋጆች እና በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ሆኗል።
የሁለቱ ተወዳዳሪዎች የክህሎት ልዩነትና የተለያየ የስፖርት መነሻ የብዙዎችን ትኩረትስቧል።
የስፖርት ቤተሰቡ ግምት፦
• የዳካይቶ ሪዩ አሰልጣኙ ማስተር ሀሰን ሞሚን ያሸንፋሉ?
• ወይንስ የጆኒ የኤምኤምኤ ቴክኒክ የበላይነቱን ይይዛል?
እርስዎ የትኛውን ተወዳዳሪ ይደግፋሉ?

የታሪኩ ጋንጋሲ አነጋጋሪ መልእክት
ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ
እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ (ታሪኩ ጋንጋሲ)
በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ድምፃዊ ታሪቁ ጋንክሲ በማህበራዊ ሚዲያው ያስተላለፈው የትችት መልእክት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በሳበው በዚህ ውድድር ዙሪያ ድምፃዊው «ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ፣ እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ» የሚል ግጥማዊ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይኸውም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን የፍትህ ማጣት፣ የጦርነት ስቃይ፣ ተቋማዊ የሌብነትና የዘረፋ ወንጀል እንዲሁም የከፋ የኢኮኖሚ ውደቀት ችላ በማለት ህዝቡ ጥልቅ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ እያለ በእንደዚህ አይነት የትግል ትዕይንቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ለመኮነን እንደሆነ ተገልጿል።
ድምፃዊው ይህን ማህበራዊ ተቃርኖ በማንሳት የሰጠው አስተያየት በበርካቶች ዘንድ ድጋፍና የተለያየ ትችት በማስተናገድ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሰፊ አከራካሪ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል።

ንቃተህሊና (ዮሐንስ ምስክር) በMMA Adwa Fight ድል አበሰረ! 🥊
#ethiopia | የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ምድር ካፋ ፍሬ የሆነው ንቃተህሊና፣ በዛሬው ETFC 02 የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር ከተጋጣሚው ሮቤል ገብረስላሴ ጋር ያደረገውን አሰደናቂ ፍልሚያ በከፍተኛ ብቃት በአሸናፊነት አጠናቋል!
የፅናት ውጤት፡
በETFC 01 ያመለጠውን አጋጣሚ በስፖርታዊ ጨዋነትና በትጋት በማስተካከል፤ የሚዲያ ጫናዎችን በረጋ መንፈስ ተቋቁሞ ለዛሬው ድል በቅቷል።
የስፖርቱ አለኝታ፡
የMMA ስፖርት በሀገራችን አደባባይ እንዲወጣና ተገቢውን ቦታ እንዲይዝ በድፍረት የታገለ የቁርጥ ቀን ልጅ።
በኬጁ ውስጥ እጅን በአፍ የሚያስጭን ውብ እንቅስቃሴ በማሳየት የክልሉና የሀገሩ ኩራት መሆኑን አስመስክሯል።
እንኳን ደስ አለህ!
ድል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን!
#mma #etfc02 #adwafight #nqatehilina #ethiopia #kaffa

Sponsored by
Surafel
1 month ago
የምሽቱ ትልቁን ፍልሚያ ጆኒ አሸነፈ
በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው የኢቲኤፍሲ 2 (ETFC 2) ኮከቦች ምሽት በጉጉት በተጠበቀውና በዋናው የዋንጫ ፍልሚያ (Main Event) በይፋ ፍጻሜ አግኝቷል!
በሚድል ዌይት (Middleweight MMA Bout) ዘርፍ በጆኒ እና በሴዶ መካከል የተደረገው ይህ አስደናቂና አቃጣጣኝ ፍልሚያ የመላው ተመልካች ቀልብ የሳበ ነበር።
በከፍተኛ የኤምኤምኤ (MMA) ቴክኒክ፣ የላቀ ብቃትና ፍጹም የድል ወኔ ተጋጣሚውን ሴዶን ያሸነፈው ጆኒ፡ የምሽቱን ትልቅ ድል በመቀዳጀት አዲሱ የ ETFC 2 ቻምፒዮን (Champion) በመሆን ዘውዱን ደፍቷል!

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በአዲስ አበባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በከፍተኛ ድምቀት እየተካሄደ በሚገኘው የETFC 002 - Adwa Fight Night' የማርሻል አርት እና የቦክስ ምሽት፣ ቀደምት ሻምፒዮኑ መስፍን እና ድንቁ ቦክሰኛ አብርሃም ተጋጣሚዎቻቸውን በብቃት በማሸነፍ አሸናፊነታቸውን አረጋገጡ።
በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው አንደኛው የቦክስ ፍልሚያ፣ የቀድሞው የ'ኢቲኤፍሲ 001' ሻምፒዮን የሆነው መስፍን ከአቤኔዘር ጋር ያደረገውን እልህ አስጨራሽ ግጥሚያ በድል አጠናቋል። መስፍን በዚህ ውድድር ላይ ያሳየው የተዋጣለት የቦክስ ጥበብ እና የበላይነት፣ በዘርፉ ያለውን የሻምፒዮንነት ክብር በድጋሚ ያስመሰከረበት ሆኖ አልፏል።
በሌላ በኩል በዕለቱ ስድስተኛ መርሐ ግብር ሆኖ ወደ መድረክ የመጣው የቦክስ ፍልሚያ፣ በአብርሃም እና "ታይሰን" በሚል ቅጽል ስሙ በሚታወቀው ሀይማኖት መካከል የተካሄደ ነበር። የተመልካችን ትንፋሽ ባስያዘው፣ እንዲሁም ከፍተኛ ጉልበት፣ አስደናቂ ቴክኒክ እና ጽናት በታየበት በዚህ ማራኪ ፍልሚያ፣ ስፖርተኛው አብርሃም ጠንካራ ተጋጣሚውን ሀይማኖትን ርቱዕ በሆነ መንገድ በማሸነፍ የምሽቱን ሌላኛውን ደማቅ የድል ታሪክ ጽፏል።
እነዚህ ተከታታይ እና ልብ አንጠልጣይ ግጥሚያዎች፣ የዓድዋ ፋይት ናይት ስፖርታዊ ምሽትን ይበልጥ ያደመቁት ሲሆን፤ ስፖርተኞቹ በቦክስ መድረክ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ክህሎት፣ አካላዊ ጥንካሬ እና ጽናት ለስፖርት ቤተሰቡ ፍንትው አድርገው ያሳዩበት ማራኪ መድረክ ሆኗል።

የኮልፌው ቡጢኛ
የ2ኛው የኢትዮጵያ ታዋቂ ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ የ71 ኪሎ ግራም የቦክስ ውድድር መስፍን በበላይነት አጠናቀቀ
#ethiopia | በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሰፊ ትኩረትስቦ በተካሄደው 2ኛው የኢትዮጵያ ታዋቂ ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ የዓድዋ ፋይት ናይት መርሃ ግብር መስፍንና አቤኔዘር በ71 ኪሎ ግራም የቦክስ ፍልሚያ ተገናኝተዋል።
አመሻሹን በተካሄደውና 5 ዙሮችን በወሰደው ብርቱ ፉክክር መስፍን የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት በድምር ነጥብ የብልጫ ውጤት በማስመዝገብ የአሸናፊነቱን ድል ተጎናጽፏል።
#etfc #adwafightnight #boxing #adwawictorymemorial #ethiopianboxing #sports #ethiopiansports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በሴቶች የሞይ ታይ ፍልሚያ ዘሀራ የበላይነቷን አረጋግጣለች
#ethiopia | ሁለተኛው የአድዋ ፋይት ናይት ውድድር በታላቅ ድምቀት መካሄድ ጀምሯል።
ይህ የስፖርት ዘርፍ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ፍላጎትና መነቃቃትን እየፈጠረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ታዋቂ ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ (ETFC) አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ ውድድር በሴቶች የሞይ ታይ ፍልሚያ በዘሀራ እና በያብስራ መካከል ከተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ዘሀራ ማሸነፍ ችላለች።
በዛሬው ምሽት ከሚደረጉት ዋና ዋና ውድድሮች መካከል በጉጉት የሚጠበቀው የሴዶ እና የጆኒ የኤምኤምኤ ፍልሚያ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ የቦክስ ውድድሮች ይከናወናሉ።
#etfc #adwafightnight #muaythai #mmamatch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
ሰዓታት በቀሩት በተጠባቂው የአድዋ ፋይት ናይት 02 አትሌቶች የፊት-ለፊት የፍጥጫ መርሃ ግብር አካሄዱ‼️
ETFC 002 – Adwa Fight Night ዛሬ ምሽት በፍልሚያ ዝግጅት የሚሳተፉ ተጋጣሚዎችን የሚያስተዋውቀው “Fighters Face-Off” መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል።
የፍልሚያ ዝግጅቱ በMMA፣ Muay Thai እና Boxing የፍልሚያ ዘርፎች የሚካሄዱ ውድድሮችን ያካተተ ሲሆን፣ የተፋላሚዎቹ የፊት-ለፊት መቆም ለዋናው የፍልሚያ መድረክ የሚያደርሰውን የውድድር ድባብ አሳይቷል።
👊 ተፋላሚዎቹ ፊት-ለፊት ተገናኙ
በመርሃ ግብሩ የሚቀጥለውን የፍልሚያ ውድድር የሚያደርጉ ተፋላሚዎች በፊት-ለፊት ከመቆማቸዉ በተጨማሪ የሚዛን ልኬት አካሒደዉ ለዉድድር ብቁ መሆናቸዉን አረጋግጠዋል ። ይህም ተጋጣሚዎቹ ወደ ዋናው የፍልሚያ ቀን እየተቃረቡ መሆናቸውን ያመላከተ መርሃ ግብር ሆኗል።
የFighters Face-Off መርሃ ግብሩ በአዲስ አበባ Adwa 00 Museum – Piazza ተካሂዷል። በዝግጅቱም የፍልሚያ አዘጋጆች፣ ተጋጣሚዎች ፣ታዋቂ ቲክቶከሮችና ዩቲውበሮች እና የሚዲያ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ዝግጅቱ በSweat Box እና ETFC – Adwa Fight Night ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ M-Pesa፣ GoFere እና AbbayTV ከአጋር የሚዲያና የንግድ አጋሮች መካከል ተጠቅሰዋል።
የፍልሚያው ትኩሳት እየጨመረ ነው‼️
የዛሬው የFace-Off መርሃ ግብር የAdwa Fight Night 002 ዋና የፍልሚያ ዝግጅት በተመለከተ በተጋጣሚዎችና በፍልሚያ ደጋፊዎች ዘንድ ያለውን ትኩረት ያሳየ ሆኗል።
በዚህም የአድዋ ፋይት ናይት 002 የፍልሚያ ዝግጅት ወደ ዋናው የውድድር መድረክ እየተቃረበ እና ሰአታት የቀሩት ሲሆን፣ የፍልሚያ ደጋፊዎችም ተጋጣሚዎቹን በድርጊት ለማየት በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።
🥊 ETFC 002 – Adwa Fight Night ነሀሴ 21 2018 ዓ, ም ከምሽቱ 10 ሰአት ጀምሮ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት ይከናወናል።

🥊 ታሪክ የሚሰራበት ምሽት ቀኑ ደረሰ! 🔥
በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ETFC (የአድዋ ፋይት ናይት) ታላቅ ፍልሚያ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል! የደምና የላብ፣ የጥንካሬና የብቃት መፈተሸ በሆነው በዚህ ድንቅ ምሽትMMA፣ Boxing፣ Muay Thai ቀለበቱ ውስጥ የሚደረጉትን እሳት የሚያነሱ ግጥሚያዎች የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው በadarash.com በይነመረብ በቀጥታ ስርጭት (Live) ይከታተሉ!
🔗 እንዳይረሳ adarash.com
በቅርቡ ሌላኛውን የቅን ልቦች የሶሻል ሚዲያ የቅን ልቦች ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት በ adarash.com በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፍ ይሆናል።

ሴዶ ከግጥሚያው ሊያመልጥ አይችልም፤ ጆኒ እምቢ ቢል እንኳ ከእኔ ጋር ይደባደባል» — የETFC 2 አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ
አዲስ አበባ — በETFC 2 Cage ውድድር ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል "በተቃዋሚዬ ጆኒ ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል" በሚል ከግጥሚያው ራሱን ማግለሉን ካስታወቀ በኋላ፣ የውድድሩ አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ በሰጡት አጣዳፊ ምላሽ ሴዶ ከውድድሩ ሊያመልጥ እንደማይችልና ግጥሚያው እንደማይቀር በጽኑ አስታወቁ።
የውድድሩ አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ ሴዶ አሁን ላይ ጨርቅ እየወረወረና የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደረ ከውድድሩ ለመውጣት ቢሞክርም በህግና በውል የተያዘ በመሆኑ ከፋይቱ ማምለጥ እንደማይችል ገልጸዋል። "ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሚከታተለው ውድድር ላይ እንደዚህ አይነት ሰበብ አያመልጥም" ያሉት አዘጋጁ፣ ሴዶ ከሀገር እንዳይወጣ በኤርፖርትና አስፈላጊ ቦታዎች ላይ የደህንነት ጥበቃ ክትትል እንዲደረግ መደረጉንም አብራርተዋል።
በተጨማሪም አዘጋጁ ሁኔታውን በቁጣና በቀልድ አቀላቅለው ሲናገሩ «ሴዶን ጆኒ እንኳ እምቢ ብሎ የማይደባደበው ከሆነ፣ ከእኔ ጋር ይደባደባል፤ ከእኔ ጋር ይገጥማል!» በማለት ውድድሩ በማንኛውም ሁኔታ እንደማይቀርና Cage ውስጥ መግባቱ ግዴታ እንደሆነ አጥብቀው ገልጸዋል።
የETFC 2 Cage ውድድር የታቀደበት ቀንና ሰዓት ሳይቀየር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አረጋግጠዋል።
Via: ETFC 2

ሴዶ ማርሻል እስከ 1 ዓመት እስራት ሊቀጣ ይችላል» — ጠበቃ ሰብለ አሰፋ::
በETFC 2 Cage ውድድር ውዝግብ ዙሪያ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጡ
አዲስ አበባ — በETFC 2 Cage ውድድር ዝግጅት ወቅት ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል "በተቃዋሚዬ ጆኒ ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል" በሚል ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን አስመልክቶ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠበቃ ሰብለ አሰፋ በቪዲዮ በሰጡት መግለጫ፣ ሴዶ ያቀረበው "በእንቁላል መተት ተሰርቶብኛል" የሚለው አቤቱታ በህግ ፊት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር በጆኒ ላይ የተፈጸመ የሐሰት ስም ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ገልጸዋል።
እንደ ጠበቃ ሰብለ ገለጻ፣ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 613 መሠረት፣ አንድ ሰው ያለበቂ ማስረጃ በሌላው ሰው ላይ የሐሰት ክስና ውንጀላ በማቅረብ መልካም ስሙንና ክብሩን ካደፈረሰ ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ካደረገ፣ በተጎጂው አቤቱታ አቅራቢነት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ሊቀጣ ይችላል።
በተጨማሪም ውድድሩ መሰረዙ ከተረጋገጠ ወይም የተወደዱ ተወዳዳሪዎች ባለመሰለፋቸው ምክንያት ቅሬታ ያላቸው የትኬት ገዢዎችና ተመልካቾች የውድድሩን አዘጋጆች ካሳ የመጠየቅ ሙሉ ሕጋዊ መብት እንዳላቸው ጠበቃ ሰብለ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የውድድሩ አዘጋጆች (ETFC) ሴዶ ማርሻል በገባው ውል መሠረት ባለመወዳደሩ ምክንያት ለደረሰባቸው የወጪና የገቢ ኪሳራ እንዲሁም ለተመልካቾች ለሚከፍሉት ካሳ በፍትሐብሔር ሕግ መሠረት ከሴዶ ላይ የጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የሴዶ ማርሻል ''መልዕክት'' እስከ አንድ ዓመት በእስር ሊያስቀጣው ይችላል ተባለ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ (ETFC) ውድድር ጥቂት ቀናት ብቻ በሜቀሩበት ወቅት ተወዳዳሪው ሴዶ "ድግምት ተሰርቶብኛል" በሚል ከውድድሩ መውጣቱን ማስታወቁ በማህበራዊ ሚዲያ እና በስፖርቱ አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ፈጥሯል።
ሴዶ ከውድድሩ አራት ቀናት ቀደም ብሎ ባስተላለፈው መልዕክት ከተጋጣሚው ጆኒ ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ እንደማይቀርብ ይፋ አድርጓል።
ተወዳዳሪው በእንቁላል ድግምትና ስህር እንደተሰራበት በመግለጽ ከተለየ የውጭ አገር ተደባዳቢ ጋር ካልሆነ በስተቀር ከተጠቀሰው ተጋጣሚው ጋር ወደ ሪንግ እንደማይገባና የውድድሩን ቲሸርት አውልቆ በመመለስ አቋሙን አስታውቋል።
ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያዋ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ እንደሚያስረዱት ሴዶ ያቀረበውን የድግምት ክስ በህግ ፊት የሚያስረዳ አደራጅ ማስረጃ ካላቀረበ፣ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ መሰረት በሰው ስም እና ክብር ላይ የሚፈጸም የሀሰት ሀሜትና ስም ማጥፋት ወንጀል ተደርጎ ሊወሰድበት ይችላል።
ይህም አሰራር የተጋጣሚውን መልካም ስም ያጎደለ በመሆኑ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ሊያስቀጣው የሚችልበት ህጋዊ እድል እንዳለ ይጠቁማል።
በሌላ በኩል ለውድድሩ ቲኬት የቆረጡ ተመልካቾች እና የውድድሩ ስፖንሰሮች መብት በህግ የተጠበቀ በመሆኑ የውድድሩ አዘጋጆች (ETFC) አማራጭ ውድድር የማቅረብ ወይም የገንዘብ ተመላሽ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
በተጨማሪም የውድድሩ አዘጋጆች ሴዶ በገባው ውል መሰረት ውድድሩን በማቋረጡ ምክንያት የደረሰባቸውን የገንዘብና የመድረክ ኪሳራ በፍትሐብሔር ክስ የመጠየቅ ሙሉ ህጋዊ መብት እንዳላቸው ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

በETFC 2 Cage ውስጥ የተፈጠረው «የእንቁላል እና የመተት» አወዛጋቢ ውዝግብ
አዲስ አበባ — በነሐሴ 21 ቀን ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ በሚቀሩበት በአሁኑ ወቅት፣ ታዋቂው የኢትዮጵያ ሚክስድ ማርሻል አርትስ (MMA) ተወዳዳሪ ሴዶ ማርሻል ከሚጠበቀው የETFC 2 ግጥሚያ ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታወቀ።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰራጨው የቪዲዮ መግለጫ፣ ሴዶ የለበሰውን የETFC ስፖንሰርሺፕ ማሊያ አውልቆ በመጣል ከባላጋራው ጋር Cage (ኬጅ) ውስጥ እንደማይገባ ገልጿል።
ሴዶ ለውሳኔው እንደ ምክንያት ያቀረበው ተቃዋሚው «በእንቁላል አማካኝነት ድግምት እና መተት» ፈጽሞብኛል የሚል ሲሆን፣
"ውድድሩ የቀረው 4 ቀን ነው የቀረው፤ ነገር ግን እኔ አልወዳደርም። እንቁላሉን አስጠይቄበታለሁ—ድግምት እና መተት ተሰርቶበታል። ከዚህ በኋላ ከዚህ ሰው ጋር አልጫወትም። ትኬት የገዛችሁ ወይም ስፖንሰር ያደረጋችሁ ከፈለጋችሁ ሌላ ተደባዳቢ ከውጭ አምጡልኝ፤ ከእሱ ጋር ግን በፍጹም አልገባም!"
የውድድሩ አዘጋጆች በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር ባይኖርም፣
የስፖርቱ አፍቃሪዎች ግን አቋሙን አልተቀበሉትም።
ብዙዎች "ሴዶ እምቢ ቢልም፣ ተጎትቶ Cage ውስጥ መግባት አለበት"
እንዲሁም "እንቁላሉን በልተህም ቢሆን Cage ውስጥ ትገባለህ!"በማለት አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የጆኒ እና ሴዶ MMA ፍልሚያ መግቢያ ትኬት VVIP 100 ሺ ብር መሆኑ ተገለፀ::
ቀን: ነሐሴ 21
ቦታ: አድዋ 00 ሙዚየም (Adwa 00 Museum)
ቲኬት ለመግዛት: በ M-Pesa
የቲኬት ዓይነቶች እና ዋጋ:
1. VVIP Ringside - 100,000 የኢትዮጵይ ብር
* ልዩ የሪንግ አጠገብ መቀመጫ
* ያልተገደበ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት
* ወደ ተወዳዳሪዎች ልብስ መቀየሪያ ክፍል የመግባት እድል
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
2. VVIP Premium - 50,000 የኢትዮጵይ ብር
* 2ኛ ተከታታይ ረድፍ መቀመጫ
* 2 የምግብ እና 10 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
3. VVIP Normal - 30,000 የኢትዮጵይ ብር
* ከ 3ኛ እስከ 5ኛ ረድፍ መቀመጫዎች
* 2 የምግብ እና 7 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
4. VIP - 20,000 የኢትዮጵይ ብር
* 1 የምግብ እና 4 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
5. Regular - 10,000 የኢትዮጵይ ብር
6. Early Bird - 4,000 የኢትዮጵይ ብር
(በተወሰነ ቁጥር የቀረበ)
ቲኬትዎን አሁኑኑ በ M-Pesa ይቁረጡ!
ቲኬቱም እያለቀ ነው ተብሏል.......
Via ETFC
Seledadotio
Seledadotio
ቀን: ነሐሴ 21
ቦታ: አድዋ 00 ሙዚየም (Adwa 00 Museum)
ቲኬት ለመግዛት: በ M-Pesa
የቲኬት ዓይነቶች እና ዋጋ:
1. VVIP Ringside - 100,000 የኢትዮጵይ ብር
* ልዩ የሪንግ አጠገብ መቀመጫ
* ያልተገደበ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት
* ወደ ተወዳዳሪዎች ልብስ መቀየሪያ ክፍል የመግባት እድል
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
2. VVIP Premium - 50,000 የኢትዮጵይ ብር
* 2ኛ ተከታታይ ረድፍ መቀመጫ
* 2 የምግብ እና 10 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
3. VVIP Normal - 30,000 የኢትዮጵይ ብር
* ከ 3ኛ እስከ 5ኛ ረድፍ መቀመጫዎች
* 2 የምግብ እና 7 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
4. VIP - 20,000 የኢትዮጵይ ብር
* 1 የምግብ እና 4 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
5. Regular - 10,000 የኢትዮጵይ ብር
6. Early Bird - 4,000 የኢትዮጵይ ብር
(በተወሰነ ቁጥር የቀረበ)
ቲኬትዎን አሁኑኑ በ M-Pesa ይቁረጡ!
ቲኬቱም እያለቀ ነው ተብሏል.......
Via ETFC
Seledadotio
Seledadotio
2 months ago
የሴዶ እና የጆኒ ታላቅ የMMA ፍልሚያ ነሐሴ 21 ይካሄዳል!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የማርሻል አርትስ እና የቦክስ ስፖርት ታሪክ ያልተነካውን እምቅ አቅም ለዓለም ለማሳየትና ስፖርቱን ለወጣቶች የቋሚ ገቢ ምንጭ ለማድረግ ያለመው ''አድዋ ፋይት ናይት 2" (ETFC 002) ታላቅ የውድድር ምሽት ነሀሴ 21 እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት ተገለፀ።
ነሀሴ 21 በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ በስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው እና በጉጉት የሚጠበቀው ዋና ፍልሚያ (Main Event) በጆኒ (Johnny) እና በሴዶ (Sedo) መካከል የሚደረገው ድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ግጥሚያ እንደሆነ ተገልጿል።
ዛሬ በተሰጠው የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተወዳዳሪዎች በፊት ለፊት ፍጥጫ (Face-to face) የተገናኙ ሲሆን እርስ በእርስ ያቀረቧቸው የተፎካካሪነት እና የስነ-ልቦና የበላይነት የመውሰጃ አስተያየቶች በስፍራው የነበረውን ስሜት ያጋገሉት ሲሆን፣ ሁለቱም ስፖርተኞች ለነሐሴ 21ዱ ታላቅ ፍልሚያ ያላቸውን ከፍተኛ ዝግጁነትና የማሸነፍ በራስ መተማመን አሳይተዋል።
የውድድሩ አዘጋጅና የስዊት ቦክስ መስራች እና ስራ አ አቶ ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው፣ ETFC 002 የቀደመው ETFC 001 ከተካሄደበት ፍጥነትና ሁኔታ በተሻለ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
አዘጋጆቹ ለፕሮግራሙ መዘገየት ይቅርታ በመጠየቅ፣በተወዳዳሪዎቹ የስነ-ምግባር ጥንካሬ ላይ ሙሉ እምነት እንዳላቸውና ስፖርተኞቹ ሀገራቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ማስጠራት የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በምሽቱ 11 የተመረጡ ፍልሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ 4 የቦክስ (Boxing) 4 የኤምኤምኤ (MMA) 3 የሙአይ ታይ (Muay Thai) ፍልሚያዎች ናቸው።
በዝግጅቱ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ልዩ ቦታ የተሰጠው ሲሆን፣ አትሌት አብስላት እና ዛራ በተወዳዳሪነት የሚሳተፉ ሲሆን በቀጣዩ «አድዋ ፋይት ናይት 003» ውድድር ላይ ደግሞ የሴት ተወዳዳሪዎች ቁጥር እንዲጨምርና ሰፊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ በቀደሙት ዝግጅቶች የነበረውን የመቀመጫ መደራረብ ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ የተሰራ ሲሆን በዚህም ተመልካቾች ትኬት በሚቆርጡበት ወቅት ቀጥታ የመቀመጫ ቦታቸውን (Seat) መርጠው እንዲይዙ እንደሚደረግም ነዉ የተገለፀዉ።
አዘጋጆቹ እንዳብራሩት፣ በቅርቡ በሚካሄዱት ETFC-003 እና ETFC-004 የውድድር መድረኮች ላይ የሀገር ውስጥ ስፖርተኞች ከውጭ ሀገር ተወዳዳሪዎች ጋር እንዲጋጠሙ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ይህም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደ ኡሲክ (Usyk) ያሉ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ቦክስ ውድድሮችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማዘጋጀት ለተያዘው ታላቅ ዕቅድ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
ይህ ዝግጅት በአድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች አስተዋጽኦ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስፖርት አፍቃሪያን የነሐሴ 21ዱን የሴዶ እና ጆኒ ፍልሚያ በከፍተኛ ጉጉት በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
📷 ከበደ መክብብ

4 months ago
"MMA" ውድድር አዘጋጅ ETFC ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ጥምረት ፈጠረ
#fastmereja I በኢትዮጵያ ታሪክ በከፍተኛ ዝግጅት የሚካሄደው ግዙፉ የ"MMA" (Mixed Martial Arts) ውድድር፣ ለስኬታማነቱ ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።
የMMA ውድድር ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ውድድሩ በሀገሪቱ የቱሪዝም እና የመዝናኛ ዘርፍ አቅም ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ፣ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
በስምምነቱ መሰረት ተወዳዳሪዎች ለ1 ወር በኩሪፍቱ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ስምምነቱ ለአንድ አመት እንደሚቆይ ተነግሯል።
ስምምነቱ የMMA ተወዳዳሪዎች በኩሪፍቱ ሪዞርቶች ልዩ ቅናሾችን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጋራ የጤና እና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገራዊ የጤና ንቅናቄዎችን እና የተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት መንገድ ይከፍታል።

Comments