1 month ago
የ251 ሚሊዮን ህጻናት የእውቀት በር ተዘግቷል
#ethiopia | በመላው ዓለም 251 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ።
ይህ አኃዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ በትምህርት እኩልነት ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን የሚያሳይ ሲሆን በተለይም በታዳጊ እና በጦርነት በሚታመሱ ሀገራት ላይ ችግሩ እጅግ የከፋ መሆኑን አመላክቷል።
የመንግስታቱ ድርጅት ባወጣው መረጃ መሠረት በተለያዩ ሀገራት በተከሰቱ ጦርነቶች እና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ትምህርት ቤቶች እንዲወድሙ እንዲዘጉ ወይም ለተፈናቃዮች መጠለያነት እንዲያገለግሉ ተደርገዋል ብሏል።
ይህም ሚሊዮኖች ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።
እንደዚሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች የትምህርት ቁሳቁስ የዩኒፎርም እና የትራንስፖርት ወጪዎችን መሸፈን ባለመቻላቸው ህጻናት ከትምህርት እንዲርቁ ምክንያት ሆኗል ብሏል።
በተጨማሪም ሕፃናት ለቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገቢ ለማስገኘት ሲሉ ገና በለጋ እድሜያቸው ወደ ሥራ ዓለም እንዲሰማሩ ይገደዳሉ።
በገጠር አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሰለጠኑ መምህራን እጥረት በመኖሩ ምክንያት በርካታ ሕፃናት የመማር ዕድላቸው መዘጋቱን ድርጅቱ ገልጿል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በትምህርት እኩልነት ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን ያሳየ ሲሆን በተለይም በታዳጊ እና በጦርነት በሚታመሱ ሀገራት ላይ ችግሩ እጅግ የከፋ መሆኑን አመላክቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #educationforeverychild #unesco #globalnews #educationmatters

Comments