3 months ago
የአርቴታ “ሂደቱን እመኑ” መርሕ እና የ22 ዓመታት ትዕግሥት ያፈራው ፍሬ
***************
ትናንት ምሽት በቪታሊቲ ስታዲየም የተሰማው የዳኛ የመጨረሻ ፊሽካ ድምፅ፣ ከበርንማውዝ ይልቅ በለንደን ከተማ ለሚገኙ የአርሴናል ደጋፊዎች የነፃነት አዋጅ ይመስል ነበር።
በለንደን ከተማ ብቻም ሳይሆን በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የክለቡ ደጋፊዎች ልብ ውስጥ የነበረውን የ22 ዓመታት የዋንጫ ጥም የቆረጠ ታሪካዊ ክስተት ነው።
በ37ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በበርንማውዝ ሜዳ አንድ አቻ መለያየቱን ተከትሎ፣ የሰሜን ለንደኑ አርሴናል እ.አ.አ ከ2004 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሣቱን አረጋግጧል።
“አርሴናል ሻምፒዮን ሆነ!” የሚል ድምፅ መስማት፣ “አርሴናል ሻምፒዮን ሆነ!” የሚል ጽሑፍ ማንበብ ለበርካቶች ከሰበር ዜናም በላይ ነው። ምክንያቱም ይህ ድል አንድ የሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ብቻ አይደለምና። ይልቁንም ለ22 ዓመታት የዘለቀ የናፍቆት፣ የልብ ስብራት፣ የትዕግሥት እና የፅናት መገለጫ ነው።
አርሴናል ለመጨረሻ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሣ እ.አ.አ በ2004 በአርሴን ቬንገር መሪነት ዓመቱን ሙሉ ሳይሸነፍ ‘The Invincibles’ ተብሎ በታሪክ የወርቅ ቀለም የጻፈበት ወቅት ነበር።
ከዚያ በኋላ ግን የሰሜን ለንደኑ ክለብ ያሳለፈው ጊዜ በፈተናዎች የተሞላ ነው።
➡️ ከሃይበሪ ወደ ኤምሬትስ ስታዲየም የተደረገው ሽግግር ክለቡን ለዓመታት ለከፍተኛ ዕዳ በመዳረጉ አርሴናል ኮከብ ተጫዋቾችን ለመሸጥ ተገደደ።
➡️ በሊጉ ከታላላቆቹ አራት ውስጥ (Top 4) መግባት ባለመቻል የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ማጣት እና የደጋፊዎች ተስፋ መቁረጥ ክለቡን ክፉኛ ፈትነውት ቆይተዋል።
➡️ ባለፉት ጥቂት የውድድር ዓመታት ደግሞ ዋንጫውን ለመጨበጥ ተቃርበው በመጨረሻዎቹ ሳምንታት በማንቸስተር ሲቲ ሲነጠቁ የነበረው የደጋፊዎች ስሜት እጅጉን ሲጎዳ ቆይቷል።
አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የክለቡን መንበር ሲረከቡ ቡድኑ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብቶ ነበር። ወጣቱን ስብስብ በመገንባት፣ የክለቡን ባህል በመቀየር እና በደጋፊው እና በቡድኑ መካከል የነበረውን የሻከረ ግንኙነት በመጠገን ረጅም መንገድ ተጉዘዋል።
ቡድኑ በተደጋጋሚ ሲወድቅ እና ሲነሣ፣ ትችቶች ሲበራከቱ፣ አርቴታ ግን “ሂደቱን እመኑ” (Trust the Process) በሚል መርሕ ተጓዙ። ይህ መርሐቸው በተፈለገው ፍጥነት ውጤት ባለማምጣቱ ብዙዎች እንዲያሾፉባቸውም አድርጓቸው ነበር።
ያ ሁሉ ታዲያ ትናንት ምሽት ተቀየረ፤ “ሂደቱን እመኑ” የሚለው መርሐቸው ትናንት ምሽት አሳማኝ ፍሬ አፈራ! የአርሴናል የሊጉን ዋንጫ የመጠበቂያ ጊዜው አከተመ።
አርቴታ የተማመኑባቸው ወጣቶች እምነታቸውን አልበሉም፤ የሳካ ድንቅ ብቃት፣ የኦዴጋርድ መሪነት እና የመላው ቡድን አንድነት ለአርሴናል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።
በትናንቱ ውጤት ከለንደን እስከ አዲስ አበባ፣ ከቶኪዮ እስከ ኒው ዮርክ በዓለም ዙሪያ ያሉ የአርሴናል ደጋፊዎች ወደር በሌለው በደስታ ባሕር ውስጥ ናኙ፤ የደስታ ዕንባ ያፈሰሱም በርካቶች ናቸው።
ከተማዎች በመኪና ጡሩምባዎች እና በደጋፊው ጩኸት ተሞሉ፤ ማኅበራዊ ሚዲያው ቀይ እና ነጭ በለበሱ ደጋፊዎች ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ተጥለቀለቀ።
ላለፉት 22 ዓመታት በሌሎች ክለቦች ደጋፊዎች ይደርስባቸው የነበረውን ስላቅ እና ብሽሽቅ በትዕግሥት ያሳለፉ የአርሴናል ደጋፊዎች ትናንት ምሽት በኩራት አንገታቸውን ቀና ማድረግ ችለዋል።
ጎልማሶች እና አባቶች ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ላሉ ወጣቶቹ “አርሴናል ዋንጫ ሲያነሣ እንዲህ ነበር” እያሉ የሚተርኩበት ዘመን አብቅቶ፣ አዲሱ ትውልድ የራሱን ታሪክ በዓይኑ ያየበት ምሽት ሆኗል።
በለንደን ጎዳናዎች ላይ የሚታዩት ቀይ እና ነጭ ማሊያ የለበሱ ደጋፊዎች በደስታ ሲጨፍሩ፣ አንዳንዶቹም ላለፉት 22 ዓመታት ያሳለፉትን ውጣ ውረድ እያሰቡ የደስታ እንባ ሲያፈሱ ተስተውለዋል።
ለ22 ዓመታት ዋንጫን አለማየት ማለት ለአንድ ትልቅ ክለብ ረጅም ዘመን ነው። አርሴናል በዚህ ጉዞ ውስጥ መሳቂያም፣ መሳለቂያም ሆኖ ነበር፤ ነገር ግን አልፈረሰም።
ትናንት ምሽት የተገኘው ድል ስሜቱ እጅግ ከፍ ያለ የሆነውም ለዚህ ነው። ይህ ድል በስቃይ ያለፉበት እና በብዙ ላብ የተገነባ፣ በብዙ ትዕግሥት ያበቀሉት በመሆኑ ጣዕሙን ለየት ያደርገዋል።
በዮናስ በድሉ
#ebc #premierleague #football #arsenal #champions2026

Comments