10 days ago
እውነትም እድሜ ቁጥር ነው!
#ethiopia | በ90 ዓመታቸው የሰውነት ቅርጽ ውድድር አሸናፊ የሆኑት ጃፓናዊ!
90 ዓመት ሞልቷቸዋል ነገር ግን አሁንም በሰውነት ቅርጽ ውድድር ድል እየተቀናጁ ይገኛሉ።
በ90 ዓመታቸው በጃፓን በሰውነት ቅርጽ ውድድር ዋንጫዎችን በማንሳት ላይ የሚገኙት እኚህ አዛውንት አድናቆት እየጎረፈላቸው ይገኛል።
እኚህ አዛውንት ምንም አይነት ማበረታቻ መድሃኒት ወይም ተጨማሪ የኬሚካል ፕሮቲኖችን ተጠቅመው እንደማያውቁ ይናገራሉ።
በወጣትነታቸው በሰውነት ቅርጽ በርካታ ዋንጫዎችን ያሸነፉት ካናዛዋ በ34 ዓመታቸው ስፖርቱን አቁመው የነበረ ቢሆንም በ50 ዓመታቸው እንደገና ወደ ሚወዱት ውድድር ተመልሰዋል።
ለውጤታቸው ሚስጥሩ የተመጣጠነ የጃፓን ባህላዊ ምግብ ሩዝ፣ አሳ እና አኩሪ አተር በቂ እረፍት እና በቀን ለሰዓታት የሚያደርጉት ጠንካራ እንቅስቃሴ እንደሆነ ይናገራሉ።
በ90 ዓመታቸው በጃፓን ብሔራዊ የሰውነት ቅርጽ ውድድር ላይ በመሳተፍ በእድሜ አንጋፋው ተወዳዳሪ በመሆን የራሳቸውን ታሪክ አሻሽለዋል።
"እድሜ ቁጥር ነው የሚሉት እኚህ አዛውንት አዕምሮህ ካመነበት እና አካልህን ካከበርከው በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሆነህ የፈለግከውን ማሳካት ትችላለህ ብለዋል።
በአሁኑ ዘመን በሰውነት ግንባታ ስፖርት ውስጥ በርካታ ወጣቶች ፈጣን ለውጥ ለማምጣት ሰው ሰራሽ ማበረታቻዎችን በሚጠቀሙበት ወቅት እኚህ አዛውንት ለብዙዎች ትልቅ አርአያ ሆነዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #toshisukekanazawa #naturalbodybuilding #bodybuildingmotivation #fitnessmotivation

Comments