10 months ago
የአሜሪካ ቪዛ ማስያዣ ክፍያ ጉዳይ
በአበበ ፈለቀ
#ethiopia | ወደ አሜሪካ የB-1 እና የB-2 የቢዝነስ እና የጉብኝት ቪዛ ለሚጠይቁ ሰወች እንደ ሁኔታው የ5፣ የ10 እና የ15 ሺህ ዶላር ማስያዣ የሚጠይቅ ድንጋጌ መውጣቱ ይታወቃል።
ይሄ ከነሃሴ 14፣ 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ አመት የሚቆየው የሙከራ መርሃ ግብር “ሁሉም ሃገራት ላይ ተፈጻሚ ነው” የሚለው እሳቤ የተሳሳተ ነው። ይሄን ቅድመ ሁኔታ እንዲያሟሉ የሚጠየቁ ሃገራት፣ በአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት መስርያ ቤት ሪፖርት መሰረት፣ ከዚህ ቀደም ወደ አሜሪካ መጥተው ያልተመለሱ ወይም የዘገዩ በርካታ ዜጎች ያሉባቸው ሃገራት እንደሆኑ ነው የተገለጸው።
በዚህም መሰረት በአሁኑ ሰአት ቅድመ ሁኔታው ተግባራዊ እንዲሆንባቸው የተመረጡት የመጀመርያወቹ ሃገራት ማላዊ እና ዛምቢያ ናቸው። እስከ አሁን ባለው መረጃ ከሁለቱ ሃገራት ሌላ ይህ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ሃገር ላይ ተፈጻሚ አይደለም።
ያም ሆኖ በዚሁ የአንድ አመት የሙከራ መርሃ ግብር ጊዜ ውስጥ ሌሎች ሃገራት በዚሁ ዝርዝር ውስጥ ሊጨመሩ ይችላሉ። ሃገራቱ መጨመራቸው በተገለጸ በ15 ቀናት ውስጥ ቅድመ ሁኔታው ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል ማለት ነው።
#usvisa #visausa #visa #b1b2visa #usa #ethiopia #followersreels

Comments