9 days ago
የአሸናፊዎች አሸናፊ ውጊያ ይደረጋል‼️
ህወሃት የ 1983 ታሪክን እንደግማሁ እያለ ነው።
የሕወሓት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ) ከሰሞኑ በአንድ መድረክ ላይ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሁን ከተጣመርናቸው ኃይሎች ጋር መዋጋታችን አይቀርም ብለዋል፡፡ የሀላፊዋ ንግግር የጽምዶ ኃይሎችን የትብብር መሰረት የሚያናጋ ነው ተብሏል፡፡
ወይዘሮ ፈትለወርቅ ቃል በቃል የተናገሩ፡-
‹‹ዋናው ነገር ብልፅግናን ለመጣል ፍላጎት ያሳይ እንጂ የትኛውም ስብስብ እርስ በራሱ እሳትና ጭድ ቢሆንም እንኳን አብረን እንሰራለን። ብልፅግናን ከጣልን በኃላ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመለየት ሌላ ዙር ፍልሚያ ይኖረናል።
ለዚህም እየተዘጋጀን ነው፤ ይህ በተለያየ መልክ የተጀመረውን ትብብራችንን ስናየው የተለያየ ፍላጎት ያለን ሃይሎች ሆነን ነው ትብብር እየፈጠርን ያለነው። በአላማ፣ በፕሮግም፣ ወደፊት በረዥም ጊዜ እቅድ ምናምን አንድ ነን ማለት አይደለም። ትብብራችን በዛች በምታገናኘን ነገር ብቻ ነው።
እኛ ከፋኖ የምንለይበት የፖለቲካ አቋም አለን። ከሻዕቢያ ይሁን ከሌሎች የተለያዩ ሃይሎች የምንለያይባቸው መዓት ጉዳዮች አሉ። አንድ የሚያደርገን ግን የብልፅግና ስርዓት የሁላችንም ስጋት ነው የሚለው ነው። ይቺ ብቻ ናት የምታገናኘን።
እንደ ተሞክሮ ልንወስደው የሚገባን ነገር ደግሞ እንኳን አሁን በብዙ ጉዳዮች ልዩነት ካለንና በዓላማ ከማንገናኛቸው የተለያዩ ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና ኢህአዴግም እኮ ፈርሷል።
ኢህአዴግ እኮ የኦሮሞ፣የአማራ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ሃይሎች አራት ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነን የፈጠርነውና በፕሮግራም ወይም አላማ አንድ የነበረ ድርጅት ነበር። ግንኙነታችንም ስትራቴጂካዊ ነበር[ታክቲካል አልነበረም] ፣ በተለያየ ቋንቋ የተፃፈች አንዲት ፕሮግራም ነበር የነበረችን።
ግንባር ከመሆናችን ውጭ አንድ ድርጅት ማለት ነበርን፤ በዚህ ደረጃ የነበርን ሰዎች እኮ ተካክደናል[እንኳን ይሄ በዓላማ ከማይመስሉን ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና]›› ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
Via :- Andafta
Seledadotio

2 months ago
ኦብነግ ከፋኖ ጋር መነጋገሩን ይፋ አደረገ
ከአንድ ወር በፊት በአስመራ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተገናኙት የኦብነግ አንጃ መሪ የሆኑት አብዱራህማን መህዲ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ንግግር እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ትናንት ባወጣው ዘገባ፣ ከሰላማዊ ትግል ራሱን ያገለለው የኦብነግ አንጃ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ እና አማጺ ኃይሎች ጋር ጥምረት እንዲፈጥሩ ከግብጽ እና ኤርትራ መንግስታት ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ እየተሰባሰቡ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው፤ ከሚሰባሰቡት ኃይሎች መካከል ኦብነግ አንዱ ነው ብሏል፡፡ እንደ ፋኖ፣ ህውሃት እና ኦነግ ሸኔ ካሉ ሀይሎች ጋር ጥምረት መፍጠራቸውን በአፍሪካ ኢንተለጀንስ የተጠየቁት የቡድኑ መሪ አብዱራህማን መህዲ፤ ‹‹ጥምረት የመፍጠር ደረጃ ላይ ባንደርስም፤ ከፋኖም ሆነ ሌሎች ሀይሎች ጋር ተነጋግረናል፤ ለመስራትም ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን ውይጥቱ የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም›› በማለት መልሰዋል፡፡
አፍሪካን ኢንተለጀንስ እንደዘገባው፣ የኦብነግ አንጃ ከሌሎች ሀይሎች ጋር ትብብር እንዲፈጥር፣ በሱዳን፣ ኤርትራ እና ግብጽ መንግስታት ጫና እየተደረገበት ሲሆን፤ በቅርቡም በአስመራ እና በፖርት ሱዳን ስብሰባዎችን ማደረረጋቸውን ጠቅሷል፡፡via:- andafta

5 months ago
በትግራይ በርካታ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው!
በመቀሌ፣ ሽሬ፣ አዲግራት፣ መኮኒ ሰላማዊ ሰልፎች እየተደረጉ መሆኑ ታውቋል። በሰልፎቹ ላይ የፌዴሬሽን ምክርቤትን ውሳኔ የሚቃወሙ መልእክቶች በስፋት ተላልፈዋል።
Andafta.com

የሮበርት ሙጋቤ ልጅ በ"ግድያ ሙከራ" ወንጀል ተከሰሰ
#ethiopia | የሟቹ የሮበርት ሙጋቤ ታናሽ ልጅ ቤላርሚን ቻቱንጋ፣ በጆሃንስበርግ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአንድ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በተተኮሰ ጥይት ምክንያት ከባድ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
የክሱ ዝርዝር ሁኔታ
* የግድያ ሙከራ፦ ቻቱንጋ በወጣቱ ላይ ለደረሰው የጥይት ቁስል በቀጥታ ተጠያቂ ተደርጓል። ጥቃት የደረሰበት ወጣት በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል በፅኑ ሁኔታ (Critical Condition) ላይ ይገኛል።
* ተደራቢ ክሶች፦ ከግድያ ሙከራው በተጨማሪ፣ "የፍትህ ሂደትን ማደናቀፍ" ጨምሮ በሁለት ተጨማሪ የወንጀል ክሶች ተጠልፏል።
* የጥበቃ አባሉ ተሳትፎ፦ በወቅቱ ከቻቱንጋ ጋር የነበረው የቅርብ ጥበቃውም በተመሳሳይ ወንጀል ተካፋይ በመሆን ተከሷል።
የፖሊስ ምርመራ
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በወንጀሉ ስፍራ የጥይት ቀለህ ማግኘቱን ቢያረጋግጥም፣ ጥቃቱ የተፈጸመበት መሣሪያ ግን እስካሁን አልተገኘም። ይህም በምርመራው ሂደት ላይ የራሱን ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገምቷል።
ቀጣይ ሂደት
በዚምባብዌና በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነው የቻቱንጋ ጉዳይ፣ የዋስትና ጥያቄው ውሳኔ ለመስጠት ለቀጣዩ ሳምንት ቀጠሮ ተይዟል። እስከዚያው ድረስ የፕሬዝዳንቱ ልጅ በቁጥጥር ስር ሆኖ ጉዳዩን ይከታተላል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #andafta #robertmugabe #chatungamugabe #southafrica #crimenews #zimbabwe #breakingnews #johannesburg #africapolitics

10 months ago
"ሰራዊቱ ለትልቅ ግዳጅ ይዘጋጅ..." ጀነራል አበባው ታደሰ
‹‹ሁለት ነገር መጠንቀቅ አለብን፤ የዲጂታል ጦርነት፣ በአእምሯችን የሚመጣውን ጦርነት፣ በስድብ የሚመጣውን ጦርነት በቅጡ እናውቀዋለን፡፡ በመንደር የሚመጣውንም ጦርነት በቅጡ እናውቀዋለን፤ ማን እንደሚልከውም እናውቃለን፡፡
ለዚያ በቂ ዝግጅት አድርገናል፡፡ ስለዚህም ደማችሁንም አጥንታችሁንም ከስክሳችሁ ለዚያ ታላቅ ግዳጅ ተዘጋጁ››
ይህን ንግግር ያሰሙት ጀነራል አበባው ታደሰ ከቀናት በፊት በባቱ ከተማ ተገኝተው ነው፡፡via.andafta
seledadotio

1 year ago
አል-ፋሽጋ ዳግም በኢትዮጵያውያን እጅ ገባ
ለዘመናት የኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የእርሻና የኑሮ መሰረት የነበረው ለም መሬት፣ አል-ፋሽጋ፣ ዳግም ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ ተመልሷል።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅት የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም፣በሱዳን ጦር ተወርሮ የነበረው ሰፊና ለም መሬት፣ አሁን በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ገበሬዎችና ሚሊሻዎች ቁጥጥር ስር ውሏል።
የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙትን የመተማና የቋራ ወረዳ ለም መሬቶችን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር።
በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ መንግሥትም ችግሩን በዲፕሎማሲና በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል፡፡
በዚህ የሱዳን ወረራ ወቅት ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከእርሻቸው ከመፈናቀላቸውም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብልና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው አይዘነጋም፡፡
የሱዳን ባለሥልጣናት ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው ሲሉ መክሰሳቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ #andafta

#ethiopia | ለዘመናት የኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የእርሻና የኑሮ መሰረት የነበረው ለም መሬት፣ አል-ፋሽጋ፣ ዳግም ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ ተመልሷል።

Sponsored by
Surafel
Comments