21 days ago
አሐዱ ባንክ 4ኛ ዓመቱን በእንጦጦ የችግኝ ተከላ እና በበጎ አድራጎት ሥራዎች እያከበረ ይገኛል
#ethiopia | አሐዱ ባንክ ወደ ስራ የገባበትን አራተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ።
ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የባንኩ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በእንጦጦ ተራራ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና ብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅ የሚያግዙ ከ600 በላይ አገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል።
የአሐዱ ባንክ የማርኬቲንግ እና ኮሚኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ አብይ መልካ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት፣ በዛሬው እለት ከ600 በላይ የሚሆኑና ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር ዘላቂ ጠቀሜታ ያላቸው ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል።
ተለይተው ከተተከሉት ዝርያዎች መካከል እንደ ኮሶ፣ ብርብራ፣ ዋንዛ፣ ዝግባ እና ቀረሮ ያሉ እፅዋት የሚገኙበት ሲሆን፣ ይህም ቀደም ሲል በቦታው ላይ በስፋት ይስተዋል የነበረውንና ከፍተኛ የውሃ ፍጆታ የሚጠይቀውን የባህር ዛፍ ተክል በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ያለመ ነው።
አቶ አብይ አክለውም፣ ባንኩ ችግኞቹን ከመትከል ባለፈ በየሦስት ወሩ ክትትልና እንክብካቤ እንደሚያደርግላቸውና ይህንንም ሥራ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ተቋም ጋር በመተባበር በኃላፊነት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአሐዱ ባንክ የኩባንያ ሴክሬተሪ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ጽሕፈት ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ቢኒያም አህመድ በበኩላቸው ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት፣ ይህ የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴ ባንኩ በአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅዱ ውስጥ ካካተታቸውና ትኩረት ከሰጣቸው መርሆዎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው ብለዋል።
አቶ ቢኒያም እንደገለጹት፣ የችግኝ ተከላው በአንድ ጀንበር ዘመቻ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን፣ ባንኩ በቋሚነት ከተረከበው ቦታ በተጨማሪ በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉት ከ108 በላይ በሚሆኑ ቅርንጫፎችም ጭምር በየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ የሚደረግና የባንኩን መሠረታዊ እሴት የሚያንጸባርቅ ዘላቂ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ባንኩ ከአካባቢ ጥበቃ በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ በሆኑ የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል። የማርኬቲንግ ዳይሬክተሩ አቶ አብይ እንደገለጹት፣ ባንኩ በየዓመቱ እንደ መቄዶንያ፣ ጌርጌሴኖን እና የሰበታ ደናግላን ገዳም ላሉ ተቋማት የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የ204 የሚሆኑ አቅመ-ደካማ ሕፃናትን የትምህርትና የመኖሪያ ወጪዎች በየወሩ በመሸፈን እያሳደገ ይገኛል።
ከዚህም ባሻገር የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የአሐዱ ባንክ ሠራተኞቹ እና ደንበኞች በተደጋጋሚ የሚሳተፉበት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ዘንድሮሞ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በአራት ዓመታት የአገልግሎት ዘመኑ ፈጣን ዕድገት እያሳየ የመጣው አሐዱ ባንክ፣ በበጀት ዓመቱ 1.15 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡንና በቀጣይም ከኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ወደ ሰፊ የአክሲዮን ሽያጭ እንቅስቃሴ በመግባት ደንበኞቹንና ባለአክሲዮኖቹን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑ ይታወሳል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#greenlegacy #greeninitiative
#indigenoustrees #entotomountain
#gullele #addisababa #ethiopia
#ahadubank #ahadubank4thanniversary

Comments