9 months ago
⚽️ በካፍ ቤት ምን እየተካሄደ ነው?
ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? 🤔
#ethiopia | "ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም... ኢትዮጵያ፣ ቦትስዋና ወይስ ደቡብ አፍሪካ?"
ትናንት የተደረገው የካፍ ኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ስብሰባ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። የ2028 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገርን ይወስናል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ነገሮች ባልተለመደ መልኩ ፀጥ ብለዋል።
ጋዜጠኛ ዐቢይ ዘላለም እንደዘገበው ዋና ዋና ነጥቦች
እነዚህ ናቸው፡-
1️⃣ የገቢ ጉዳይ:
ስብሰባው በዋናነት ካፍ ከኮትዲቯር በኋላ የ90% የገቢ ጭማሪ ማሳየቱ እና ከ17 ግዙፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱ እንደ ስኬት ተወርቶበታል።
2️⃣ ያልተጠበቀው ዜና:
ቦትስዋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር በጋራ የ2028 ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረቧ ለኢትዮጵያ ያልተጠበቀ ክስተት ሆኗል።
3️⃣ የኢትዮጵያ ተስፋ:
ካፍ የመንግስትን (የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይን) ከፍተኛ ቁርጠኝነት ቢወድም፤ "እንገነባለን" ከሚል ቃል ይልቅ "የተገነባ" ጋራንቲ ይፈልጋል።
4️⃣ ዲፕሎማሲ:
አቶ ኢሳያስ ጅራ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ እንደ ድሮው (እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ዘመን) በካፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ አይደለችም።
ዛሬ ምሽት ምን ይፈጠራል?
በሞሮኮ ሰዓት አቆጣጠር 7:00 (በእኛ ምሽት) ፕሬዝዳንቱ ፓትሪስ ሞትሴፔ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ። ውሳኔው ምን ይሆን?
"መንግስት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥል፤ እድሉ ከተገኘ መልካም ካልሆነም ለወደፊቱ መሰረት ይሆናል!"
#ዐቢይ ዘላለም
#caf #afcon2028 #ethiopia #football #abiyzelalem #patricemotsepe

🌍 የአፍሪካ ዋንጫ 2028 አዘጋጅ ሀገር ዛሬ ትታወቃለች!
#ethiopia | የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በሞሮኮ መዲና ራባት በሚያደርገው ወሳኝ ስብሰባ፣ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያስተናግደውን ሀገር ማንነት በይፋ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ፍላጎት
ኢትዮጵያ ይህን ታላቅ አህጉራዊ ውድድር በሀገሯ ለማዘጋጀት ያላትን ከፍተኛ ፍላጎትና ዝግጁነት ገልጻ ጥያቄዋን አቅርባለች። ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት በስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየች ያለችው ሞሮኮም ውድድሩን የማዘጋጀት ፍላጎት ማሳየቷ ለውሳኔው ከፍተኛ ፉክክር ይፈጥራል ተብሎ ተገምቷል።
📋 በራባቱ ስብሰባ ምን ይጠበቃል?
ከረፋድ በኋላ የሚጀምረው ይህ የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በአስተናጋጅ ሀገር ምርጫ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን፡
* በአህጉራዊ እግር ኳስ መዋቅራዊ ለውጦች ላይ፣
* በክለቦች ውድድር መሻሻሎች እና፣
* በሌሎች ቁልፍ ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ዋንጫን ወደ ምሥራቅ አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የመመለስ ዕድሉ ምን ያህል ሰፊ ይሆን? ወይንስ በድጋሚ ወደ ሰሜን አፍሪካ ያመራል? ምላሹን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የምናገኘው ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#አፍሪካዋንጫ #ካፍ #ኢትዮጵያ #ሞሮኮ #እግርኳስ #afcon2028 #caf #ethiopia #morocco #footballnews

Comments