2 months ago
ዳሽን ባንክ ለዲቦራ ፋውንዴሽን 30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
********************
ባለፋት 6 ወራት 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓት በተለያዩ መርሐ ግብሮች በማክብር ላይ የቆየው ዳሽን ባንክ የማጠቃለያ መርሐ ግብሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዷል።
በማጠቃለያ በመርሐ ግብሩ፣ ባንኩ 30ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ለዲቦራ ፋውንዴሽን 30 ሚሊዮን ድጋፍ አድርጓል።
ባንኩ በ3 አስርት ዓመታት የስራ ሂደቱ ለስኬቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ መስራቾች እና ባለሙያዎች በ9 የተለያዩ ዘርፎች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
ከባንኩ መስራቾች አንዱ ለሆኑትና ስያሜውን ላወጡለት እንዲሁም ታማኝ ደንበኛው ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲን የክብር የወርቅ ዋንጫ ተበርክቷል።
በተጨማሪም ባንኩ 30ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ለ30 ታማኝ ደንበኞቹ እውቅና ሰጥቷል።
በዳሽን ሱፐር አኘ ግብይት ለሚፈፅሙ ደንበኞች የተዘጋጀው የዳሽን ዕድል የስጦታ መርሐ ግብር የመጨረሻውን ሽልማት በዕጣ ላሸነፈው ጥበቡ አቸነፍም የBYD ሴጉል መኪና ተበርክቷል።
በማጠቃለያ በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ጠንካራ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የባንኩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገለጸዋል።
ባንኩ በቀጣይ ዓመታትም ስኬቱን በማስቀጠል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ በተለይም ወጣቶች፣ ሴቶችና ግብርናን ትኩረት በማድረግ ቢሠራ ከፍተኛ ሀገራዊ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝ አመላክተዋል።
በ14.9 ሚሊዮን ብር፣ በ11 ባለሃብቶች በ11 ቅርንጫፎች የተመሠረተው ዳሽን ባንክ በ30 ዓመት ጉዞው ቅርንጫፎቹን 906 ማድረስ ችሏል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት በ11 ሺህ 300 ሠራተኞቹ ለ7.8 ሚሊዮን ደንበኞቹ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በኤዶምያስ ንጉሴ
#ethiopia #dashenbank #30thanniversary #ebc

Comments