1 day ago
ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድ አገኘ
👉ራሚስ ባንከ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪከ አዲስ ምዕራፍ የከፈተለትን ታላቅ ስኬት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
በይፋ አብስሯል፡፡
ባንኩ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው የሚገኙ 2 ሚልየን 101ሺ 106 አክስዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) በይፋ መመዝገባቸውና የምዝገባ መግለጫው በመጽደቁ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና ገጽ ላይ ለመመዝገብ ያቀረበው ማመልከቻ ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪክ ውስጥ በ ESX ዋና ገጽ ለመመዝገብ የመርህ ደረጃ ፈቃድ ካገኙት ከመጀመሪያዎቹ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ አድርጎታል።
የራሚስ ባንከ የዳይሬከተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ራቢ ሼክ ሁሴን፥ ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በፅኑ የሸሪዓ መርሆች፣ በግልጽነት እና በጠንካራ ተቋማዊ አስተዳደር ላይ በመቆም የህብረተሰቡን እምነት ያተረፈ ሲሆን፣ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙን በመጠቀም በምስራቅ አፍሪካ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዋና ማዕከል የመሆን ታላቅ ሀገራዊ ግቡን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ብስራት ሰምቷል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሊ እንደገለጹት ይህ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተሰጠው የምዝገባ ፈቃድ የራሚስ ባንክን የፋይናንስ ጥንካሬ፣ የኮርፖሬት አስተዳደር ብቃት እና ተቋማዊ አስተማማኝነት በግልጽ ያረጋገጠ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

2 days ago
ከቤት ደጃፍ እስከ አፍሪካ ክብር፤ የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ ከፍታ
****************
“ኑ ቡና ጠጡ፣ ቡና ፈልቷል” የሚለው ጥሪ በኢትዮጵያውያን የዘወትር ሕይወት ውስጥ ትልቅ የፍቅርና የእንግዳ ተቀባይነት ግብዣ ነው።
በዚሁ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት ወቅት ማኅበራዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፤ ጥልቅ ትስስር ይፈጠራል።
የኢትዮጵያዊነት አንዱ መገለጫ የሆነው የቡና ስነ ስርዓት ከእርሻ ማሳዎች እስከ ሲኒያችን ድረስ የአርሶ አደሩ እጅ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን የሚደግፍ ታላቅ እሴት ነው።
ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ የቡና ባህል በቤትና በማኅበረሰብ ደረጃ ብቻ ተወሰኖ አልቀረም።
ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና ሌላ አዲስ የክብር ገጽታውን ለአፍሪካና ለዓለም አሳይቷል።
በአንድ ቀን 10 ሺህ ሲኒ ቡና በአንድ ሥፍራ በማቅረብ፣ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥርዓቱ በአፍሪካ የድንቃድንቅ መዝገብ ውስጥ ዕውቅና አግኝቷል።
በመሆኑም “ኑ ቡና ጠጡ” የሚለው ጥሪ ከቤት ደጃፍ አልፎ በአህጉራዊ የክብር መዝገብ ውስጥ በመግባት፣ ከ“ኑ ቡና ጠጡ” ወደ “የኢትዮጵያን ባህልና አብሮነት ይዩ” ወደሚል ሰፊ አህጉራዊ ጥሪ ተሸጋግሯል።
ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ እና የአፍሪካ ቀዳሚ ቡና አምራች ሀገር ስትሆን፣ የመጀመሪያው የቡና ፍሬ ተለቅሞና ተሰብስቦ ለዓለም የተበረከተው እዚሁ በኢትዮጵያ ምድር ነው።
ሀገራችን በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ3.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስመዝገብ ችላለች።
ይህም ኢትዮጵያ ባለፉት 17 ዓመታት በአጠቃላይ ካገኘችው 3.3 ቢሊዮን ዶላር የገቢ መጠን ጋር የሚቀራረብ ነው።
በተጨማሪም በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች በሚተከሉበት የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ውስጥ ሰፊውን ቁጥር የሚይዙት የቡና ችግኞች ናቸው።
ይህም ደኖችን መልሶ ለማቋቋም፣ ሥነ-ምህዳርን ለመጠበቅ እና የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስፈልገውን አየር ንብረት ለመፍጠር አስችሏል።
ከዚህ ዕድገት ጎን ለጎን ኢትዮጵያ የቡና በሽታን ለመለየትና ለማከም የሚያስችሉ አዳዲስ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን እና ምርምሮችን በማሳደግ ላይ ትገኛለች።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #ethiopiancoffee #coffeeculture

3 days ago
የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ተሰጠው
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመምህራን ሙያ ብቃትና ትምህርት ጥራት ዘርፍ የ2026 ዩኔስኮ ሃምዳን ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።
ኮሌጁ ከ124 የዓለም ሀገራት ከተውጣጡ የትምህርት ተቋማት ጋር ተወዳድሮ 1ኛ በመውጣት የ 100ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆኑ ተገልጿል።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን አቶ የሻምበል ጸሐይ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት የዓለም አቀፍ መምህራን ቀንን አስመልክቶ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት የጎንደር ዩኒቨርስቲ በትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን በማመረት ረገድ ባከናወናቸው ስራዎችና ለትምህርት ጥራት ባበረከተው አስተዋጽኦ ዕውቅና አግኝቷል።
ሽልማቱ የማስተማር ሂደትን ለማሻሻል ፣ የመምህራንን ብቃት ለማሳደግና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚሰሩ ተግባራትን የሚያበረታታ መሆኑን አብራርተዋል።
የጎንደር መምህራንትምህርት ኮሌጅ ከሚሰጠው ስልጠና ጎን ለጎን ለቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች የሚያገለግሉ መርጃ መሳሪያዎችን ከ 98 ትምህርት ቤቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ከ15ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ኮሌጁ እስካሁን ከ65ሺህ በላይ መምህራን ማፍራት መቻሉ ተገልጿል። በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ ካሉ 10 መምህራን ትምህርት ኮሌጆች መካከል 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል።
በቃልኪዳን ኃይሌ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

5 days ago
መልሶ መጠቀም ላይ ያተኮረ ሐሳብ ያላቸው 41 ስራ ፈጣሪዎችን ደግፎ ለውጤት ማብቃቱን 'ሪች ፎር ቼንጅ' አስታወቀ
ከ74 በላይ ፕሮጀክቶች ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው 'ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ' የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ግብዓቶችን መልሶ በመጠቀም ዘርፍ ለተሰማሩ 41 ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ በማድረግ ለፍሬ ማብቃቱን ገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መቅድም ጉልላት፣ ተቋማቸው "በ'ሰርኩላር ኢኮኖሚ' ዘርፍ በሐሳብ ደረጃ ያሉ ጅምር ሥራዎችን ወደ ተግባር ለማሸጋገር እስከ 10 ሺህ ዶላር የሚደርስ የፋይናንስ ድጋፍ፣ የሥልጠና እና የገበያ ትስስር እያመቻቸ ይገኛል" ብለዋል።
በሌላ በኩል በዘርፉ የተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች የማሽነሪ፣ የካፒታል እና የብድር መያዣ ማጣት ትልቅ ፈተና እንደሆነባቸው ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።
ይህንን ዘላቂ ችግር ለመፍታት የመንግሥት፣ የፋይናንስ ተቋማትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑን መቅድም ጉልላት አፅንኦት ሰጥተዋል።
በደረጄ መንግስቱ

7 days ago
ግሪክ ለአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የጥገኝነት ጥያቄዎችን በጊዜያዊነት ማገድ እንዲችሉ ጥያቄ አቀረበች
ግሪክ የህብረቱ ስደተኞች ስምምነት ትልቅ መሻሻል ቢያሳይም ድንገተኛ ቀውሶችን ለመቆጣጠር በቂ አለመሆኑን ገልጻለች። ኔዘርላንድም ይህንን ሀሳብ በመደገፍ እንደ ሴኡታ ያሉት መጠነ-ሰፊ የመጤዎች መረባረብ ከጥገኝነት ይልቅ እንደ ድንበር አስተዳደር ጉዳይ ሊታይ ይገባል ብላለች።
ባለፈው ሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ብቻ ከ72 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ስፔን ከሰሜን አፍሪካዊ ግዛት ሴኡታ መግባታቸው ይገመታል። ምንም እንኳን አብዛኞቹ ቢመለሱም፣ 10 ሺህ ያህሉ አሁንም በመቆየታቸው በአውሮፓ ከተሞች ውስጥ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወሰዱ ጥሪዎች እንዲጠናከሩ አድርጓል።
የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ኮሚሽነር ማግኑስ ብሩነር ፍልሰት የጸጥታ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ፣ ከአለም አቀፍ ህግጋት እና መሰረታዊ መብቶች ጋር የተጣጣመ ድንበር የመጠበቅ አቅም እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በዚህም ስብሰባ ላይ አባል ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት ውጪ የመመለሻ ማዕከላት እንዲያቋቁሙ የሚያስችል አዲስ ደንብ ጸድቋል። ሩዋንዳ ከበርካታ የአውሮፓ ሀገራት ጋር እንደዚህ አይነት ማዕከልን አስተናግዳለው በሚል ቀዳሚ ውይይቶችን አድርጋለች። ግሪክ፣ ኔዘርላንድ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያ እና ዴንማርክን ያካተተው የአምስት ሀገራት ቡድን በጥር 2027 ዓ.ም. ዝውውሮችን ለመጀመር እቅድ ይዟል።ይህ ዜና አውሮፓ ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እና ድንበርን አጥብቆ የመቆጣጠር አቅጣጫን እየተከተለች መሆኑን ያሳያል።
ትግስት ላቀው

10 ሺህ የቡና ሲኒዎች የተሰበሰቡበት ዝግጅት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰፈረ
በኢትዮጵያ የቡና ታሪክና ባህልን ከቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት 10 ሺህ ባህላዊ የቡና ሲኒዎች የተሰባሰቡበት ዝግጅት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ማስፈሩ ተገለጸ።
ምስራቅ አፍሪካ ኢንተርቴመንት ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ መርሃ-ግብር፣ በልዩ ዲዛይን የተገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህል እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ እስከዳር ግሩም እንዳስረዱት፣ የቡና ሥነ-ሥርዓት ለሽምግልና እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች የሚያገለግል ባህላዊ እሴት ነው።
ባህሉን በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ እና የቱሪዝም አበርክቶውን ለማሳደግ በቀጣይ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሥራ አስኪያጅ አሸናፊ ዓለሙ በበኩላቸው፣ ክንውኑ ሀገራዊ የቡና ከፍታን ከማሳየት ባለፈ ለአፍሪካ የባህልና ቱሪዝም ልማት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94

8 days ago
በአንድ ቦታ 10 ሺህ ስኒ ቡና መጠጣቱን ተከትሎ የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ተመዘገበ
#ethiopia | በአዲስ አበባ 10 ሺህ ስኒ ቡና በአንድ ቦታ በማዘጋጀትና በማጠጣት የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ተመዘገበ
በአዲስ አበባ 10 ሺህ ስኒ ቡና በአንድ ቦታ በማዘጋጀትና በማጠጣት የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ መመዝገቡ ተገለጸ።
የቡና ጠጡ ሥነ-ሥርዓቱ በኢስት አፍሪካ ቢዝነስ ግሩፕ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓልንና የዓለም የቡና ቀንን በማስመልከት መካሄዱ ታውቋል።
በዝግጅቱ 100 ኪሎ ግራም ቡና እና 10 ሺህ የቡና ስኒዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። ለዚህም 200 ሊትር የሚይዝ ትልቅ ጀበና እና 18 ሜትር ዙሪያ ያለው ረከቦት ተዘጋጅቷል።
10 ሺህ ስኒ ቡና መጠጣቱም በሶፍትዌር በተደገፈ የቆጠራ ሥርዓት መረጋገጡ ተገልጿል።
በተለይም የቡና ጠጡ ሥነ-ሥርዓቱ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔን በዓል ለማክበር ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን በባህላዊ የቡና ሥነ-ሥርዓት ለመቀበልና ቡና እንዲጠጡ ለመጋበዝ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
አዘጋጆቹ ዝግጅቱ የኢትዮጵያን የቡና ባህልና ቅርስ ለአፍሪካና ለዓለም ማስተዋወቅ፣ የቡና ባህሉንም በሰፊው ማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
#ethiopia #ethiopiancoffee #coffeeceremony #coffeeculture #africanrecord #guinnessrecord #addisababa #irreecha #horafinfinne #worldcoffeeday #ethiopianculture #coffeelovers

Sponsored by
Surafel
8 days ago
በአዲስ አበባ 10 ሺህ ስኒ ቡና በማጠጣት በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለመመዝገብ ያለመ መርሃ ግብር ተካሄደ
#fastmereja I በዘንድሮው የኢሬቻ ዋዜማ የኢትዮጵያን የቡና ባህል፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትስስር የሚያጎላ ታላቅ የቡና መጠጣት እና በአፍሪካ ድንቃድንቅ ሪኮርድ የማስመዝገብ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በግዮን ሆቴል ተካሂዷል።
በኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይንመንትና ኤቨንት ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር በርካታ ሴቶች ቡናውን በማፍላትና በማስተናገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፣ 10 ሺህ ቡና ሲኒ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በአንድ ቦታ ተሰባስበው ቡና እንዲጠጡ ተደርጓል።
ዝግጅቱ የኢትዮጵያን የቡና ባህል በዓለም አቀፍ እና በአፍሪካ ደረጃ በድንቃድንቅ መዝገብ (Guinness World Records) ላይ ለማስመዝገብ ያለመ ታላቅ ጥረት አካል መሆኑም ተጠቅሷል።
በዝግጅቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ታድሟል።

9 days ago
ሞዴል ሀሴት ደረጄ የ«ጎዶ ሀውሲንግ ስማርት ሪል ስቴት» ብራንድ አምባሳደር ሆና ተመረጠች
የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ በአዲስ አበባ በማስገንባት ላይ ያለው ጎዶ ሀውሲንግ ስማርት ሪል ስቴት ፕሮጀክት ሞዴል ሀሴት ደረጄን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙ አስታውቋል።
ሞዴሏ ከአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት ውል መፈራረሟን ተከትሎ የሪል ስቴት ፕሮጀክቱን በማስተዋወቅና በማስተዋወቂያ ሥራዎች ላይ እንደምትሳተፍ ታውቋል።
በአዲስ አበባ በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚገነባው ፕሮጀክቱ በቴክኖሎጂ የተደገፉና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጄ ማሙዬ እንደገለፁት የፕሮጀክቱን ግንባታ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 27 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ እንደሚደረግበት ተናግረዋል።
ተቋሙ እስካሁን ካከናወናቸው የቤት ልማት ሥራዎች ውስጥ 500 የሚደርሱ ቤቶች መሸጣቸውን ተገልጿል። ቀሪ ቤቶችም ለገዢዎች በማስተዋወቅና በመሸጥ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።
አዲሱ የቤት ልማት ፕሮጀክትም በ30 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ዕቅድ ተይዟል።
አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት 500 ሺህ ቤቶችን በመገንባት የሀገሪቱን የቤት ፍላጎት ለመመለስ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ገልጿል።
የቤት ልማት ሥራውንም ከአዲስ አበባ ባሻገር ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ለማስፋፋት ዕቅድ መያዙ አስታውቋል።

11 days ago
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሕገወጥ መንገድ ወደ መሬት ባንክ ተዘዋውረዋል የተባሉ የይዞታ ቅሬታዎችን ለመመርመር ኮሚቴ አቋቋመ
የከተማው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከ250 በላይ የሚሆኑ የይዞታ ባለቤቶች ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች መርምሮ ውሳኔ የሚሰጥ አሠራር መዘርጋቱን አስታውቋል። ቢሮው እንዳለው ቅሬታዎቹ የተነሱት በ2015 ዓ.ም በመላው ከተማ በተካሄደው ባዶ መሬት ጥናትና ኦዲት ሲሆን፣ በወቅቱ 3 ሺህ 744 ሄክታር መሬት (10 ሺህ 97 ይዞታዎች) ከሕገ-ወጥ ይዞታዎች ተመልሰው ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል።
የመሬት ባንክና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ክፍሎም አሰፋ እንደገለጹት፤ ኦዲቱ በዘመቻ መልክ የተካሄደ በመሆኑ ቅሬታዎች ሊነሱ ችለዋል። ለዚህም በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ የተቋቋሙት ኮሚቴዎች የእያንዳንዱን ይዞታ ነባራዊ ሁኔታ መርምረው የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ብር ሜትሪክስ ዘግቧል።
ቢሮው የሕጋዊ ባለቤቶች መብት እንዲከበር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ፣ እንዲሁም የሕዝብና የመንግሥት መሬት ከወረራ እንዲጠበቅ የተጀመረው የማስተካከያ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዳለበት ማሳሰቡም በዘገባው ተመልክቷል።
Seledadotio

12 days ago
በ2015 ዓ.ም ወደ መሬት ባንክ በገቡ ይዞታዎች ላይ ከ250 በላይ ቅሬታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቋመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2015 ዓ.ም በተከናወነው ከተማ አቀፍ የባዶ ቦታ ልየታና ኦዲት ወቅት ያላግባብ ወደ መሬት ባንክ ገብተዋል ተብለው የቀረቡ ከ250 በላይ ቅሬታዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መርምሮ ውሳኔ የሚሰጥ አጣሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታወቀ።
በወቅቱ በተካሄደው የባዶ ቦታ ልየታ 3 ሺህ 744 ሄክታር ወይም 10 ሺህ 097 ፕሎቶች "ከሕገ-ወጥ ወረራ ተመልሰው ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ ተደርጓል" ሲሉ የመሬት ባንክና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ አቶ ክብሮም አሰፋ ገልጸዋል።
ስራው በአጭር ጊዜና በዘመቻ መከናወኑን ተከትሎ የቀረቡትን ከ250 በላይ የቅሬታ ማመልከቻዎች እንደየይዞታው ሁኔታ መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥ አጣሪ ኮሚቴ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ቢሮው አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

13 days ago
1ሺህ 400 እናቶችን ያሳተፈው የቢሊ ነፂ የ45 ቀናት የክብደት መቀነስ ፕሮግራም ተጠናቀቀ።
👉አንደኛ ለወጣችው ክብደት ቀናሽ እናት የ100ሺ ብር ሽልማት ተበርክቷል።
የ3ኛው የቢሊ ነፂ የክብደት መቀነስ ውድድር ታላቁ ፍጻሜና የሽልማትF ሥነ-ሥርዓት የተካሄደ ሲሆን በ45 ቀናት በቆየው በዚህ ዙር 1 ሺህ 400 እናቶች መሳተፋቸው ተገልጿል።
ተሳታፊዎቹ በአመጋገብ ለውጥ፣ በእንቅስቃሴና በተከታታይ ጥረት ያሳዩትን የአካል ለውጥ ተከትሎ ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።የቢሊ ነፂ ፊቲነስ መሥራች ቢሊሱማ ደበሌ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት የክብደት መቀነስ ሂደት በአመጋገብና በእንቅስቃሴ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ከአዕምሮና ከአመለካከት ለውጥም መጀመር እንዳለበት ተናግረዋል።
በተለይም እናቶች ከቤታቸው ሳይወጡ በኦንላይን ኮችንግ፣ በአመጋገብ መመሪያና በቤት ውስጥ በሚከናወኑ የእንቅስቃሴ ሥልጠናዎች እንዲሳተፉ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
ቢሊሱማ ደበሌ የክብደት መቀነስ ልምዳቸውን የጀመሩት ከራሳቸው ላይ መሆኑን ጠቁመው በተለያዩ የክብደት መቀነስ ሂደቶች 50 ኪሎ ግራም ያህል መቀነሳቸውን ተናግረዋል።
በራሳቸው ልምድ ያጋጠሟቸው ችግሮችና የጤና ፈተናዎች ሌሎች ሴቶችን ለመደገፍ እንዳነሳሷቸውም ተናግረዋል።በተለይም ከወሊድ በኋላ የሚከሰቱ የክብደት ለውጦችና የአእምሮ ጫናዎች ብዙ እናቶችን እንደሚፈትኑ የተጠቋሞ ሲሆን የቢሊ ነፂ ፕሮግራም የአካል ለውጥን ብቻ ሳይሆን የራስ መተማመንና የአዕምሮ ዝግጁነትንም ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገልጿል።
በውድድሩ አንደኛ የወጣችው ተሳታፊ ከ112 ኪሎ ግራም አካባቢ በመነሳት 18 ኪሎ ግራም በ15 ቀን መቀነሷ ተገልጿል።
ለአንደኛ ደረጃ 100 ሺህ ብር፣ ለሁለተኛ ደረጃ 70 ሺህ ብር እና ለሶስተኛ ደረጃ 50 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል። ከ4ኛ እስከ 10ኛ ደረጃ ለወጡ ተሳታፊዎችም እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር ተሸልመዋል።
በቀጣይ በተለይም ከወሊድ በኋላ በክብደት መጨመርና በከፍተኛ ጫና ውስጥ ያሉ እናቶችን በነፃ ለመደገፍ የሚያስችል ትልቅ ማዕከል ለመመስረት ዕቅድ አለኝ ሲሉ የቢሊ ነፂ ፊቲነስ መሥራች ቢሊሱማ ደበሌ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ሳምራዊት ስዩም

14 days ago
#ጥቆማ
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የስልጠና ዘርፎችን በማካተት ለ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን የስልጠና መስኮች የሚያስተዋውቅበት የመረጃ ሳምንት ከመስከረም 14/2019 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት ሆኗል።
ተቋሙ የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች፦
➻ በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች
➻ በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች
➻ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) (ደረጃ 8) በሁለት ፕሮግራሞች
በኢንስቲትዩቱ የሚሰጠው ስልጠና 50 በመቶ የንድፈ-ሃሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ እንደሆነ ተገልጿል።
ተቋሙ በ16 የሳተላይት ካምፓሶች እና በሁለት ማዕከላት አማካኝነት ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
@tikvahuniversity Photo

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የደለቡ የእርድ እንስሳት እንደላሉ ተነገረ።
የሰሜን ሸዋ ዞን ለመስቀል በዓል ለአዲስ አበባ እና ለሸገር ከተማ ነዋሪዎች በቀን ከ10 ሺሕ በላይ የእርድ እንስሳት እያቀረበ መሆኑን የዞኑ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የደለቡ ሠንጋዎች፣ 1.4 ሚሊዮን የሚሆኑ በጎች እና ከ519 ሺሕ በላይ ፍየሎች ባጠቃላይ ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የደለቡ የእርድ እንስሳት መመዝገባቸውን የዞኑ ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት የእንስሣት ዝርያ ማሻሻያና ማደለብ ቴክሎነጂ ማስፋፍያ ባለሞያ ወይዘሮ ሽብሬ ፍቃዴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
የገበያ ዋጋ ለማረጋጋትም በሬ እንደየደረጃቸው ከ150 ሺሕ እስከ 370 ሺሕ ብር፤ በግ እና ፍየል ከ15 ሺሕ እስከ 30 ሺሕ ብር ድረስ እየተሸጡ ይገኛሉም ተብላል ።የመኖ ውድነት፣ የገበያ መዋዠቅ እና የበሽታ አደጋዎች በዋናነት የተጠቀሱ የዘርፉ ችግሮች መሆናቸውን የተናገሩት ባለሙያዋ ወይዘሮ ሽብሬ አዘውትሮ ክትባት በመስጠት ጥንቃቄ እየተደረገ ነውም ብለዋል።
ለበዓሉ ከሚቀርቡት እንስሳት መካከል አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት በጎች እና ሰንጋዎች ሲሆኑ፣ ህብረተሰቡ በጋራ ለሚያከናውነው እርድ ለስላሳ ቀይ ስጋ ያላቸው የኮርማ በሬዎች ተመራጭ መሆናቸው ተገልጿል።

15 days ago
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የሥልጠና ዘርፎችን በማካተት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።
👉 የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዘመኑንና የወደፊቱን የገበያ ፍላጎት ያማከሉ ናቸው ያላቸውን አዳዲስ የሥልጠና መስኮችን በማካተት የተማሪዎች ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ።
ኢንስቲትዩት እነዚህን ተጨማሪ የስልጠና መስኮች ያስተዋወቀው ከመስከረም 14/2019 ዓም ጀምሮ ክፍት የሚሆን የመረጃ ሳምንትን ይፋ ባደረገበት መርሃ ግብር ላይ ነው።
ተቋሙ ላለፉት ከ15 ዓመታት በላይ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብቸኛው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት
• በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች፣
• በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች እንዲሁም
• በሦስተኛ ዲግሪ (ደረጃ 8 / ፒኤች.ዲ) በ2 ፕሮግራሞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በተለይም በ2018 ዓ.ም ደግሞ የዓለም ገበያ የክህሎት ፍላጎትን ያገናዘቡ ናቸው የተባሉትን 11 መስኮች ማለትም :-
- ባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ፣
- የሳይበር ደህንነት፣
- አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣
- ኢንተለጀንት ሮቦቲክስ፣
- ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ
- ሆርቲካልቸር
- ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ፊኒሺንግ
- ሌዘር ፕሮዳክት
- በTVET ሊደርሺፕ እና ማኔጅመንት
- በማኑፋክቸሪንግ
- ፋሽን ዲዛይን እና በአዳዲስ ኢነርጂ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራና የወደፊት የሥልጠና መስኮች (Emerging Skills) ተቀርጸው ወደ ተግባር መግባታቸው ተገልጿል።
ሥልጠናው 50 በመቶ የንድፈ-ሀሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ ነው የተባለ ሲሆን ተቋሙ በ16 ሳተላይት ካምፓሶችና በ2 ማዕከላት አማካኝነት ከ 10 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።
ኢንስቲትዩቱ ከቻይና እና አልጄሪያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥምረት የዲግሪ ፕሮግራሞችን ከመስጠት ባሻገር፣ በየዓመቱ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሌሎች የጎረቤት ሀገራት ዜጎች ነፃ የሥልጠና ዕድል እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።
የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

17 days ago
አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡
አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡
እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡
መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

"አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል" አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
#fastmereja I የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ አፈ-ጉባኤው በሰጡት መግለጫ፤ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡
ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻም መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

18 days ago
የእናቶች ሞት ከፍተኛ የሆነባቸውን ክልሎች በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) ሚኒስቴሩ አንድ እናት አንድ ህይወት አንድ የጋራ ኃላፊነት በሚል መሪ ቃል ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩም 100ሺ የነበረውን የእናቶች ሞት 141 መቀነስ የተቻለ ሲሆን በሚቀጥሉት 4 ዓመታት 70 ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተገልጻል፡፡
በ 2030 የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የተያዘው እቅድ እንዲሳካ የጤና ባለሙያዎች እና የበላይ አመራሮች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ናቸው፡፡
የእናቶች ሞት ከፍተኛ የሆነባቸውን ክልሎች በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ አንስተው በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት አሁንም አሳሳቢ የማህበረሰብ የጤና ስጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ለእናቶች ሞት ቀዳሚ መንስኤ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅርፍ ባለፉት ዓመታት ከተሰሩ ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ጊዜውን ያገናዘበ እና በአዳዲስ ጥናቶች ላይ መሰረት ያደረጉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን ገልፀዋል።
የጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎች እና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመተባበር የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤናቸውን ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በህይወቴ ጌትነት
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/a...
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradio

23 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አትሌት ሩቲ አጋ በዶፒንግ ጊዜያዊ እገዳ ተጣለባት፡፡ የ32 አመቷ ኢትዮጵያዊት የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ሩቲ አጋ ላይ ጊዜያዊ እገዳ መጣሉን የአለም አትሌቲክስ የፀረ ዶፒንግ ተቋም አስታወቀ፡፡ በአትሌቷ ላይ እገዳው የተጣለው ‹‹ሜልቲፕሬድኒሶሎን›› የተባለ በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር በሰውነቷ ውስጥ በመገኘቱ እንደሆነም ገልጿል፡፡
እንዲሁም በምርመራ ሂደት ጣልቃ በመግባትም ክስ ያቀረበባት ሲሆን እገዳው ጊዜያዊ እንደሆነና ይግባኝም ማቅረብ እንደምትችል አስረድቷል፡፡ አትሌቷ በማራቶን፣ በግማሽ ማራቶን፣ በ10 ሺህ እና በ5 ሺ ሜትር ውድድሮች ጥሩ ሰአት ያላት ናት፡፡ ‹‹ሜልቲፕሬድኒሶሎን› የተሰኘው ንጥረ ነገር በአለም አቀፉ ፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲ በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር ቢሆንም በተለያዩ ላብራቶሪዎች በተደረገ ጥናት በአካል ብቃት ላይ ያን ያህል ለውጥ የሚያመጣ አይደለም፡፡

24 days ago
በኦሮሚያ ክልል በወጣቶች በጎ ፈቃድ 23 ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እስካሁን 23 ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል አለ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ።
በቢሮው የወጣቶች በጎ ፈቃድ አስተባባሪ ዳይሬክተር አሚኖ አማን ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር 10 ነጥብ 4 ሚሊየን ወጣቶችን ለማሳተፍ ታቅዶ እየተሰራ ነው።
በዚህም እስካሁን ድረስ 7 ነጥብ 9 ሚሊየን ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራው መሳተፋቸውን ጠቅሰው÷ በወጣቶቹ በተከናወኑ የተለያዩ ሥራዎች 23 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ወጣቶቹ ከ40 በላይ በሚሆኑ የሥራ ዘርፎች በበጎ ፈቃድ መሳተፋቸውን እና ሥራው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተመራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የተከናወነው የበጎ ፈቃድ ሥራ በገንዘብ ሲተመን ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰው ÷ የበጎ ፈቃድ ሥራ በሀገር ደረጃ የተሰጠው ትኩረት የወጣቶችን ተነሳሽነት ይበልጥ ማጎልበቱን ተናግረዋል።
ወጣቶች በከተማ ትራፊክ ማሳለጥ፣ በደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካማ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ቤት መገንባትና ማደስ እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ድጋፎች መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ እስካሁን 26 ሺህ 500 ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 18 ሺህ 620 ቤቶች መገንባታቸውንና ከ10 ሺህ በላይ ቤቶች ደግሞ መጠገናቸውን አስረድተዋል።
የበጎ ፈቃድ ሥራ ከመንግሥት ካዝና የሚወጣን ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
በዮናስ ጌትነት

የኢሬቻ ዋዜማ በደማቅ ዝግጅቶች ሊከበር ነው
#ethiopia | «ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት እና የአብሮነት» በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የዘንድሮው የፊንፊኔ ኢሬቻ ዋዜማ ፌስቲቫል፣ ባህልን፣ ስፖርትን፣ ኪነ-ጥበብንና ማህበራዊ ትስስርን በሚያጣምር መልኩ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ዝግጅቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር በመተባበር እያዘጋጀ ያለው ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴመንት እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር በዘርፉ ከ10 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑም ኹነቱን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
ፌስቲቫሉ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን፣ ከታቀዱት ዋና ዋና መርሃ ግብሮች መካከል እስከ 50 ሺህ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፈው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ይገኝበታል። ሩጫው ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለመቻቻልና ለአንድነት መልዕክት የሚያስተላልፍ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የበዓሉ ሌላው ልዩ መርሃ ግብር የ10 ሺህ ሲኒ የቡና ሥነ-ሥርዓት ነው። በጊዮን ሆቴል ከ8 እስከ 10 ሜትር ርዝመት ባለው ግዙፍ እረከቦት ላይ የሚከናወነው ይህ መርሃ ግብር የሃይማኖት አባቶችን፣ የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮችን በማሳተፍ የሰላም ውይይት የሚካሄድበት ይሆናል።
በዋዜማው ሌሊቱን ሙሉ የሚቆየው ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርትም በዓሉን ከሚያደምቁ ዝግጅቶች መካከል ተጠቅሷል። ከቀኑ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በሚቆየው ኮንሰርት በርካታ ታዋቂ አርቲስቶች የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
የ«ሚስ ዩኒቲ» የቁንጅና ውድድርም የፌስቲቫሉ አካል ሲሆን፣ የተለያዩ ባህሎችንና የሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጉላት የታቀደ መሆኑ ታውቋል።
ከእነዚህ ዝግጅቶች በተጨማሪ የኦሮሚያ ባህላዊ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል፣ የከተማዋን የኮሪደር ልማት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ጉብኝት እና ከሰላም ውይይቶች ጋር የሚቀናጁ መርሃ ግብሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
ለሙዚቃ ኮንሰርት የመግቢያ ትኬት ዋጋ መደበኛ 1,000 ብር፣ ቪአይፒ 10,000 ብር እና ቪቪአይፒ 20,000 ብር መሆኑም ተገልጿል።
#irrecha #finfinnee #irrecha2019 #ethiopia #peaceandunity #irrechafestival #eastafricaentertainment

25 days ago
የኢሬቻ ዋዜማ ፌስቲቫል ዝግጅት ሊካሄድ ነዉ!
#fastmereja :- የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ በዓሉ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበርየሚያስችሉ አራት ታላላቅ ሁነቶችን ያካተተ «የኢሬቻ ዋዜማ ፌስቲቫል» መዘጋጀቱን ተገለፀ።
ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴመንት እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር በመተባበር ነዉ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ዋዜማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ የተገለፀዉ።
በዘርፉ ከ10 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ተቋሙ፣ «ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት እና የአብሮነት» በሚል መሪ ቃል መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል የሚካሄደውን የዋዜማ ፌስቲቫል ባህልን፣ ስፖርትን፣ ኪነ-ጥበብንና ወንድማማችነትን ያቀናጁ አራት ዋና ዋና መርሃ-ግብሮችን በማካተት እንዳዘጋጀ ገልጿል።
የፌስቲቫሉ አራት ዋና ዋና መርሃ-ግብሮች
-የ50 ሺህ ሰዎች የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ፡ «ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለመቻቻል እና ለአንድነት» በሚል መሪ ቃል እስከ 50 ሺህ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት የጎዳና ሩጫ ይካሄዳል።
-የ10 ሺህ ሲኒ የቡና ሰረሞኒ ፡ በጊዮን ሆቴል ከ8 እስከ 10 ሜትር ርዝመት ባለው ግዙፍ አረከቦት ላይ የሚከናወን ሲሆን፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮች የሰላም ውይይት ያደርጉበታል።
-ታላቁ ሌሊቱን ሙሉ ኮንሰርት፡ ከቀኑ 12:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፤ በርካታ ዝነኛ አርቲስቶች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
-የ«ሚስ ዩኒቲ» የቁንጅና ውድድር፡ የሕብረ-ብሔር ውበትና አንድነትን የሚያጎላው የቁንጅና ውድድር ሌላው የበዓሉ አካል መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ለኮንሰርቱ የመግቢያ ትኬት ዋጋ መደበኛ 1,000 ብር፣ ቪአይፒ 10,000 ብር እና ቪቪአይፒ 20,000 ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በመጨረሻም መላው ሕዝብ በዝግጅቱ ላይ ተገኝቶ አብሮነቱን እንዲያሳይ ጥሪ ቀርቧል።
📷ከበደ መክብብ

29 days ago
የኢትዮጵያ ተወካይ ወጣቶች በዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል ለመሳተፍ ሩሲያ ገቡ
#ethiopia | በሩሲያዋ የካቲሪንበርግ ከተማ ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የ2026 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ተወካዮች ቦታው ደርሰዋል።
በዚህ ታላቅ መድረክ ከ196 አገራት የተወጣጡ 10 ሺህ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች እና 10 ሺህ የሩሲያ ወጣቶችን ጨምሮ በድምሩ 20 ሺህ ታዳሚዎች ይገኛሉ።
በተጨማሪም የልዩ ልዩ አገራት መሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ባለቤቶች፣ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት ተወካዮች እና ከያኒያን ይታደማሉ።
ኢትዮጵያን ወክለው ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተመረጡት እነዚህ ወጣቶች በዝግጅቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሲሆን፣ በተለይም የኢትዮጵያን ቡና እና የተለያዩ ባህላዊ ሀብቶቻችንን የማስተዋወቅ ሥራ ያከናውናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#russia #youthfestival #ethiopiancoffee #culture #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
1 month ago
አዋሽ ባንክ በአበባየሆሽ / ሽኖዬ ቲክቶክ ውድድር የ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዋሽ ባንክ መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የአበባየሆሽ / ሽኖዬ የቲክቶክ ቻሌንጅ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
ተወዳዳሪዎች በአበባየሆሽ ወይም ሽኖዬ ግጥም በማዘጋጀትና የፈጠራ ጥበብን በማሳየት እስከ 1 ሚሊየን ብር መሸለም ይችላሉ፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን በአማርኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ ግጥም በማዘጋጀት በአበባየሆሽ ወይም ሽኖዬ ዜማ ፈጠራ የታከለበት የቲክቶክ ቪዲዮ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የተሰራውን ቪዲዮም ከጳጉሜን 3 አስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ቲክቶክ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ መወዳደር፣ ማሸነፍና መሸለም ይችላሉ ፡፡
ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1. የአዋሽ ባንክን አጠቃላይ ገጽታን በተመለከተ
2. የአዋሽብር ፕሮ የዲጂታል አገልግሎት እና
3. የአዋሽ ሬሚት የዲጂታል አገልግሎት።
ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ዜማ የግጥም ይዘት ከተዘረዘሩት አንዱን በመምረጥ መወዳደር ይችላሉ።
አዋሽ ባንክ ለውድድሩ ያዘጋጀው ሽልማት፡-
1ኛ. 1 ሚሊየን ብር
2ኛ. 700 ሺህ ብር
3ኛ. 500 ሺህ ብር
ተወዳዳሪዎች የሰሩትን የቪዲዮ ማስፈንጠሪያ በዚህ ቴሌግራም https://t.me/+ma2_m3DGlTsx... መላክ ይጠበቅባቸዋል።
ተወዳዳሪዎች ለውድድር ብቁ ለመሆን ቢያንስ 500 ሺህ ቪው እና 10 ሺህ ላይክ ማግኘት አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ እና የመወዳደሪያውን ደንብና ሁኔታዎች ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን https://t.me/awash_bank_of... ይጫኑ!
ተወዳዳሪዎች የአዋሽ ባንክን የቲክቶክ ገጽ መጥቀስ https://www.tiktok.com/@aw... አለባቸው።

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከ2ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዛሬው ዕለት ከ2ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀምሯል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ፥ ተቋሙ በተለያዩ መልኮች ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በሪፎርም ወደ ትርፋማ ምዕራፍ ተሸጋግሯል ብለዋል።
በዚህም ተቋሙ ትርፉን በ42 እጥፍ ማሳደግ መቻሉንና በዛሬው ዕለትም ከ2ሺ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው ግንባታ በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ በአልሚዎች ትብብር የሚገነባ ሲሆን ባለስድስት ወለል ሕንፃና በቂ የመኪና ማቆሚያ፣ዘመናዊ መዝናኛ ቦታዎችን ከነሱቆቹ የያዘ ነው።
ዋና ስራ አስፈጻሚው በሱቆቹ ለልማቱ የሚነሱት 230 ነባር ተከራዮችን ጨምሮ ተጨማሪ ዜጎች እድል እንደሚፈጠርላቸውም አስረድተዋል።
ኮርፖሬሽኑ በአንድ ዓመት ውስጥ አስር ህንፃዎችን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙንና ወደ 10 ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ግንባታዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አንስተዋል።
በሌላ በኩል የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመርካቶ ያስገነባውቸን 399 ሱቆችንም በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በአሸናፊ ሽብሩ

ለአዲስ ዓመት የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተከናውኗል ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ህብረተሰቡ በደስታና በመረጋጋት እንዲያከብር የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የጥገና ሥራ ማከናወኑን ገልጿል።
በአዲስ ዓመት በዓል ወቅት የሚያጋጥሙ የኃይል ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ 24 ሰዓት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክ ቡድን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀት ወደ ሥራ መግባቱን ተቋሙ ተናግሯል።
በተጨማሪም በሁሉም የአገልግሎቱ ሪጅኖችና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አጣዳፊ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ የጥገና ቡድኖች ተደራጅተዋል። በዚህም በነሐሴ ወር በመላ አገሪቱና በአዲስ አበባ 2 ሺህ 110 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ የኃይል መስመር ተፈትሿል።
በፍተሻው የተለዩ 10 ሺህ 308 የኃይል መቆራረጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮችም ተስተካክለዋል ተብሏል። ከ8ሺህ በላይ ትራንስፎርመሮች የተፈተሹ ሲሆን በ6 ሺህ 877 ትራንስፎርመሮች ላይ የተለዩ የቴክኒክ ችግሮች ተፈትዋል።
በበዓሉ ዋዜማ ሊከሰት የሚችለውን ተጨማሪ የኃይል ጭነት ለመቋቋምም 178 ትራንስፎርመሮች አቅማቸው ተሻሽሏል። በተጨማሪም ከ3 ሺህ በላይ ትራንስፎርመሮች የዘይት መሙላትና የጥገና ሥራ ተደርጎላቸዋል። በበዓሉወቅት ለሚያጋጥሙ ድንገተኛ የኃይል ችግሮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም 24 ሰዓት የሚሰሩ የቴክኒክና የጥገና ቡድኖች መዘጋጀቱን የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ተቋሙ በበዓሉ ወቅት ደንበኞች ኃይል ቆጣቢ ቁሳቁሶችን እንዲጠቀሙና የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶቻቸውን ለአደጋ እንዳያጋልጡ ጥሪ አቅርቧል። የኤሌክትሪክችግር ወይም የጥገና ጥቆማ ሲኖር ደንበኞች በ905 በነፃ በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ ሲሉ አቶ አንዋር አብራር ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ያለፍላጎታቸው ሴቶችን በወሲብ ንግድ ላይ ያሰማሩት አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡
በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አስተዳደር በመጠጥ ግሮሰሪ ንግድ ፈቃድ ሽፋን ሴቶችን ያለ ፍላጎታቸው ለወሲብ ንግድ ሲዳርጉና ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ አምስት ግለሰቦች እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን የከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
የሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹ በዘይበላ ወላሼ ቀበሌ «ኤል ክላሲኮ» የተባለ የምሽት ጭፈራ ቤት በመክፈት ሴቶችን በአስተናጋጅነት ካስቀጠሩ በኋላ በግዳጅ ለዝሙት አዳሪነት እንዲሰማሩ አድርገዋል።
ፖሊስ ባደረገው ማጣራት አንደኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ የንግድ ፈቃዱን በማውጣትና ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን የተቀጠሩ አስተናጋጆችን ያለፍላጎታቸው የግብረ-ሥጋ ድፍረት ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ማድረጉ በበቂ ማስረጃ ተረጋግጧል።የቀረበውን የዐቃቤ ሕግ ክስና የፖሊስ ማስረጃ የመረመረው የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፋል።
በዚህም መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ ድርጊቱን በዋናነት በመምራትና በግዳጅ የመድፈር ጥቃት በመፈጸሙ በ23 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ200 ሺህ ብር መቀጮ፤ 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ደሴ በ10 ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር መቀጮ፤ 3ኛ ተከሳሽ ወርቁ ደሜ በ6 ዓመት እስራት እና በ45 ሺህ ብር መቀጮ፤ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ተመስገን ፍቃዱ እና ቤክና መሐመድ ደግሞ እያንዳንዳቸው በ1 ዓመት ከ8 ወር እስራትእንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

በሀሰተኛ ሰነድ ማጭበርበር ወንጀል ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ።
ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ ጠዋት ከእስር ተፈተው በአሁኑ ሰዓት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
ግለሰቡ በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማውጣት በመሞከራቸው፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የአምስት ዓመት እስራት እና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተፈርዶባቸው የነበረ መሆኑ ይታወሳል።
ከእሳቸው ጋር አብረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ሌሎች ሁለት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው የአራት ዓመት እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው እንደነበር አይዘነጋም።
ተከሳሾቹ የወንጀል ሕጉን እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ተላልፈዋል በሚል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው በኋላ፣ ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ በይፋ ከእስር ተለቀዋል።

2 months ago
ኤርትራዊቷ ሞዴል ስኒት ሀብተአብ በ2 ሰዓት ውስጥ 100ሺ ድምጽ አገኘች
#fastmereja I በዓለም አቀፉ Miss World ውድድር ኤርትራን ወክላ በመሳተፍ ላይ የምትገኘው ሞዴል ስኒት ሀብተአብ በህዝባዊ የኦንላይን ድምፅ አሰጣጥ በዓለም ደረጃ የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ አዲስ ታሪክ አስመዘገበች።
በቀረበው ወቅታዊ መረጃ መሰረት ሞዴል ስኒት ሀብተአብ በተደረገላት ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በሁለት ሰዓታት ውስጥ ብቻ 100 ሺህ ተጨማሪ ድምፆችን በማከማቸት አጠቃላይ ያገኘችውን የድምፅ መጠን ከ700 ሺህ ወደ 800 ሺህ በላይ ማሳደግ ችላለች። ይህም በውድድሩ የህዝብ ድምፅ ምዕራፍ እየመራች ሲሆን የድምፅ አሰጣጡ ፍጥነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ ታይቷል።
በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ሞዴል ሩት ድምጽ አሰጣጥ ምሽቱን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ቅስቀሳ እየተደረገላት ሲሆን በርካታ ድምጽ እያገኘች ትገኛለች።

Comments