1 month ago
ጆኒ ተጋጣሚውን ሴዶን በመጀመሪያው ዙር በመርታት የMMA የክብር ቀበቶውን ተቀዳጀ
#Ethiopia | በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው ደማቅ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር ጆኒ ተጋጣሚውን ሴዶን በመጀመሪያው ዙር በፍጥነት በማሸነፍ የክብር ቀበቶውን ተረክቧል።
በተደራጀ የመድረክ ዝግጅት፣ በታዳሚዎች ደማቅ ተሳትፎና በስፖርተኞች ብርቱ ፉክክር የተካሄደው "አድዋ ፋይት ናይት 2" የሀገራችንን የማርሻል አርት ውድድር ደረጃ ከፍ ባደረገ መልኩ ተጠናቋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከዋናው የMMA ፍልሚያ በተጨማሪ የቦክስ እና የሞይታይ (Muay Thai) ውድድሮች ተካሂደው የተመልካቹን ቀልብስበዋል።
በዕለቱ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች በተገኙበት ጆኒ የበላይነቱን በማስመስከር የደማቁ ምሽት አሸናፊ መሆን ችሏል።
#mma #adwafightnight #adwafightnight2 #johnny #ethiopiamma #martialarts

2 months ago
"ከሀገሬ አልኮበለልኩም፤ በቀረችኝ እድሜዬ ሀገሬን ማገልገል ነው የምፈልገው" — ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ከሀገር ኮበለሉ ተብሎ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ይሰራጭ የነበረውን መረጃ ሙሉ በሙሉ በማስተባበል ዛሬ በአካል ተገኝተው ምላሽ ሰጡ።
ኮሚሽነሩ በሰጡት ማብራሪያ "እኔ ከሀገሬ አልኮበለልኩም፤ አልሸሸሁም፤ በቀረችኝ አጭር እድሜዬም ሀገሬን ነው ማገልገል የምፈልገው" ሲሉ የተዛመተውን ሀሰተኛ ወሬ አክሽፈውታል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት ፕሮፌሰር መስፍን ሀገር ጥለው መውጣታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችና መገናኛ ብዙሃን ሲናፈሱ መቆየታቸው ይታወሳል።
የፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በዛሬው ዕለት በአካል መገኘትና የሰጡት የማስረገጫ ቃል ባለፉት ቀናት ሲናፈሱ የነበሩትን ውዥንብሮች በሙሉ የሻረ ሲሆን እሳቸውም የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ያረጋገጠ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago
''የውቦች ንግስት''
በምህረት
#Ethiopia | ምህረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአዲስ ከተማ መሰናዶ ተከታትላ ጨርሳለች።
ቀጥሎም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት በመመረቅ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ናት።
የጋዜጠኝነት ሞያን ከከፍታ የትምህርት ሥልጠና እና የማማከር ተቋም ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በፋክት ቼኪንግ እና ሌሎችም ተያያዥ ሥልጠናዎችን ከሌሎች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ተቋማት በሰርተፊኬት ማግኘት ችላለች።
ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሙሉ የልጅነት ሕይወቷ ያለፈው በደብረ ገሊላ አማኑኤል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ላለችበትም መሰረት የጣለችው ሰንበት ትምህርት ቤት በነበረችበት ወቅት ነው። በተለይም በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ዝንባሌ ሊኖራት የቻለው ከልጅነት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤት እና በመደበኛ ት/ቤት በነበራት ተሳትፎ ነው። እንደ ግጥም ፣ መነባንብ ፣ ድራማ እና ሌሎችም ላይ የበዛ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ይህ ተሳትፎ አሁንም ድረስ ተከትሏት በመምጣት ለፍሬ እንደደረሰ ታምናለች።
በት/ቤት ፣ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ብሎም በከተማ አቀፍ በነበሩ የሥነ-ጸሑፍ ውድድሮች ፣ መድረኮች እና መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ሽልማቶችን እና የምስጋና ወረቀቶችን ማግኘት ችላለች። በመንፈሳዊም በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ በነበሯት ተሳትፎዎች በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች። እስከዛሬ ድረስም በተለያዩ የሥነ-ጸሑፍ መድረኮች ሥራዎቿን እያቀረበች ትገኛለች።
ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀች በአጼ ፋሲል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሁለት ዓመት ያህል በመምህርነት አገልግላለች። በሞያው በቆየችባቸው ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የምስጋና እና የደረጃ ሽልማቶችን ማግኘት ችላለች።
ከዚያ በመቀጠል በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራች ሲሆን ፤ የራሷን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እና ሥራዎች በመሥራት ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በሐገሬ ቴሌቪዥን በከፍተኛ ሪፖርተርነት መደብ እየሠራች የምትገኝ ሲሆን ፤ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በዚሁ ጣቢያ የዜና ክፍል ባልደረባ በመሆን ቆይታለች።
ከልጅነት ጀምሮ የተከተላት የሥነ-ጽሑፍ ፍቅር አሁንም ድረስ ተከትሏት የመጣ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የሆነውንና ” የውቦች ንግሥት” ስትል የሰየመችውን መጽሐፏን ለአንባቢያን ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% እንዲሆን ተወሰነ
📌10,000 ብር (ወርሃዊ ኪራይ) * 11.5% (አዲሱ ስሌት) = 1150 ብር (ጭማሪ)
#Ethiopia | የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር በመዲናዋ በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሠራሮችን ለመግታትና የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ያስችላል ያለውን አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል።
ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎም በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ዕድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅሕፈት ቤቶች በይፋ መተግበር ጀምሯል።
ቢሮው እንዳመለከተው ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው።
ቢሮ'ው ''አዲሱ አሠራር በአንድ በኩል አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዮች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና ከሥነ-ልቦና ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል'' ብሏል።

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያገኙትን የ50 ሺህ ዶላር ሽልማት ወደ ኢትዮጵያ ልከውታል
#Ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/ኢየሱስ በየካቲት 2023 ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ያገኙትን የ50 ሺህ ዶላር የሽልማት ገንዘብ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ ለሚያደርጉ ሁለት ድርጅቶች በሙሉ መለገሳቸው ታውቋል።
ይህ የተበረከተው የገንዘብ ድጋፍ "ማምስ ፎር ማምስ" ለተሰኘው ድርጅትና "የትግራይ ሴቶች ማኅበር" በእኩል መጠን መከፈሉን ሁለቱ ተቋማት ማክሰኞ ዕለት በመቀሌ ከተማ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ድርጅቶቹ እንደገለጹት የተደረገላቸው ይህ ልገሳ በጦርነቱ ወቅት የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች የመልሶ ማቋቋሚያና የዕለት ተዕለት የኑሮ መደገፊያ እገዛዎችን ለማቅረብ የሚውል ሲሆን ይህም ተጎጂዎቹ የደረሰባቸውን ቀውስ ተቋቁመው ሕይወታቸውን በአዲስ መልክ መልሰው እንዲገነቡ አቅም ይፈጥርላቸዋል ተብሏል።

Sponsored by
Surafel
3 months ago
''ለበዓለ ሲመት አንደግስም ፤
ቡና አፍልተን ፈንድሻም ቆልተን እናልፈዋለን'' ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
#Ethiopia | የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱሏቸው ጥያቄዎች መልስ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲያቸው ብልጽግና ማሸነፉን ተከትሎ የዛሬ አምስት ዓመት ''አዲስ ምዕራፍ'' በሚል ማዕቀፍ የመስቀል አደባባይን የመዝጊያ ፕሮግራም ጨምሮ በተዋረድ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲደረገ የቆየ ቢሆንም ዘንድሮ ግን እንዲህ ያለ ነገር እንደማይኖር ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባስተላለፉት መልዕክት “ለበዓለ ሲመት ድግስ አንደግስም፤ ቡና አልፍልተን ፈንድሻም ቆልተን እናልፈዋለን” ብለው ክብረ በዓሉን ያለምንም የተጋነነ ወጪና አላስፈላጊ ብክነት እናልፈዋለን ፤ መንግስት ያለ ድግስ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል ።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን ለመቀላቀል የ295 ሚሊዮን ዶላር አክሲዮን ልትገዛ ነው
#Ethiopia | የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያጸደቀው የሕግ ረቂቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲጸድቅ፤ ኢትዮጵያ የባንኩ ይፋዊ አባል ለመሆን የሚያስችላትን የ295 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን 2,945 አክሲዮኖች ትገዛለች።
ከተቀመጠው ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ ውስጥ አገሪቱ 20 በመቶውን ማለትም 58.9 ሚሊዮን ዶላር ቅድመ ክፍያ የምትፈጽም ሲሆን ቀሪው 80 በመቶ ክፍያ ደግሞ በ14 ተከታታይ ክፍያዎች በ13 ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
አዲስ ልማት ባንክ በ5 ዓመት ስትራቴጂው 30 በመቶ የሚሆነውን ብድር በአባል አገራት የሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመስጠት ያቀደ በመሆኑ በስፑትኒክ ዘገባ መሠረት ይህ አባልነት ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባላት ጋር በራሷ የገንዘብ ኖት የመገበያየት ሰፊ ዕድል ይፈጥርላታል።

5 months ago
ዓለም ዋንጫ ወደ ሀገሬ መጥቷል!
— ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆነ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ተቀየረ! ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም ዋንጫን በቀጥታ የማስተላለፍ ብቸኛ መብት ማግኘቱን በይፋ አስታውቋል።
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚዘጋጀውን የ2026 የዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup 2026) ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ በነፃ (FTA - Free To Air) በቀጥታ ያስተላልፋል።
ከሰኔ 04 እስከ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም. የሚካሄዱትን ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልካቾች በቤታቸው ሆነው ያያሉ።
ከዓለም ዋንጫ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸውን የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድሮች እስከ 2029 ዓ.ም. ድረስ በብቸኝነት የማስተላለፍ መብትንም ተቆጣጥሯል።
ጨዋታዎቹን በጥልቅ ትንታኔ፣ በልዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶችና በደመቁ ስቱዲዮዎች ለማቅረብ ጣቢያው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
"ይህ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የስፖርት ወዳጆች ትልቅ ኩራት ነው። የግል ጣቢያዎች እንዲህ ባለ ዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደራቸው ለኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት ነው። አሁን ኳስ ለማየት 'ሳተላይት' እና 'ክፍያ' ብሎ መጨነቅ ቀረ፤ ሀገሬ ቴሌቪዥን ዓለምን ወደ ቤታችን አምጥቶታል።"
የስፖርት ድግሱ በሀገሬ ቴሌቪዥን ይደምቃል!
#getu #hagerietv #fifaworld Cup2026 #ethiopianmedia #sportnews #worldcupinethiopia #athletics2029 #breakingnews #ሀገሬቴሌቪዥን #ዓለምዋንጫ #ስፖርት #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

9 months ago
ስፖርት ቱሪዝም በአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች
#Ethiopia | ምሽቱ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ደምቋል !
በአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን አዘጋጅንት፤ በስፖርት አፍቃሪያን ንቁ ተሳትፎ አድዋ ሙዚየምና አካባቢው ልዩ ውበት ተላብሷል፡፡
"ስፖርት ቱሪዝም በአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች!"
#addisababa #adwamuseum #masssport #fitcorner #healthylifestyle #ethiopia #tourismethiopia #citylife

Comments