3 months ago
"ኢራን ትራምፕን ለመግደል ሞክራለች" — የአሜሪካ መከላከያ
የኔታ ሚዲያ
የአሜሪካ ጦር በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ አቅዶ የነበረውን የኢራን ልዩ ቡድን መሪ መግደሉን አስታወቀ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴዝ (Pete Hegseth) በፔንታጎን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢራን ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለመግደል ሞክራ ነበር ነገር ግን መጨረሻ ላይ የሳቁት ትራምፕ ናቸው ብለዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት ባለፈው ማክሰኞ (የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.) የአሜሪካ ጦር ባከናወነው ኦፕሬሽን ትራምፕን ለመግደል አቅዶ የነበረውን የልዩ ክፍል መሪ አድኖ ገድሏል ሆኖም የተገደለው ግለሰብ ማንነት በስም አልተጠቀሰም።
እ.ኤ.አ. በ2024 የአሜሪካ መንግስት ፋርሃድ ሻኬሪ የተባለ የ51 ዓመት አፍጋኒስታናዊ ግለሰብ ላይ ክስ መስርቶ ነበር ግለሰቡ ትራምፕ ከመመረጣቸው በፊት ግድያ እንዲፈጽም በኢራን ታዝዞ እንደነበር ተገልጿል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ በወቅቱ የቀረበውን ክስ መሰረት ቢስ ውሸት በማለት አስተባብለውታል።
ዶናልድ ትራምፕ በ2024 ብቻ ሁለት የግድያ ሙከራዎች አስተናግደዋል። በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ በጠመንጃ ጆሯቸውን ተመተው የነበረ ሲሆን፣ በሴፕቴምበር ወር ደግሞ በፍሎሪዳ ጎልፍ ሲጫወቱ ሌላ ተኳሽ ተይዞባቸዋል።
ባለፈው ወር ብቻ ኦስቲን ቲ ማርቲን የተባለ የ21 ዓመት ወጣት በጠመንጃና በነዳጅ ጋን የታጥቆ የትራምፕ መኖሪያ በሆነው ማር-አ-ላጎ (Mar-a-Lago) ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥሶ በመግባቱ በደህንነት ኃይሎች ተገድሏል።
እንደ አሜሪካ አቃቤ ህግ መረጃ ፋርሃድ ሻኬሪ በሰባት ቀናት ውስጥ ትራምፕን ለመግደል እቅድ እንዲያቀርብ በኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) ታዝዞ ነበር።
ሻኬሪ ግን በሰባት ቀን ውስጥ እቅዱን ማቅረብ አልችልም ማለቱን ተከትሎ ኢራን ትራምፕ በምርጫው አይሸነፍም ብላ ስላላሰበች ከምርጫ በኋላ መግደል ይቀላል በሚል እቅዱን ለጊዜው አዘግይታው እንደነበር ተገልጿል።
ሻኬሪ በልጅነቱ ወደ አሜሪካ የገባ ቢሆንም በታጠቁ ዘረፋ ወንጀሎች ለ14 ዓመታት ታስሮ ከቆየ በኋላ ከአሜሪካ ተባሮ ወደ ኢራን ማቅናቱ ይታወቃል።

4 months ago
#በእንተ - ግርማ!
#ethiopia | በግርማ ሙዚቃዎች ውስጥ ሁሉ ያለችው ሴት አንድ ናት፡ ፡የሚወዳት የሚያኮርፋት፣ የሚቀርባት የሚርቃት እሷን ብቻ ነው-እጸገነትን፡፡ እጸገነት ገብረሥላሴ የልጅነቱ ናት፤ የልጁም እናት፡፡ በንጹሕ ልቡ የወደዳት፤ የምትወደው፡፡ “ሴት አላምንም” ፣ “ትወጅኝ እንደሁ”፣"ቁርጡን ንገሪኝ"እና “ፍቅር እንደክራር”ብሎ ያዜመላት፡፡ “ይበቃናል” ብሎ ያንጎራጎረውም ለእጸገነት ነው- የራቀችው ቢመስለው፡፡ ግን አይሆንለትም፡፡"ጥሩልኝ ቶሎ" ይላል፡፡
አቃተኝ ፍፁም መለየት
እሷን ከመሰለ ወጣት
ጥሩልኝ ቶሎ በፍጥነት
ትድረስ በነፍሴ ሳልሞት
ፍፁም ፍፁም አልተዋትም
ካለሁ በሕይወት አረሳትም...
"ጥሩልኝ ቶሎ" የግርማ የአፍላነት ዜማ ነበር፡፡ ኋላ ግን የአሳዛኝ ሕይወቱ ማጀቢያ ሙዚቃ ሆነ፡፡ በፍቅራቸው ሰሞን ስትጠፋበት "ጥሩልኝ ቶሎ"ብሎ ያንጎራጎረላት እጸገነት በጎልማሳነቱ ዘመን ጥላው ሔደች-ወደ አምላኳ፡፡ ግርማ ከእዚያ በኋላ ሙዚቃን ፈራ፡፡ በብዙ ጉትጎታ ተመልሶ ሲመጣም ከእጸገነት መራቅ ተሳነው፡፡ “Mistakes on purpose” ብሎ በሰየመው የሙዚቃ አልበሙ ላይም “በመልክሽ አይደለም” በተሰኘ ዜማው የልጅነት ፍቅሩን ዘከረ፡፡ በካንሰር ሕመም ካለፈች 32 ዓመታት ቢሞላትም ዛሬም ፎቶዋን አቅፎ እንደሚተኛ አንጎራጎረ፡፡
እስኪመሽ እናፍቃለሁ፤ እስክተኛም እጓጓለሁ ምክንያቱም ጸጊን ስለማገኛት አለ፡፡ ግርማ ዕድሜውን ሙሉ የዘፈነላት ሴት አሁንም አብራው እንዳለች ያስባል፡፡ በጊዜ ቤቱ ገብቶ ከፎቶዋ ጋር ሲጫወት ያመሻል፡፡ እኔም ተራው ደርሶኝ በድጋሚ እስካገኛት እያለ ፡፡...!
#በቅርብ በድጋሚ ለንባብ ከበቃው #ጠመንጃና ሙዚቃ መጽሐፍ የተወሰደ፤
ጠመንጃና ሙዚቃ ምን ይዟል?
1- የኢትዮጵያን ፖለቲካና ሙዚቃ ታሪክ በስፋት ተርኳል
2- ከአንድ ሺህ በላይ የግጥም፣ የዜማና የቅንብር ሥራዎችን መረጃዎች በዝርዝር አቅርቧል
3-አርባ ያህል የሙዚቃ ሰዎችን የሕይወት ታሪክ አካቷል
4-የኢትዮጵያን ማኅበራዊ ታሪክ በስፋት መርምሯል
በጃፋር መጽሐፍት ያገኙታል

11 months ago
ገበያ ላይ ጠፍቶ የነበረው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ በቃ
#ethiopia | የተወዳጁን ሙዚቃኛ ኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎች የሚተርከው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በአንባብያን ጥያቄ መሰረት በድጋሚ ለገበያ መብቃቱ ተነገረ፡፡
በደራሲና ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) የተዘጋጀው መጽሐፉ ለንባብከ ከቃበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራን ያኖረው ኤልያስ መልካ ሕልፈተ ሕይወቱ የፊታችን መስከረም ስድስት ዓመት ይሞላዋል፡፡
“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ የተናፋቂውን ኤልያስ መልካ አነጋጋሪ የግል ፍልስፍና እና የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርክ ሲሆን በወጣበት ዓመትም በኢ-ልብወለድ ዘርፍ ከዓመቱ አምስት ምርጥ መጽሐፍት አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡
ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ምርምርን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ሙዚቃ፣ታሪክና ፖለቲካ ላይ ያተኮረውን “ጠመንጃና ሙዚቃ” የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባብያን አድርሷል፡፡
“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ ጃፋርን መጻሕፍት ቤንት ጨምሮ በሁሉም የመጻሕፍት መድብሮች ለአንባብያን ቀርቧል::

ክረምት መውጫ
#ethiopia | ክረምት እንደመሆኑና ብዙ ሰው ምን ላንብብ ጠቁመኝ ባለኝ መሰረት ቀለል ያሉ ሁሉም ሰው ሳያነባቸው መሞት የለበትም ብዬ የማስባቸውን ከእንግሊዘኛ 20 ከሀገር ውስጥ 20 እንዲሁም ከትርጉም 20 በርግጥ ቁጥሩ አንሷል ቢሆንም በቀላሉ የሚገኙት ብዬ ካሰብኩት ነው።
ሌሎች መጽሀፍቶቼን በየ ስርቻው ደብቄ እነኚህን ግን ፊት ለፊት አስቀምጬ በየ ሆነ ግዜው የምደግማቸውና በፍጹም ለሰው የማላውሳቸው አንብቤ የወደድኳቸው መጽሀፍቶች ናቸው እያየን ደሞ እንጨምራለን አሰልቺ እንዳይሆን ብዬ ነው 🙌
#ከ_እንግሊዘኛ_መነበብ_አለባቸው_ብዬ_ከማስበው_ውስጥ :-
📌 the brother Karamazov by Dostoyevsky
📌 crime and punishment by Dostoyevsky
📌 notes from underground by Dostoyevsky
📌 The Trial by Franz Kafka
📌metamorphosis by Franz Kafka
📌Animal Farm by George Orwell
📌 Nineteen Eighty-Four by George Orwell
📌Thus Spoke Zarathustra by Nietzsche
📌Beyond Good and Evil by Nietzsche
📌The Birth of Tragedy
📌The Stranger by albert Camus
📌The Plague by albert camus
📌The Myth of Sisyphus
📌Being and Nothingness by Jean-Paul Sartre
📌The World as Will and Representation by Schopenhauer
📌The Interpretation of Dreams by Sigmund Freud
📌Man and His Symbols by Carl Jung
📌Man's Search for Meaning by Viktor Frankl
📌Night by Elie Wiesel
📌the old man and the sea by Hemingway
📌sapiens by yuval harari
ቀለል ያለውን ለመጥቀስ ያክል እና እንደልብ ስለሚገኙ እንጂ ሌላ ብዙ የምለው ነበረኝ 😃
#ከ_አማርኛ_መነበብ_አለባቸው_ብዬ_ከማስበው_ውስጥ
📌 እግረመንገድ በ ስብአት ገ/እግዚአብሔር
📌አምስት ስድስት ሰባት በ ስብአት ገ/እግዚአብሄር
📌እነሆ ጀግና ስብአት ገ/እግዚአብሔር
📌ማስታወሻ በ ዘነበ ወላ
📌ኦሮማይ በ በአሉ ግርማ
📌ሀዲስ በ በአሉ ግርማ
📌ጥበብ በ ሀይለጊዮርጊስ
📌የፍልስፍና አጽናፍ በ አለማየሁ ገላጋይ
📌ቅበላ በ አለማየሁ ገላጋይ
📌ዋሪሳ በአለማየሁ ገላጋይ
📌 ማእበል ጠሪ ወፍ በአለማየሁ ገላጋይ
📌የስንብት ቀለማት በ አዳም ረታ
📌ግራጫ ቃጭሎች በ አዳም ረታ
📌ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ በአዳም ረታ
📌መረቅ በአዳም ረታ
📌የቅኔ ውበት በ ከበደ ሚካኤል
📌 እሳት ወይ አበባ በ ጸጋዬ ገብረመድህን
📌አደፍርስ በዳኛቸወ ወርቁ
📌የባስሊቆስ እንባ በ ትእግስት ታፈረ
📌በፍልስፍና መደመም በ ዋለልኝ
📌ጠመንጃና ሙዚቃ በ ይነገር ጌታቸው
📌ፊታውራሪ ተክለሀዋሪያት በ ግርማቸው (ልጃቸው ነው ኦቶባዮግራፊ)
📌ልኡል እራስ እምሩ (ኦቶባዮግራፊ)
ከ ሀያ እንዳይበልጥብኝ እንጂ ብዙ የምለው ነበረኝ 😅
ከ_ትርጉም_መነበብ_አለባቸው_ብዬ_ከማስበው_ውስጥ
📌ካፖርቱ ተርጓሚው ጠፍቶኛል
📌እፎይታ ትርጉም ተሾመ ዳምጠው
📌ፓፒዮ ተርጓሚው ጠፋኝ
📌የመጨረሻው ፈተና በ ማይነግረው
📌እምዮ ሳህለስላሴ
📌እናት ተርጓሚው ተረስቶኛል
📌ምጽአተ እስራኤል በማሞ ውድነህ
📌መከረኞቹ ሳህለስላሴ
📌ብርቅርቅታ አብይ ደምሴ
📌ሆሞዲየስ በ ዳግም
📌ግራጋቢው ዘመን በ ተስፋጽዮን
📌ቡቃያው በ ሙሉብርሀን ታሪኩ
📌 የሀገር ልጅ ሳህለስላሴ
📌ቼሆቭ አጫጭር በበላይነህ አሰጉና በ ጌታቸው
📌ሁለት አጫጭር ታሪኮች (ቱርጌኒቭ) በ ደስታ ታደሰ
📌ያንገት ጌጡ በ አውግቸው ተረፈ
📌ታራስ ቡልባ በበካፋ ሀይለ
📌ሌቭ ቶሎስቶይ ካሳይ ገብሬ
📌ሽማግሌውና ባህሩ ተርጓሚው ተዘነጋኝ
📌የሩሲያ ልቦለድ ታሪኮች በ መኩሪያ
በያሬድ ግርማ

Comments