Logo
Getu Temesgen
ገበያ ላይ ጠፍቶ የነበረው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በድጋሚ ለንባብ በቃ
#ethiopia | የተወዳጁን ሙዚቃኛ ኤልያስ መልካ ሕይወትና ሥራዎች የሚተርከው “የከተማው መናኝ” መጽሐፍ በአንባብያን ጥያቄ መሰረት በድጋሚ ለገበያ መብቃቱ ተነገረ፡፡

በደራሲና ጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) የተዘጋጀው መጽሐፉ ለንባብከ ከቃበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራን ያኖረው ኤልያስ መልካ ሕልፈተ ሕይወቱ የፊታችን መስከረም ስድስት ዓመት ይሞላዋል፡፡

“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ የተናፋቂውን ኤልያስ መልካ አነጋጋሪ የግል ፍልስፍና እና የሕይወት ውጣ ውረድ የሚተርክ ሲሆን በወጣበት ዓመትም በኢ-ልብወለድ ዘርፍ ከዓመቱ አምስት ምርጥ መጽሐፍት አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡

ይነገር ጌታቸው (ማዕረግ) በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ ምርምርን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ሙዚቃ፣ታሪክና ፖለቲካ ላይ ያተኮረውን “ጠመንጃና ሙዚቃ” የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባብያን አድርሷል፡፡

“የከተማው መናኝ” መጽሐፍ ጃፋርን መጻሕፍት ቤንት ጨምሮ በሁሉም የመጻሕፍት መድብሮች ለአንባብያን ቀርቧል::

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.