Logo
YenetaTube
"ኢራን ትራምፕን ለመግደል ሞክራለች" — የአሜሪካ መከላከያ
የኔታ ሚዲያ

የአሜሪካ ጦር በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ አቅዶ የነበረውን የኢራን ልዩ ቡድን መሪ መግደሉን አስታወቀ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴዝ (Pete Hegseth) በፔንታጎን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢራን ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለመግደል ሞክራ ነበር ነገር ግን መጨረሻ ላይ የሳቁት ትራምፕ ናቸው ብለዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት ባለፈው ማክሰኞ (የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.) የአሜሪካ ጦር ባከናወነው ኦፕሬሽን ትራምፕን ለመግደል አቅዶ የነበረውን የልዩ ክፍል መሪ አድኖ ገድሏል ሆኖም የተገደለው ግለሰብ ማንነት በስም አልተጠቀሰም።

እ.ኤ.አ. በ2024 የአሜሪካ መንግስት ፋርሃድ ሻኬሪ የተባለ የ51 ዓመት አፍጋኒስታናዊ ግለሰብ ላይ ክስ መስርቶ ነበር ግለሰቡ ትራምፕ ከመመረጣቸው በፊት ግድያ እንዲፈጽም በኢራን ታዝዞ እንደነበር ተገልጿል።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ በወቅቱ የቀረበውን ክስ መሰረት ቢስ ውሸት በማለት አስተባብለውታል።

ዶናልድ ትራምፕ በ2024 ብቻ ሁለት የግድያ ሙከራዎች አስተናግደዋል። በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ በጠመንጃ ጆሯቸውን ተመተው የነበረ ሲሆን፣ በሴፕቴምበር ወር ደግሞ በፍሎሪዳ ጎልፍ ሲጫወቱ ሌላ ተኳሽ ተይዞባቸዋል።

ባለፈው ወር ብቻ ኦስቲን ቲ ማርቲን የተባለ የ21 ዓመት ወጣት በጠመንጃና በነዳጅ ጋን የታጥቆ የትራምፕ መኖሪያ በሆነው ማር-አ-ላጎ (Mar-a-Lago) ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥሶ በመግባቱ በደህንነት ኃይሎች ተገድሏል።

እንደ አሜሪካ አቃቤ ህግ መረጃ ፋርሃድ ሻኬሪ በሰባት ቀናት ውስጥ ትራምፕን ለመግደል እቅድ እንዲያቀርብ በኢራን አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) ታዝዞ ነበር።

ሻኬሪ ግን በሰባት ቀን ውስጥ እቅዱን ማቅረብ አልችልም ማለቱን ተከትሎ ኢራን ትራምፕ በምርጫው አይሸነፍም ብላ ስላላሰበች ከምርጫ በኋላ መግደል ይቀላል በሚል እቅዱን ለጊዜው አዘግይታው እንደነበር ተገልጿል።

ሻኬሪ በልጅነቱ ወደ አሜሪካ የገባ ቢሆንም በታጠቁ ዘረፋ ወንጀሎች ለ14 ዓመታት ታስሮ ከቆየ በኋላ ከአሜሪካ ተባሮ ወደ ኢራን ማቅናቱ ይታወቃል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.