1 month ago
ወደ ሊዮን ከተማ በረራ ተጀምሯል።
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፈረንሳይ ሊዮን ከተማ በረራ መጀመሩን ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመዳረሻ መረቡን የማስፋፋት ስትራቴጂው አካል የሆነውን ወደ ፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የሚያደርገውን አዲስ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት በይፋ ማስጀመሩን አበሰረ።
ይህ አዲስ መስመር ለአየር መንገዱ በፈረንሳይ ሶስተኛ፣ በአውሮፓ ሀገራት ደግሞ 23ኛ መዳረሻ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ በአጠቃላይ የዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ቁጥር ወደ 146 ከፍ አድርጎታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የበረራ አገልግሎቱ መጀመር አየር መንገዱ አፍሪካን ከዓለም ጋር የማገናኘት ተልዕኮውን ለማሳካት የተገኘ ተጨማሪ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም በረራው ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ሰፊ አማራጭ ከመፍጠሩም በላይ፣ በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትስስር በማጠናከር በኩል ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አስረድተዋል።
አየር መንገዱ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የታጠቁ ግዙፍ አውሮፕላኖችን በመጨመር የመዳረሻ መረቡን የማስፋፋት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ላሜክ በበኩላቸው፣ ሊዮን የኢኮኖሚ እና የንግድ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ወደ ከተማዋ የተጀመረው በረራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
አምባሳደሩ አያይዘውም፣ በቢሾፍቱ እየተገነባ በሚገኘው አዲሱ አየር መንገድ የጥናት እና የቴክኒክ ስራዎች ላይ የፈረንሳይ ተቋማት እየተሳተፉ እንደሚገኙ በመግለጽ፣ በአቪየሽን ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ትብብር አድንቀዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፈረንሳይሊዮን #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

በመጨረሻም ሌብሮን ጀምስ ሎስ አንጀለስ ሌከርስን ተሰናበተ
#ethiopia | የቅርጫት ኳስ ታላቁ ኮከብ ሊብሮን ጀምስ የሎስ አንጀለስ ሌከርስን እንደሚለቅ አሳውቋል።
የኢኤስፒኤን (ESPN) የቅርጫት ኳስ ዘጋቢ ሻምስ ቻራኒያ ባወጣው መረጃ መሰረት ሌብሮን ጀምስ ቀጣዩን የሙያ ዘመኑን በሌላ ቡድን ለመቀጠል እንደወሰነ ገልጿል።
ሊብሮን ጀምስ ይህ ውሳኔ ከገንዘብ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብሏል።
ጀምስ ውሳኔውን ተከትሎ በሰጠው ቃለምልልስ ለዚህ ውሳኔ የደረስኩት በገንዘብ ምክንያት አይደለም ብሏል።
አክሎም በሙያው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የራሱን ደስታ እና እርካታ ለማግኘት ባለው የቆየ ፍላጎት የተነሳ እንደሆነም አክሏል።
ሊብሮን በሌከርስ ቆይታው በ2020 የኤንቢኤ (NBA) የአመቱ ሻምፒዮናን ጨምሮ በርካታ ድሎችን የተጎናጸፈ ኮኮብ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነበር።
አሁን ግን ለቀጣይ ህይወቱ የበለጠ ደስታ የሚሰጠውን አማራጭ መምረጡን ገልጿል።
ሊብሮን ጀምስ ከሌከርስ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣይ መዳረሻው የት ይሆናል የሚለው ጥያቄ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።
በተለይም ጎልደን ስቴት ዋሪየርስ እና ክሊቭላንድ ካቫሊየርስ ሊብሮንን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች እንደሆኑ እየተነገረ ይገኛል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#lebronjames #charania #nbachampion #espnnews #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemsgenmediacommunication

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 4 ግዙፍ ፕሮጀክቶች አስመረቀ
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 4 ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።
ለምረቃ የበቁት እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፦ ዘመናዊ የዳታ ሴንተር (የመረጃና የቴክኖሎጂ ቋት)፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲየም፣ የእንስሳት ህክምና ማስተማሪያ ሆስፒታል እና የመምህራን የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች (አፓርታማዎች) ናቸው።
በምረቃ መርሀ- ግብሩ ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን እንደገለፁት የእንስሳት ህክምና ማስተማሪያ ሆስፒታል በሀገሪቱና በአካባቢው ያለውን እምቅ የእንስሳት ሀብት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
የማህበረሰቡ የኑሮ ዋስትና ለሆኑት እንስሳት የጤና ዋስትና ከመስጠቱ ባለፈ፣ ለእንስሳት ህክምና ሳይንስ (Veterinary Science) ዘመናዊ ማስተማሪያና የምርምር ማዕከል ሆኖ ያገለግላልም ሲሉ ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ በአይነቱ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካም ጭምር ልዩና ብቸኛ መሆኑ ገልጸዋል።
ዘመናዊው የዳታ ሴንተር የዩኒቨርሲቲውን የዲጂታልና የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።
ሌላው የመምህራን መኖሪያ አፓርታማዎች የቀድሞውን የተማሪዎች ዶርሚተሪ ወደ መምህራን መኖሪያነት በመቀየር የወጪ ቆጣቢነትና የሀብት አጠቃቀም ብልሃትን በተግባር ያሳየ እንደሆነ ተናግረዋል።
የስፖርት ማዕከሉ ደግሞ የተማሪዎችን ጤናማ ሕይወት ከመደገፍ ባለፈ በዩኒቨርሲቲውና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ትስስር እንደሚያጠናክርም ገልፀዋል::
የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ- ልማት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት ሚኒስቴር ጥራት ያለው ከፍተኛ ትምህርትን፣ በተግባር የተደገፈ ምርምርንና ማህበረሰብ-አቀፍ አገልግሎትን ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ደረጀ አረጋኸኝ በበኩላቸው ግንባታዎቹ በጥራት ተጠናቀው ለዚህ መብቃታቸው በቅንጅት የመስራት ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ጎንደርዩኒቨርስቲፕሮጀክት #ትምህርትሚኒስትር #የኢትዮጵያኮንስትራክሽንባለስልጣን #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

ዩስራ ሆም በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ ከፈተ
#ethiopia | ባለፈው ጥር ወር ላይ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በብስራተ ገብርኤል አካባቢ የከፈተው ዩስራ ሆምስ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በዛሬው እለት በጉርድ ሾላ ከፍቷል።
በአሜሪካ ለ80 ዓመታት አለም አቀፍ ብራንድ ሆኖ የዘለቀው አሽሊ ፈርኒቸር ለዩስራ ሆም በሰጠው የብቸኛ ወኪልነትና አቅራቢነት ፍቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የዩስራ ሆም መሥራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩስራ ኑርሁሴን ረጃ፣ እንዲሁም የአሽሊ ፈርኒቸር የሥራ መሪዎች በተገኙበት ተመርቋል።
በዓለም የፈርኒቸር ኢንዱስትሪ ስመጥር የሆነው የአሜሪካው አሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱ፣ የሀገሪቱን የግንባታና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) ዘርፍ ተስፋ ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል።
የዩስራ ሆም መሥራች ወይዘሮ ዩስራ ኑር ሁሴን ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ፣ የታሪክ እና የባህል ፀጋዎች በመጠቀም አዳጊ የቱሪዝም ተስፋ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቀደሚ እየሆነች ትገኛለች ብለዋል።
በአሽሊ ፈርኒቸር የአፍሪካ እና የእንግሊዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ማርክ ማራስ በምረቃ መርሀ ግብሩ ዕለት በሰጡት መግለጫ ዩስራ ሆም ከአሽሊ ፈርኒቸር የሚጠበቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱን ተናግረዋል።
በዚህም የወኪልነት እና የአቅራቢነት ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል።
አሽሊ ፈርኒቸር በፍሬንቻይዝ ለዩስራ ሆም ምርቶቹን በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል ሲሉም ሚስተር ማርክ ተናግረዋል።
የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ዕድገቷ የሚታይ እና እኛ ልንፈጥር ላሰብነው ገበያ የምትመች ናት ሲሉም ለከተማዋ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።
የአሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ከሀገሪቱ የቱሪዝም እና የግንባታ ዘርፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክረዋል ሲሉ የዩስራ ሆም የሥራ መሪዎች ተናግረዋል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል ሆቴሎች እና አልሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር በመጓዝ ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል ተብሏል።
የ80 ዓመታት ልምድ ያለው የአሽሊ ፈርኒቸር የንድፍ እና የጥራት ደረጃዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው፣ ለሀገር ውስጥ የፈርኒቸር ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር እንደሚፈጥርም ተነግሯል።
በአጠቃላይ የአሽሊ ፈርኒቸር እና የኢትዮጵያ ግንኙነት መጀመር፣ የሀገሪቱን የንግድ ኢንቨስትመንት ከማሳደጉም በላይ የቱሪዝም ዘርፉ የሚፈልገውን ዘመናዊ ገፅታ ያላብሳል ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ዩስራሆምጉርድሾላ #አሽሊፈርኒቸር #ፈርኒቸር #አሜሪካኤምባሲ #ኢርቪንማሲንጋ #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

Sponsored by
Surafel
1 month ago
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና አሸናፊዎች ተለዩ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በቀዳሚነት በተካሄደው ውድድር ቤተልሔም ዳንኤል በ80 ኪ.ሜ የሴቶች ኤሊት ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።
እንዲሁም ፍሊሞን ዘርአ ብሩክ በ140 ኪ.ሜ የወንዶች ኤሊት ውድድር ቀዳሚ ሆኗል።
ሁለቱም አሸናፊዎች በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።
ውድድሩ በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና (ሀCI) ላይ ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ የተደረገ ዋና መድረክ እንደሆነ ተነግሯል።
ባለፉት ዓመታት በተደረጉ መሰል ብሔራዊ ሻምፒዮናዎች ላይ የተገኙ ውጤቶች ስፖርተኞቻችን በጀርመን እና በቻይና ፕሮፌሽናል ክለቦችን እንዲቀላቀሉ ዕድል የፈጠሩ ነበር ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#የኢትዮጵያብስክሌትሻምፒዮና #ካናዳሞንትሪያል #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

የዶናልድ ትራምፕ ምስል የተካተተበት ፓስፖርት አገልግሎት ላይ ሊውል ነው
#ethiopia | የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካን 250ኛ ዓመት ልደት ለመዘከር በቀረቡ የፓስፖርት ንድፎች ላይ የትራምፕን ፎቶግራፍ አካተተ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አርብ ዕለት በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አዲሱን የፓስፖርት ገፆች የሚያሳይ ንድፍ ያጋሩ ሲሆን፤ ፓስፖርቱ የአሜሪካን የነፃነት እወጃ ከጀርባቸው ያደረገ የራሳቸውን ፎቶራፍ እና ፊርማን ያካተተ ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዳለው ፓስፖርቱ በሚቀጥለው ሳምንት ለዜጎች ይቀርባል።
አዲሱ ፓስፖርት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የፌደራል ሕንፃዎች፣ ድረ ገፆች እና ሰነዶችን ጨምሮ የአገሪቱ ተቋማት ላይ የራሳቸው ስም እና ምሥል በመለጠፍ እያደረጉት ያለው ተከታታይ እርምጃ የቅርቡ ነው።
"የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አዲስ ፓስፖርት እንኳን ደኅና መጣችሁ፤ ነገር ግን መልካም ሁኑ ይላል" ሲሉ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።
"እንኳን ደኅና መጣችሁ፤ ነገር ግን መልካም ሁኑ" የሚለው ፅሁፍ ትራምፕ ባገሩት የፓስፖርቱ ገፅ ላይ አይታይም።
በኤክስ ገፁ ላይ የትራምፕን ልጥፍ ያጋራው ዋይት ሐውስ አዲሱን ሰነድ "የአርበኛ ፓስፖርት" ብሎታል።
የአዲሱ ሰነድ አቅርቦት አሁን ላይ የተገደበ እና ፓስፖርቱ ለአሜሪካ ዜጎች ብቻ የቀረበ ነው።
ይህን ፓስፖርት ለማግኘት አሜሪካዊያን በበይነ መረብ ወይም በፖስታ ቤት ማመልከት አይችሉም።
እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ፓስፖርቱ የሚገኘው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ የፓስፖርት ማዕከል በአካል በመቅረብ ብቻ ነው።
በተመረጡ የልደት በዓሉን በሚዘክሩ ሁነቶች ላይም ማመልከቻዎች እንደሚከፈቱ ቢቢሲ ጠቁሟል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#አሜሪካ #ዶናልድትራምፕ #ፓስፖርት #ቢቢሲዜና #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

ሁሉ ነገራቸው ለሰጡን የኮርያ ዘማቾች የምናደርገው ድጋፍ የፍቅር ስጦታችን ነው፦በኢትዮጵያ የደቡብ ኮርያ አምባሳደር
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሚገኙት ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ እና ወርልድ ቱጌዘር (World Together) በጋራ በመሆን 'ዘ ፋይናል ሳሉት' (The Final Salute) የተሰኘ የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል።
ድጋፉ የኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞች ማህበር በመተባበር የሚደረግ ሲሆን በኮርያ ጦርነተ ለተሳተፉ አርበኞች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ይህ የ12 ወራት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞችን ታሪክ ለማክበር እና ያላቸውን ምኞት ለማሳካት ያለመ መሆኑን ነው የተገለጸው።
በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙት 46ቱ አርበኞች በአብዛኛው ከ90 ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ቢገጥሟቸውም ከኮሪያ ጋር ያላቸውን ታሪካዊ ትስስር ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱ ተገልጿል።
ለዚህም አስፈላጊው የልብስ ወጪ ይሸፈናል፤ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በኮሪያኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች በተቀረጸ የመታሰቢያ መልእክት የታጀቡ ትላልቅ የፎቶ ምስሎች ይሰጣቸዋል ተብሏል።
በቃለ መጠይቅ አማካኝነት አምስት አርበኞች ተመርጠው እንደ የቤተሰብ መገናኘት፣ የህክምና ድጋፍ ወይም ወደ ደቡብ ኮሪያ የመመለስ ጉዞ ያሉ የረጅም ጊዜ ምኞቶቻቸው ይፈጸማሉ።
ፕሮጀክቱ የአርበኞቹን ፎቶግራፎች እና ዘጋቢ ፊልሞች የሚያሳይ የህዝብ ኤግዚቢሽን እና ለእነሱ ክብር የሚሰጥ ዝግጅት ያደርጋል ተብሏል።
ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ከ2012 ጀምሮ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞች እና ቤተሰቦቻቸው በትምህርት፣ በኑሮ ማሻሻያ እና በቤቶች ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
ለዚህ መርሀ ግብር የገንዘብ ድጋፉን የሚያደርገው ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ነው ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ኤልጂኤሌክትሮኒክስ #ወርልድቱጌዘር #ኮርያኤምባሲ #የኮርያዘማቾችማህበር #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

Comments