1 month ago
በአውሮፕላን አደጋው እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ 11ሰዎች ሞተዋል
#ethiopia | በፈረንሳይ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
በምስራቅ ፈረንሳይ ቶምብላይን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የአነስተኛ አውሮፕላን መከስከስ አደጋ አብራሪውን ጨምሮ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ለአንድ ፓራሹት ማሰልጠኛ ት/ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሲቭል አውሮፕላን ከናንሲ ኢሴይ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ መከስከሱ ተመላክቷል፡፡
በተፈጠረው አደጋም አብራሪውን ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የ11ዱም ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከሟቾች መካከል አምስቱ የትምህር ቤቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ መምህራን እንደነበሩ ተጠቁሟል፡፡
የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በተከሰተው አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገልጾ የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
#ፈረንሳይቶምብላይንከተማ #ፈረንሳይየአውሮፕላንአደጋ #ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኬሽን #getutemesgenmediacommunication

የመንግሥት ኃላፊዎችን አምስት ዓመት የሚያስረው አዋጅ ፀደቀ።
#ethiopia | መረጃን የደበቀ ማንኛውም የመንግሥት ኃላፊ አምስት ዓመት የሚያሳስረው አዋጅ በምክር ቤቱ ጸድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነጻ መረጃ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
የዚህ አዋጅ አላማ ሙስናን፣ ሕገ-ወጥ አሠራርን ወይም የሥራ ብቃት ማነስን ለመሸሸግ ሲሉ መረጃና ሰነድ የሚደብቁ ወይም እንዲጠፉ የሚያደርጉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ነው።
ጥፋቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት የማንኛውም የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት የበላይ ኃላፊ፣ የመረጃ ኃላፊ ወይም ትዕዛዝ ሰጪ አካል እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ይላል።
#የሕዝብተወካዮችምክርቤት #የነጻመረጃረቂቅአዋጅ #ጊጡተመስገንሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

2 months ago
ካናዳ መግባት አትችልም
#ethiopia | ጋናዊው የመካከለኛ መስመር ተጨዋች ቶማስ ፓርቲይ ካናዳ ለመግባት መከልከሉን ተከትሎ አገሩ ከፓናማ ጋር የምታደርገው የመክፈቻ ጨዋታ ላይ አይሳተፍም።
የ32 ዓመቱ ተጨዋች እ.አ.አ ከ2020 እስከ 2022 ድረስ በአራት ሴቶች ሰባት የአስገድዶ መድፈር እና አንድ ከወሲባዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ክሶች ቀርበውበታል።
ተጨዋቹ በሚቀጥለው ዓመት ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን፤ ጥፋተኛ አይደለሁም ብሏል።
ፊፋ ባወጣው መግለጫ የቀድሞው የአርሰናል ተጨዋች እና የአሁኑ የስፔኑ ቪሪየል ተጨዋች የጋና ቡድን ስልጠና ማዕከል ከነበረው ቦስተን ወደ ካናዳ ለመግባት የቪዛ ማመልከቻው በካናዳ መንግሥት ውድቅ እንደተደረገበት አረጋግጧል።
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ መሪ ድርጅት "ፊፋ የቪዛ አሰጣጥን ጨምሮ በአስተናጋጅ አገራት የኢሚግሬሽን ሂደት ተሳትፎ የለውም።
"የአስተናጋጅ አገሩ መንግሥት ማን ቪዛ ማግኘት እንዳለበት እና ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ማን እንደሚፈቀድለት የመጨረሻውን ውሳኔ ይወስናል" ሲል አክሏል።
በካናዳ መንግሥት ድረ ገፅ የጉብኝት ሕግ ዝርዝር ላይ "ወንጀል ሰርተው ወይንም በወንጀል ፍርድ ተሰጥቶብዎ ከሆነ ወደ ካናዳ መግባት ላይፈቀድልዎ ይችላል" ይላል።
ቶማስ ፓርቲይ ሁሉንም የቀረቡበትን ክሶች ጥፋተኛ አለመሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ እስካሁንም የጥፋተኝነት ብይን ሳይሰጠው የፍርድ ቤት ቀጠሮውን እየተጠባበቀ ነው።
የካናዳ የኢምግሬሽን፣ ስደተኞች እና ዜግነት ቢሮ ለቢቢሲ በላከው መግለጫ "ካናዳ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በማስተናገዷ ኩራት ይሰማታል።
የካናዳዊያንን ደኅንነት እና ፀጥታ በመጠበቅ የተሳካ ሁነት ለማዘጋጀት እየሰራች ነው።
"ካናዳ ትላልቅ ሁነቶችን ማዘጋጀት የካናዳን የኢምግሬሽን ሕጎች አይቀይርም የሚል ፅኑ አቋም አላት" ብሏል።
"ወደ ካናዳ የሚመጣ ማንኛውም ሰው በግለሰብ ደረጃ ይመዘናል፤ ይህም ባሉ እውነታቸው እና በሚተገበሩ ሕጎች ተመስርቶ ነው" ሲል መግለጫው አክሏል።
የአሜሪካ የጉሙሩክ እና ድንበር ጥበቃ ቢሮ በበኩሉ አሜሪካ የፓርቲይ የፍርድ ቤት ጉዳይን እንደምታውቅ፤ ነገር ግን በዚህ ጊዜ በወንጀል ብይን ስላልተሰጠው ወደ አሜሪካ እንዲገባ መደረጉን ገልጿል።
#bbcnews #ቶማስፓርቴ #tomaspartie #ጊጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgen #mediacommunication

Comments