4 months ago
የኡጋንዳው ጄኔራል የቱርክ መንግስት ቱርካዊት ቆንጆ ይዳረኝ አሉ
📌ጄኔራል ሙሁዚ ኬይነሩጋባ በቱርክ ላይ የ1 ቢሊዮን ዶላር እና የጋብቻ ጥያቄ በማቅረብ ማስጠንቀቂያ ሰጡ
#ethiopia | የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ እና የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ኬይነሩጋባ፣ በቱርክ ላይ በሰነዘሩት ያልተለመደ ጥያቄ እና ማስጠንቀቂያ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስበዋል።
ጄኔራሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው (X) ባሰፈሩት መልዕክት፣ ቱርክ ለኡጋንዳ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል የጠየቁ ሲሆን፤ ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት ኡጋንዳ በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር በከፈለችው መስዋዕትነት ቱርክ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ሆናለች የሚል መከራከሪያን ነው። ከገንዘብ ጥያቄው በተጨማሪም "ከሀገሪቱ እጅግ ቆንጆ የሆነችውን ሴት ሚስት ማድረግ እፈልጋለሁ" የሚል አነጋጋሪ የግል ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።
የተሰጠው የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ
ጄኔራል ሙሁዚ ቱርክ እነዚህን ጥያቄዎች በ30 ቀናት ውስጥ ካልፈጸመች የሚከተሉትን እርምጃዎች እንደሚወስዱ ዝተዋል፡
* በካምፓላ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ እንዲዘጋ ማድረግ፤
* የቱርክ አየር መንገድ (Turkish Airlines) ወደ ኡጋንዳ እንዳይበር ማገድ፤
* ማንኛውንም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ማቋረጥ።
ይህ ድርጊት በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ መሻከር የሚያሳይ ሲሆን፣ በተለይም ኡጋንዳ ከቱርክ ኩባንያ ጋር የነበራትን የቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ስምምነት ሰርዛ ወደ ቻይና ማዞሯ እና ቱርክ መንግስት ተቺዎችን አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ ለግጭቱ ዋና መንስኤዎች እንደሆኑ ይታመናል።
ጄኔራል ሙሁዚ ከዚህ ቀደምም መሰል አወዛጋቢ የሆኑ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክቶችን በማህበራዊ ገጻቸው ሲያጋሩ እንደነበር ይታወሳል። የኡጋንዳ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #uganda #turkey #generalmuhoozi #diplomacy #breakingnews #ኡጋንዳ #ቱርክ #ጄኔራልሙሁዚ #መናኸሪያሬዲዮ #ዜና

Comments