12 days ago
ተስፋዬ ገሠሠ
ጎምቱ የጥበብ ባለሟል
የሕይወት ታሪክ
ደራሲ፦ ደረጀ ትዕዛዙ
የአዘጋጁ መልዕክት
#ethiopia | የሰው ልጅ ሲፈጠር በምክንያት ነው። እግዚአብሔር አዶልፍ ሂትለርን እና ሞሶሎኒን በአንድ በኩል፤ ማሃትመ ጋንዲ እና አልበርት አንስታይን በሌላ ቋት ሲፈጥር፤ ሕይወትን ፅንሰ ሀሳብ ለመስጠት፤ ለሰዎች ወጥ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዳይኖር ፈልጎ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ይቻላል።
እነዚህ በአንድ ወቅት በተግባራቸው ዓለም ያገናኛቸው ሰዎች፤ ማንነታቸው ቢፈተሽ ማህበራዊ እርከናቸው፤ ስብዕናቸው የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። ባሕሪያቸው ከተወለዱበት፤ ከያዙትና አብረው ከኖሩት ማህበረሰብ ሊቀዳ እንደሚችል ሁሉ፤ ከየራሳቸውም የዚያ ሥራቸው ነፀብራቅ እንደሆነ ይታመናል። መልካምነትና መጥፎነት ዘወር ብሎ ምንጩ ከዚያው ነው። የሆነው ሆኖ፤ ቅንና አስተዋይ ልቦና መታደል ግን መልካም መታደል ነው። ሁሉም በሚፈፅሙት ተግባር ምድራዊም ሆነ በሰማይ የሚጠየቁበት ወይም የሚመሰገኑበት ነገር እንዳለ ሁሉ፤ እነሱም በየራሳቸው የተደሰቱበት ወይም ተፀፅተው ያለፉባቸው ጊዜያት ስለመኖራቸው አይጠረጠርም።
የሰው ልጅ በማንነቱ፤ በቀለሙ እና በተግባሩ ዥንጉርጉር ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ በኖረበት ዘመናት ሁሉ በተግባሩ ለዚች ዓለም ይነስም ይበዛም ስለማንነቱ የሚያስቀምጠው አሻራ አለው። መታወቂያው እንደየ ተግባሩ ቢለያይም ሁሉም ታሪክ አለው። የግለሰቦች ታሪክ የሀገር ታሪክ አካል የሚሆንበትም አገባብ አለ። ይህ የሚሆነው ደግሞ ታሪክ ከቃል ትሬት ወደ ጽሑፍ ተለውጦ ሲመዘገብ፤ በአግባቡ ሲሰነድ፤ ሲያያዝ፤ ከዚያም አልፎ ለቀጣዩ ትውልድ ሲተላለፍ ነው። "የግለሰቦች ታሪክ ስብስብ የሀገር ታሪክ ይሆናል" የሚለውም ከዚሁ ጋር ነው።
ከዚህ ሀሳብ በመነሳት ይህ መጽሐፍ ምን ይዟል? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።፤ ዋናው ነገር ገልጦ ማነበብ ነው። መጽሐፉ የዕድላቸው እና የሥራቸው ስለ አጋጣሚያቸው ጎምቱ የጥበብ ባለሟል ተባለው ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ሥራዎችን ይተርካል:: ተስፋዬ ማን ነው? በኖሩባቸው ዓመታት ምን ሠሩ፤ አሻራቸው በሀገር ታሪክ ውስጥ ምን ፋይዳ አለው? የሚሉና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮችን ይጠይቃል፤ ይመልሳል፤ ይተነትናል።
ተስፋዬ በአንድ ሙያና ሥራ ብቻ የተወሰነ አይደለም:: የሕይወቱን ከሥራው ጋር እያነፃፀርኩ ማቅረቤም ለዚሁ ነው። ይህ ደግሞ ታሪኩ ሲነበብ ሰልችቶት እንዳይፈጠር ይረዳል የሚል እምነት አለኝ።
አብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል ሲዘጋጅ ባለ ታሪኩ በሕይወት ስለነበረ ለመረጃ መብዛትና ተአማኒነት በአጅጉ ጠቅሞኛል። ከዚህ ቀደም ስለ ባለ ታሪኩ የተጻፉና የተነገሩ አጠራጣሪ ታሪኮችንና መረጃዎችን በቃለ መጠይቅ ለማጣራት ዕድሉን ፈጥሮልኛል።
ተስፋዬ በባህሪው "እንዲህ አደረግሁ፤ እንዲህ ፈጠርሁ..." እያለ ማንነቱን የመጎረድም ሆነ የመጎዳት ሰው አይደለም። ድንቅ ድንቅ ተግባሮቹ፤ መናገር የማይፈልጋቸው በጎ ሥራዎቹ ብዙ ናቸው። ስለዚህም በአመዛኙ በደራሲያን ደረጃ የተቀመጡ፤ በማስረጃዎችና በእውነቶች ተረጋግጠው እንዲወጡ ለማድረግ ጥሬአለሁ።
የጥበብ ሰው "አንቱ" አይባልም ከሚል ሀሳብ በመነሳት በአብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል "አንተ"ን ብጠቀምም፤ አልፎ አልፎ እንደጽሑፉ አገባብና እንደየሁኔታው አጠራር "ጋሽ ተስፋዬ"፤ "ተጋባዥ ፕሮፌሰር ተስፋዬ" እና "አንቱ"ን ተጠቅሜበታለሁ። በዚህም የባለታሪኩን የመጫወቻም ሆነ የማህበራዊ ክብር የጎደልሁ ሁኚ እንደማይታሰብኝ አተማመናለሁ። እሱም ይህ እንዲሆን ፍቃዱን ሰጥቶኛል። አልፎ አልፎ ሌሎች የጥበብ ሰዎችንም በዚህ መልኩ መጥራቴ አልቀረም።
አልፎ አልፎ በታሪክ አፅንኦት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እና በቃለ መጠይቅ ያገኛኋቸውን ሀሳቦች እንዳሉ አስቀምጣቸዋለሁ። በዚህም ወዳጆቹን፤ የሥነ ጥበብ ተማሪዎቹን፤ ቅርበት ያላቸው ቤተሰቦቹን እና ዘመዶቹን ጭምር አነጋግሬ የእውነተኝነት ቃላቸውን እንደ አግባቡ አሰፍሬአለሁ። አንዳንድ በሕይወት የሌሉና እኔ በአካል ያላገኘኋቸው ጥቂት ወዳጆቹ፤ በተለያዩ ወቅቶችና መድረኮች ስለ ተስፋዬ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ስብስቤ አድርጌ አቅርቤአለሁ። ሥራዎቹን፤ በተለያዩ ጊዜያት ስለ እሱ የተጻፉና የተነገሩ ጉዳዮችን ፈትሻለሁ። የግል ማስታወሻና የተወሰኑ የዕለት ማስታወሻዎቹን /Daily diary/ ጭምር በርብሬአለሁ። ለዚህ ይጠቅማል፤ ይበጃል ያልኩትን ቁም-ነገር፤ ፍሬ-ነገር፤ ይሆናል ልክነቱን ነቅሼ በማውጣት በአስፈላጊው ቦታ አስፍሬአለሁ። ይህ ነው የዚህ መጽሐፍ ሂደት።
ይህ መጽሐፍ፤ የሕይወት ታሪክ (Biography) አጻጻፍ መርሁን የተከተለ እንዲሆን አድርጌአለሁ። ጋሽ ተስፋዬ የዚችኛውን ዓለም የጥበብ አውራ ኖሮ በ84 ዓመት ዕድሜው ወደማይቀረው ሄዷል። ከዚችኛዋ ዓለም በአካል ሞት ቢለይም ሥራውና ማንነቱ ግን እንዲህ ሲወሳ እና ሲዘከር ይኖራል።
መልካም ንባብ
***
የመጽሐፉ የጀርባ
“ግልጽነትን የሚያደፋፍርህ እውነት ነው። ሐሰት ውስጥህ ካለ ለመናገር ትሸማቀቃለህ። እርግጥ የፖለቲካ ሰዎች ይህንን ሊያደርጉት ይችላሉ፤ የፖለቲካ ሰው ግን ዲፕሎማት ነው። የሚናገረው የት፤ መቼ፤ እንዴት፤ ለማን፤ የሚሉትን አጢኖ፤ መትሮ ነው።
እኔ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፤ ተፈጥሮዬ አልፈቀደም። ስለዚህ ፊት ለፊት እናገራለሁ። መስዋዕትነት መክፈል አለብኝ፤ ይሁኑ! ይክፈል፤ እውነትን የያዘ ሁሉ ግን አሸናፊ ነው። በነጻ ህሊና ይኖራል።”
“ከፖለቲካዊ ሹመቱ በሕዝብ የታመነበት ሽልማት ይበልጥብኛል። ያስተማርኳቸው የጥበብ ልጆቼ በመድረክ፤ በፊልም፤ በሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ተሰማርተው ማየት ደስታ ይሰማኛል። ፍሬ አለኝ፤፤ ትልቁ ሽልማቴ እነሱ ናቸው።”
***
የአዘጋጁ ቀደሙት ሥራዎች፦
ደራሲ ደረጀ ትዕዛዙ
ጳውሎስ ኞኞ ከ1926-1984 (የሕይወት ታሪክ)
ሳተናው (የአጫጭር ልብወለዶችና የግጥሞች ስብስብ)
#የሕይወትታሪክ #ተስፋዬገሠሠ #መጽሐፍ #ኪነጥበብ #ደራሲደረጀትዕዛዙ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

18 days ago
ምስጋና #አርቲስት
አዲስ ከተማ ነው ተወልዶ ያደገው። ለሰፈሩም ሰፈሩ ላበቀለውም «የኛ አዲስ ከቴ እግርኳስ ክለብ» ልዩ ፍቅር አለው፤ የአራዳ ልጅ ምልክት እየተባለ የሚጠራው ለኔ ደሞ ክላስ ሜቴ የነበረው አርቲስት አብረሃም ፀጋዬ — በ«ቤቶች»፣ «ሲስተርሊ ብራዘርሊ» እና «ልጄስን» በተሰኙ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎቹ እንዲሁም በ«ሌዲስ ፈርስት X»፣ «ጥቁር እና ነጭ»፣ «ፈላሺያው» እና «የሰማይ ፈገግታ» ፊልሞቹ የሚታወቅ የጥበብ ሰው ነው። አንባቢ ትውልድን ለማፍራትና ንባብን ለማበረታታት አምስት መጽሐፍትን በአምስት ሺህ ብር ገዝቶ አርአያ ሆኗል፤ እናመሰግናለን!
መፅሀፉን ማግኘት ለምትፈልጉ 0930363882
CBE 1000115018845
Abyssinia 31362587
tele bir 0930363882
(Ahenafi Malet)

21 days ago
ዘ-ሐበሻ ዜና) ባለፈው ጥር ወር ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየችው አንጋፋዋ የሆሊውድ ተዋናይት ካትሪን ኦሃራ በ78ኛው የፕራይምታይም ኤሚ ሽልማት (Emmy Awards) ላይ ልብ የሚነካ የክብር ስንብት ተደርጎላታል። መስከረም 14፣ 2026 በሎስ አንጀለስ በተካሄደው በዚህ ደማቅ መድረክ ላይ፣ ታዋቂዎቹ ተዋንያን ማካውሊ ካልኪን፣ ዳን ሌቪ እና አኒ መርፊ በመድረክ ላይ በመገኘት ስለ ተዋናይቷ ያላቸውን ጥልቅ ትዝታ አጋርተዋል።
በታዋቂው "ሆም አሎን" ፊልም ላይ የእናቱን ገጸ-ባህሪ የተጫወተችውን ኦሃራን ያስታወሰው ማካውሊ ካልኪን፣ "ስለ እሷ ሳስብ ወደ አእምሮዬ የሚመጣው 'እማማ' የሚለው ቃል ነው፤ እሷ የሁላችንም እናት ነበረች" ካለ በኋላ፣ ተመልካቹን "በነገራችን ላይ፣ ዛሬ ማታ ለእናቶቻችሁ ደውሉ" ሲል ስሜት በሚነካ መልኩ መልእክቱን አስተላልፏል።
በ"ሺትስ ክሪክ" የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ላይ አብሯት የሰራው ዳን ሌቪ በበኩሉ፣ ከካትሪን የተማረው ትልቁ የሕይወት እና የሙያ ትምህርት "ሁልጊዜም እሺ ማለት" መሆኑን ተናግሯል። "ዕድሜዋ ከ60 በላይ ሆኖ፣ የቆዳ ሚኒ-ስከርት እና ባለ 8 ኢንች ጫማ አድርጋ፣ እንግዳ በሆነ አክሰንት ለምትጫወተው ገጸ-ባህሪ እሺ ማለት... ተመልካችን እንደማታስበረግግ ማመን ነው። ሌሊት ላይ 'ውድ ዳን፣ አንዳንድ ሀሳቦች አሉኝ' ብላ በኢሜል ለምትልክልህ የጽሑፍ ማስተካከያ ሁሌም እሺ ማለት... ምክንያቱም ሀሳቧ ሁልጊዜም ታሪኩን የተሻለ ያደርገዋልና!" በማለት የኦሃራን ልዩ የጥበብ ችሎታ እና ለሥራ ባልደረቦቿ የነበራትን ትህትና መስክሯል።
አንድ እውነተኛ የጥበብ ሰው ከማለፉ በኋላም ቢሆን በሥራ ባልደረቦቹ እና በተመልካቹ ልብ ውስጥ እንዴት ዘልዓለማዊ ሐውልት ማቆም እጅጉን ያስደስታል። ካትሪን ኦሃራ በሆሊውድ የኪነ-ጥበብ ዓለም ውስጥ የነበራት የእናትነት ፍቅር፣ የፈጠራ ነጻነት እና ለሥራዋ የነበራት ትህትና ለትውልድ የሚሻገር ትምህርት ሆኖ አልፏል። የጥበብ ሰዎች ስኬት የሚለካው በሚያገኙት ሽልማት እና በሚሰበስቡት ሀብት ብቻ ሳይሆን፣ አብረዋቸው በሚሰሩ ሰዎች ሕይወት ላይ በሚያሳርፉት በጎ አሻራ መሆኑን ይህ የክብር ስንብት በሚገባ አሳይቶን አልፏል።
#emmyawards

26 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ተወዳጁ እና ዕውቁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለመላው ኢትዮጵያውያን የ2019 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን አስተላልፏል። ድምፃዊው በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው አጭር ነገር ግን ጥልቅ መልእክት፣ መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ዘመን እንዲሆን ተመኝቷል። በተለይም አገሪቱ አሁን ካለችበት ፈታኝ እና አስቸጋሪ ሁኔታ ወጥታ "የኢትዮጵያን ትንሣኤ የምናይበት ብሩህ ዘመን እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ" ሲል ጽፏል። ቴዲ አፍሮ ይህንን የአዲስ ዓመት መልእክቱን ያጠናቀቀው፣ ዘወትር በሚታወቅባቸውና መለያዎቹ በሆኑት "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!" እና "ፍቅር ያሸንፋል!" በሚሉ ቃላት ነው።
የቴዲ አፍሮ የአዲስ ዓመት፣ የበዓላት እና ወቅታዊ መልእክቶች ሁልጊዜም በብዙኃኑ ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቁ እና ትኩረት የሚስቡ ናቸው። በዘንድሮው መልእክቱ ላይ "ኢትዮጵያ ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ ወጥታ" የሚለው አገላለጹ፣ አገሪቱ አሁን ላይ እያለፈችበት ያለውን የጸጥታ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ውጥረት በግልጽ የሚያንጸባርቅ ነው። ቴዲ አፍሮ በሙዚቃዎቹም ሆነ በመልእክቶቹ ዘወትር ለኢትዮጵያ አንድነት፣ አብሮነት እና ለፍቅር የሚቆም አርቲስት እንደመሆኑ መጠን፣ አሁን ላይ ለሕዝቡ እጅግ የሚያስፈልገውን የተስፋ (የትንሣኤ) መልእክት በማስተጋባት አገራዊ ስሜትን አነቃቅቷል።
እውነተኛ የጥበብ ሰው ማለት በክፉም ሆነ በደጉ ጊዜ ከሕዝቡ ስሜት ጋር አብሮ የሚመታ፣ ተስፋ መቁረጥ ሲበዛ የተስፋ ብርሃን የሚያሳይ ነው! ቴዲ አፍሮ ባስተላለፈው መልእክት እንዳስገነዘበው፣ ይህ አዲስ ዓመት የሰላም እና የፍቅር መነሻ እንዲሆን፣ ሁላችንም አገራችንን ከተዘፈቀችበት ፈተና ለማውጣት "ፍቅር ያሸንፋል" በሚለው መርህ ቂም በቀልን ትተን በአንድነት ልንቆም ይገባል! መልካም አዲስ ዓመት!

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢትዮጵያዊነትን በዜማ፣ ባህልን በቅንብር፣ እንዲሁም የሀገር ፍቅርን በውብ ግጥም አዋህዶ ለበርካታ አስርት ዓመታት በአድማጮች ልብ ውስጥ የዘለቄታ ዙፋን የገነባው ተወዳጁ ድምፃዊ ይሁኔ በላይ፤ አዲስ የሙዚቃ አልበም ይዞ ብቅ ሊል ዋዜማ ላይ እንደሚገኝ ለዘ-ሐበሻ አስታውቋል።
"ዞማዬ" የተሰኘው ይህ 10ኛ የሙዚቃ አልበም ድምጻዊው ሙሉ 12 ዓመታትን በከፍተኛ የሙያ ብስለት፣ በስሜትና በጥበብ ፍለጋ ተጨንቆና ተጠቦ ያዘጋጀው የጥበብ ማዕድ መሆኑ ተነግሮለታል።
የሀገራችንን ህብረ-ቀለማት በሚያንጸባርቀው በዚህ አልበም ውስጥ ስምንት ልዩ ልዩ የዜማ ስልቶችን የያዙ ሙዚቃዎች ተካተዋል። እነሱም፦
1. መላ አለው
2. እኔስ ባገሬ
3. እንጃልኝ
4. ዞማዬ
5. እኔ ሆይ
6. አገኜሽኝ
7. ተይ ዘው ዘው
8. እቴ አዶ ወሸባ የተሰኙት ናቸው።
አልበሙ ስለ ሀገር፣ ፍቅር እና ባህል የሚያወሱ፤ ልብን የሚነኩ፣ መንፈስን የሚያድሱና የቆየ ትዝታን የሚቀሰቅሱ መሳጭ ግጥሞችና ዜማዎችን ያሰባሰበ ነው። በስራው ላይ የዝነኛውና አንጋፋው የግጥምና ዜማ ደራሲ አበበ ብርሃኔን ጨምሮ የሌሎች ታላላቅ የጥበብ ባለሙያዎች አስደናቂ አሻራ አርፎበታል።
ሙዚቃዎቹን አስቀድመው ያደመጡ ታዋቂ ግለሰቦችና የጥበብ ሰዎች በስራው ጥራትና ውበት እጅግ መደመማቸውን የገለጹ ሲሆን፣ አልበሙ ለህዝብ ክፍት እስኪሆን ድረስ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
ከዳሞት ምድር ተነስቶ እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ የዘለቀው እና የኢትዮጵያ ባህላዊ ዜማ ውበት የሆነው ይሁኔ በላይ፤ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር በቆላ ደጋ ዳሞት አውራጃ በምትገኘው በውቧ ፍኖተ ሰላም ከተማ ተወልዶ ያደገ ነው።
ከጎጃሙ የኪነት እንቁ "ግሽ አባይ" ተነስቶ እስከ ግዙፎቹ የሙዚቃ መድረኮች የተጓዘው ይህ የባህል አምባሳደር፤ ጥበብን በዕውቀት ከተፈጥሮ ድምፁ ጋር፣ ባህሪውን በህዝብ ፍቅር አምቆ፣ አቋሙን ደግሞ በሀገር ወዳድነት አፅንቶ የኖረ ብርቅዬ የጥበብ ሰው ነው።
ይህ የሀገር ፍቅር ህያው ምስክር የሆነው የይሁኔ በላይ ድምፅ፣ ዳግም የጥበብ አፍቃሪዎችን ልብ በሀሴት ሊሞላ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። ነገ ቅዳሜ አንድ የቪድዮ ክሊፕ በራሱ ዩቱብ ቻናል ላይ እንደሚለቅ፣ እንዲሁም ሐሙስ ዕለት ደግሞ ሙሉ የሙዚቃ አልበሙ እንደሚለቀቅ ድምጻዊው ነግሮናል።

3 months ago
የአቤን አንጀት የምታርሰው ሙዚቃ
#ethiopia | ሁለገቡ የጥበብ ሰው አበበ ብርሃኔ ግጥምና ዜማቸው በሌሎች ከተሰሩ የሙዚቃ ስራዎች መካከል የሚወደው አንድ ሙዚቃ አለ።
አቤ እጅግ ከሚወዳቸው የሙዚቃ ስራዎች መካከል የቴዎድሮስ ታደሰን "ሰርካለም" የተሰኘው ሙዚቃ ሙዚቃ እንደሆነ በአንድ ወቅት ከጋዜጠኛ ሔኖክ ወ/ገብርኤል ጋር በሙዚቀኞች ብፌ ፕሮግራም ላይ በነበረው ቆይታ ተናግሮ ነበር።
ይህ ሙዚቃ ለአቤ ሁሉ ነገሩ ነው።
የጥበብ ሰው አበበ ብርሃኔ የቴዎድሮስ ታደሰን "ሰርካለም" ሲያዳምጥ ልክ በውስጡ የተደበቀ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ጥልቅ ስሜት የሚቀሰቀስበት ይመስላል።
አበበ ብርሃኔ በሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከ800 በላይ የግጥምና የዜማ ስራዎች የሰራ ታላቅ የጥበብ ሰው ነው።
በይልማ ገ/አብ እና በዜማ ደራሲው አበበ መለሰ የተሰራው ይህ ሰርካለም ሙዚቃ ስራ ግን ለአበበ ብርሀኔ ቀዳሚ የሙዚቃ ምርጫ ነው።
የቴዎድሮስ ታደሰን "ሰርካለም" ሲሰማ ምርጫው መሆኑን ከመመስከር ወደ ኋላ አይልም።
ለእርሱ ይህ ሙዚቃ ከአድማጭነት አልፎ የህይወት አጋሩ ሆኗል።
አበበ ለዚህ ሙዚቃ ያለው ክብር እንደ ተራ አድናቂ አይደለም።
ሙዚቃው ሲጀምር አበበ ወደ ትዝታው ጥግ ይጓዛል።
"ሰርካለም" ለእርሱ እንደ አንድ ታሪካዊ መጽሐፍ ገጾች ያለፉትን ጣፋጭና መራራ የህይወት ምዕራፎች ሁሉ እያገላበጠ የሚያስታውሰው ነው።
የሙዚቃው ዜማና የቴዎድሮስ ታደሰ ድምፅ በአበበ ልብ ውስጥ ልዩ የሆነ የመረጋጋት ስሜት ይፈጥራል የአንጀቱ መታረሻም ይኸው ነው።
"ሰርካለም" የጥበብ ጥግ ነው። በሙዚቃው ውስጥ የሚሰማው የፍቅር የናፍቆትና የህይወት ትርጉም ከአበበ የጥበብ እይታ ጋር ይዋሃዳል።
አበበ በግርምት ሲናገር እንዲህ ይላል
እንዴት እንዲህ አይነት ሙዚቃ ይሰራል የሚል።
የግጥሙ ጥልቀት የዜማው ጥራት እና ውበት ይደንቀኛልም ይላል።
"ሰርካለም" ለእርሱ የትላንት ናፍቆቱ የዛሬ ኩራቱ እና የነገ ተስፋው የሆነ ሙዚቃ ይመስላል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ኢትዮጵያሙዚቃሰርካለም #አበበብርሀኔቴዎድሮስታደሰ #ይልማገብረአብአበበመለሰ

የአንጋፋዋ ድምፃዊት አርቲስት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ”
ሀገራችን ካፈራቻቸው እጅግ ድንቅና አንጋፋ ድምፃውያን መካከል አንዷ የሆነችው አርቲስት ራሔል ዮሐንስ በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ተከትሎ፣ ሥርዓተ ቀብሯ ዛሬ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ምህረት ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴደራል ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል።
ሁላችንም አንድ ቀን በምናገኘውና በማይቀረው የሞት መንገድ ቀድማን የተጓዘችው የዚህች ታላቅ ድምፃዊት ሕይወት ማለፍ መላውን የኪነጥበብ ማህበረሰብና የሀገራችንን ሕዝብ በታላቅ ሐዘን ውስጥ ጥሏል።
በሕይወት ዘመኗ በሙዚቃው ዓለም የራሷን ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ፣ በሕይወቷ የመጨረሻ ዓመታት ላይ ሙሉ በሙሉ ከዓለማዊ ሙዚቃ በመራቅ ራሷን ለመንፈሳዊ አገልግሎትና ለምስጋና መዝሙሮች አውላ እንደነበር ይታወሳል።
በትዳርና በቤተሰብ ሕይወቷም የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት ለመሆን የበቃች ሲሆን፣ የ14 የልጅ ልጆች እንዲሁም የ5 የልጅ ልጅ ልጆችን የመሳም ታላቅ የእድሜና የሕይወት ጸጋን አግኝታለች።
ይህች ድንቅ የጥበብ ሰው ዛሬ ምድራዊ ጉዞዋን አጠናቃ ወደ ዘላለማዊ እረፍቷ ብትሸኝም፣ ያበረከተቻቸው ስራዎችና ያሳየችው በጎነት ሁልጊዜም ሲታወሱ ይኖራሉ።
እኛም ለታላቋ ድምፃዊት ቤተሰቦች፣ ለአድናቂዎቿና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጣሪ ጽናቱንና መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።
Nahom Records

የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ በባህርዳር ተካሄደ
#ethiopia | በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ በአርቲስት ወይንሸት አበጀ እና በአርቲስት አሸናፊ ማህሌት አዘጋጅነት በብሉ ናይል ሪዞርት (አቫንቲ) ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የተካሄደው "የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ" በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ታጅቦ ተጠናቋል።
በመርሃ ግብሩ አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎችና የ2018 ዓ.ም. የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴአትርና ሲኒማ ጥበባት ዲፓርትመንት ተመራቂዎች በጋራ የተለያዩ ጥበባዊ ሥራዎችን ለታዳሚዎች አቅርበዋል።
በዝግጅቱ ላይ ዶክተር አየለ አናውጤ የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና አቶ ገብረማርያም ይርጋ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ታሪክ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኃላፊዎቹ ባህርዳርን የጥበብና የጥበበኞች ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በማብራራት፣ የአንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች ሚና ለዚህ እቅድ ስኬት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎችም ለዘንድሮ ተመራቂዎች ወደ ሙያው ዓለም ሲገቡ ሊያስተውሏቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች ከሕይወት ልምዳቸው በመነሳት ምክርና ተሞክሮ አካፍለዋል። በተጨማሪም የባህርዳር ከተማ ወጣት ከያኒያን ጥበባዊ ሥራዎቻቸውን ለታዳሚው አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ አርቲስት ወይንሸት አበጀ ለዝግጅቱ ስኬት ላበረከተችው አስተዋፅኦ ከባህርዳር ከተማ ወጣቶች የክብር ስጦታና ሜዳሊያ ተበርክቶላታል። እንዲሁም አርቲስት አሸናፊ ማህሌት እና አንጋፋው አርቲስት ተስፉ ብርሃኔ የሜዳሊያ ሽልማት ተቀብለዋል።
በርካታ ታዳሚዎችን ያሳተፈው መርሃ ግብር በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት ተጠናቋል።
ለዝግጅቱ መሳካት ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ አባይ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ዘመን ኮንስትራክሽን፣ ልህቀት ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን፣ ብሉ ናይል ሪዞርት እና ቶሎ ትራንስፖርት ድጋፍ አድርገዋል።

የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ ተካሄደ
የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፣በአርቲስት ወይንሸት አበጀና በአርቲስት አሸናፊ ማህሌት አዘጋጅነት በብሉ ናይል ሪዞርት (አቫቫንቲ) ትናንት ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ በተካሄደው የጥበብ ዝግጅት የተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በዚህ መርሐ-ግብር አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች እና የዘንድሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴአትርና ሲኒማ ጥበባት ዲፓርትመንት ተመራቂዎች በጋራ ተስናስለው ጥበባዊ ስራዎችን አቅርበዋል ።
በመርሐ-ግብሩ ላይ አየለ አናውጤ (ዶክተር) የአ.ብ.ክ.መ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ፣ አቶ ግ/ማርያም ይርጋ ባህል፣ ኪነጥበብና ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የስራ ሀላፊዎቹ አያይዘውም የባህርዳር ከተማን የጥበብ እና የጥበበኞች ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ገለጻ አድርገዋል። ከተማዋ ለምታስበው የጥበብ ከተማነት እቅድም የአንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ለዚህም ስኬት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ተናግረዋል።
አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎችም በተለየ ሁኔታ የዘንድሮ ተመራቂዎች ወደ እውነተኛው የጥበብ አለም ሲመጡ ማስተዋል ስላለባቸው ጉዳዮች የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል። የከተማዋ ወጣት ከያኒያንም የጥበብ ስራዎችን ለታዳሚው አቅርበዋል።
ሌሎች ስለባህርዳር ከተማ እና የጥበብ ቁርኝት እንዲሁም መሰል መርሐ-ግብሮች በተጠናከረ መንገድ ስለማከናወን መልእክቶች በተላለፉበት ዝግጅት ለዚህ ዝግጅት መቃናት ታላቁን ሚና ለተወጣችው አርቲስት ወይንሸት አበጀ ከከተማው ወጣቶች የክብር ስጦታ እና ሜዳሊያ ተበርክቶላታል። አርቲስት አሸናፊ ማህሌት እና አንጋፋው አርቲስት ተስፉ ብርሐኔም የሜዳልያ ሽልማት ተቀብለዋል።
ደማቅና በርካታ ታድሚያንን ያሳተፈው የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ በአቶ ግርማው አሸብር የባህርዳር ዩንቨርሲቲ የውስጥ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልእክት ተቋጭቷል።
የጥበብ ሰው መገናኛ መድረክ የተቃና እንዲሆን የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፣ አባይ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ዘመን ኮንስትራክሽን፣ ልህቀት ዲዛይን እና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን፣ ብሉ ናይል ሪዞርት እና ቶሎ ትራንስፖርት ድጋፍ አድርገዋል።

Sponsored by
Surafel
4 months ago
ሁለገቡ አርቲስት ሰማህኘ በለው ዛሬ
ቅዳሜ በባህር ዳር ከተማ ይታወሳል !
የጎጃም ግሸ አባዩ ፈርጥ : የባህል አምባሳደሩ : የሀገር ባለውለታው ሁለገቡ አርቲስት ሰማህኘ በለው ተወልዶ ባደገባት ገፅታዋንም በጥበብ ስራው ሲገነባት በኖረው ባህር ዳር ከተማ ይዘከራል ::
የአርቲስቱ የልጀነት ጓደኞች : ቤተሰቦች : የጥበብ ቤተሰቦች እና አድናቂዎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የክብር ስንብትና የምስል ሃዘን ዝግጅት ይታወሳል ።
የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ፕሮሞተር ደመወዝ ገነቱ መርዓ ግብሩ እንደሚከተለው መዘጋጀቱን ገልፆል ።
🔘የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሃዘን ስሜቱን በሚገልጽ አለባበስ (ጥቁር በመልበስ) ከጠዋቱ 2:00 ላይ በባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት፣ ከአዲስ አበባ የሚመጡትን የሟችን ባለቤት ወይዘሮ ገበያነሽ አባተ እና ልጁ ቢኒያም ሰማኸኝን ጨምሮ የሟች ጓደኞቹን ይቀበላል ።
🔘የከተማዋ ነዋሪ በቀድሞው አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም ወይም በጃካራንዳ ሆቴል ፊት ለፊት ቅዳሜ ጠዋት 2:30 ሰዓት ላይ ይሰበሰባል።
🔘 ነዋሪው የሟች ቤተሰቦችና እንግዶች በማርሽ ባንድ በሃዘን ዝግታዊ ድባብ ታጅበው በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና ወደ አደባባዩ የሚወስደውን የክብር ጉዞ ያደርጋሉ።
🔘በባህር ዳር ከተማ ህዝብ ጥንታዊና ጥልቅ የልቅሶ ባህል፣ ወግና ስርዓት መሠረት፣ ለታላቁ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ልብን የሚነካና የህዝብን ስብራት የሚገልጽ የሙሾና የልቅሶ ስነ-ስርዓት ይከናወናል።
🔘የባህል የኪነ-ጥበብ ሰማይ ኮከብ የነበረው የአርቲስት ሰማኸኝ በለው፣ ለሀገርና ለወገን ያበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ፣ ያሳለፈው ውጣ ውረድና አጠቃላይ የህይወት ታሪኩ ለሃዘንተኛው ይነበባል።
🔘ውድ ህይወቱን ለጥበብ በሰጠው አርቲስት መታሰቢያ ላይ፣ በሀገር ታዋቂ ሰዎች፣ የስራ ባልደረቦቹ፣ ቤተሰቦቹና ጥልቅ ሃዘን በገባቸው አድናቂዎቹ አማካኝነት የክብር የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል።
🔘የሟች ነፍስ በሰላም እንድታርፍ፣ በሃይማኖቱ መንፈሳዊ ህግና ስርዓት መሠረት ታላቅ የፍትሃት ጸሎት በሃይማኖት አባቶች ይመራል።
🔘ስለ አርቲስት ሰማኸኝ በለው መልካምነት፣ ሰብዓዊነትና ታላቅነት በህይወት በነበረበት ጊዜ አብረውት የነበሩ የቅርብ ወዳጆቹ፣ የሙያ አጋሮቹ፣ የቤተሰብ አባላትና የልብ ጓደኞቹ ልብ የሚነካ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።
🔘 እንዲሁም ሌሎች የአዳራሽ ልዪ ልዪ ፕሮግራሞች እንደሚኖሩ ታውቋልደ
🔘መላው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ለአርቲስቱ
የመጨረሻውን ክብር እንድትሰጡ ኮሚቴው ጥሪውን ያስተላልፋል።
"የጥበብ ሰው አይሞትም፣ በስራዎቹ ሁልጊዜም በልባችን ይኖራል!"
ኮሚቴው...

ረዳት ፕሮፌሰር እና ሠዓሊ ልዑል ሣኅለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውስጥ ለረጅም ዘመናት በሥነጥበብ መምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ታዋቂው ሰዓሊና ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም በሀገራችን ዘመናዊ የሥነጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ ታዋቂ ሰዓልያን መካከል አንዱ ሲሆኑ የፖይንት ግሩፕ የሥነጥበብ ስብስብ መሥራችና አባልም ነበሩ።
ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በትምህርት ቤቱ ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነትና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት በመሥራት በርካታ ተተኪ የጥበብ ባለሙያዎችን ያፈሩ ተወዳጅ መምህር ነበሩ።
በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ጠንካራ ሙያተኛ እንደነበሩ ይነገራል።
ታዋቂው የጥበብ ሰው ልዑል ሣኅለማርያም በሙያዊ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ሕይወት ተሳትፏቸው፣ በደግነታቸውና በሰው ወዳድነታቸው በብዙዎች ዘንድ የተመሰገኑ ነበሩ።
የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውንም በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በግልና በቡድን ለዕይታ በማቅረብ ትልቅ ስም ያተረፉ ባለሙያ ናቸው።
የደራሽ የጥበብ ሰው የቀብር ሥነሥርዓት ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈጸም ታውቋል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የጥበብ ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍስ ይማር።
#aleschooloffineartsanddesign #addisababauniversity #ethiopianart #leulsahlemaryam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የሀዘን መግለጫ
የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር፤ የጥበብ ሰው፣ የህዝብ ድምፅ እና የለውጥ አጋራችን የነበረው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ስንሰማ እጅግ ጥልቅ የሆነ ሀዘን ተሰምቶናል።
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው በሙዚቃ ስራዎቹ የሀገራችንን ባህልና እሴቶች በመጠበቅ ረገድ የማይረሳ አሻራ ጥሏል። ከጥበብ ስራው ጎን ለጎን ደግሞ፣ እንደ ማህበረሰብ የሚገጥሙንን የጤና ችግሮች በመቅረፍ ረገድ የነበረው አበርክቶ የሚዘነጋ አይደለም።
በተለይም ከጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ጋር በመተባበር፤ ድምጻዊት ቤተለሄም ዳኛቸው እና ትዕግስት መኮንን ጋር በመሆን በነጻ ያበረከቱት “እኛ ለእኛ” የተሰኘ ሙዚቃ፣ ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የነበረው አስተዋጽኦ የላቀ ነበር።
በተጨማሪም፣ "ደቦት እንስራ" በሚለው እና በማህበረሰቡ ዘንድ "እያበል እያ እያ" በሚል በሚታወቀው ተወዳጅ ስራው እንዲሁም በሌሎች የቅስቀሳ ስራዎች፣ ማህበሩ የሚያከናውናቸውን የገቢ ማሰባሰቢያና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች በቅንነትና በታማኝነት በመምራት፣ ለብዙዎች ህይወት መትረፍ እና ለበሽታው ስርጭት መቀነስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
እንደ ማኅበር፣ ለሰጠን የላቀ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ለነበረን የትብብር ዘመን ምስጋናችንን እያቀረብን፣ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው የጥበብ ቤተሰብ እንገልጻለን።
ለአርቲስቱ ነፍስ ዘላለማዊ እረፍትን፣ ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ መጽናናትን እንመኛለን።
ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር

ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
ዘመኑን የዋጀ መከላከያ ሠራዊት፤ ለኢትዮጵያ ልዕልና መሰረት
ከመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮዎች መካከል የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ፣ የሕዝብን ደህንነት ማረጋገጥና ቀጣናዊ ሰላምን ማስከበር ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡
በዓለም ላይ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጡ ባሉበት በዚህ ዘመን የሀገራት የመከላከያ አቅም በቁጥር እና በወታደራዊ መሳሪያዎች ብቻ የሚለካበት ጊዜ አልፏል።
አሁን ላይ የሚካሄዱ ዘመናዊ ጦርነቶች አሸናፊነት በቴክኖሎጂ፣ በመረጃ፣ በሳይበር ሥርዓት እና በፈጣን ውሳኔ ሰጪነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡
ከእነዚህ መሰረታዊ መርሆች አንጻር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዘመኑን ለመዋጀት በተለያዩ ዘርፎች የለውጥ ጉዞ ላይ ይገኛል። ሠራዊቱ ለሀገር ባንዴራ፣ ክብርና ነጻነት ራሱን የሚሰዋ እንዲሁም ለቀጣናው ሀገራት መከታ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ የውጭ ወረራዎችን በመመከት ነጻነቷን ያስጠበቀች ከመሆኗ ባለፈ የአፍሪካ ጸረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ቀንዲል ናት፡፡
አሁን ላይ ያለው የጸጥታ ፈተና ደግሞ ከትናንቱ በእጅጉ የተለየ ነው ፤ ከባህላዊ የድንበር ጥቃት ባሻገር የሽብር አደጋዎች፣ የሳይበር ጥቃቶች፣ የሀሰት መረጃ ዘመቻዎችና የተደራጁ ወንጀሎች አዳዲስ ፈተናዎች ሆነው ብቅ ብለዋል።
ስለሆነም ነባራዊ ሁኔታውን የሚመጥን በሁለንታዊ አቅሙ የጎለበተ ዘመናዊ ሠራዊት መገንባት እነዚህን የወቅቱ ፈተናዎች በድል ለመወጣት ያስችላል፡፡
የኢትየጵያ መከላከያ ሠራዊት ከጦር ዝግጅት በላይ በቴክኖሎጂ እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ አቅም እንዲገነባ እየተከናወነ የሚገኘው ሥራም የሚደነቅ ነው፡፡
የኢትየጵያ መከላከያ ሠራዊት ታሪክን በደምና በአጥንት ቀለም ከመጻፍ አልፎ፣ የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ በእውቀት፣ በሥራ እና በቴክኖሎጂ ምሰሶ ላይ የሚያቆም ግዙፍ ሃይል እየሆነ ነው፡፡
በለውጡ መንግሥት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎች የኢትዮጵያ መከላከያ በስልጠና፣ በአደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ ተጨባጭ ለውጦችን አስመዝግቧል።
የድሮን ቴክኖሎጂ፣ የዘመናዊ የመረጃ ሥርዓቶች አጠቃቀም፣ የልዩ ኃይል ስልጠናዎች እና የፈጣን ምላሽ አቅሞች የዚህ ለውጥ አካል ሆነው ይጠቀሳሉ።
ከዚህ ባለፈም መከላከያው በዘመናዊ የጦር ስልቶች እና በዲጂታል ግንኙነት ስርዓቶች ላይ ያደረገው ትኩረት ዘመኑን የመዋጀት ሒደቱ እየተጠናከረ መሆኑን ያሳያል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት÷ ሠራዊቱ እጅግ ዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅ የየብስ፣ የአየርና የሳይበር ምህዳርን በበላይነት የሚቆጣጠር አስፈሪ የብረት ክንድ ሆኗል።
መከላከያ ሠራዊት የጠላትን ትንኮሳና ጥቃት በስነ ልቦና የበላይነት፣ በዘመናዊ ትጥቅ እና በላቀ ወታደራዊ ሳይንስ የማክሸፍ አቅሙ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱንም አውስተዋል፡፡
እያንዳንዱ መኮንን አካላዊ ጀግንነትን ብቻ ሳይሆን፣ አውዳሚ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶችን በብልሃት እና በፍጥነት የሚያከሽፍ፣ የተረጋጋ አዕምሮ ያለው የዘመኑ የጥበብ ሰው ሆኖ ተቀርጿልም ነው ያሉት፡፡
የሠራዊቱን ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም ይበልጥ ለማሳደግም በዘርፉ የሚከናወነው ዘመኑን የመዋጀት ሥራ የዓለምን ብሎም የቀጣናውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡
የሳይበር ደህንነት አቅምን ይበልጥ ማጠናከር፣ የሀገር ውስጥ የመከላከያ ኢንዱስትሪን ማሳደግ፣ የሰው ኃይል ሙያዊ ብቃትን ማጎልበት እና በምርምርና ፈጠራ ላይ ትኩረት መስጠት ቀጣይ ተግባራት ናቸው።
የዘመናዊ መከላከያ ጥንካሬ የሚለካው በሚገዛው መሳሪያ ብዛት ሳይሆን፣ በራሱ የሚፈጥረው ዕውቀት፣ ቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል ብቃት መሆኑንም መረዳት ግድ ይላል፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ መከላከያ ዘመኑን ከመዋጀት አንጻር ሲታይ፣ በታሪካዊ የጦር ጀግንነት ላይ ብቻ የማይመረኮዝ፣ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ እና በሙያዊ ብቃት የተደገፈ ዘመናዊ ተቋም ለመሆን የጀመረው ጉዞ ይበልጥ ማጠናከር አስፈላጊ ነው፡፡

የአርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለገብ የጥበብ ሰው አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
አርቲስት ኪዳኔ ባጋጠመው ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን÷ ሥርዓተ ቀብሩ ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ነው የተፈጸመው።
አርቲስቱ በሙያው ባገለገለበት ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ የሽኝትና ሻማ የማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
ለተለያዩ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችና የበዓል ፕሮግራሞች ላይ ባቀረባቸው የጥበብ ስራዎች ድምቀት የነበረው አርቲስት ኪዳኔ÷ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ፋና 80 የውዝዋዜ እና የዳንስ ተሰጥኦ ውድድር ላይ በአማካሪነት በመስራት ሙያዊ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
ሁለገቡ ከያኒ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስ በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተዘዋውሮ በሙያው ሀገሩን እና ወገኑን በታማኝነትና በትጋት አገልግሏል።

ተፈጸመ
#ethiopia | በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች በስፋት የሚታወቀው አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የአርቲስቱ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ፣ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ( አማኑኤል አጂፕ ) ከቀኑ 6:00 ሰዓት ተፈጽሟል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሙያ ህይወቱ በታማኝነት ባገለገለበት ታሪካዊው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የሽኝት እና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ተከናወናል።
***
የሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው
አጭር የህይወት ታሪክ
የመድረኩ እንዝርት ሁለገቡ የጥበብ ሰው አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከእናቱ ከወ/ሮ ብዙነሽ ጓንጉል እና ከአባቱ ከአቶ ምስጋናው ደርኬሮ ሰኔ 15/ 1958 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ አማኑኤል አጂፕ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ተወለደ፡፡ ለአቅመ ፊደል ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በደጃዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ ከተማ ትምሀርት ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ተምሮ አጠናቋል።
ከውዝዋዜ ጋር ገና ተማሪ እያለ የተወዳጀው ሁለገቡ ከያኒ ኪዳኔ ምስጋናው የጥበብ ጉዞውን በቀበሌ ኪነትና በከፍተኛ ኪነት ውስጥ አድርጎ መዳረሻውን በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ በማድረግ በ1977 ዓ.ም በውዝዋዜ ሙያ ለመቀጠር በቅቷል፡፡ የአርቲስት ኪዳኔ የሙያ ፍቅር፣ ችሎታና ስነምግባር ያስደመማቸው የውዝዋዜ ክፍል አሰልጣኞችና ኃላፊዎች ከተወዛዋዥነት ወደ ረዳት አሰልጣኝነት እንዲያድግ በማድረጋቸው ከ1983-1990 ዓ.ም ድረስ በረዳት አሰልጣኝነት ሙያ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ጥበበኛው ኪዳኒ በረዳትነት የጀመረውን የአሰልጣኝነት ስራውን ከፍ በማድረግ ከ1991 እሰከ 1992 በቋሚ አሰልጣኝነት ተመድቦ በርካታ ባለሙያዎችን በክህሎት፣ በስነምግባርና በጥበብ አሰልጥኖ ለውዝዋዜ ሙያ መስፋፋትና አድገት የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል፡፡
በውዝዋዜ ጥበብ በማለዳው የተነደፈው ኪዳኔ በእውቀት፣ በልምድና በፈጠራ እየጎመራና አንቱታን እያተረፈ ሲመጣ አድማሱን በማስፋት በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተዛውሮ ከ1992 እሰከ 2007 ዓ.ም በዋና አሰልጣኝነትና በኬሮጋራፈርነት በርካታ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ ግዘፍ የነሱ መድረኮች ላይ የቀረቡ የውዝዋዜ ስራዎችን በማዘጋጀት፣ በማማከርና በመምራት ከሰው ልብና አእምሮ የማይጠፉ ደማቅ ኪነጥበባዊ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ፈጣን የፈጠራ፣ የማደራጀትና የመምራት አቅም የነበረው ብርቱ የጥበብ ሰው ነበር፡፡ በርካታ ተወዛዋዦች የሚገኙበት የጥበብ መድረክ ካለ እዛ የጥበብ መድረክ ላይ ኪዳኔ መኖሩ ሳይታለም የተፈታ ህልም ነበር፡፡ የኪዳኔ የፈጠራ፣ የውዝዋዜ ችሎታና የውዝዋዜ ዝግጅት ጥበብ የታየባቸው አያሌ የውዝዋዜ ጥበብ ስራዎች ህያው መስክሮቹ ናቸው፡፡ በፋሽስት ጣሊያን የተዘረፈው የአክሱም ሀውልት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ለነበረው አቀባበል በተዘጋጀው የኪነጥበብ መድረክ ላይ በአዲስ አበባና በአክሱም ከተማ ግዙፍ የውዝዋዜ ዝግጅት፣ በህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ በተዘጋጀው የጥበብ መድረክ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ፣ በባህዳር ጣና ሐይቅ ላይ የውዝዋዜ የጀልባ ላይ ትርኢት፣ የአዲስ ዓመት የበዓል ዝግጅቶች ላይ ጥበብ፣ ባህል፣ ፈጠራና ውበት የተመላባቸው በርካታ ተወዛዋዦች የተሳተፉባቸውን የጥበብ ስራዎች በማዘጋጀት የጥበብና የሀገር ባለውለታነቱን አስመስክሯል፡፡
በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከአስራ አምስት ዓመት በላይ በአሰልጣኝነት ሲሰራ ከቆየ በኋላ ከ2007 እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቀድሞ የሙያ ቤቱ የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አደራሽ ተዛውሮ በአሰልጣኝነትና በኬሮግራፈርነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከተወዛዋዠነት፣ አሰልጣኝነት፣ አዘጋጅነትና አማካሪነት ባሻገር በድምጻዊነትና በቴአትርና ፊልም ተዋናይነትም በመሳተፍ ሁለገብ ከያኒነቱን ያስመሰከረ ድንቅ ጥበበኛ ነበር፡፡ በርካታ የሙዚቃ ቪዲዮ ስራዎች ላይ የኪዳኔ ደማቅ የፈጠራና የጥበብ አሻራ ያረፈባቸው ውዝዋዜዎችና ዝግጅቶች ዛሬም፣ ነገም ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡
አሰልጣኝና ኬሮግራፍር እንዲሁም የውዝዋዜ አማካሪ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው በሞያው በሰራባቸው አመታት በርካታ
1. ባለሙያዎች ወደ ሙያው እንዲገቡና የሙያው ስነምግባር እንዲኖራቸው አደርጓል፡፡
2. የባህል ውዝዋዜ ትምህርት ቤት በሌለበት ዘመን በቴአትር ቤቶችና ከቴአትር ቤቶች ውጪ የነበሩ ወጣቶችን አሰልጥናል፤
3. ከከተማ ውጪ በመሄድ ቱባ ባህሎችን በማጥናትና በማምጣት የተለያዩ የባህል ጭፈራዎችንና አለባበሶችን አስተዋውቋል፡፡
4. የውዝዋዜ ሙያ እንደሙያ እንዲታይና አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የተለያዩ መድረኮች ላይ እና ጥናቶች ላይ በመሳተፍ አስተዋኦ አበርክቷል፡፡
5. በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጁ በርካታ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫሎች ላይ በመጋበዝ በዳኝነትና በአማካሪነት ሰርቷል፡፡
6. ከአዲስ አበባ ውጪ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶችን ከማሰልጠን አልፎ በደቡብ ክልል ውስጥ የባህል ባንድ ለማቋቋም በቅቷል፡፡
7. በከተማችንና በተለያዩ ከተሞች በተከበሩ የብሄሔር ብሄረሰቦች ክብረ በዓላት ላይ የጥበብ ስራዎችን አቅርባል፡፡
8. በተለያዩ ጊዜ የተከበሩ የአደባበይ በአላት አድዋና የካቲት12 የመሳሰሉት ላይ ስራዋችን አቅርባል፡፡
9. በታላቁ ህዳሴ ግድብ ድረስ በመሄድና ታስቦ በሚከበርበት ጊዜም ስራዎችን አቅርቧል፡፡
10. በመንግስት መስረታና በበአለ ሲመቱ ዝግጅት ላይ ታላቅ የውዝዋዜ ትርኢት በኬሮግራፈርነት ሰርቷል፡፡
11. ሀገራችን የጦርነትና የተፈጥሮ ችግር በገጠማት ጊዜ ከኪነ ጥበብ ስራው ጋር ቀዳሚ በመሆን በርካታ አነቃቂ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
12. የተለያዩ የሀገር መሪዎች፣ አንባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ሲመጡና ሲሸኙ በአየር መንገድና በከንቲባ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ደማቅ አቀባበል በማደረግ እና ትርኢቶችን በማቅረብ ባህላችንን አስተዋውቋል፡፡
13. በከተማ ደረጃ የሚዘጋጁ ትላልቅ ሴሚናሮች፤ጉባኤዋችና ሲንፖዚየሞች ላይ የተለያዩ የኬሮግራፈር ስራዎችን ሰርቷል፡፡
ሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ላበረከታቸው ኪነጥበባዊ ስራዎች የምስጋናና የእውቅና የምስክር ወረቀቶችን፡-
Ø ከኢፌድሪ ፊዴሬሽን ምክር ቤት
Ø ከኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር
Ø አዲስ አበባ ዩንቪርስቲ
Ø ከአዲስ አበባ ባህል ኪነ የጥበብና ቱሪዝም ቢሮ
Ø ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
Ø ከሀገር ፍቅር፤ከቴአትርና ባህል አደራሽ፤ከራስ ቴአትር፤ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአተር እና ሌሎችም በርካታ ተቋማት በክብር ተቀብሏል፡፡
አሰልጣኝ፣ ኬሮግራፍርና የውዝዋዜ አማካሪ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ሙያው እንዲያድግና ባለሙያውም እንዲጠቀም በነበረው ፍላጎትና ቁጭት ምክንያት ሙያው በተለያዩ ትልልቅ ሆቴሎችና የባህል ምሽቶች እንዲሰራና ባህላችን የበለጠ እንዲተዋወቅ በማማከርና በመደገፍ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ከበርካታ የሀገራችን ታዋቂና ተወዳጅ ሙዚቀኞች ጋር ትላልቅ መድረኮችና በከተማ ደረጃ በቀረቡ ታላላቅ ህዝባዊ በአላትና የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ የኪሮግራፈር ስራዋችን
Ø በሸራተን አዲስ ሆቴል
Ø በሚሊንየም አዳራሽ
Ø በኢግዚብሽን ማዕከል
Ø በመስቀል አደባባይ
Ø በአዲስ አበባ ስቴድየም
Ø በጊዮን ሆቴል
Ø በሂልተን ሆቴል
Ø በስካይላት ሆቴል በመገኘት ጥበባዊ ስራዎችን ያቀረበ ሲሆን ትልልቅ የቀጥታ የቴሌብዥን ስርጭ የነበራቸውን ግዙፍ መድረኮችም ላይ ልዩ የኬሮግራፈርነት ሙያውን ድንቅ ብቃት አስመስክሯል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው በተለያዩ ቴአትርና ሙዚቃዊ ቴአትሮች ላይ በትወናና በዝግጅት ሰርቷል፡፡ በትወና የተሳተፈባቸው ስራዎች፦
Ø ጤና ያጣ ፍቅር
Ø ሮሚዮና ጁሌት
Ø የቀለጠው መንድር
Ø ሊስትሮ ኦፔራ
Ø ከልሺን አውልቂ
Ø ፎርፌ
Ø ኦቴሎ
Ø ቴዎድሮስ
በሙዚቃዊ ድራማ ኬሮግራፈር ዝግጅት፡-
Ø ፎርፌ
Ø ኢትዮጵያዊነት ጥልቅ ነው
Ø ከልሽን አውልቂ
Ø ሊስትሮ ኦፔራ
Ø ሉሲ
Ø ሀገር ማለት ሰው ነው እና ሌሎችም የጠቀሳሉ፡፡
በፊልም ትወና፡-
Ø በህይወት ዙሪያ
Ø ሔሮሽማ
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከመድረክ ስራዎቹ በተጨማሪም በተላያዩ ታዋቂና አንጋፍ እንዲሁም ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ቪዲዮ ስራዎች ላይ በኬሮግራፈርነትና በአማካሪነት ሰርቷል፡፡
Ø ለክብር ዳ/ር ጥላሁን ገሠሠ
Ø ለድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የሰራቸው ስራዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
አርቲስት ኪዳኔ በተለያዩ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችና የበዓል ፕሮግራሞች ላይ ባቀረባቸው የጥበብ ስራዎች ውበትና ድምቀት የነበረ ሲሆን በፋና ቴሌቭዥን ፋና ሰማንያ የውዝዋዜና ዳንስ ተሰጥኦ ውድድር ላይ በአማካሪነት በመስራት ሙያዊ አስተዋፅዎ አድርጓል፡፡
ሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ በሙያው አድማስ ተሸግሮ በዱባይ እና በታይላንድ ኢትዮጰያንና ባህሏን ያስተዋወቀ ብርቱ የጥበብ ሰው ሰሆን በቅርብ በሀገራችን እና በአለም ህዝቦች ዘንድ አንድ ጊዜ ተሰርቶ ያልተደገመውን የህዝብ ለህዝብ ተጓዥ የሙዚቃ የባህል ቡድንን የሚያስታውስ የሀገረሰብ ሙዚቃዎችን፣ ጭፈራዎችንና ባህላችንን የሚያስተዋውቅ ሉሲ ድንቅነሽ ኢትዮጵያ በሚል በመላው ሀገር ተዟዙሮ የቀረበውን ትርኢት ከባህል ሚንስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶት በዋና አዘጋጅነት የውዝዋዜውን ዝግጅት መምራት የቻለ ድንቅ ጥበበኛ ነበር፡፡
ሁለገቡ ከያኒ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ግንቦት 23/2018 ዓ.ም ድረስ በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተዛውሮ በሙያው ወገኑን፣ ሀገሩንና ሙያውን በጥበብ፣ በታማኝነትና በትጋት ሲያገለግል የኖረ፣ በጥበብ ስራዎቹ ስሙን ከመቃብር በላይ ማኖር የቻለ ታላቅ ጥበበኛ ነበር፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናዉ የጋብቻ ህይወቱን ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛዉ ከወ/ት አይናለም ተፈራ ጋር የካቲት 2 /2018 በክብር ፈፅሟል። ይሁንና ይህ ታላቅ ጥበበኛ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ በአዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል እና በሆፕ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በተወለደ በ60 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል፡፡
የአርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው የሽኝትና የጧፍ ማብራት ፕሮግራም ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ለረዥም ዓመታት በሙያው ባገለገለበት አንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ግንቦት 25/ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ከተከናወነ በኋላ የቀብር ሰነ ስርዓቱ በአማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት በመላው ሰራተኞቹና የሙያ አጋሮቹ ስም በሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፈጣሪ ነፍሱን በመዓዛ ገነት እንዲያሳርፍ ይመኛል፡፡ እንዲሁም ለውድ ቤተሰቦቹ፣ ለዘመዶቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በሙሉ ፈጣሪ ልባዊ መጽናናትን እንዲሰጣቸው ይመኛል፡፡
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት-ኮምኒኬሽን
#ኪዳኔምስጋናው #ሀገርፍቅርቴአትር #የጥበብሰው #ሀዘን #ኪነጥበብ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ኪዱ አረፈ

የአርቲስቱ የቀብር ስነ ስርዓት ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአማኑኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6:00 ሰዓት ይፈጸማል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሙያ ህይወቱ በታማኝነት ባገለገለበት ታሪካዊው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የሽኝት እና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ይከናወናል።
***
የሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው አጭር የህይወት ታሪክ

5 months ago
የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደርና የ"እስክስታው ንጉሥ" መላኩ በላይ 50ኛ ዓመት ልደት ተከበረ
#fastmereja I የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜና ሙዚቃ በዓለም መድረክ ያስተዋወቀው የጥበብ ሰው ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ፣ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ያበረከተውን የዘለቀ አሻራ የሚዘክር የክብር መርሃ-ግብር 50ኛ ዓመት የልደቱ በዓል በማስመልከት ተካሄደ። "የእስክስታው ንጉሥ" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው መላኩ፣ የሀገርን ባህል ከዘመናዊነት ጋር በማቀናጀትና ለወጣቱ ትውልድ የጥበብ ዕድል በመፍጠር ረገድ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ታላቅ ምስጋና ቀርቦለታል።
ይህ የ50ኛ ዓመት ልደት የምስጋና ስነ-ሥርዓት እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሀያት ሬጄንሲ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን
ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ በኢትዮጵያ የጥበብ ታሪክ ውስጥ በተለይም "ኢትዮ-ከለር" የተሰኘውን የባህል ሙዚቃ ቡድን በማቋቋም፣ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶችን በአንድ መድረክ በማገናኘት ረገድ የሚጠቀስ ስም አለው።
ከግል ስኬቱ ባለፈ፣ በካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘውን የ"ፈንድቃ" የባህል ማእከልን ከትንሽ አዝማሪ ቤትነት ወደ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መገኛነት በመለወጥ፣ የኢትዮጵያን ባህልና ማንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ (እንደ TED እና Lincoln Center ባሉ መድረኮች) እንዲታወቅ አድርጓል።
ከዚህም በተጨማሪ ከታዋቂው የማካሌስተር ኮሌጅ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የውዝዋዜ ጥበብ በምርምርና በትምህርት እንዲደገፍ የላቀ ሚና ተጫውቷል።
እ.አ.አ በ2020 በCommunity Cultural Development ዘርፍ የክብር "Prince Claus Award" ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የባህል ዘርፍ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ማረጋገጫ ተደርጎ ይወሰዳል።
ይህ በክብር እንግዶችና በጥበብ ወዳጆች ታጅቦ የተከናወነው የምስጋና ምሽት፣ ለሀገር ባለውለታው መላኩ በላይ የሚገባውን ክብር ለመስጠትና የጀመረውን የጥበብ ጉዞ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

ከስኬት ማማው በስተጀርባ ያሉት ብርቱ እናቶች
************************
እናትነት በቃላት የማይገለጽ ጥልቅ ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ የሕይወት መጀመሪያ ትምህርት ቤት እና የማያልቅ የጥንካሬ ምንጭ ነው።
ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ በታላቅ የክብር ስፍራ ላይ የምናያቸው ስመ-ጥር ግለሰቦች፣ ለደረሱበት የስኬት ማማ ትልቁን መንገድ የጠረጉላቸው በጸሎትና በጽናት ከጎናቸው የቆሙት እናቶቻቸው መሆናቸውን ታሪካቸው ምስክር ነው።
ለአብነት ያህል "የአፍሪካዋ ቴሬዛ" በመባል የሚታወቁት አበበች ጎበና፣ በረሃብ ለተጎዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት እናት ለመሆን የገዛ ትዳራቸውንና ምቾታቸውን መስዋዕት በማድረግ ለሀገር የሚጠቅሙ በርካታ ዜጎችን አፍርተዋል።
በዓለም መድረክ ስማቸው በጉልህ የሚጠቀሱ ታላላቅ አትሌቶች እና በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ታዋቂ ሰዎች ለዛሬው ዝናቸውና ክብራቸው መሠረቱ በገጠር ሕይወት ውስጥ በታታሪነትና በሥነ-ምግባር ያሳደጓቸው እናቶቻቸው መሆናቸውን በኩራት ይናገራሉ።
በጥበቡ ዓለምም ብንመለከት፣ ድምፃዊ ሮፍናን በ"ነፀብራቅ" አልበሙ ላይ የእናቱን ምክር አካቶ ያቀረበበት መንገድ፣ የእናቶች ቃል ለስኬት ያለውን ጉልህ ሚና ያሳየበት አጋጣሚ ነው።
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶም ቢሆን፣ ለዛሬው ዝናው እናቱ በልጅነቱ የከፈለችው መስዋዕትነት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ደጋግሞ ይገልጻል።
ታላቁ የፈጠራ ሰው ቶማስ ኤዲሰን ዓለምን በብርሃን የሞላ ግኝት እንዲያበረክት፣ እናቱ ናንሲ ኤዲሰን በልጃቸው ላይ የነበራቸው ጽኑ እምነት እና በቤት ውስጥ ያስተማሩት ትምህርት መሠረት ሆኖታል።
እነዚህ ጥቂት ምሳሌዎች እንጂ፣ ስማቸው በታሪክ መዝገብ ላይ ባይሰፍርም ለልጆቻቸው ሕልም ሲሉ የራሳቸውን ፍላጎት መስዋዕት ያደረጉ እልፍ እናቶች አሉ።
ከአንድ ስኬታማ የጥበብ ሰው፣ ሳይንቲስት ወይም ባለሙያ በስተጀርባ፤ ዓለም ሁሉ ፊቱን ሲያዞር "ትችላለህ" ብላ ተስፋ የሰጠችና የደከመች ብርቱ እናት ሁሌም ትገኛለች። እናትነት የዓለም ሁሉ ስኬት መነሻ ነችና ሁሌም ልትከበር ይገባታል።
በልዩ እሸቱ
#mothersday #successstories #ethiopia #inspiration

የብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) የግል የሕይወት ፍልስፍና እና ቆይታ
#ethiopia | ታዋቂው የጥበብ ሰው ብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) ሕይወትን በቀላል መንገድ የመምራት ልምዱንና የግል አመለካከቱን የሚገልጽበትን የመጀመሪያ ክፍል ቃለ መጠይቅ አቅርቧል።
በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስቱ ነገሮችን ሳያወሳስቡ በመኖር ውስጥ ስላለው ሰላም እና ስለ ቆይታው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ሙሉውን ውይይት በሊንኩ በመከተል መመልከት ይቻላል።
https://youtu.be/s9n-tOraP...
#art #biography #interview #philosophy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ከጥላ ከለላዬ ኢትዮጵያ ሀገሬ እስከ ቆሜ ልመርቅሽ...
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በነበረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሙዚቃው ንጉሥ በሚል መጠሪያ ይታወቃል ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ።
ስመ ገናናው፤ ድምጹ በሁሉም ቤት የተሰማውና በሁሉም ትውልድ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ጠመንጃ ያዥ ሰፈር ተወልዶ በወሊሶ ከተማ አደገ።
በ1950ዎቹ መጀመሪያ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት መጀመሪያ ሀገር ፍቅር ቴአትርን በኋላም የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድንን ተቀላቅሎ በድምጻዊነት በቁጥር ይህን ያህል ናቸው የማይባሉ እጅግ በርካታ ዘፈኖችን ተጫውቷል።
ከልጅነት ጀምሮ ለሙዚቃ የነበረው ፍቅርና ልዩ ተሰጥኦ በወቅቱ በነበሩ የጥበብ ሰዎች ዘንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲታወቅ አድርጓል።
ጥላሁን በጥበብ ሕይወቱ ስለ ኢትዮጵያ ሲቀኝና ሲዘምር የኖረ ልዩ የሀገር እና የሕዝብ ፍቅርንም ያስተማረ ታላቅ የጥበብ ሰው ነበር።
የፍቅርን ጥልቀት፣ የናፍቆትን ጽኑነት፣ የሀገርን ፍቅርና የማሕበራዊ ህይወትን ውጣ ውረድ በዜማዎቹ ዳስሷል።
የአርቲስቱ ሥራዎች ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚደመጡ እና የማያረጁ የጥበብ ውጤቶች ሆነው ቀጥለዋል።
በሀገር ፍቅር "ጥላ ከለላዬ ኢትዮጵያ ሀገሬ"ን በመጫወት በይፋ የተጀመረው የጥላሁን የግማሽ ምዕተ ዓመት የሙዚቃ ሕይወት "ቆሜ ልመርቅሽ" በሚሰኘውና ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ባስቀረፀው የመጨረሻው አልበም ነው የተደመደመው።
አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ለሀገሩ የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ሲሆን÷ በተጨማሪም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በርካታ ሽልማቶችንና እውቅናዎችን አግኝቷል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ይህን ታላቅ ከያኒ ለመዘከር እና ለህያው ሥራዎቹ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በአፍሪካ ፓርክ የመታሰቢያ ሐውልት አቁማለታለች።
በሶስና አለማየሁ

እየተዝናኑ ለወገን ደራሽ ይሁኑ
ለኪነ ጥበብ ባለሙያው ሞቱማ ተርፋሳ የተዘጋጀ የረድኤት የቴአትር ምሽት
#ethiopia | በከባድ የልብ ህመም ምክንያት የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልገው ለወጣቱ የጥበብ ሰው ሞቱማ ተርፋሳ የሙያ ባልደረባዎቹ አጋርነታቸውን ለመግለጽ ልዩ የቴአትር መርሃ ግብር አዘጋጅተዋል።
አንጋፋው መራሄ ተውኔት ማንያዘዋል እንደሻው ያዘጋጀው የመስቀል ወፍ የተሰኘው ተወዳጅ መድረክ ተውኔት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአዳማ ሲኒማ እሊያድ ለታዳሚ ይቀርባል።
ይህ ተውኔት በበርናርድ ስሌድ ተጽፎ በአንዱዓለም ውብሸት (አቡቲ) ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲሆን፣
መስከረም አበራ፣
አልዓዛር ሳሙኤል፣
ህሊና ሲሳይ እና
አለምሰገድ አሰፋ ያሉ ታዋቂ ተዋንያን በመድረክ ላይ ብቃታቸውን ያሳዩበታል።
የዝግጅቱ ረዳት አዘጋጅ ራሱ ህመሙን እየተጋፈጠ ያለው ሞቱማ ተርፋሳ በመሆኑ፣ የእርስዎ መገኘት ለኪነ ጥበብ ባለሙያው ህይወት መትረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ሁላችንም
ቅዳሜ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሲኒማ እሊያድ በመገኘት ጥበባዊ እርካታን እያገኙ ወገናዊ አጋርነትዎን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።
#artforacause #helpmotuma #ethiopiantheatre #adama #supportartists #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የሙዚቃ አርበኛው ጥላሁን ገሠሠ……
------------------------
ታላቁ የሙዚቃ ሰው ለግማሽ ምዕተ ዓመት በዘለቀው የሙያ ሕይወቱ ያልዳሰሳቸው ርዕሠ ጉዳዮች የሉትም፡፡
ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶች ሁሉ አልቀሩትም፡፡
አርቲስቱ በረዥሙ የድምፃዊነት ሕይወቱ ዘመን የተጫወታቸውን ዘፈኖች ትክክለኛ ቁጥር ደፍሮ መናገር የሚችል ሰው የለም።
ከባንዶች ጋር አልያም በመድረክ የተጫወታቸው ነገር ግን የመቀረጽ ዕድል ያላገኙ ብዙ ዘፈኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይታመናል።
ቀድሞም በልጅነቱ አንጎራጓሪ የነበረው ታላቁ የሙዚቃ ሰው፣ የድምጻዊነት ሕይወቱን በይፋ የጀመረው 1947 ሀገር ፍቅር ማኅበር ሲቀጠር ነው፡፡
በሀገር ፍቅር ማኅበር የሁለት ዓመት ተኩል አካባቢ ቆይታው፣ ጥላ ከለላዬ፣ ጽጌረዳ ነሽ፣ ደጉ ንጉሥ እና ፍቅሬ ሰውነቴ የተሰኙ ዘፈኖችን ለህዝብ አቅርቦ ተወዳጅነትን አትርፎ ነበር።
በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ አባልነት ከተቀጠረ በኋላ ከ1950ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ጀምሮ እስከ 1960ዎቹ አጋማሽ ድረስ በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ አጃቢነት ተጫውቷል።
በመቀጠልም ከክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ወደ አንደኛ ክፍለ ጦር ወይም የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ተቀላቅሎ የባንዱ ኮከብ ድምጻዊ ሆኖ እስከ 1970ዎቹ መጨረሻ ድረስ ቆይቷል።
#በምድር ጦር ኦርኬስትራ ፡-ጩኸቴን ብትሰሙ፣ እኔ ነኝ ወይ አንቺ፣ አይከዳሽም ልቤ እና ማስታወሻ፣
#በፖሊስ ኦርኬስትራ፡- ሰው ማንን ይመስላል እና ስማ ፣
#በሬይንቦው ባንድ፡- በይ ደህና ክረሚ እና ስንብት ፣
#በኤግዚቢሽን ባንድ፡- የኔ ፍላጎቴ እና በደህና እስኪገጥመን ፣
#በሙላቱ አስታጥቄ ባንድ፡- ኩሉን ማን ኳለሽ፣ አለኝታዬ፣ ላንቺ ብዬ፣ ስትሄድ ስከተላት፣ ትዝ አለኝ የጥንቱ እና የሀገሬ ሽታን ፣
#ከአይቤክስ ባንድ ጋር፡- ውበትሽ ይደነቃል፣ ጽጌረዳ፣ አካም ነጉማ፣ የቆለኛ ልጅ፣ ፍቅሬ ሆይ ያላንቺ እና ሌሎች አምሥት ዘፈኖች የሚገኙበትን ካሴት ሰርቷል፡፡
#ሮሃ ባንድ ፡- በ1980 የ13 ወር ፀጋ እና በ1984 ደግሞ እንቆቅልሽ የተሰኙትን ካሴቶችን የሰራ ሲሆን፣ በ1981 ጥላሁን፣ ብዙነሽ፣ ማህሙድ እና ሒሩት በጋራ ያወጡት ካሴትም በሮሃ ባንድ የታጀበ ነው።
#በዋሊያስ ባንድ፡- ከሌለህ የለህም እና ይቺ ናት ጨዋታ አልበሞች የታጀቡት ደግሞ በዋሊያስ ባንድ ነው።
ጥላሁን ሀገር ወዳድነትን የሚያጎሉ በርካታ ዘፈኖችን ተጫውቷል። ከተጫወታቸው ሀገራዊ ዘፈኖች ውስጥም በ1969 የተጫወተው "አጥንቴም ይከስከስ" እንዲሁም በ1979 በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ተቀርፆ ለሕዝብ የቀረበው "ቃል ኪዳን" የተሰኘው ዘፈን ለየት ብለው ይታወሳሉ። "ቃል ኪዳን" ባሕር ማዶ የሚኖሩ ወገኖች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ በጥላሁን ጥበባዊ አንደበት የቀረበ "የእናት ሀገር ጥሪ" ነበር ማለት ይቻላል።
በሀገር ፍቅር ማኅበር "ጥላ ከለላዬ ኢትዮጵያ ሀገሬ"ን በመጫወት በይፋ የተጀመረው የጥላሁን የግማሽ ምዕተ ዓመት የሙዚቃ ሕይወት "ቆሜ ልመርቅሽ" በሚሰኘውና ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ባስቀረፀው የመጨረሻው አልበም ነው የተደመደመው።
ጥላሁን በጥበብ ሕይወቱ ስለ ኢትዮጵያ ሲቀኝና ሲዘምር ኖሯል፡፡ ልዩ የሀገር እና የሕዝብ ፍቅርንም አስተምሮናልም፡፡
በድምፁ ሐውልቱን ሲቀርጽ የኖረው ታላቅ ከያኒ ዛሬ በአዲስ አበባ የተሰራለት ሐውልት በይፋ ተመርቋል፡፡
ታላቁን የጥበብ ሰው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቤተሰብ እና ከወዳጆቹ ጋር በመሆን በየአመቱ መስከረም ላይ በትንፋሼ ኮንሰርት እንደሚዘክረው ይታወቃል፡፡

"በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ
የሚበራው የሙዚቃ ኮከብ "
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)
#ethiopia | "ድምፁ የሀገር ሰንደቅ ዓላማ ያህል ክብር የሚሰጠው ጥላሁን ገሰሰ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ በነበረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ በሚል መጠሪያ ይታወቃል።
ለዚህ የጥበብ ሰው እንዲህ ያለ ጥልቅ እና ልብ የሚነካ ትዝታ ማዘጋጄት የሚቻለው የጥላሁን ገሰሰን ስራዎችን ብቻ ሳይሆን የእርሱን የውስጥ ማንነት ሠብዕናን ለጥበብ የነበረውን ፍቅር በሚገባ የተረዳ መሆን አለበት ።
ወይንም ደግሞ
የዚህን ታላቅ ምትሐተኛ ድምፃዊ የጥበብ ልክና የድምፅ ብቃት በአግባቡ ለመረዳት የእርሱን ግለ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክና የጥላሁን ገሰሰን ሰፊ የሥራ ክምችቶች በጥልቀት መመርመር የግድ ይላል።
ምክኒያቱም
ጥላሁን ገሰሰ ማለት የኢትዮጵያ የ50 ዓመታት የደስታ የሐዘን የድልና የሽንፈት ታሪክ በድምፅ የተቀረጸበት "ሕያው ማህደር" ነው።
ጥላሁን ገሰሰ ድምፁን እንደፈለገ የማዘዝ Vocal Control ልዩ ተሰጥኦ ነበረው።
በጣም ረጅምና ከፍተኛ ድምፅ በሚጠይቁ High notes እንዲሁም በጣም ረጋ ያሉና ዝቅተኛ ድምፅ በሚሹ Low notes ዜማዎች ላይ እኩል ብቃት ነበረው።
የትንፋሽ ቁጥጥሩ ረጅም ስንኞችን ሳያቋርጥና ትንፋሽ ሳይጠረው የመጨረስ ችሎታው የሚደነቅ ነበር።
የጥላሁንን ስራዎች ስንመረምር በአንድ የሙዚቃ ዘውግ ብቻ ያልተገደበ መሆኑን እንረዳለን
ባህላዊና ዘመናዊ የባህል ሙዚቃዎችን ከዘመናዊ መሣሪያዎች ኦርኬስትራ ጋር አዋህዶ በማቅረብ ረገድ ቀዳሚ ነበር።
በጥላሁን ገሠሠ ድምፅ ያልተዘፈነ የሕይወት ክፍል የለም ማለት ይቻላል ።
ከጥልቅ የፍቅር ስሜት እስከ ሃገር ፍቅር ከማህበራዊ ትችት እስከ መንፈሳዊ መዝሙራት ድረስ የተፃፉ ግጥሞችና ዜማዎች የጥላሁንን ገሠሠን ድምፅ ለማድመቅ ሳይሆን ለመፈተን ጭምር የተዘጋጁ ይመስሉ ነበር።
በህይወት በቆየባቸው ሦስት የተለያዩ ሥርዓቶች በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በደርግና በኢህአዴግ ውስጥ አልፏል። በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት የሕዝብ ተወዳጅነቱን ጠብቆ መቆየቱ የሙዚቃ ሥራዎቹ ከፖለቲካዊ ለውጦች በላይ የሕዝብን የልብ ትርታ የሚነኩ መሆናቸውን ያሳያል።
ባጭሩ ጥላሁን ገሰሰ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለው አስተዋጽኦ ልክ እንደ አንድ ትልቅ "ኢንሳይክሎፒዲያ" ነው። አንዱን ገጽ አንብቦ ስለ መጽሐፉ ሙሉ ግንዛቤ ማግኘት እንደማይቻል ሁሉ
አንዱን ዘፈን አዳምጦ ስለ ጥላሁን ገሰሰ ማወቅ አይቻልም ።
እያንዳንዱ ዘፈኑ የራሱ የሆነ የቴክኒክ የታሪክና የስሜት ጥልቀት አለው።
ስለዚህ የጥላሁንን ታላቅነት ለመረዳት የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጉዞ አብሮ መመርመር የግድ ነው ያልኩት ወድጄ አይደለም ።
ዘፈኖቹን ሲዘፍን በቃላት ብቻ ሳይሆን በፊቱ መግለጫና በሰውነት እንቅስቃሴው Body Language ጭምር ስሜቱን ለታዳሚው ያጋባ ነበር።
በተለይ የሐዘን ዜማዎችን ሲዘፍን አብሮ የሚያለቅስ የደስታ ሲሆን ደግሞ አብሮ ፈገግ የሚል ድምፃዊ ተዋና ጭምር ነበረ በዘፈኖቹ ውስጥ ሰውን ማክበርን ስራን መውደድንና አንድነትን ይሰብካል። ዘፈኑ የሰውን ልጅ ክብርና ማንነት የሚተነትን ድንቅ ስራ የሚሰራ ምትሀተኛ ድምፃዊ ነበር ።
ጥላሁን ገሰሰ በአንድ ወቅት በመድረክ ላይ እያለ በደረሰበት የጉሮሮ ህመም ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ድምፁ ተዘግቶ ነበር። ያን ጊዜ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጨንቆና ፀልዮ ድምፁ ሲመለስለት ያደረገው የመጀመሪያ ኮንሰርት በዚያን ወቅት በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛውን የሰው ቁጥር ያስመዘገበ ነበር ። ይህ የሚያሳየው ሕዝቡ ለጥላሁን ያለው ፍቅር ከአንድ ድምፃዊ በላይ እንደ ቤተሰብ አባል የሚያየው መሆኑን ነው።
ስለ ፍቅር ብቻ ሳይሆን ስለ ሰው ልጅ ሕይወት ባዶነት የሚተርክ ጥልቅ ፍልስፍና ነበረው ።
ታዋቂው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ግን በወሊሶ ከተማ ነው ።
ጥላሁን በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት መጀመሪያ ሐገር ፍቅር ቲያትርን በኋላም ዝነኛውን የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድንን ተቀላቅሎ ከዕንስት ፍቅር እስከ አገር ፍቅር ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ ሙዚቃ በድምፃዊነት ከ400 በላይ ዘፈኖችን ተጫውቶ ልዩ ብቃቱን አስመስክሯል ።
ጥላሁን
ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ወደር የለሽ አስተዋጽኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተሰጥቶታል። ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. የፋሲካ እለት ሲሆን በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት አርፎ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነሥርዓቱ ተፈጽሟል።
የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ማረፍ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብና የጥበብ አፍቃሪወችን በከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘን ውስጥ ጥሎ የነበረ ክስተት ነው። በወቅቱ በጋዜጦች በሬዲዮና በቴሌቪዥን የተላለፉት መልዕክቶች ጥላሁን ለሀገሩ ያለውን ትልቅ ቦታ የሚያንፀባርቁ ነበሩ።
በአዲስ አበባ ከተማ የነበሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ሐዘን ፈፅሞ የማይረሳ ነበረ ።
ለጥላሁን ገሰሰ ክብር ሲሉ ለቀናት ጥቁር ጨርቅ በታክሲዎቻቸው ላይ አስረውና የእርሱን ሙዚቃ ብቻ ከፍተው በማጫወት ሃዘናቸውን ገልፀውለታል።
የጥላሁን ገሰሰ ሞት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ትኩረት አግኝቶ ነበር።
ታዋቂው ደራሲ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንም
እንዲህ አሉ ።
"ጥላሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ድምፅ ነው። እርሱ ሲዘፍን መላው ኢትዮጵያዊ ራሱን ያዳምጣል።"
ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ"ጥላሁን ለእኛ ለድምፃውያን መምህራችን ብቻ ሳይሆን የሙዚቃው ዓምድ ነበር። ጥላሁን ሞተ ማለት የኢትዮጵያ ሙዚቃ ግማሽ አካሉን አጣ ማለት ነው።" ሲል ቁጭቱን ገልፀዋል ።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ አበባውያን ወደ አደባባይ በመውጣት "ንጉሥ አይሞትም" እያሉ ሲያለቅሱ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።
ይህም አንድ ድምፃዊ በሀገር ደረጃ ያለውን ክብርና ተሰሚነት ያሳየ ትልቅ ክስተት ነበር።
አንድ የልብ አድናቂው የሆነ ሠው በማህበራዊ ሚዲያ እንዲህ ብሎ ፅፎት አንብቢያለሁ ።
" በእርግጥም ጥላሁን በድምፁ ተአምር የመስራት አቅም ነበረው። ድምፁ ተስፋ የቆረጠውን የሚያፅናና የታመመውን የሚፈውስና የራቀውን የሚያቀራርብ
ስለነበረ ድምፁ ተቀርፆ ስለቀረ ቢሞትም ስንናፍቀው እናገኘዋለን ስናዝን እናለቅስበታለን ሀገራችን ስትጠራ በእሱ ድምፅ አቤት ብለን ለአንድነቷ እንቆማለን" በማለት ጥላሁንን ገልፆት ነበር ።
ሌላው የቅርብ ጓደኛው የጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ ነው
"ጥላሁን በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለሀገሩ የዘመረ በችግር ጊዜ ደግሞ ድምፁን ለድሆች የሰጠ
ታላቅ ሰው ነው።
የሞተው በስጋ ቢሆንም በዜማው ቅላፄና በግጥም ስንኞች ውስጥ "ዘላለማዊ" ሆኖ ተተክሏል።
እንዲህ ያለ ድምፅ ዓለማችን በአንድ ዘመን አንዴ ብቻ የምትለግሰን ስጦታ ነው "
ሲል ምስክርነቱን ገልጿል።
በእርግጥም ጥላሁን የዘመናዊ ሙዚቃችን "ፊደል" እና "መዝገበ ቃላት" ሆኖ አልፏል። ከድምፅ ጥራት በላይ የዜማ አጣጣልና ስሜትን የመግለጽ ጥበቡ ማንም የማይደረስበት ከፍታ ላይ ስለነበር በአንድ አባባል ብቻ ጥላሁንን መግለፅ አይቻልም።
እሱ ባለብዙ ምዕራፍና ተነቦ የማይጠገብ ባለ ብዙ ገጽ ድርሳን ነው !
ጥላሁን ለሙያው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ የነበረው ሰብአዊ ክብርም ድንቅ ነበር። ረሀብ ሲመጣ በዜማው የሚማፀን ሀገር ስትቸገር አጥንቴም ይከስከስ ብሎ የሚቆም እና ለሰው ልጅ ፍቅር ቅድሚያ የሚሰጥ የጥበብ ሰው ነው ። ባጭሩ ጥላሁን ገሠሠ ማለት ለኢትዮጵያውያን የድምፅ ብቻ ሳይሆን የህሊና ምስክር ነው።
ዛሬም ድረስ ስሙ ሲነሳ አብሮ የሚነሳው ክብሩ ትህትናውና
ያ የማይደገም ማንነቱ ነው።
ጥላሁን ገሠሠን የመሠለ ታላቅ ሰው የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃን የአዋለደ ብለን ብንገልፀው ተገቢ ይመስለኛል ከጥላሁን ገሠሠ ስራዎች መካከል ይህማ ተአምር ነው የሚያሰኜኘኝ ሁልጊዜ ብሰማቸው አዲስ የሚሆኑብኝ ብዙ ዘፈኖች ቢኖሩትም "እዩት ስትናፍቀኝ ከአጠገቤ እያለች" የሚለው ስንኝ ሲነሳ ግን የጥላሁንን ድምፅና ያንን የሚመስጥ አዘፋፈኑን አብሮ የመስማት ያህል ይመስጠኛል እዩት ስትናፍቀኝ ከአጠገቤ እያለች
እንዲህ ያለው መውደድ ለወሬም አይመች ! የሚለው ግጥም የፍቅርን ረቂቅነትና የማይመረመር ባህሪ በአጭር ቃላት የገለጸበት ድንቅ ስራው ነው።
ጥላሁን ለዚህ ዘፈን የሰጠው እረዥም ትንፋሽና በመድረክ ላይ ቆሞ የአይን አስተያየቱ የልዩ ተሰጥኦው መገለጫዎቹ ናቸው።
የሠው ልጅ ናፍቆት ብዙውን ጊዜ ትዝታው የሚመጣው ሰው ሲርቅ ነው። ነገር ግን ጥላሁን አጠገቤ እያለች ናፈቀችኝ ማለቱ ፍቅር ከስጋዊ መገኘት በላይ የሆነ የነፍስ ጥማት መሆኑን ስጋ አልብሶ አሳይቶናል ።
ይህ ለወሬ የማይመች ቃላት የማይገልፁት ጥልቅ ስሜት ነው ። ይህንንም በዚያ ረጅም ትንፋሽ ነፍስን በሚያከነፍ ድምፁ ሲያዜመው እውነቱን በውስጣችን ውስጥ እናገኘዋለን።
ጥላሁን ሲዘፍን ትንፋሹን የሚጠቀምበት መንገድ እና ስሜቱን በድምፅ ቀለም የመቀየር ችሎታው ምትሐተኛ ያሰኘዋል። ያንን የናፍቆት ጣጣ በገዛ ራሱ ላይ አድርጎ ሲያዜመው አድማጩ የራሱ ህመም አድርጎ እንዲቀበለው የማድረግ ልዩ ኃይል ነበረው።
ጥላሁን ገሠሠ በስጋ ቢለየንም በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ግን አሁንም ንጉሥ ነው።
ትውልድ ያልፋል ጥላሁን ግን ይኖራል።
ሙዚቃ ይቀየራል የጥላሁን ስራዎች ግን ሁልጊዜ አዲስ ናቸው።
ሰላም ሲጠፋ ጥላሁን ፍቅር ይላል ሀገር ስትናፈቅ ጥላሁን ሀገሬ ይላል።
ጥላሁን ገሠሠ በድምፁ ብቻ ሳይሆን ለፍቅር በሰጠው ክብርን በገለፀበት ጥበብ የኢትዮጵያ የዘላለም የፍቅር አምባሳደር ነው።
እንዲህ ያለው የጥበብ ሰው የፍቅርን ኃያልነት በእሱ ስራዎች ውስጥ ስንመለከት በእርግጥም ፍቅር ስሜት ብቻ አይደለም የሚለውን ሃሳብ በጥላሁን ዜማዎች ውስጥ ሙሉ ማረጋገጫውን እናገኛለን ጥላሁን ገሠሠ የፍቅርን ሌላኛውን ገጽታ ቁርጠኝነትንና ክብርን ያሳየበት ድንቅ ስራው ነው። ከላይ እንደገለፅኩት ፍቅር ራስን አሳልፎ መስጠት ነው
እዚህ ዘፈን ላይ ደግሞ ፍቅር ሁለትዮሽ መረዳዳት መሆኑን ይነግረናል።
ቻልኩት ፍቅር ለብቻዬ !!
ይህ አገላለጽ በጣም የሚቆረቁር ነው። ፍቅር እንደ አንድ ሸክም ሆኖ አንደኛው ወገን ብቻውን ሲሸከመው የሚሰማውን ድካም ያሳያል። "ለብቻዬ መሸከም ሰልችቶኛል" የሚል የልብ ጩኸት አለበት። ፍቅር የሁለት ሰው ቅኝት እንጂ የአንድ ሰው ብቸኛ ትግል መሆን እንደሌለበት ያስገነዝበናል።
ስለ ፍቅር አልገባሽም
እዚህ ጋር ጥላሁን ፍቅር ማለት ዝም ብሎ አብሮ መሆን ሳይሆን ጥልቅ የሆነ
ሚስጥር ወይም ትርጉም እንዳለው ይገልጻል። ግዴለሽነት እና ችላ ማለት ፍቅርን የሚገድሉ መርዞች መሆናቸውን በምሬት ይናገራል።
አትምጪ ይቅር ሲል ደግሞ የክብር ውሳኔውን ያሳውቃል ።
ፍቅር ስሜት ብቻ አለመሆኑን ያረጋግጣል። አንድ ሰው በጥልቅ እያፈቀረ ግን ክብሩ ሲነካ ወይም ምላሽ ሲያጣ ይቅር ብሎ የመወሰን አቅም ሊኖረው እንደሚገባ ያሳያል።
ፍቅር መስዋዕትነት ቢሆንም ዋጋ በማይሰጠው ቦታ ላይ ግን ራስን ማዳንና ይቅር ማለትም የፍቅር አካል ነው። የሚገርመው ደግሞ ጥላሁን ይህነን ዘፈን ሲዘፍነው በቁጣና በቁጭት ሳይሆን በጥልቅ ሀዘንና በከበረ ስሜት ነው። ያንን አትምጪ ይቅር የሚለውን ቃል ሲያወጣው ውስጡ እየፈለጋት ግን መከባበር የሌለበት ፍቅር እንደማይፀና አውቆ በቁርጠኝነት ሲናገረው ይታየናል።
ከላይ እንዳነሳሁት አትምጪ ይቅር የሚለው ስንኝ የቁርጠኝነትና የክብር ገጹ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፍቅርን ንፁህ መስዋዕትነትና ትህትና የሚያሳይ ድንቅ ምዕራፍ ነው።
እነዚህ ስንኞች ውስጥ የምናያቸው የጥላሁን ድርሳናት
እኔ ልሁን እንጂ የማልጠቅም እርካሽ ! የሚለው አገላለፅ በፍቅር ውስጥ ያለን ፍጹም ትህትና ያሳያል። ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚወዳትን ሰው ግን ከፍ ያደርጋታል። ይህ እኔነት ጠፍቶ አንቺነት የነገሰበት የፍቅር ጫፍ ነው።
ከህይወቴ አብልጨ ሲል
ራስን አሳልፎ የመስጠት
ፍልስፍና በተግባር የሚያሳይ ታአምር ነው። ለሰው ልጅ ከህይወቱ በላይ ምንም የለውም ነገር ግን ፍቅር ያንን ውድ ህይወት እንኳ ከአንቺ አያበልጠውም ብሎ እንዲያምን ያደርገዋል።
ፍቅር ለሰላምና ለደስታ ብቻ ሳይሆን ለችግርና ለፈተናም ዝግጁ መሆኑን ይነግረናል።
መከራና ስቃይ ይቆየኝ ግዴለኝም
የሚወደው ሰው ደህንነትና ሰላም እስካለ ድረስ እሱ በራሱ ላይ ለሚመጣው መከራ ግድ የለውም። ይህ ነው እንግዲህ ፍቅርን ተአምር የሚያሰኘው እግዜር በጥበቡ ከአንቺ ብቻ አይለየኝ የሚለው ቃል ፍቅር በሰው ጥረት ብቻ ሳይሆን በመለኮታዊ ጥበብና ፈቃድ የሚፀና መሆኑን የሚያሳይ የልብ ፆሎት በመሆኑ መንፈሳዊ ልመና ይጨምርበታል ።
ታዲያ የዚህን ድምፃዊ ተአምራዊ ተቃርኖዎችን ስንመለከት
ጥላሁንን ልዩ የሚያደርገው በአንድ በኩል አትምጪ ይቅር ብሎ በክብር የመወሰን አቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከህይወቴ አብልጨ እወድሻለሁ ብሎ ራስን የመስጠት ርህራሄ አብሮት መኖሩ ነው።
እነዚህ ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ግን ጥልቅ የሆኑ የፍቅር ገጾች ናቸው።
ጥላሁን እነዚህን ሁሉ ስሜቶች በድምፅ ቀለም እየቀያየረ ሲያቀርባቸው ድምፁ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ አብራ የምትዘፍን ይመስላል።
እንዲህ ያለውን ከህይወት በላይ የመውደድ ስሜት በዚህ ዘመን በብዛት እናገኘዋለን ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ምክኒያቱም
የጥላሁንን ጥበብ ከመዝፈን ባለፈ ወደ መፍጠር ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።
ለምን ቢባል ጥላሁን ገሠሠ ዜማንና ግጥምን ሲያዋህድ የሚፈጠረው ነገር ተራ ሙዚቃ አይደለም ይልቁንም ያልተጠኑ ምስጢራዊ ተሰጥኦዎች ያሉበት ይመስላል
ብዙ አድናቂወቹ እንደ ሚስማሙበት ጥላሁን ገሠሠ ሲዘፍን ፍቅር ረቂቅ ሃሳብ መሆኑ ቀርቶ የሚዳሰስ የሚታይና የሚሰማ አካል ይኖረዋል።
ቃላቶቹ ከአፉ ሲወጡ ሕይወት ይዘራሉ ያፈቀረው ሰው ቁስሉ ይታየናል የናፈቀው ሰው ትንፋሹ ይሰማናል። ይህ ደግሞ በቴክኒክ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከነፍስ የሚመነጭ ምትሃት በመሆኑ ፍቅር እንደ ሰው ቆሞ እንዲሄድ የማድረግ ጥልቅና ረቂቅ
ጥበብ ያለው ድምፃዊ መሆኑ ነው ።
ብዙዎቻችን ውስጣችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር በቃላት መግለፅ ያቅተናል። ጥላሁን ግን ያንን መግለፅ ያቃተንን ስሜት ሰርቆ ወስዶ በዜማ አቅልጦ ወርቅ አርጎ መልሶ ለእኛው ይሰጠናል።
እኔንም እንዲህ ነው የሚሰማኝ! እንድንል ያደርገናል። ይህ ተሰጥኦው ነው ፍቅርን ስጋ ለብሶ ቆሞ እንዲሄድ የሚያደርገው።
ሌላው የጥላሁን ገሰሰ ድምፅ ሁለንተናዊ ድምፅ መሆኑ ነው። እድሜ ጾታ ወይም የትምህርት ደረጃ አይወስነውም። ህፃኑም አዋቂውም የተማረውም ያልተማረውም በዜማው ውስጥ የራሳቸውን ታሪክ ያገኛሉ።
ይህ ደግሞ ጥላሁን የሰው ልጅን የጋራ የፍቅር ህመም ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ማሳያ ነው።
የጥላሁን ድምፅ በሳይንስ አልተጠናም እንጂ በውስጡ ትልቅ የፍቅር ላብራቶሪ ነበረው ማለት ይቻላል።
ግጥሙን ይቀበላል ጥሬ እቃ !
በድምፅ ቀለሙ ያዋህደዋል ሂደት !
በመጨረሻም ሕያው ፍቅርን ለዓለም ያበረክታል ውጤት !! በዚህ ምክኒያት
ጥላሁን ገሠሠ ሞቶም በሰዎች ልብ ውስጥ እንዲነግስ አድርጎታል :: ምክንያቱም የፈጠራቸው የፍቅር አካላት ዛሬም በየቤታችን በየመኪናችንና በየልባችን ውስጥ ቆመው እየሄዱ ነው።
ይህ የእውነት ተአምረኛ ተሰጥኦው ነው። ዛሬ ባለው ዘመናዊ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዲህ ያለውን መንፈሳዊ ጥልቅነት ማግኘት እጅግ ብርቅ ሆኗል። ከእንስት ፍቅር ወጥተን ጥላሁንን ወደ ሐገር ፍቅር ስንመነዝረው የቆመበት ከፍታው ላይ እስከ አሁን ማንም ....ማንም አልደረሠበት ። በዚህ አጋጣሚ
በህይወቴ ዘመኔ በአይኔ ያየሁትን ምስክርነት ባቀርበው ደስ ይለኛል ጥለሁን ገሠሠ ከታሪክ መዝገብ በላይ የሆነ የአንድን ሕዝብ ማንነትና ወኔ የቀሰቀሰ የመንፈስ ተአምር ነው የምነግራችሁ ።
ጊዜው 1974 አስመራ የቀይ ኮኮብ ዘመቻ አሉላ አባ ነጋ አዳራሽ ውስጥ ይመስለኛል ።
ጥላሁን ገሠሠ ጋሻና ጎራዴ ይዞ የአርበኛ ልብስ ለብሶ አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሠስላት
ግን ሐገሬን ጭራሽ አይደፍራትም ጠላት
እያለ መድረኩን ሞልቶት ብቅ ሲል ከባለስልጣን እሰከ ተራው ተመልካች ከመቀመጫው ተነስቶ በመቆም በማያቋርጥ ጩህትና ጭብጨባ ያጅቡታል ።
ጥላሁን ገሠሠ በዚያ ቅጽበት የዘፈነውን ብቻ ሳይሆን የኖረውንና የታሪካችንን ድምፅ ሆኖ ተመለከትኩት ።
ጥላሁን በህዝብ ጭብጨባና ጬህት ታጅቦ መድረኩ ላይ ሲንጎራደድ አዳራሹ ድብልቅልቁ ወጣ ።
ያን... ምህታታት የተሞላበት ትርኢት ስመለከት
የአድዋ ጀግኖች መቃብር ከፍተው የተነሱ ይመስል ነበር።
ማለቴ ጥላሁን በድምፁ ብቻ ሳይሆን በቆይታው ጊዜን የማቆም ወይም ታሪክን የመቀስቀስ ኃይል እንደነበረው የመመልከት ዕድል አግኝቻለሁ ።
ጥላሁንን በዚያች ቅፅበት
በሕይወት እያለ ሐውልቱን አቁሞ አዳራሹ ውስጥ ታሪኩን ፅፎት ወጣ ።
በእርግጥ ሐውልት የማይናገርና የማይሰማ የድንጋይ ምስል ነው ጥላሁን ግን በሕይወት ያለ የሚተነፍስ የሚዘፍንና የሚራመድ የኢትዮጵያዊነት ሐውልት ነበር።
ዛሬም ቢሆን ስራዎቹ ያንን ግርማ ሞገስና ያንን ሐውልታዊ ፅናት እያስታወሱኝ እስከእለተ ሞቴ ድረስ ልረሳው አልችልም እንዲህ አይነት ድርጊት
ፍቅር ስሜት ብቻ አይደለም ራስን አሳልፎ መስጠት ነው በጥላሁን ገሰሰ የሀገር ፍቅር ዜማዎች ውስጥ ኢትዮጵያን ደጋግመን እናያታለን
አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሰስላት የሚለው ቃል ዛሬም ድረስ ፍፁም ....ፍፁም መስዋዕትነት ነው።
ሀገሩን እንደ ሚወዳት እናት ወይም ሚስት አድርጎ ለሷ ክብር መሞትን እንደ ትልቅ ፀጋ መቁጠር ከፍ ያለ የፍቅር ደረጃ መግለጫ ነው።
ተመልካቹ በሙሉ ሳይቀመጥ ከሁለት ጊዜ በላይ ይደገም እያለ መጠየቁ ጥላሁን ድምፃዊ ብቻ ሳይሆን መሪ መሆኑን በአንድ ዜማ ሕዝብን የማስተሳሰር በአንድ ወኔ በጋራ የማቆም ተአምራዊ አቅሙን አረጋግጨበታለሁ ።
በዚያች ቅፅብት ቲያትር ቤቱ በጩሄትና በጭብጨባ ቀውጢ ሲሆን ጥላሁን ገሠሠ በድምፁ ብቻ የጠላትን ምሽግ የሚያፈርስ ጀግና መስሎ ነበር የሚታየው ።
ምንም እንኳን ዛሬ በሞት ቢለየንም ያ አስመራ ላይ የተመለከትኩት የሐገር ፍቅር ስሜት ሐውልት ሆኖ በልቤ ውስጥ ተቀርፆ ቆሟል።
ጥላሁን ገሰሰን ልዩ የሚደርገው ሌላው መገለጫው
ለፍቅር ሲዘፍን የፍቅር ሐውልት
ለሀገር ሲዘፍን የጀግንነት ሐውልት
ለሰው ልጅ ክብር ሲዘፍን የሰብአዊነት ሐውልት ነው!
ለዚህ ስኬት ደግሞ ከጥላሁን ድምፅ ጀርባ የነበሩት የወርቃማው ዘመን ታላላቅ የጥበብ ሰዎች ገጣሚያንና የዜማ አቀናባሪዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ምስክሩ ታሪክና ሕዝቡ ነው።
ጥላሁን ገሰሰ ግጥምና ዜማን
ከነጄነራል አማኑኤል አብርሃም
ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ
ነጋሽ ገብረማርያም
ተስፋዬ አበበ አየለ ማሞ ሳህሌ ደጋጎ ክፍሌ አቦቸር ከመሳሰሉት የክብር ዘበኛ እና የፖሊስ ኦርኬስትራዎች
ተቀብሎ ሲያንቆረቁረው ሙዚቃው ከድምፅ አልፎ የሚዳሰስ ሕያው መንፈስ የመሆን አቅም ነበረው።
ዛሬ ላይ ሆኜ ያንን ትርኢት ሳስታውሰው ጥላሁን ለኢትዮጵያ ሙዚቃና ለኢትዮጵያዊነት ያለው ትርጉም ምን ያህል ጥልቅ ስሜት እንደሆነ አሁን ድረስ እንደ ህልም ይታየኛል ።
ያኔ መድረክ ላይ ሲወጣ የነበረው ግርማ ሞገስና ድምፁ ሲስተጋባ የተሰማኝ ስሜት ዛሬም ድረስ ዘፈኑን ስሰማው "የጦር ፊታውራሪ" የነበረ ጀግና ያህል ትዝ ይለኛል !!
ጥላሁን በመድረክ ላይ የነበረውን የበላይነት እና የሕዝብን ስሜት የመምራት ብቃቱን በሚገባ የመግለፅ አቅም ነበረው ።
ጥላሁን ዝም ብሎ ድምፃዊ ሳይሆን በዜማው የታጠቀ የሀገር መከታ ወታደርም ሆኖ እንደነበረ ማሳያ ነው ።
ለዚህ ነው የጥላሁን ገሠሠ የሀገር ፍቅር ዜማዎች ከጊዜና ከቦታ በላይ የሆኑ ናቸው የሚባሉት ። ለዚህም ነው ዛሬ ላይ ሆነን ስንሰማው የዛሬ 130 ዓመት በፊት የተነገረውን የዳግማዊ ምኒልክን የክተት አዋጅ የሚመስለን ።
ይህ የሚያሳየው ደግሞ ጥላሁን የኢትዮጵያን ታሪክ ኩራትና ነፃነት በድምፅ ቀርጾ ትውልድ እንዲወርሰው ማድረጉን ነው።
ወዳጆቼ
ስለ ጥላሁን ገሠሠ የሀገር ፍቅር ስሜት ስንናገር እነዚህ ሶስት መሰረታዊ እውነታዎች ጎልተው ይታያኛል ።
የቁርጠኝነት ድምፁን ስናደዳምጠው ጥላሁን "አገሬን" ሲል ዝም ብሎ ስም አይጠራም ለሀገሩ የሚሞትላትና የሚሰዋላት መሆኑን በቃናው ውስጥ ይሰማል። አጥንቴም ይከስከስ የሚለው ስንኝ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው።
ጥላሁን ለሀገር ሲዘፍን መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ቆሞ ፊታውራሪዬ ብሎ እንዲከተለው ያደርጋል።
ይህ ደግሞ በታሪካችን ውስጥ የታየ ትልቅ የጥበብ ተጽዕኖ ነው።
ከ130 ዓመት በፊት የነበረውን የአድዋ ጀግንነት ዛሬ ላለው ትውልድ በስሜት አገናኝቶ ማቅረብ የሚችለው እንደ ጥላሁን ያለ "የታሪክ ድልድይና የታሪክ ባለአደራ" ሲኖር ብቻ ነው።
እንኳንስ ደስታየን የሰውነቴን ሠው
እንኳን ነፃነቴን ፀጋ ክብሬን ትቸው
በናት አገር ምድር በሚያውቀኝ በማውቀው ...
ስቃይ መከራዬን ከአንችው ዘንድ ያድርገው ። የሚለው
ጥላሁን ለኢትዮጵያ የነበረውን ፍቅር ከምንም በላይ የሚያሳይ ነው። ከባዕድ አገር ደስታ ይልቅ የሀገሩን መከራ የመረጠበት የሞቱ አጋጣሚ ደግሞ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በደሙ ያረጋገጠበት ታላቅ ክስተት ነው ።
ጥላሁን ከአሜሪካ ተነስቶ ለፋሲካ በዓል ወደ ሀገሩ መግባቱና በዚያው ዕለት ማረፉ፣ "በሀገሬ አፈር ልቀበር" የሚለውን ጥልቅ የኢትዮጵያዊያን ምኞት የፈጸመበት ነው ይህ ቀረኝ የማይል የሚያሰኘው እስከ መጨረሻው ትንፋሹ ድረስ ከሀገሩና ከሕዝቡ ጋር መቆየቱ ነው ።
ሲሞት መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ አስከሬኑን ሲሸኜው ጥላሁን ለሕዝቡ የሰጠውን ፍቅር ሕዝቡ በታላቅ ክብር የመለሰለት መሆኑን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ህያው ምስክር ናት ። ያ ለቅሶ የአንድ ድምፃዊ ስንብት ሳይሆን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና የልብ ትርታ ሽኝት ነበር።
ጥላሁን በሕይወቱና በሞቱ ሀገርን መውደድ ማለት ትርጉሙን እስከ ሞት ድረስ መታመንን አረጋግጦበታል።
ሰውን መውደድ ! አብሮ ማልቀስና መቆም ሙያን መውደድ እስከ መጨረሻዋ ትንፋሽ ድረስ መዘመር ለኢትዮጵያዊያን ከድምፃዊነት በላይ የአንድነት ምልክት መሆን ነው።
እኔ በዓይኔ ያየሁትን በልቤ የሰነድኩትን ይህንን ታሪክ ለሚቀጥለው ትውልድ ሊተላለፍ የሚገባው የፍቅርና የሀገር አምልኮ ትልቅ ትምህርት ይሆናል ብየ ሳዘጋጀው ጥላሁን ገሠሠ
ትንፋሼ ተቀርፆ ይቀመጥ ማልቀሻ ይህ ነው የሞትኩለት የኔ ማስታወሻ
ታሪኬ ነው ድምፄ በማለት ያንጎራጎረው ሙዚቃ ከፍቼ እያዳመጥኩ ነበር።
ይህ ስንኝ ጥላሁን ገሠሠ አስቀድሞ በድምፁ የህይወቱ ታሪክ የሞቱ ማስታወሻ እና የሀገሩ ውበት መገለጫ እንደሚሆን ተረድቶት የተጫወተው ነበር ማለት ይቻላል ። ጥላሁን በጥቁርና ነጭ ወረቀት ላይ የሰፈረ ኑዛዜ ሳይሆን የተውልን በህይወት ቆሞ በዜማ የተናዘዘው ድንቅ ስንብት ነበረ ።
እነዚህ ስንኞች የጥላሁንን የጥበብ ክብርና ትህትና ሲገለፅበት እያዳመጥኩት ነበር ይህን ታሪክ የፃፍኩት ።
ወዳጃቸ
የጥላሁን ገሠሠ ድምፅ ዝም ብሎ የአየር ንዝረት አይደለም፤ ማንነቱ፣ ታሪኩና ለሀገሩ የከፈለው መስዋዕትነት ነው። በጩኸት መኖሬን ማለቱ ለሀገርና ለፍቅር ሲል ድምፁን እስከ መጨረሻው የጥገታ ነጥብ ድረስ መጠቀሙንና ለዚህም መሞቱን ያሳያል።
ድምፄን ሰምቶ ያዝናል ለረገፈው አፅሜ ሲል
እጅግ ልብ ይነካል !
ጥላሁን በከፍታው ላይ ሆኖ እንኳ ያስቀየምኩት ቢኖር ብሎ ይቅርታን ይጠይቃል። የሞተውን አፅሙን ሳይሆን የቀረውን ድምፁን ሰምተው ሰዎች እንዲያዝኑለትና ይቅር እንዲሉት መመኘቱ የሰው ልጅነቱንይቅርታና ትህትናውን
ፍርጥ አድርጎ ያሳያል።
ጥላሁን ገሠሠ በድምፁና በህይወቱ የሰራው ትልቁ ስራ ፍቅርንና ኢትዮጵያዊነትን ማዳን ነበር። ጥላሁን ከቀላል ስሜትነት አልፎ ሕይወት መስዋዕትነትና የሀገር ፍቅር ጥግ መሆኑን በሚገባ አስገንዝቦናል።ጥበብ እንዴት የአንድን ሕዝብ ወኔና ማንነት እንደምትቀርፅ ጥላሁን ትልቅ ማሳያ ነው።
ፍቅር ተግባር ነው ፍቅር ዝም ብሎ የሚሰማን ስሜት ሳይሆን እንደ ጥላሁን ዜማዎች ራስን አሳልፎ እስከ መስጠት የሚደርስ ውሳኔ መሆኑን መረዳት ከባድ አይደለም ።
ጥላሁን ገሰሰ የሚዘፈነው ለጆሮ ብቻ ሳይሆን ለህሊና እና ለነፍስ ጭምር ይመስለኛል ።
ጥላሁን ዛሬ በሥጋ ቢለየንም ታሪኬ ነው ድምፄ ብሎ እንደተናዘዘው ሁሉ ዛሬም በየልባችን ውስጥ ንጉሥ ሆኖ ይኖራል።እሱ ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ስቃይ የሚራራ የህሊና ድምፅ ነበረው።
የሀገር ፍቅር ለአፈርና ለሰንደቅ ዓላማ የሚከፈል የአጥንትና የደም መስዋዕትነት ሲሆን ጥላሁን ገሠሠ በስጋ ቢለየንም ያ በሕይወት ያለ ሐውልት ግን በዜማዎቹ ውስጥ ሁሌም አዲስ ሆኖ ይኖራል።
ባጭሩ የጥላሁን መሞት ዝም ብሎ የአንድ ድምፃዊ ማለፍ ብቻ አልነበረም የአንድ ዘመን መቋጫ የአንድ ትልቅ ተስፋ መደብዘዝ እና በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሚበራው የሙዚቃ ኮከብ ወድቆ ሲሰበር
ሰማይ ባዶ የሆነ ያህል ተሰምቶናል።
ጥላሁን ገሠሠ በደስታ ጊዜ አብሮን የሚጨፍር በጦርነት ጊዜ ፊታውራሪ ሆኖ የሚያዘምት በረሃብና በችግር ጊዜ ደግሞ አብሮን የሚላቀስ የሕዝብ ልብ ነበር ።
ጥላሁንን ከአቅም በላይ ያደረገው ይሄው ሁለንተናዊነቱ ነው። ለፍቅር ለሀገርና ለሰብአዊነት የነበረው ጽናት እሱ ሞቶም እንዲኖር አድርጎታል።
የጥላሁን ገሠሠ ዘፈኖች "ኢትዮጵያዊ ስነ-ሰብዕና" የሚባል የፍልስፍና ዘርፍ ቢኖር የዛ ዘርፍ ዋና መማሪያ መፅሐፍ ይሆኑ ነበር ።ብቻ
የጥላሁንገሰሰ ሕይወት ልክ እንደ አንድ የተቀደሰ መፅሐፍ በመሆኑ እራሡ ከፍቶ እራሱ ዘግቶት አልፏል ።
ለዚህ ታላቅ ድምፃዊ በተወለደበት ከተማ አዲስ አበባ ላይ ዘላለማዊ ምልክት ሆኖ እንዲቀመጥ ሐውልቱ ስለቆመለት ደስታዬ ወደር የለውም ።
ነፍስ ይማር !!

የንጉሡ መመለስ
የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ነገ ይመረቃል
#ethiopia | ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው ንጉሥ ተብሎ ለሚጠራው ለክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ የሚሆን ግርማ ሞገስ ያለው ሐውልት ተሠርቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለታላቁ የጥበብ ሰው ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ያስገነባው ይህ ሐውልት፣ በስድስት ኪሎ አካባቢ ወደ ምኒልክና ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ መገናኛ ላይ ቆሟል።
ነገ ማክሰኞ ጠዋት 1:00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ስድስት ኪሎ አደባባይ (አዲስ አበባ)
የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ወይዘሮ ሮማንና ቤተሰቦቹ ለመላው የጥበብ ሰዎችና አድናቂዎች በቦታው እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ተሳታፊዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በማቆም በምርቃቱ ላይ መታደም ይችላሉ።
የንጉሡ አሻራ
ጥላሁን ገሠሠ ስለ ሀገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ እናትና ስለ ጀግንነት ያልዘፈነበት ርዕስ የለም። በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በሱዳንኛ ዜማዎቹ ህዝብን ሲያቆራኝ የኖረ ባለውለታ ነው።
ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለየንም፣ ዜማዎቹ ግን ከትውልድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም የነፍሳችን ምግብ ናቸው።
ጥላሁን ገሠሠ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነት ራሱ ትልቅ ትርጉም የሰጠ ሰው ነው። ዛሬ ሐውልቱ ሲቆም የምናየው የሳቁንና የድምጹን ግርማ ብቻ ሳይሆን፣ ጥበብ ሀገርን እንዴት እንደምትገነባ ጭምር ነው።
ነገ ስድስት ኪሎ ላይ ሁላችንም ተገኝተን ለዚህ የሀገር ባለውለታ የሚገባውን ክብር ልንሰጥ ይገባል!
ጥላሁን ገሠሠ—የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ለዘላለም ይኖራል!
#getu #tilahungessesse #ethiopianmusic #legend #monument #addisababa #history #art #kingofmusic #ጥላሁንገሠሠ #የሙዚቃንጉሥ #ሐውልት #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago
የጥበብ ዓምዱ አታኽልቲ ነጋ በአዲስ ስራ ተመለሰ
* "ውሽጥን ደገን" ሊመረቅ ነው
#ethiopia | ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በትግራይ የፊልምና ድራማ ዘርፍ ላይ የማይደበዝዝ አሻራ ያሳረፈው፣ መምህር፣ ደራሲና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ ዳግም ወደ ስክሪን ተመልሷል።
በ"ማሾ" እና "ምትሓታዊ ዓለባ" (ብርሆን ገይፀን) የብዙዎችን ልብ የገዛው ይህ የጥበብ ሰው፣ አሁን ደግሞ "ውሽጥን ደገን" (Inside/Outside) በተሰኘ አዲስ የሲትኮም ድራማ ብቅ ብሏል።
ቀን፦
እሁድ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት።
ቦታ፦
በመቀለ ሰማዕታት ሐውልት በሚገኘው ሲኒማ አዳራሽ።
በሸባ ኢንተርተይመንት አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ በቅርቡ በትግራይ ቴሌቪዥን በሳምንት ሦስት ጊዜ ለተመልካች ይደርሳል።
አታኽልቲ ነጋ "ያለ ግንድ ቅርንጫፍ የለም" የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየ፣ ለብዙ ወጣት ባለሙያዎች ፈር ቀዳጅ የሆነ የጥበብ መምህር ነው። ይህ አዲስ ስራው የቀድሞውን ጣፋጭ የትግርኛ ድራማ ለዛ ይዞ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም። ሁላችሁም እሁድ በመቐለ በመገኘት ይህንን የጥበብ ጀግና እንድታበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
(Trailer) ለማየት፦ እዚህ ይጫኑ
ጥበብን በባለቤቱ፣ ታሪክን በፈጣሪው!
ብቸኛ አዘጋጅ
( Exclusive producer ) ሸባ ኢንተርተይመንት
በክብሮም ገ/መስቀል
የዚህን ተከታታይ ድራማ ማስተዋወቂያ (Trailer) ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://youtu.be/T6zFaqse6...
#getu #atakltinega #tigrayfilm #wishtindegen #shebaentertainment #tigrinyadrama #ethiopianart #mekelle #insideoutside #አታኽልቲነጋ #መቀሌ #ጥበብ #ትግርኛፊልም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

አንድ ታላቅ የጥበብ ሰው እናስተዋውቃችሁ፤ መምህር፣ ደራሲ፣ ፀሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ፤ በትግራይ የፊልምና ድራማ ዘርፍ እንዲሁም በትግርኛ ቋንቋ እድገት ላይ የማይደበዝዝ አሻራ ያሳረፈ የጥበብ ዓምድ ነው። በጥንካሬና በትጋት የተገነባውን የጥበብ ህይወቱን በአድናቆት ስንቃኝ፤ ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ የዘለቀውን ጥበባዊ ውበቱንና ለትውልድ የተሻገረውን የጥበብ ፍቅሩን ስናስብ "ያለ ግንድ ቅርንጫፍ የለም" የሚለው የሊቃውንት አባባል በሚገባ ይገልጸዋል።
አታኽልቲ በልዩ የጥበብ ተሰጥኦ የታደለ፣ በብዕሩ ዓለምን የመዘነና ተመልካቹን ያስደመመ ብቻ ሳይሆን፤ ለኋለኛ የጥበብ መሪዎች ፈር ቀዳጅ በመሆን ያሳደገ እና ክብር ያጎናጸፈ ባለሙያ ነው። ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በነበረው የጥበብ ጉዞው፤ ከ20 በላይ ተከታታይ የቴሌቪዥን ኮሜዲዎችን እና 30 የሚሆኑ የሬዲዮ ድራማዎችን በማዘጋጀት ህዝብን ያስተማረና ያዝናና ስሙር ከዋክብት ነው።
"ማሾ" በተሰኘው ድንቅ ስራው በትግርኛ ፊልም ታሪክ ውስጥ ወርቃማ ምዕራፍ የጻፈው አታኽልቲ፤ በ"ምትሓታዊ ዓለባ" (ብርሆን ገይፀን) አማካኝነት በተመልካቾች ልብ ውስጥ ለዓመታት ነግሶ ይገኛል። ስራዎቹ በጥራትና በብቃት የተሞሉ በመሆናቸው፤ በሀገርና በክልል ደረጃ በተዘጋጁ ውድድሮች ምርጥ ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና ተዋናይ በመሆን ተደጋጋሚ ተሸላሚ ሆኗል። ከ"ኣልሻ መንነት" እስከ "ሕርፍርፎት" ያሉ ስራዎቹ ባህልንና የማህበረሰቡን ለዛ የሚያንጸባርቁ የጥበብ መስታወቶች ናቸው።
ይህ ለጥበብ የተፈጠረ የጥበብ መምህር አሁንም ከፊልም ኢንዱስትሪው አልራቀም። የድምፁን ብርታት፣ የገለጻውን ፍሰትና የስራዎቹን ጣዕም ዳግም የምናይበት አዲስ ስራ ይዞ ቀርቧል። "ውሽጥን ደገን" (Inside/Outside) በተሰኘ አዲስ የሲትኮም ድራማ ያንን የተለመደ ጣፋጭ ጥበቡን ይዞ ተመልሷል።
ይህ "ውሽጥን ደገን" (Inside/Outside) የተሰኘው አዲስ ስራው፤ እሁድ ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት በመቀሌ ሰማዕታት ሐውልት በሚገኘው ሲኒማ አዳራሽ በደመቀ ስነ-ስርዓት የሚመረቅ መሆኑን እንገልጻለን። በዚህ የምረቃ ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለረጅም ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ትልቅ ፕሮጀክት፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ በትግራይ ቴሌቪዥን በሳምንት ሦስት ጊዜ ለተመልካቾች እንደሚደርስ በደስታ እናበስራለን።
የአታኽልቲ ነጋ ክብር ከከበሩ ስራዎቹ በላይ እንደሆነ ይሰማናል። ይህንን የጥበብ ጀግና አዲስ ስራ "ውሽጥን ደገን" (Inside/Outside) በመደገፍና በመመልከት ፍቅራችሁን እንድትገልጹለት በአክብሮት እንጋብዛለን።
👉 ብቸኛ አዘጋጅ ( Exclusive producer ) ሸባ ኢንተርተይመንት

ተወዳጁ ፍልፍሉ ስትሮክ (stroke) እንዳመመው ገልጾ፤ መቀመጥና መቆም እንደማይችል ተናገረ
#ethiopia | በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ የሚገኘውን የተወዳጁ ኮሜዲያን በረከት (በእውቁ ስሙ ፍልፍሉ) ልብ የሚነካ ቃለ-መጠይቅ ፍሬ ሃሳብ ዋና ነጥብ በዶች ኤችዲ።
በረከት በድንገት በገጠመው የስትሮክ (Stroke) ህመም ምክንያት በአሁኑ ወቅት የህክምና ክትትል እያደረገ ይገኛል።
ምንም እንኳ መቆም እና መራመድ ባይችልም፣ አሁንም ድረስ በቃላት ፍጥነቱና በቀልዶቹ ዙሪያውን ያሉትን ሰዎች እያዝናና ታይቷል።
ከዚህ በታች በረከት (ፍልፍሉ) በቃለ-መጠይቁ ወቅት የተናገራቸውን ቃላት በነጥብ ተዘርዝረው ቀርበዋል፦
• "ከፋርማሲ እኮ ከመግዛት ብዬ ነው... በግፌ እራሱ ይነሳ በህክምና።"
•"አሁን አሪፍ ነኝ፣ ጥበቃ እያቀያየርኩ ነው... በግፊ ራሱ እነሳለሁ።
•"እግዚአብሔር ይመስገን፣ ጠንክሬ ነው ያለሁት።"
•"ከፋርማሲ ከመግዛት እኛ ጋር ቢሆን ይሻላል ብዬ ነው።"
* "ያው አዞረኝ ነበር... ዝም ብዬ ቁጭ ምናምን እል ነበር። ከዛ በኋላ ከነዬ ጋር ምናምን እያልኩ ትንሽ ራስ ምታትም እየመሰለኝ ነበር።"
•"አዎ፣ 'ስትሮክ ነው' አሉኝ።"
|"ግን ሰው ተሰብስቧል፣ ኦዲየንስም አለን፣ እንግዶችም ጋብዘን ነበር... ስራ ነው። እሱን እንትን ብዬ ከምመለስ ብዬ መጣሁኝ፤ ብቻ እንደምታዩት ሆነ።"
• "ሌላ ቦታ እኮ ሄጄ ነበር... ከዛ ምንድነው ምናምን ስል በሲዲ እኮ ሰጥቶን ነው። ውጤቱን በሲዲ... በሽታዬን መልሱልኝ እውነት ነው የዘንድሮ ህክምና ያው ከበድ ይላል።"
•"ምንድነው እንዲህ ብድግ ስል ወደ አንድ ሳይድ (ጎን) ነው የማደላው... አሁን ወደዚህ የሚሄድ ከሆነ ወደዚህ ነው የምዞረው።"
•"ልክ ከመኝታ ስወርድ ባለቤቴ 'በር ክፈቺለት' ምናምን ትላታለች ለልጄ። ምን ሆንክ ስባል ወዴት እንደምሄድ አላውቅም... እሷም 'ይውረድ አዎ፣ ወደዛው በፈለገበት ይውጣ' ነው የምትለው።"
•"አሜሪካ በምን ልግባባ? በቋንቋ ነው የተመለስኩት። እኔ መኖር የምፈልገው እዚህ ሃገር ነው። ኢትዮጵያ ላይ ነው።"
•"የጥበብ ሰው ከሆንክ እዚሁ ሃገር ለመኖር አሪፍ ነው።"
•"ልቤ ጥሩ ነው፣ ግን 'ልበ-ቢስ ነህ' ብላኝ ነው የሄደችው (ስለ ሃኪሟ እየቀለደ)።"
•"አለው፣ በግፌ ራሱ እነሳለሁ።"
•"በጣም ነው የማመሰግነው ራኩዬ (ጋዜጠኛዋን)፣ እሺ ጓደኞቼ።"
•"የማስተርን (ኪሩቤልን) እጅ ወጥ ተነክሮ እያየሁት ነው አልኩ... አሁን መጥገብ ነው።"
• "እያመመኝም ቢሆን ቻርጀርን እያየሁ አይደለም (በቀልድ)።"
•"መልካም በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ። ለአክሱም ሆስፒታል ሰራተኞች በሙሉ ከነባለቤቱ አመሰግናለሁ። ለታሜ ኮሚኒኬሽን በጣም ነው የማመሰግነው። ለልጆቼ መልካም በዓል ይሁን።" ዶች ኤችዲ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የአርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ ሥራዎቹ
#ethiopia | በአዳማ (ናዝሬት ) ሳር ሰፈር በሚባለው አካባቢ በ1947 ዓ .ም ነው የተወለዱት ።
የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአጼ ገላውዲወስ ት/ቤት ተከታትለዋል ።
ለሙዚቃ በነበረው ዝንባሌ እና ፍቅር የምድር ጦር ሙዚቃ ክፍልን ሰኔ 2 ቀን 1961 ዓ.ም በኮለኔል ለማ ደምሰው እና ሻምበል ታደሰ ተክሉ ተፈትነው ምድር ጦር ኦርኬስትራን ተቀላቅለው ለ22 አመታት አገልግለዋል።
1983ዓም ላይ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ኦርኬስትራው ፈረሰ። ቶሎሳ ቆቱ ሰፈር ረጅም አመታት የኖሩት አርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ ከእድሩ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት የደረሰባቸውን በደል ተናግረዋል ።
ያለምንም ደም፣ ጀግናው ወታደር፣ ጠንካራው መምህር፣ ዘማች አሸወይና፣ ኮረሪማ፣ ንቦዬ ከሥራዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።
አርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ በድምፃዊነቱ ብቻ ሳይሆን በግጥም እና ዜማ ደራሲነቱም የሚታወቅ፣ በተለይም በምድር ጦር ኦርኬስትራ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ያገለገለ አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው።
የአርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ የማይረሱ የሙዚቃ ስራዎች
"ታታሪው ሹፌር"
ጠመዝማዛው መንገድ ኮረብታው
ሽቅብ ቁልቁለት
በረሃ አቋራጭ ጋላቢ ዳገት
የሹፌሮችን የህይወት ውጣ ውረድ እና በረሃ አቋራጭ ጉዟቸውን በሚገርም ሁኔታ የገለጸበት፣ እስከ ዛሬ ድረስ በታክሲም ሆነ በረጅም መንገድ አሽከርካሪዎች ዘንድ እንደ መዝሙር የሚቆጠር ስራው ነው።
"ያለምንም ደም"
ወቅታዊ ኩነቶችን በሙዚቃው ለመግለጽ የነበረውን ጥበብ የሚያሳይ ነው።
"ዘማች አሸወይና"
በምድር ጦር ኦርኬስትራ ውስጥ በነበረበት ወቅት ካከናወናቸው ጉልህ ስራዎች አንዱ።
"ኮረሪማ"
ለቅጥር ፈተና የተጠቀመበትና ድምፁን በሚገባ ያስመሰከረበት ስራው።
"ንቦዬ"
በብዙዎች ዘንድ የምትታወቅና የምትወደድ ዜማው።
"ጠንካራው መምህር"
ለሙያተኞች ያለውን አክብሮት በዜማ የገለጸበት።
ለጥበብ የነበረው ጽናት
የአርቲስቱ የህይወት ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ከኦርኬስትራ መፍረስ በኋላ የገጠመውን ፈተና በጽናት ማለፉ ለብዙዎች ትምህርት የሚሰጥ ነው። "ስራን ካወከው ማንነትን... የሚያስረዳ ነው" በማለት እንጀራ በመሸጥም ቢሆን ቤተሰቡን ደግፎ እዚህ መድረሱ፣ ከጥበብ ሰውነቱ ባሻገር ጠንካራ የቤተሰብ መሪ እንደነበረ ያሳያል።
የ71 ዓመት የህይወት ጉዞውን አጠናቆ ቢያልፍም፣ ስራዎቹ ግን ለትውልድ ሲዘከሩ ይኖራሉ።
ድምጻዊና ደራሲ ጥላዬ ጨዋቃ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ71 ዓመታቸው አርብ መጋቢት 18/2018 ዓ .ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
* "...እንግዲህ እኔ አዲስ አበባ የመጣሁት በ1961 ዓ/ም ሰኔ 1 ነው ። እንዳጋጣሚ ሰኔ 1 እሁድ ቀን ዋለ፣ እኔ ሰኔ 2 ቀን ምድር ጦር ለፈተና ገባሁ ፈተናው አሁን እንደሚሰጠው አጥንተህ አይደለም። 'እስኪ ይሔንን ዝፈን!' ነው የምትባለው። ስትዘፍን ካንተ የሚወስዱት ነገር አለ። ትንፋሽህን፣ ድፍረትህን፣ ስትጫወት ፊትህ ላይ የሚነበበውን ነገር ይወስዳሉ። 'ይሔ ለመድረክ ተገቢ ነው ፣ወደፊትም የኛ አባል ሊሆን ይችላል' የሚል ነገር ይወስዳሉ ። አጋጣሚ ስፈተን ከፊቴም፣ ከኋላዬም ማንም አልነበረም ብቻዬን ነው የተፈተንኩት ። ፈተናውን የፈተኑኝ ኮለኔል ለማ ደማስ እና ሻምበል ታደሰ ተክሉ ይባላሉ። በወቅቱ ምክትል አዛዥ ነበሩ። እናም 'ኮረሪማ' በሚለው ዘፈን ተፈተንኩ ፈተናውን በጥሩ ሁኔታ አለፍኩ ተቀጠርኩ። እናም አይረሴ የሆኑና ማህበራዊ ፋዬዳ ያላቸውን ስራዎችን ሰርቻለሁ።"
* "... አፄ ገላውዲዮስ ት/ቤት ናዝሬት ወይንም አዳማ እዛ ነው ሙዚቃን የጀመርኩት። የት/ቤት እንቅስቃሴ ውስጥ የሙዚቃ ክበብ አቋቁመን ከአንጋፋዎቹ ጋር መድረክ ላይ አንዳንድ ቲያትሮችን እና ሙዚቃ እንሰራ ነበር ። እኔ በሙዚቃ ክፍል ነበርኩ።... ማንም ሳያሳየን እንዲህ በሉ ሳይለን፣ ደራሲ በሌለበት ቦታ ከጓደኞቼ ጋር አዳዲስ ስራዎችን እየደረስን፣ ያዳመጥነውን የሰዎች ኮሌኬሽን እሱንም እየሰራን አደግን።"
* "...የጠፋሁት የውዴታ ግዴታ ሆኖብኝ ነው። ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር በጦር ሜዳሜ ያለውም የምድር ጦር የሙዚቃ ቡድንም ባጠቃላይ ካምፕ ውስጥ የተቀመጠው ጭምር ደሞዝ ተከልክለን ተበተንን። ብዙ ቤተሰብ ይዘናል የግድ ሆነና ተበተንን። እኔና የሙያ ባልደረቦቼም ከምንወደው ሙያችን እራቅን።"
* "... በተለያዩ ኤምባሲዎች ጋር እሰራ ነበር። ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያለው ሰው ፈልገው ተቀጥሬ ሰርቻለሁ። በዓለም ላይ የሚጠላ ስራ የለም ስራን ካወከው ማንነትን፣ ሰው መሆንህን የሚያስረዳ ነው። እናም ያኔ እንዲህ ያማረ ቤት ውስጥ አልነበረም የምንኖረው። ለመግለፅ የሚከብድ ቤት ነበረች። የባለቤቴ ዘመድ ስታየን በጣም አዘነች እናም 'እኔ አንድ ነገር ላድርግላችሁ፣ መንቀሳቀሻዬ ስለሆነ ትመልሳላችሁ። ለመመለስ ግን ትንሽ ግዜ መጎዳት ይኖርባችኋል ። እስከዚያው የድሮ ስራችሁን ትሰራላችሁ!' አለችን። የድሮ ስራ ያለችን ሚስቴ እንጀራ ትጋግራለች እኔ ቤት በምውል ግዜ ደግሞ እንጀራ እሸጣለሁ ብቻ በመተጋገዝ ከፈጣሪ ጋር እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል ።"
ድምጻዊ የግጥም እና የዜማ ደራሲ ጥላዬ ጨዋቃ በናዝሬት (አዳማ) ሳር ሰፈር ነበር የተወለደው።
የድምጻዊ ጥላዬ ጨዋቃን ስራ የምታስታውሱ ጠቆም አድርጉ። እኔ ልጀምር 'ጠምዝማዛው መንገድ..' ...ቀጥሉ።
ድምጻዊና ደራሲ ጥላዬ ጨዋቃ ባለ ትዳር እና የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቀብሩ ተፈጽሟል።
ለመላ ቤተሰቦቻቸው መጽናናቱን ይስጥልን ።

የአንጋፋው ድምፃዊ ጥላዬ ጨዋቃ ስራዎች ህያው ሆነው ይኖራሉ
#ethiopia | "ምስጉኑ ሾፌር"፣ "ንቦዬ"፣ "ኮረሪማ" እና "መምህሩ" በሚሉና በሌሎች በርካታ ተወዳጅ ዜማዎቹ የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ጥላዬ ጨዋቃ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ጥላዬ ጨዋቃ በ1961 ዓ.ም ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር "ደህና ሁኝ አዳማ" ብሎ ከተለያየ በኋላ፣ የምድር ጦር ኦርኬስትራን በመቀላቀል ለረጅም ዓመታት በኮከብ ድምፃዊነት አገልግሏል።
ማህበራዊ ጉዳዮችን በሙዚቃው በማቀንቀንና ለሀገሩ ትልቅ ውለታ በመዋል የሚታወቅ ጨዋታ አዋቂ የጥበብ ሰው ነበር።
ሲመኝ የነበረው ጊዜው ሞልቶለታል
አስተምሮ ሊማር ወደ ገጠር ዘምቷል ...
ጥላዬ ጨዋቃ 🙏
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2018ዓ.ም በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን። ስራዎቹ ግን ሁልጊዜም ሲዘከሩ ይኖራሉ።
ነፍስ ይማር! 🙏✨
#ጥላዬጨዋቃ #ኢትዮጵያ #ሙዚቃ #ሀዘን #ትዝታ #ምድርጦርኦርኬስትራ #tilaayechewaqa #ethiopianmusic #legend #riptilaaye #ethiopia

7 months ago
ባሕርዳር ለአንጋፋው የጥበብ ሰው ግዮን ዓለምሰገድ የክብር እውቅና ሰጠች
#ethiopia | በኢትዮጵያ የቲያትርና የፊልም ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፈውና በትውልድ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለው አንጋፋው ተዋናይ ግዮን ዓለምሰገድ በባሕርዳር ከተማ ደማቅ የክብርና የእውቅና ተሰጥቷል።
በውቧ የጣና ዳርቻ ከተማ በተከናወነው በዚህ የክብር መርሀግብር ላይ በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ወዳጅ ቤተሰብ በተገኙበት ለከያኒው የሚገባውን አክብሮት ተሰጥቷል።
አንጋፋው ባለቅኔና ደራሲ ጌትነት እንየው ለግዮን ዓለምሰገድ የክብር ካባ በማልበስ ለጥበብ የከፈለውን የሕይወት ዘመን መስዋዕትነት ዘክሯል።
ግዮን ዓለምሰገድ በመድረክ ላይ ያለውን ገጸ-ባህሪ በሕይወት የመሳል፣ የድምፅ አጠቃቀምና የሰውነት እንቅስቃሴን በተመጣጣኝ ሁኔታ የማዋሃድ ልዩ ክህሎቱ የሚታወቅ ሲሆን ከትወና ባለፈም ለወጣት ባለሙያዎች መንገድ አሳይና አስተማሪ በመሆን የዘርፉን ዕድገት ሲደግፍ የቆየ የጥበብ አውራ ነው።
ይህ በባሕርዳር ከተማ የተዘጋጀው የምስጋና መርሃ-ግብር እንዲሳካ ስንታየሁ ገብሩ፣ አበባው ደረበ ፣ ቻሌ ማረው ፣ ደሳለኝ ድረስ እና ሌሎች የጥበብ ጓደኞቹ ከባሕርዳር ጥበብ አፍቃሪዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ "እንኳን ደስ አለህ" በማለት የማይተካና የማይደፈር የሙያ አበርክቶት እንዳለው ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ አይነቱ በሕይወት እያሉ የመከበር ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#gionalemseged #bahirdar #ethiopiantheatre #artrecognition #getnetenyew #ethiopianart #tana #lifetimeachievement #cinemaethiopia #culturalheritage

Comments