4 months ago
ድንቅ የሕክምና ስኬት በአገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
#ethiopia | በናዳ ምክንያት ወገቡ ተሰብሮ ተስፋው ጨልሞ የነበረው ወጣት፣ በሆስፒታላችን የሕክምና ባለሙያዎች ብቃት ዳግም ወደ ሕይወት ተመልሷል።
አንድ ወጣት በስራ ላይ እያለ በደረሰ የናዳ አደጋ የአከርካሪ አጥንቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰብሮ ነበር።
የጭንቅላት፣ የሕብለሰረሰር እና የአከርካሪ አጥንት የሕክምና ቡድኑ ለ4 ተከታታይ ሰዓታት የፈጀ እጅግ ውስብስብ ቀዶ ሕክምና አከናውነዋል።
ቀዶ ሕክምናው በስኬት ተጠናቆ ታካሚው በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል።
ይህ ስኬት ሆስፒታላችን ዘመኑ የደረሰበትን የሕክምና ቴክኖሎጂና ጥበብ በመጠቀም ለወገኑ የሚሰጠውን አገልግሎት በተግባር ያሳየበት ነው። "ችግር ቢኖርም፣ መፍትሔው እኛ ጋር አለ!" የሚለውን መመሪያችንን በተግባር አረጋግጠናል።
በናዳና መሰል አደጋዎች ከሚመጡ ጉዳቶች ራስዎን ይጠብቁ። ድንገት አደጋ ቢከሰት እንኳ ወደ ሆስፒታላችን ፈጥነው በመምጣት አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት እንደሚችሉ እናሳስባለን።
አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
- እንጅባራ፣ ኢትዮጵያ
የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል!
#agewmidirhospital #medicalsuccess #spinesurgery #injibara #ethiopiandoctors #healthexcellence #hoperestored #ethiopia #የጤናመረጃ #አገውምድር #ሕክምና

5 months ago
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ ህጻናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ፤ መፍትሄውስ ምን ይሆን?
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት ከተለያዩ የአፈጣጠር የጤና ችግሮች ጋር እንደሚወለዱ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ። ከእነዚህ ችግሮች መካከል «ስፓይና ቢፊዳ» (Spina Bifida) እና ተያያዥነት ያለው የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ወይም «ሃይድሮሴፋለስ» (Hydrocephalus) በዋናነት ይጠቀሳሉ።
የሴንትራል መላ ሮተሪ ክለብ፣ ሪችአናዘር ፋውንዴሽን፣ አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና የጤና ሚኒስቴር በመተባበር «የአፈጣጠር ችግሮችን መቆጣጠርና መንከባከብ» በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ እንደተገለጸው፥ እነዚህ የጤና እክሎች ሕጻናትን ለዕድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ብሎም ለሞት ያጋልጧቸዋል።
የችግሩ ዋነኛ መንስኤ ምንድነው?
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የስፓይና ቢፊዳ (የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር ክፍተት) ችግር የሚከሰተው በእናቶች የፎሊክ አሲድ (Folic Acid) እጥረት፣ በሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፣ እንዲሁም እናቶች በሚጠቀሟቸው አንዳንድ መድኃኒቶች ምክንያት ነው።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች የሚከተሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል
* የአመጋገብ ዘይቤ፡ እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆኑ ሴቶች በተፈጥሮ ፎሊክ አሲድ ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር አለባቸው።
* ቅድመ ዝግጅት፡ እርግዝና ከማቀድ 3 ወራት በፊት ጀምሮ እና በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እንክብሎችን መውሰድ እጅግ አስፈላጊ ነው።
* የበለፀጉ ምግቦች፡ በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ የስንዴ ዱቄቶችን እና ዘይቶችን መጠቀም ችግሩን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል።
ይህ አገር አቀፍ መድረክ፤ ከአፈጣጠር ችግር ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የህይወት ጥራት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስልቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthnews #ethiopianhealth #ministryofhealth #spinabifidaawareness #folicacid #healthypregnancy #addisababa #የጤናመረጃ #ኢትዮጵያ

6 months ago
"ልጄ ቀኝ እና ግራ እግሩ እኩል አደሉም ወይም ሲራመድ ይስበዋል ምን ሊሆን ይችላል?"
#ethiopia | ይህ ከአንድ ወላጅ የተጠየቅኩት ጥያቄ ነው:: መራመድ በጀመሩ ህፃናት የእግር ቁመት እኩል አለመሆን ወይም አንዱ መሰለል ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንደኛው ከነርቭ መወጠር ጋ የተገናኘ ነው::
በእግር ላይ ያለው ምልክት ቆይቶ ከወራት ወይም ዓመታት በሁአላ ቢሆንም የሚታየው ችግሩ ግን የሚከሰተው ቀድሞ ነው:: በአብዛኛው በተፈጥሮ ነው የሚከሰተው:: ቀድሞ ማወቅም ይቻላል::
በተፈጥሮ የሚከሰት የህብለሰረሰር መወጠር (Tethered cord) ወደ እግር የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ስለሚያመጣ አንደኛው እግር ከሌላኛው እኩል አያድግም:: ልጁም እግሩን በነፃነት ማዘዝ እየከበደው ይመጣል:: ይሄንንም ለማካካስ ሲል በተርከዝ መርገጥ ትቶ በ ግር ጣቶች ብቻ ለመርገጥ ይሞክራል:: እግሩም እየተወጠረ መሄድ ስለሚከብደዉ እየሳበው ይሄዳል::
ከዚህ ባለፈ የነርቭ መልክት መተላለፍ መዛባት ወደ ሽንት ፊኛ ሲደርስ ሽንት መቆጣጠር አለመቻል ይሄም በልጆች ቀኑን ሙሉ ዳይፐር አንደረጠበ መቆየት ይኖራል:: ሽንት በፊኛ እየተጠራቀመ ሲመጣ ወደ ኩላሊት እየተመለሰ ኩላሊት ዉስጥ መጠራቀም እና ተደጋጋሚ የኩላሊት እንፈክሽን ያመጣል አለፍ ሲልም ኩላሊት ስራ ሊያቆም ይችላል::
ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ደግሞ ድርቀት ያመጣባቸዋል:: ይህ መወጠር ከአርከካሪ ጎን ያሉ ጡንቻዎችን በማዛባት የአከርካሪ መጣመም ሁሉ ያመጣል::
እንዴት ማወቅ ይቻላል?
ችግሩ ከዉስጥ ቢሆንም ከቆዳ ላይ የሚያሳየው ምልክት አለ:: ለምሳሌ ከጀርባ ላይ ያለ አንድ ቦታ ችምችም ያለ ፀጉር: መሃል ወገብ ላይ ያበጠ ወይም የተከማች ስብ: መሃል ወገብ ላይ ያለ Dimple (መሰርጎድ) : የአከርካሪ መጣመም እና የመሳሰሉት::
ሕክምና አለው?
አዎ መታከም ይችላል:: ነገር ግን ሕክምናው ህመሙ እንደታወቀበት ጊዜ ይወሰናል:: ተጨማሪ የMRI ምርመራ ያስፈልጋል:: በዋነኘት የተወጠርዉን ህብለሰረሰር በማላቀቅ ያንን ተከትሎ የሚመጣዉን መዘዝ መቀነስ ነው:: አንዴ የደርሰዉን ጉዳት መመለስ ግን እጅግ አዳጋች ነው ሲሉ ለሐኪም ገጽ ተናግረዋል::
N.B ለእያናዳንዱ ታካሚ የራሱ የህክምና እና የክትትል plan ያስፈልጋል:: ሁሉም አንድ አይነት ስላልሆነ::
References
1. Guggisberg, D., et al. (2004). Skin markers of occult spinal dysraphism in children: a review of 54 cases. Child's Nervous System
2. International Survey on the Management of Skin Stigmata and Suspected Tethered Cord. Child's Nervous System, Vol. 26
3. Kulkarni, A. V., et al. (2017). Evaluation and management of tethered cord syndrome in occult spinal dysraphism. Child's Nervous System.
ቸር ያሰማን!
ዶ/ር ሱራፌል መኮንን: ረዳት ፕሮፌሰር
የህፃናት አንጎል ህብለሰረሰር ነርቭ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሺያሊስት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#የጤናመረጃ #hakimpage #የህፃናትጤና #የነርቭህክምና #ዶክተርሱራፌል #የህብለሰረሰርመወጠር #ethiopiahealth #parentingtips #pediatricneurosurgery

Comments