6 months ago
"ልጄ ቀኝ እና ግራ እግሩ እኩል አደሉም ወይም ሲራመድ ይስበዋል ምን ሊሆን ይችላል?"
#ethiopia | ይህ ከአንድ ወላጅ የተጠየቅኩት ጥያቄ ነው:: መራመድ በጀመሩ ህፃናት የእግር ቁመት እኩል አለመሆን ወይም አንዱ መሰለል ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም አንደኛው ከነርቭ መወጠር ጋ የተገናኘ ነው::
በእግር ላይ ያለው ምልክት ቆይቶ ከወራት ወይም ዓመታት በሁአላ ቢሆንም የሚታየው ችግሩ ግን የሚከሰተው ቀድሞ ነው:: በአብዛኛው በተፈጥሮ ነው የሚከሰተው:: ቀድሞ ማወቅም ይቻላል::
በተፈጥሮ የሚከሰት የህብለሰረሰር መወጠር (Tethered cord) ወደ እግር የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ስለሚያመጣ አንደኛው እግር ከሌላኛው እኩል አያድግም:: ልጁም እግሩን በነፃነት ማዘዝ እየከበደው ይመጣል:: ይሄንንም ለማካካስ ሲል በተርከዝ መርገጥ ትቶ በ ግር ጣቶች ብቻ ለመርገጥ ይሞክራል:: እግሩም እየተወጠረ መሄድ ስለሚከብደዉ እየሳበው ይሄዳል::
ከዚህ ባለፈ የነርቭ መልክት መተላለፍ መዛባት ወደ ሽንት ፊኛ ሲደርስ ሽንት መቆጣጠር አለመቻል ይሄም በልጆች ቀኑን ሙሉ ዳይፐር አንደረጠበ መቆየት ይኖራል:: ሽንት በፊኛ እየተጠራቀመ ሲመጣ ወደ ኩላሊት እየተመለሰ ኩላሊት ዉስጥ መጠራቀም እና ተደጋጋሚ የኩላሊት እንፈክሽን ያመጣል አለፍ ሲልም ኩላሊት ስራ ሊያቆም ይችላል::
ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል የሚሄድ የነርቭ መልክት መዛባት ደግሞ ድርቀት ያመጣባቸዋል:: ይህ መወጠር ከአርከካሪ ጎን ያሉ ጡንቻዎችን በማዛባት የአከርካሪ መጣመም ሁሉ ያመጣል::
እንዴት ማወቅ ይቻላል?
ችግሩ ከዉስጥ ቢሆንም ከቆዳ ላይ የሚያሳየው ምልክት አለ:: ለምሳሌ ከጀርባ ላይ ያለ አንድ ቦታ ችምችም ያለ ፀጉር: መሃል ወገብ ላይ ያበጠ ወይም የተከማች ስብ: መሃል ወገብ ላይ ያለ Dimple (መሰርጎድ) : የአከርካሪ መጣመም እና የመሳሰሉት::
ሕክምና አለው?
አዎ መታከም ይችላል:: ነገር ግን ሕክምናው ህመሙ እንደታወቀበት ጊዜ ይወሰናል:: ተጨማሪ የMRI ምርመራ ያስፈልጋል:: በዋነኘት የተወጠርዉን ህብለሰረሰር በማላቀቅ ያንን ተከትሎ የሚመጣዉን መዘዝ መቀነስ ነው:: አንዴ የደርሰዉን ጉዳት መመለስ ግን እጅግ አዳጋች ነው ሲሉ ለሐኪም ገጽ ተናግረዋል::
N.B ለእያናዳንዱ ታካሚ የራሱ የህክምና እና የክትትል plan ያስፈልጋል:: ሁሉም አንድ አይነት ስላልሆነ::
References
1. Guggisberg, D., et al. (2004). Skin markers of occult spinal dysraphism in children: a review of 54 cases. Child's Nervous System
2. International Survey on the Management of Skin Stigmata and Suspected Tethered Cord. Child's Nervous System, Vol. 26
3. Kulkarni, A. V., et al. (2017). Evaluation and management of tethered cord syndrome in occult spinal dysraphism. Child's Nervous System.
ቸር ያሰማን!
ዶ/ር ሱራፌል መኮንን: ረዳት ፕሮፌሰር
የህፃናት አንጎል ህብለሰረሰር ነርቭ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሺያሊስት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#የጤናመረጃ #hakimpage #የህፃናትጤና #የነርቭህክምና #ዶክተርሱራፌል #የህብለሰረሰርመወጠር #ethiopiahealth #parentingtips #pediatricneurosurgery

Comments