6 days ago
አርሴናል በቪኒሲየስ ጁኒየር ዙሪያ ፍላጎቱን አጠናክሯል፤ ነገር ግን ስምምነት ገና አልተደረሰም
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሴናል የሪያል ማድሪዱን ብራዚላዊ ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት እያጠናከረ መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ የስፖርት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ሆኖም እስካሁን በሁለቱ ክለቦች መካከል ይፋዊ የዝውውር ድርድር አልተጀመረም።
ሪያል ማድሪድ ከ26 ዓመቱ አጥቂ ጋር የኮንትራት ማራዘሚያ ውይይት እያደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም። ይህም አርሴናል ሁኔታውን በቅርብ እንዲከታተል አድርጎታል።
እንደ Sky Sports እና The Guardian ዘገባ፣ አርሴናል ቪኒሲየስ አዲስ ኮንትራት ካልፈረመ የክለቡ ቀጣይ ዋነኛ የዝውውር ኢላማ እንደሚሆን ይታመናል። ሆኖም ዝውውሩ በግዙፍ የዝውውር ክፍያና ደመወዝ ምክንያት በእጅጉ አስቸጋሪ እንደሚሆን ተገልጿል።
በመሆኑም በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው "Breaking" የሚለው ምስል ቪኒሲየስ ወደ አርሴናል መዛወሩ ተጠናቋል የሚል ይፋዊ ማረጋገጫ አይደለም። እስካሁን ያለው ሁኔታ የፍላጎት ደረጃ ላይ ያለ እና ውይይቶች ገና ያልተጠናቀቁ መሆናቸውን የታማኝ የስፖርት ምንጮች ያስረዳሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

30 days ago
አርጀንቲና ከ2-0 መመራት ተነስታ ግብፅን 3ለ2 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች
#ethiopia | የ2026 የዓለም ዋንጫ የ16 ዙር ጨዋታ ላይ የዓለም ሻምፒዮኗ አርጀንቲና ከሁለት ግቦች መመራት በኋላ አስደናቂ ተመላሽ በማድረግ ግብፅን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ ማለፏን ዓለም አቀፍ የስፖርት ዜና አውታሮች ዘግበዋል።
ግብፅ በመጀመሪያው አጋማሽ ያሳየችው ጠንካራ አቋም አርጀንቲናን በፈተና ውስጥ ከቶታል። የግብፅ ግብ ጠባቂ ሙስጠፋ ሾቤር የሊዮኔል ሜሲን የፍፁም ቅጣት ምት ጨምሮ በርካታ ወሳኝ ኳሶችን በማዳን ቡድኑን አስቀድሞ በሁለት ግቦች ልዩነት እንዲመራ አስችሎ ነበር።
ይሁን እንጂ አርጀንቲና በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አስደናቂ ተመላሽ አደረገች። ሊዮኔል ሜሲ በአንድ ግብና በአንድ የግብ ማመቻቸት ቡድኑን ወደ ድል ሲመራ፣ አርጀንቲና 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ጨዋታውን በማሸነፍ የዋንጫ ተስፋዋን አስቀጥላለች።
በዚህ ውጤት አርጀንቲና በሩብ ፍጻሜው በስዊዘርላንድ እና በኮሎምቢያ ጨዋታ አሸናፊ ከሚሆነው ቡድን ጋር ትገናኛለች።

2 months ago
ማርከስ ራሽፎርድ ወደ እናትቤቱ
#ethiopia | እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በባርሴሎና ቤት የነበረውን የውሰት ዘመን አጠናቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ዮናይትድ ለመመለስ ተቃርቧል።
ተጫዋቹ በካምፕ ኑ ስኬታማ የውሰት ጊዜን ቢያሳልፍም፣ ከብሉግራናዎቹ ጋር የሚኖረው ቆይታ በዚህ ክረምት እንደሚያበቃ ተረጋግጧል።
የባርሴሎና አመራሮች ተጫዋቹን በ30 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ በቋሚነት የመግዛት ፍላጎት እንደሌላቸው ለኦልድትራፎርዱ ክለብ በይፋ አስታውቀዋል።
የራሽፎርድ የውሰት ውል በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የሚያበቃ ሲሆን፣ ከሰኔ 30 ጀምሮ በይፋ የማንችስተር ዮናይትድ ተጫዋች ሆኖ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዴኮ ራሽፎርድ በክለቡ መልካም ጊዜን እንዳሳለፈ ገልጾ፣ ሆኖም ዮናይትዶች የጠየቁት የዝውውር ዋጋ ክለቡ ካቀደው በጀት በላይ መሆኑን አረጋግጧል።
ካታላኖቹ ተጫዋቹን በድጋሚ በውሰት ውል ለማቆየት ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ የማንችስተር ዮናይትድ አቋም ካልተቀየረ ግን የ28 ዓመቱ አጥቂ ወደ እንግሊዝ የመመለሱ ነገር በእጅጉ አይቀሬ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ማርከስ_ራሽፎርድ #ማንችስተር_ዮናይትድ #ባርሴሎና #የተጫዋቾች_ዝውውር #የስፖርት_ዜና

12 months ago
🌐 The daily postን 1000+ Subscribers በማድረስ እናበረታታቸው።
በተከፈተ አጭር ጊዜ ውስጥ የተረጋገጡ፡
🎤 ሀገርኛ ዜናዎች
🎤 ዓለም አቀፍ ዜናዎች
🎤 የስፖርት ዜናዎች
🎤 አስገራሚ ታሪኮችን
በፍጥነትና በጥራት እያቀረበ ይገኛል።
ሊንኩን ተጭነው join ያድርጉና +1000 Subscribers እናድርሰው
https://t.me/dailynews151

1 year ago
የስፖርት ጋዜጠኛ ቀን ታላቁ መሰወር ሲታወስ !
‹‹ዳኙ ሊመታ ነው፤ ዳኙ ገላግለን . . . ወይኔ ዳኙ አ - ገ - ባ -፤ ደንሶ አገባ ዳኙ፣ ቀኝ አሳይቶ ግራ፣ ግራ አሳይቶ ቀኝ በጣም አስደናቂ ግብ ነው . . . ›› ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ደስታና ሲቃ፣ ስሜትም በተቀላቀለበት ድምፀት ታኅሣሥ 17 ቀን 1980 ዓ.ም. ያስተጋባው ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ነበረ፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ በስፓርት ጋዜጠኝነት ከቀደምቶቹ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፣ የጅብራተሩ አለት ይድነቃቸው ተሰማ፣ ይንበርበሩ ምትኬ፣ ጎርፍነህ ይመርና አይተኬው የቀጥታ ዘገባ ባለሟሉ የድሬዳዋ ፍሬ ደምሴ ዳምጤ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ጋዜጠና ደምሴ ዳምጤን በሬዲዮ መስማት ሜዳው ውስጥ ቀጥታ ጫወታን ከመከታተል የበለጠ ሃሴትን ያጎናጽፋል። በዚህም በዘመኑ ”እግር ካስን በሬዲዮ የሚያሳይ!” ተብሎለታል።
ስፖርት ዘጋቢነት ድንቅ የሆኑ ባለሙያዎች ስራቸውን አስቀምጠውልን አልፈዋል። በርካቶች ደግሞ የነሱን ፈለግ ተከትለው ድርሻቸውን ተወጥተዋል። ገና በለጋ እድሜው በ16 ዓመቱ ወደ ስፓርት ጋዜጠኝነት ሙያ የተሰማራው ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤም ከነዚህ ተርታ ይመደባል። ይህን የአገር ቅርስ ለአፍታ እናስታውሰው።
በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ሁነኛ ሥፍራ ያለው ደምሴ፣ የስፖርት ዜናዊነቱን የጀመረው ምሥራቃዊቷ ድሬዳዋ ከተማ በአማተርነት እየዘገበ ወደ አዲስ አበባ መላክ በጀመረበት ጊዜ ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያና ብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ጋዜጠኛና ‹‹የስፖርት ፋና›› ጋዜጣ መሥራች ከነበረው ታላቁ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ተሰማ ጋር ቅርበት ስለነበረው ከድሬዳዋ የሐረርጌን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየዘገበ ይልክ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ተወልዶ ያደገው ድሬደዋ ሲሆን በኢትዮጵያ ሬድዮ ከመቀጠሩ በፊት የስፖርት ፊሪላንስ ጋዜጠኛ ሆኖ ከትውልድ ስፍራው ይሰራ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ደከመኝ ሳይል የሰራና በዚህም በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ባለሙያ ነበር፡፡
በሙያውም አትላንታ፣አቴንስና ቤጅንግ ኦሎምፒኮችን በስፍራው በመገኘት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፏል፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ለ 40 አመት ከሁለት ወር ያህል የ ኢትዮጵያ እግር ኳስናአትሌቲክስ ነባራዊ ምስክር ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምሥራቅና በመካ ከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ድል ሲያደርግ ጋዜጠኛ ደምሴ በውስጣዊና ውጫዊ ደስታረስርሷል ፡ በአትሌቲክሱም ዘርፍ በጀግኖች አትሌቶች ድል የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍብሎ ሲውለበለብ የደስታ ሳግ እየተናነቀው ድሉን በልዩ የስሜት የበላይነት ዘግቧል፡፡ ከ ሞስኮ እስከ ባርሴሎና ፡ከ አትላንታ እስከ ሲድኒ ፡ ከ አቴንስ እስከ ቤጂንግ ደምሴየ ሀገር ኩራቶች አብሪ ከዋክብቶች የደመቁበትን ደማቅድል ለሚወደው ህዝብበአይረሴና ተናፋቂ ድምፁ አስተጋብቷል ፡ ታሪክ ሲሰራ ከታሪክ ቀማሪዎች ጋርተገኝቷል፡፡ ታሪካቸውን ሰንዷል እነሆ አብሮም ታሪክ ሆኗል ፡፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ በ 40 ዓመታት የኢትዮጵያ ስፖርት ውጣ ውረድ ውስጥ ደሙእስኪንተከተክ ድረስ ተችቷል፡፡ ጮኋል ገምግሟል ፡፡ ስፖርትና ስፖርትን ብቻ ዘግቧል፡፡ ስነ- ስፖርትን ዘምሯል፡፡ ለብዙ ወጣቶች በተለያዩ ስፖርቶች መሳተፍና የስፖርት ጋዜጠኞች መፈጠር ከፍላጎት መቀስቀሻ ምንጭነት ያለፈ የሙያ ስነ ምሳሌ ሆኗል ፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ የሀገር ፍቅር ያለው ባለሙያ ነው ፡፡ የሀገር ፍቅሩንም በስራው ላይ ባሳየው ትጋት አስመስክሯል፡፡ ለሙያውም ዋጋ ከፍሏል ፡፡ ለምሳሌ ደራርቱ ቱሉበባርሴሎና ኦሎምፒክ ያሸነፈች ጊዜ ሌሊት በእግሩ ከቤቱ እስከ ሬዲዮ ጣቢያ ድረስ መሄዱ ትልቅ ምስክር ነው ፡፡ ጥርሱን በስፖርት ዘገባ ነቅሏል ለማለት ይቻላል ፡፡ ለአንድባለሙያ በህዝብ ዘንድ መወደድ ከባድ ነው፡፡ ደምሴ ግን ፍቅሩን አግኝቶታል ፡፡ብንል ማጋነን አይሆንም ።

Sponsored by
Surafel
Comments