4 months ago
ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት
የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ማንነት?
#ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ የስነዳ ሥራ ታሪካቸው መዝገበ አእምሮ ላይ የሚሰነድላቸው ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ይጠቀሳሉ።ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በታሪክና ባህል ዙሪያ በርካታ መፅሐፍትን በመድረስ ትልቅ አሻራ አኑረዋል።ከ30 በላይ መፅሀፍትን የደረሱት እኒህ ሰው የሀይማኖት ሰባኪ፣ ፀሀፊ እና ዲስኩር አቅራቢ በመሆን ለአገራቸው አገልግሎት ሰጥተዋል። የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን የመሠረቱት ዲያቆን ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ፣ የኢቢሲ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ተሹመዋል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ታሪክ ሰንደውታል።
#ቅድመ ነገር
በነገረ ሀይማኖት፣ በሥነጽሑፍ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በጥናትና ምርምሮች ከምልዓት በተጠጋ መሰጠት ያገለገሉ ሰው ናቸው፣ ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
የተወለዱት ደሴ ከተማ ነው። በወላጅ አባታቸው የንግድ ሥራና እንቅስቃሴ ምክንያት፣ ነፍስ በማያውቁበት እድሜ የመላ ቤተሰቡ ቋሚ መኖሪያ ወደ ባህርዳር ከተማ ተዛወረ። በመሆኑም አብዛኛውን ለሕይወት ስንቅ ሆኖ የቆያቸውን የእውቀት መሠረት ያገኙት በዚሁ በባህርዳር ከተማ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጼ ሰርጸ ድንግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መለስተኛ ደረጃን በፋሲል መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ከዚህ መደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ወላጅ እናታቸው ለትምህርትና ንባብ የሰጡት ትኩረት የንባብ ልምዳቸውን በእጅጉ እንደቃኘው በተለያየ ጊዜ በሰጧቸው ቃለመጠይቆች ደጋግመው ያወሳሉ።
#የሥነጽሑፍ ፍቅር
በልጅነት እድሜ ከዘመናዊ ትምህርት ጎን ለጎን፣ ባደጉበት ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርትን በሚገባ ቀስመዋል። ይህም አገልግሎታቸው ከፍ ብሎ ቤተክርስትያንን በዲቁና እንዲያገለግሉ የክህነት መዓረግ አስገኝቷቸዋል። ከዚያም ባሻገር ወደ አካባቢው ከሚያቀኑ በእውቀትና በመንፈሳዊ ጽናት የታወቁ አባቶች መምህራን ብዙ ትምህርትን የመቅሰም እድል ነበራቸው፣ ተጠቅመዉበታልም።
ይህ ሁሉ ተዳምሮ በልጅነት እድሜ የተለያዩ ሥነጽሑፋዊ ሥራዎችን እንዲጽፉ፣ አልፎም በትምህርት ቤት በጠዋት የተማሪዎች ሰልፍ ሰዓት መድረክ ላይ ወጥተው እንዲያቀርቡ አስችሏቸዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳሉም በሰልፍ ሰዓት ለተማሪዎች ዜና ያቀርቡ ነበር። በንባብ የተገነባ መሠረት ላይ የተጣለ ማንነታቸውም ለሥነጽሑፍ በተለየ እንዲሳቡ አድርጓቸዋል።
#ከአዲስ አበባ እስከ ኬንያ
ከባህር ዳር አዲስ አበባ ያቀኑት በ1982 ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ እንደገቡም ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በዲፕሎማ ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። በዚያም ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአቅራቢያ በሚገኘው በኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጡ ነበር።
የአንደኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ታድያ በፖለቲካ እንቅስቃሴ የተናጠችው ኢትዮጵያ፣ ወጣት ተማሪዎቿ ወደ ብላቴ እንዲሄዱ ተወሰነባት። ዲያቆን ዳንኤልም በዚህ መሠረት ወደብላቴ የውትድርና ማሠልጠኛ ከሄዱ ተማሪዎች መካከል ሆኑ። ይህ ከተለያዩ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ወጣቶችን በአንድ እንዲሰባሰቡ እድል የፈጠረው አጋጣሚ፣ ለዳንኤል የተለያዩ ባህሎችን፣ የሀገር መልኮችን እንዲያዩ እድል የፈጠረላቸው ነበር።
የብላቴ ሥልጠና ተጠናቅቆ ምረቃ ሳይደርስ ግን ደርግ ወርዶ ኢሕአዴግ ገባ። በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም አብዛኞቹ ወደ ኬንያ ሄዱ። ዳንኤልም በኬንያ የተወሰኑ ወራት ቆይተው፣ ኢሕአዴግ መንበረ ሥልጣኑን አደላድሎ ከያዘ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ወጣቶች ሁሉ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተባለና ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ። በአንድ ዓመት ውስጥም የሦስት መንፈቅ ትምህርት ተከታትለው ዲፕሎማቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀብለው አጠናቀቁ።
#መምህርነት
ከዚህ በኋላ በተመረቁ ተማሪዎች ምደባ መሠረት ሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር (በቀድሞ አጠራር) ደረሳቸው። ምንም እንኳ አዲስ አበባ ላይ ሥራ ያገኙና ምደባውን መተው የሚችሉ ቢሆንም፥ “እንዲሁ በነጻ የተማርኹትን ያህልም ቢሆን ማገልገል አለብኝ” በማለት ምድባውን ተቀብለው፣ እንደውም ‘ቢቻል ሰው ሊሄድ የማይመርጥበት ራቅ ያለ ስፍራ መድቡኝ’ አሉ። በጊዜው ግን አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት የደረሳቸው በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር ጅሩ ነበርና በዚያ የአማርኛ መምህር ሆነው ማገልገል ጀመሩ።
በዚያም የመምህራን እጥረት ስለነበር፣ ከአማርኛ ባለፈ ታሪክ እና አካባቢ ሳይንስ (ጂኦግራፊ) ያስተምሩ ነበር። ከዚያ ጎን ለጎን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስጠትና በማስተማር የአካባቢውን ማኅበረሰብ አገልግለዋል።
የማገልገል ጽኑ ፍላጎት እና ባመኑበት ‘ለብቻም ቢሆን የመቆም’ ጽናት ውስጥ ሆነው፣ የመምህርነት አገልግሎታቸውን ጨርሰው አዲስ አበባ ተመለሱ።
ቀጥለውም ዲፕሎማ በተመረቁበት ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል። ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊትም ሆነ በኋላ፥ በማኅበረ ቅዱሳን በመደበኛ አገልግሎት ሠርተዋል። ሐሳብ አመንጭቶ መጽሐፍ ከመጻፍ በላይ የማሳተምና ማሰራጨት ክብደቱን በመረዳት የመጽሐፍ ህትመት ሥራ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም ‘አግዮስ’ የተባለውን የራሳቸውን የመጽሐፍ ማሳተሚያና ማሰራጫ ከፍተው በዘርፉ ሠርተዋል።
ከዚህም ባሻገር የምክር አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም በ2010 ዓ.ም የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።
#የመጽሐፍ ሥራዎች
መሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሠላሳ ሦስት በላይ መጻሕፍትን ለአንባብያን አድርሰዋል። እነዚህም እንደ ‘ብቻዬን እቆማለሁ’፣ ‘ጠጠሮቹ እና ሌሎችም’፣ ‘የሰርቆ አደሮች ስብሰባ’ ከሚሉና ከመሳሰሉ ከተወሰኑ የወግ ስብስብ መጽሐፎች ባለፈ፣ ዳጎስ ያሉ በጥናትና ጥልቅ ንባብ ላይ የተመሠረቱ፣ ሃይማኖታዊ ብሎም ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ናቸው።
ዳንኤል እስከ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መሥራች ናቸው። ከዚህም ባሻገር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን መሥራቾች መካከል ይገኙበታል። በዚህ ማኅበር ውስጥ የሚታተሙ መጽሔት፣ ጋዜጣና መጻሕፍት ዝግጅት ክፍል ላይም ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና ሐመር መጽሔትም ላይ በርካታ የጽሑፍ ሥራዎቻቸው ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ በቅርብ በፋና ሚድያ ኮርፖሬት የቦርድ አባል ብሎም ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ለሀገር ይጠቅማል ብለው ባመኑበት መስክ እና ተቋም የቦርድ አባልና ሊቀመንበር ሆነዋል፣ ሠርተዋል።
‘የዳንኤል ክብረት ዕይታዎች’ የሚለው መጦመሪያ ድረገጻቸው ላይ የሚያሰፍሯቸው ጽሑፎች ብሎም በተለያዩ መድረኮች በመገኘት የሚያቀርቧቸውና የሚሰጧቸው ማኅበራዊ ኂሶች ብዙ ትኩረት የሚስቡና ተጽእኖ ፈጣሪ ነበሩ፣ ናቸው። በቃል ብቻ ሳይሆን በመጽሐፎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል። ለተጨማሪ ጥናትና ምርምር የሚሆኑ የሆኑ ሥራዎቻቸውም ጥቂት አይደሉም።
ብዙ የደከምኩባቸው የሚሏቸው ሁለት መጻሕፍት አሉ። አንደኛው ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘው በአቡነ ተክለሃይማኖት የሕይወት ታሪክ ዙሪያ የሠሩት ሲሆን ሌላው ‘አራቱ ኃያላን’ የተሰኘ መጽሐፍ ነው። በቅርብና መጨረሻ ላይ ለንባብ ካቀረቡት ዳጎስ ያለ መጠን ያለው ‘የትርክት እዳና በረከት’ መጽሐፋቸው በፊትም፣ ‘እጨጌ እንባቆም ከየመን እስከ ደብረሊባኖስ’፣ ‘ራዕየ ዮሐንስ’፣ ‘ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ’ የተሰኙ የመጽሐፍ ሥራዎቻቸው ከብዙ በጥቂት የሚጠቀሱ ናቸው።
#ቤተሰብ
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ከትዳር አጋራቸው ወይዘሮ ጽላት ጌታቸው ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በትዳር ቆይተዋል። በዚያም ሦስት ወንዶች (አቤሜሌክ ዳንኤል፣ ባሮክ ዳንኤል እና ባህራን ዳንኤል) እና አንዲት ሴት ልጅ (አንኪዮን ዳንኤል) አባት ለመሆን በቅተዋል።
ሙሓዘ ጥበባት የሚለውን ማዕረግ፣ ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘውን መጽሐፍ ባስመረቁበት ወቅት ‘ስም ከግብር አብሮ ይሄዳልና...’ ሲሉ፣ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ የሰጧቸው ስያሜ ነው። ሙሓዘ ጥበባት ማለት ‘የጥበብ መፍሰሻ’ ማለት ነው።
#ምስክርነት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመገናኛ ብዙኃን አመራርና አሠራር ጥሩ እውቀትና ልምድ አለው፡፡ አዳዲስ አሠራሮች እንዲጎለብቱ ሃሳብ በማፍለቅና እንዲሳካ ጥረት የማድረግ ብቃት አለው፡፡ አሁንም የጋዜጠኞች ሙያዊ ነጻነትና የሚዲያው ኤዲቶሪያል አቅም እንዲጎለብት እንዲሁም ተቋማዊ አቅሙ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ነፃነት ተስፋዬ የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ
##########
ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በይዘት ደረጃ ካየነው በባህል ኪነጥበበ እና በታሪክ ዙሪያ የኢትዮጵያን መልክ በፅሑፎቹ እና በንግግሮቹ ለማሳየት ከፍተኛ አበርክቶ ሰጥቷል። ፅሑፎቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናቶች የተሠሩባቸው አሁንም ይበልጥ ሊጠኑ የሚገባቸው ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው። ዲያቆን ዳንኤል በፅሑፎቹ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፍልስፍናዎችን፣ ጥበባትን፣ ታሪክን፣ ሀይማኖትን፣ ባህልን፣ ሥነ ጽሁፍን ፍንትው አድርጎ በማሳየት የራሱን አሻራ ያኖረ ነው። አበርክቶውም ትልቅ ነው።
እርሱ በፅሑፍ ብቻ ሳይሆን የአደባባይ ሰው በመሆኑ ትውልድ በማነፅ፣ ሥነ-ምግባርን በማስጠበቅ፣ ኢትዮጵያን በመመርመርና በመግለጥ፣ ማኅበራዊ ኂስ በጥበብ በመስጠት፣ ያነበባቸውን መፅሀፎች ወይም ያካበተውን ዕውቀት ጥበባዊ ስልት በተላበሰ ምጡቅ መንገድ በማቅረብ ይታወቃል።
የራሱን አሳታሚ ድርጅትና የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን በመመሥረትና በመምራት ለእውቀት እና እውቅና መስፋፋት ዋና ሚና ተጫውቷል።
በመንግሥት ኃላፊነቱም ቀድሞ ሲከውን የነበረውን ተግባር በላቀ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ እንደመሆኑ መጠንም ተቋማትን በመመሥረትና በማጠናከር ሚናው ትልቅ እንደሆነ እረዳለሁ።
ዲያቆን ዳንኤል ከ30 በላይ መፅሀፍትን እንደማሳተሙ ጊዜ አጠቃቀሙ እንዴት ይሆን? የሚል ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። እርሱ ግን ምናልባት በሰላሳ አመት የጽሁፍ ታሪኩ ከሰላሳ በላይ መጻሕፍትን እና እጅግ ብዙ መጣጥፎችን በሙበርከት ፕሮሊፊክ እና ዐቢይ ሥፍራ የሚደጠው ደራሲ እና የሃሳብ መሪ መሆኑን አስመስክሯል።ለሁሉም እንደሁኔታው ጊዜ በመመደብ ለሁላችን አርዓያ ነው።
ተመራማሪው ዳንኤል፣ ከመዛግብት ተነስቶ የሚፅፋቸውን ታሪኮች አይቻለሁ። በመካከለኛው ዘመን በአገራችን የተደረጉ ብዙ ክስተቶችን ለታሪክ ጥናት እጅግ ጠቃሚ ግብዓት እንዲሆን አድርጎ ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሰነደ ነው። ይህ ቀላል አይደለም።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሳስታውስ ብላቴን ጌታ ህሩይን ያስታውሰኛል። እርሳቸው በአንድ በኩል የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ይዘው በአንድ በኩል ይፅፋሉ። ምርምሮችንም ያደርጉ ነበር። ዲያቆን ዳንኤል ድንቅ የፈጠራ ክህሎቱን በመጠቀም የሚያቀርባቸው ሥራዎች ከንባብ እና ነገሮች በጥልቀት ተረድቶ የሚያቀርባቸው በመሆኑ ኢትዮጵያን የማሳየት አቅም አላቸው ብዬ አምናለሁ። አበርክቶው እና ጽኑ ሰብዕናው በአጭሩ ተተርኮ የሚያበቃ አይደለም።
ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ የባህልና ኪነ ጥበብ ሚኒስትር ዴኤታ
######
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የማውቀው ከ20 ዓመት በፊት ነው ። የዐውደ ምሕረቱ ፈርጥ ፣የቤተክርስቲያን አጽራር መከታ ከወንድሞች ጋር ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ሲያገለግልና ለብዙዎቻችን መንፈሳዊ መሠረት ጣይ በነበረ ጊዜ አውቀዋለሁ። በሚጽፋቸው መንፈሳዊና ትዝብት አዘል ማኅበረሰባዊ ጽሑፎች ያልተማረ ,ያልተገሰጸ በነፍሱ ሀሴት ያላደረገ በዙሪያው የነበረ ማንም አልነበረም። በተለይ በማኀበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በሚያዘጋጅበት ወቅት የከተባቸው ጽሑፎች ዘመን የተሻገሩ እስካሁን ለብዙዎች መንፈሳዊ ሙላት የኾኑ ጥዑም ዘለላዎች ናቸው።
የጻፋቸው መጽሐፍት እንዲሁም በብሎጉ በዕይታ ያስቀመጣቸው ትዝብቶቹ በቤተክህነቱም በቤተመንግሥቱም ቅቡልነታቸው የበዛ ነበር።
የቀረቡት ኹሉ ግለሰባዊ ማንነቱን ሊገነዘቡለት የማይከብዳቸው ዳንኤል በዐውደ ምሕረትም ሆነ በመድረክ ራሱን ሳያካብድ ለአገርና ለቤተክርስቲያን በጥልቀት በሚያውቀው የታሪክ አረዳዱ እያገለገለ የሚገኝ ምስጉን ወንድም ነው።
ኢዮብ ስዩም

Comments