1 month ago
33.26 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የምግብ ምርቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያከናወነ ነው።
መድረኩ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ መሪነት እየተካሄደ ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም በምግብ፣ በመድኃኒት፣ በሕክምና መሣሪያዎች፣ በመዋቢያ፣ በትምባሆና በአልኮል ዘርፎች የተከናወኑ የቁጥጥር ሥራዎች በዝርዝር እየተገመገሙ ይገኛል።
በግምገማው የቁጥጥር ሥራዎች አፈጻጸም፣ የላብራቶሪ ምርመራዎች፣ የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ፣ የድህረ-ገበያ ክትትልና ቁጥጥር፣ እንዲሁም በሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ባልተጠበቁ ምርቶች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ 33.26 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የምግብ ምርቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
በመድኃኒትና በሕክምና ግብዓቶችም ያልተመዘገቡና ሕገ-ወጥ ምርቶች ተይዘው እርምጃ መወሰዱ ተመልክቷል።
የግምገማ መድረኩ የተከናወኑ ሥራዎችን ከመገምገም ባለፈ፣ በቀጣይ የሚከናወኑ የቁጥጥር ሥራዎችን የበለጠ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ ትኩረት የሚደረግባቸውን አቅጣጫዎችም ለመለየት ያግዛል።
አዲስ አበባ፤ በ2018 በጀት ዓመት በምግብ፣ መድኃኒት፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ መዋቢያ፣ ትምባሆና አልኮል ዘርፎች የሸማቾችን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ ሰፊ የቁጥጥር፣ የምርመራና የሕግ አፈጻጸም ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ።
በምግብ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 4,356 የምግብ ምርቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ለ147 የምግብ አምራችና ለ1,547 አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት የቅድመ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ተካሂዶ የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በ554 አምራቾችና በ1,509 አስመጪና አከፋፋዮች ላይ ስጋት ተኮር ድህረ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ተከናውኗል።
በሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ባልተጠበቁ የምግብ ምርቶች ላይ በተደረጉ 8 ዙር ሰርቪላንስና 8 ኦፕሬሽኖች በአጠቃላይ 33.26 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከእነዚህም መካከል 10,600 ኪ.ግ ቅቤ፣ 6,925 ኪ.ግ ማር፣ 4,680 ኪ.ግ የታሸገ የአትክልት ቅቤ፣ 700 ኩንታል ጥራቱን ያልጠበቀ ጨው፣ የተቀላቀለና ሐሰተኛ በርበሬ እና ሌሎች ምርቶች ይገኙበታል።
በመድኃኒት ዘርፍ ደግሞ 1,939 መድኃኒቶች የገበያ ፈቃድ ያገኙ ሲሆን፣ 634 የመድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት የቅድመ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ተደርጎላቸዋል።
በተጨማሪም 12 የሀገር ውስጥ አምራቾች፣ 1,226 አስመጪና አከፋፋዮች እና 8 የሜዲካል ኦክስጅን አምራቾች ላይ ስጋት ተኮር ኦዲት ተካሂዷል።
በቁጥጥር ሥራው በአዲስ አበባ 2 ኮንቴነሮች የሚሆኑ 32 ዓይነት ያልተመዘገቡ የሕክምና መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች ተይዘዋል።
በተጨማሪም በከፋ ዞን ወደ 1 ሚሊዮን ብር፣ በጅማ 1,040,078 ብር እና በበደሌ 511,596 ብር የሚገመቱ ያልተመዘገቡና ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሕክምና መሣሪያዎች ዘርፍም 293 SRA እውቅና ያገኙ መሣሪያዎች፣ 583 አዳዲስ NIVD እና 360 አዳዲስ IVD መሣሪያዎች የገበያ ፈቃድ አግኝተዋል።
በገቢ የሕክምና መሣሪያዎች ላይ በተደረገው የጥራት ቁጥጥርም 126.47 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መሣሪያዎች የመልቀቂያ ፈቃድ አግኝተዋል።
በላቦራቶሪ ምርመራ በምግብ ዘርፍ 4,371 የምግብ ናሙናዎች በባዕድ ነገር መቀላቀል ጥናት ተመርምረዋል፤ በምግብ ደህንነትና ንጽህና ደግሞ 588 ናሙናዎች ተመርምረዋል።
በሕክምና መሣሪያዎች ምርመራ ደግሞ 273 የኮንዶም፣ 315 የሲሪንጅ፣ 169 የግላቭ እና 229 የIVD ናሙናዎች ተመርምረዋል።
በትምባሆ ቁጥጥር ረገድ 107,240 ተቋማት ላይ የቁጥጥር ሥራ ተከናውኗል፤ በአልኮል ማስታወቂያ፣ ማስተዋወቅ፣ ስፖንሰርሺፕና በተከለከሉ ቦታዎች ሽያጭን ለመቀነስ የታቀዱ የቁጥጥር ዕቅዶችም 100 በመቶ መፈጸማቸው ተገልጿል።
በሕግ አፈጻጸም በኩልም 56 የወንጀል ጉዳዮች ክትትል የተደረገባቸው ሲሆን፣ በ23 ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቧል።
በተጨማሪም 20 ኬዞች ላይ ለፖሊስና ለፍርድ ቤት ምላሽና ማስረጃ ተሰጥቷል። ከሕገ-ወጥ መድኃኒት ዝውውር ጋር በተያያዘም 33 መዝገቦች ተጣርተው ለፍትሕ አካላት ተልከዋል።
4,356 የምግብ ምርቶች ተመዝግበዋል
33.26 ሚሊዮን ብር የምግብ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል
1,939 መድኃኒቶች የገበያ ፈቃድ አግኝተዋል
126.47 ቢሊዮን ብር የሕክምና መሣሪያዎች የመልቀቂያ ፈቃድ አግኝተዋል
107,240 ተቋማት በትምባሆ ቁጥጥር ተመርምረዋል
56 የወንጀል ጉዳዮች ክትትል ተደርጎባቸዋል
4,371 የምግብ ናሙናዎች በባዕድ ነገር መቀላቀል ምርመራ ተደርጎባቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #የጋዜጣዊመግለጫ #የምግብደህንነት #መድኃኒት #የሕክምናመሣሪያ #ቁጥጥር #የምግብጥራት #healthandsafety #foodsafety #medicinesafety #ethiopia #addisababa #getutemesgen #ጌጡተመስገን

8 months ago
''NAN" የተሰኘው የህፃናት ወተት የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገለጸ
#ethiopia | "Nestle" የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት በህፃናት ምግብ ምርቶቹ ላይ ብክለት መገኘቱን ተከትሎ ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ጥንቃቄ የሚሻው የምርት ዝርዝር
ብክለት ተገኝቶባቸዋል ተብለው ለሽያጭ እንዳይቀርቡ የተከለከሉት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
* የምርት መለያ፦ NAN special pro HA 0-12
* የባች ቁጥር፦ 51660742F3
* የተመረተበት ቀን፦ 15 June 2025
* የሚያበቃበት ቀን፦ 15 December 2026
* ክብደት፦ 800 ግራም
የባለስልጣኑ የቁጥጥር ስራና የሰጠው ምላሽ
የባለስልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና የህግ ማስፈጸም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ምርቱ በይፋዊ የገበያ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ ባይገባም በተለያዩ መንገዶች ሊገባ ስለሚችል በሱፐር ማርኬቶችና በማከፋፈያዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል። እስካሁን ባለው መረጃ ምርቱ በገበያ ላይ ባይገኝም ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የድርጅቱ ኃላፊነት፦ የድርጅቱ ተወካዮች ምርቱን በራሳቸው ወጪ የመሰብሰብና የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው።
* የነጋዴው ድርሻ፦ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ምርት እጁ ላይ ካለ ከመሸጥና ከማከፋፈል እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል።
* የህብረተሰቡ ጥንቃቄ፦ ህብረተሰቡ የተጠቀሰውን የባች ቁጥርና የምርት መለያ በማየት ጥንቃቄ እንዲያደርግና ካገኘም ለባለስልጣኑ እንዲጠቁም ተጠይቋል።
ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ደረጃውን የጠበቀ ምርት ማቅረብ የአምራችና የአስመጭ ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nestle #babyfoodsafety #ethiopia #efda #healthalert #nan #የምግብደህንነት #ኢትዮጵያ

Comments