29 days ago
ኪነ-ጥበብ ለተተኪ ትውልድ!
#ethiopia | የአብክመ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽ/ቤት ለሁለት ወራት ያሰለጠናቸውን ተተኪ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አስመረቀ
የአብክመ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ-ታሪክ ጽ/ቤት በባህልና ኪነ-ጥበብ ዘርፎች ለሁለት ወራት ያካሄደውን የሙያ ስልጠና በስኬት ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን አስመርቋል።
በምረቃ መርሐ-ግብሩ ላይ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አዲስ በየነ፣ ም/ኃላፊ አቶ ገብረማርያም ይርጋ፣ የባህልና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ አሰልጣኞች፣ ተመራቂዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ገብረማርያም ይርጋ፣ የምረቃው ቀን የሁለት ወራት ስልጠና መጠናቀቂያ ብቻ ሳይሆን፣ የተሸረሸረውን እሴት ለማደስ፣ የተሰበረውን ለማከምና ትውፊትን ለማስቀጠል አዲስ ትውልድ የሚዘጋጅበት ወሳኝ ቀን መሆኑን ገልጸዋል።
አንድ ክልል የሚያደርገው ልማት በመንገድ፣ በሕንፃና በመሠረተ-ልማት ብቻ እንደማይለካ ያስረዱት አቶ ገብረማርያም፣ ሰውን በማንነቱ፣ በእሴቱ፣ በታሪኩና በባህሉ ላይ ማቆምም የልማት ዋነኛ መለኪያ መሆኑን ጠቁመዋል።
የባህል ሥራ የመዝናኛ ሥራ ብቻ ሳይሆን፣ የማንነት ግንባታ፣ የእሴት ጥበቃ፣ የትውልድ ትስስርና የክልል ልማት አካል መሆኑንም አስረድተዋል።
ተመራቂዎቹ በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በድምፅና ዜማ፣ በባህላዊ መሣሪያ፣ በትወናና በተውኔት አፃፃፍ የሙያ ስልጠና ማግኘታቸውን በመጥቀስ፣ ይህ ዕውቀት ለሙያ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ አደራ መሆኑን አቶ ገብረማርያም አስገንዝበዋል።
በመሆኑም ተመራቂዎቹ ባህልን እንዲጠብቁ፣ እሴትን እንዲያጠናክሩ፣ ታሪክን በጥናት እንዲያስተላልፉ፣ ትውፊትን እንዲያስቀጥሉና ጥበብን በፈጠራ እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አዲስ በየነ በበኩላቸው፣ የባህልና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሰው ልጅን ማንነትና የማኅበረሰብን እሴት በማጠናከር ያለውን ወሳኝ ሚና በመጥቀስ፣ በስልጠናው የተገኘውን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ለክልሉ የባህልና ኪነ-ጥበብ ልማት የሚያበረክት ሥራ እንዲሠሩ ተመራቂዎቹን አሳስበዋል።
ተቋሙም የባህል ቅርስን ከመጠበቅ ባሻገር፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በማብቃት፣ የፈጠራ አቅምን በማሳደግና ባህልን ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ የሚኖረውን ሚና እንደሚያጠናክር ኃላፊው ገልጸዋል።
“ባህልን መጠበቅ፣ ጥበብን ማሳደግ፣ ትውፊትን ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ!”
#ኪነጥበብ #ባህል #ተተኪትውልድ #ዝክረታሪክ #አብክመ #ጥበብ #ትውፊት #ethiopianculture

7 months ago
የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር በዓለም አቀፍ መድረክ! 

#ethiopia | በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የባህል እና የኪነጥበብ ሙያተኞች ህብረት ዋና መስሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያዊውን አቶ ገብረማርያም ይርጋን የምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾመ።
አቶ ገብረማርያም በአሁኑ ወቅት የአማራ ባህል፣ ኪነጥበብና ዝክረታሪክ ም/ኃላፊ ሲሆኑ፣ በባህል ዲፕሎማሲው ዘርፍ ባላቸው ንቁ ተሳትፎ ይታወቃሉ።
ይህ ሹመት የኢትዮጵያንና የአፍሪካን ጥበብ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ለማውጣት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
አቶ ገብረማርያም ስለ ሹመቱ ሲናገሩ፦ "ይህን ሹመት እንደ ክብር ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ስትራቴጂክ አደራ እቀበላለሁ" ብለዋል።
ለአቶ ገብረማርያም ይርጋ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን! 👏✨
#ኢትዮጵያ #ባህል #ኪነጥበብ #ደቡብኮሪያ #ሹመት #ጌቱተመስገን #ባህልዲፕሎማሲ #ethiopia #culture #art #globalleadership #southkorea #culturaldiplomacy

Comments