2 months ago
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavoted #democracy #fanatelevision

በሀረሪ ክልል ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች እየተለጠፉ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል በሚገኙ ሦስት የምርጫ ክልሎች በተቋቋሙ 294 የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች እየተለጠፉ ነው።
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጽ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም በክልሉ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤቶች ለሕዝብ እይታ ግልጽ በሆኑ ቦታዎች እየተለጠፉ ሲሆን÷ መራጩ ሕዝብም ውጤቶቹን እየተመለከተ ይገኛል።
በተሾመ ኃይሉ

Comments