2 months ago
ከካናዳ የመጡት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ ናቸው
#ethiopia | በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የስፖርት ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሸናፊ ግርማ በሚመራው የአሸናፊ ግርማ ስፖርት አካዳሚ ስር የተደራጁት እነዚህ ታዳጊዎች የታሪካዊውን እንጦጦ ፓርክ ጨምሮ በርካታ መስህቦችን ተዟዙረው ተመልከተዋል።
ይህ አጋጣሚ ህፃናቱ የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክና የተፈጥሮ ሀብት በግንባር አውቀው እንዲረዱ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተገልጿል።
የቡድኑ አባላትና አብረዋቸው የመጡ ቤተሰቦቻቸው በትውልድ ሀገራቸው በመገኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በተለይም በመዲናዋ እየተከናወነ ባለው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴና ፈጣን እድገት መደመማቸውን የተናገሩ ሲሆን፡ እንዲህ ያሉ ክስተቶች የሀገርን መልካም ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የስፖርት ቱሪዝምን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተጠቅሷል።
#አዲስአበባ #ትውልደኢትዮጵያዊ #ካናዳ #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ #ስፖርት #አሸናፊግርማ #እንጦጦፓርክ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 months ago
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ
የሳቪዮላው አሸናፊ ግርማ መጽሐፍ በድሬዳዋ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፈውና በልዩ የጨዋታ ስልቱ "ሳቪዮላ" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው የቀድሞው ድንቅ አማካይ አሸናፊ ግርማ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ፣ ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትውልድ ከተማው ድሬዳዋ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የአሸናፊ ግርማ እናት ወይዘሮ እህተ ወንድሙ ካሳዬ በምረቃው ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በነገራችን ላይ
የአሸናፊ ግርማ አዋርድ በድሬ ተከናውኗል። በዚህ መሠረት
ለጥላሁን መገኒቾ (50,000 ብር)፣
ለፍቃዱ ተካ (25,000 ብር)፣
ለአህመድ ጁንድ (25,000 ብር) እና
ለፍስሐ በጋሻው (25,000 ብር) በክብር ተሸላሚ ሆነዋል።
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ በ350 ገጾች ተቀንብቦ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች (በአንድ ጥራዝ) የታተመ ሲሆን፣ በካናዳም ለንባብ በቅቷል።
ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚውል አሸናፊ ግርማ በምረቃው ላይ አስታውቋል።
አሸናፊ ግርማ ሦስት ጊዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሲሆን፣ በ1993 ዓ.ም በአርጀንቲና በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ ላይ ሀገራችንን ወክሎ አስደናቂ ብቃት አሳይቷል። በኢትዮጵያ ቡና ማሊያም ሁለት ጊዜ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
መጽሐፉን በ500 ብር ከጃዕፋር መጽሐፍት ቤት ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ በቀጣይም ታሪኩ በድምፅ ተተርኮ በዩቲዩብ እንደሚጫን ተገልጿል።
#getu #ashenafigirma #saviola #ethiopianfootball #diredawa #booklaunch #ethiopiancoffeefc #genenemekuria #libro #ethiopianlegend #አሸናፊግርማ #ሳቪዮላ #የኢትዮጵያእግርኳስ #ድሬዳዋ #መጽሐፍምርቃት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

⚽️ "ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና"
የፈረሰኛውና የቡናው ኮከብ አሸናፊ ግርማ ታሪክ በድጋሚ ታተመ! 📚
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የአማካይ ስፍራ ዝነኛው ተጫዋች አሸናፊ ግርማ፣ የሕይወት ታሪኩን የያዘውና በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የተጻፈው መጽሐፍ ማሻሻያዎች ተደርገውበት ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ በቅቷል።
በ350 ገፆች ተቀንብቦ በአማርኛና በእንግሊዝኛ (በአንድ ጥራዝ) የታተመ ሲሆን፣ በካናዳም ለንባብ በቅቷል።
ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚውል አሸናፊ ገልጿል።
በቀጣይ ታሪኩ በድምፅ ተተርኮ በዩቲዩብ እንደሚጫን ተነግሯል።
📅 የምርቃት ጥሪ፦
ቀን፦ ቅዳሜ የካቲት 21/2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፦ ሆቴል ደ ሊኦፖል (Hotel De Leopol)
🏆 አሸናፊ ግርማ ማን ነው? (ለማስታወስ ያህል)
የሴካፋ ጀግና፦
ሦስት ጊዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው።
የዓለም መድረክ፦
በ1993 ዓ.ም በአርጀንቲና በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ (World Youth Championship) ሀገራችንን ወክሎ ተጫውቷል።
የቡናው ፈርጥ፦
በኢትዮጵያ ቡና ማሊያ ሁለት ጊዜ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
በምርቃቱ ዕለት ከወጣቶች አካዳሚና ከአዲስ አበባ ለተውጣጡ 105 ወጣቶች መጽሐፉ በነፃ የሚበረከትላቸው ሲሆን፣ ይህም ለታዳጊዎች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራል።
መጽሐፉን በ500 ብር ከጃዕፋር መፅሐፍት ቤት ማግኘት ይቻላል።
#አሸናፊግርማ #ከአሸዋሜዳእስከአርጀንቲና #ኢትዮጵያቡና #የኢትዮጵያእግርኳስ #መጽሐፍምርቃት #ethiopianfootball #ashanafigirma #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments