3 months ago
ኢትዮጵያ በ2045 የዓለማችን ግዙፍ 10 ኢኮኖሚዎች ተርታ ትሰለፋለች ፤ አለምን ያስደመመው ስር ነቀል ለውጥ
#ethiopia #ethiocoders #madeinethiopia #ethiopianeconomy2045 #artificialintelligence #ethiopiandevelopment #addisababa #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያታምርት #ኢትዮኮደርስ #አርቴፊሻልኢንተለጀንስ
3 months ago
ያለ ፈቃድ የኤአይ (AI) ስልጠና መስጠት በሕግ ያስቀጣል!
#ethiopia | በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ስልጠና መስጠት የሚችሉት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተቋማት ብቻ መሆናቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ከአዲስ ኤፍኤም 97.1 ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በዘርፉ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል የብቃት ማረጋገጫ ሊኖረው ይገባል።
እስካሁን ባለው ሂደት ኢንስቲትዩቱ ለማንኛውም የግል ተቋምም ሆነ ግለሰብ የማሰልጠን ፈቃድ እንዳልሰጠ የገለጹት ዳይሬክተሩ ይህንን መመሪያ ተላልፎ የሚገኝ አካል በሕግ እንደሚጠየቅ አስገንዝበዋል።
ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መሰጠት እንደሚጀምርም ተጠቁሟል።
በአዋጅ ቁጥር 510/2014 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በዘርፉ ማህበረሰቡን የማሰልጠን እና ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ኃላፊነት የኢንስቲትዩቱ መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ፈቃድ በሌላቸው አካላት በሚደረጉ አደናጋሪ ስልጠናዎች እንዳይታለል እና አላስፈላጊ ወጪዎች እንዳይዳረግ ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም በዘርፉ መሰማራት የሚፈልግ አካል ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመቀናጀት እና የሀገሪቱን የኤአይ ፖሊሲና ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተመላክቷል።
በኃይለሚካኤል አበበ
#አርቴፊሻልኢንተለጀንስ #ቴክኖሎጂ #ትምህርት #ስልጠና #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የቴክኖሎጂው ጦርነት ጋለ! ቻይና የአሜሪካን የAI ምስጢሮች ሰርቃለች ተባለ
#ethiopia | ዋይት ሀውስ (White House) በይፋ ባወጣው መግለጫ፣ ቻይና እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የአሜሪካን የAI ቴክኖሎጂ ምስጢሮችን በመስረቅ የራሷን AI ገንብታለች ሲል ከሰሰ። ይህ ድርጊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ጥሎታል።
ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ?
(The "Distillation" Method)
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሀሰት አካውንቶችን በመጠቀም ወደ አሜሪካ የAI ሲስተሞች ዘልቀው በመግባት መረጃዎችን ቀድተዋል።
የቴክኖሎጂ ስርቆት (Distillation)
ሌላው ሰው ለፍቶ የሰራውን የቤት ስራ ኮርጆ እንደራስ አድርጎ እንደማቅረብ ማለት ነው። ቻይና የአሜሪካን ምርጥ የAI ክፍሎች በመቅዳት ያለምንም ወጪ የራሷን ቴክኖሎጂ ገንብታለች ተብሏል።
የአሜሪካ መንግስት በዚህ ድርጊት እጅግ መቆጣቱን የገለጸ ሲሆን፣ ቻይና ግን ክሱን "መሰረተ ቢስ" ስትል አጣጥላለች።
የትራምፕና የፕሬዝዳንት ዢ መገናኘት
የሚቀጥለው ወር ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ፣ በዚህ አዲስ የስርቆት ክስ ምክንያት እጅግ አሳሳቢና "Awkward" እንደሚሆን ይጠበቃል።
ዛሬ ዓለም በጉልበት ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂም እየተፋለመች ነው። AI የወደፊቱ ዓለም ቁልፍ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ የስርቆት ክሶች የሀገራትን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላሉ።
ቴክኖሎጂው ለበጎ ነገር ከመዋል ይልቅ ለስለላና ለስርቆት መዋሉ ያሳስባል። ትራምፕ በሚቀጥለው ወር ለሚያደርጉት ጉብኝት ይህ ክስ ትልቅ ራስ ምታት እንደሚሆንባቸው ግልጽ ነው!
የቴክኖሎጂው ጦርነት ወዴት ያመራ ይሆን?
#getu #techwar #usvschina #aisecrets #artificialintelligence #trumpximeeting #cybersecurity #globalnews #ቴክኖሎጂ #አርቴፊሻልኢንተለጀንስ #አሜሪካናቻይና #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
Comments