6 months ago
የታሸገ ውሃ የዋጋ ጭማሪ በዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ
በቅርቡ በታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በዓለም አቀፍ አለመረጋጋት የተፈጠረ እንጂ በሀገር ውስጥ ካለው የምርት አቅርቦት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደበበ ወርቁ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
የታሸገ ውሃ አምራቾች የጥሬ ዕቃ ግብዓቶችን ከውጭ ሀገራት የሚያስገቡ በመሆኑ፣ አሁን ላይ ግብዓቶቹን በሚፈለገው መጠን ማስገባት አለመቻሉን ሥራ አስኪያጁ ገልጸው፤ በዚህም ምክንያት በምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስረድተዋል።
ቀደም ሲል በታሸገ ውሃ አምራቾች በኩል የሚነሱ የውጭ ምንዛሬ እና የግብዓት አቅርቦት ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተው፣ በአሁኑ ወቅት ከአንድ መቶ በላይ አምራቾች ወደ ዘርፉ መቀላቀላቸውን ሥራ አስኪያጁ አስታውሰዋል። ያሉት አምራቾችም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ በመሆኑ ከአቅርቦት ጋር የተያያዘው ችግር መፈታቱን አብራርተዋል።
በቅርቡ በሁሉም የታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ወቅታዊ መሆኑን የገለጹት አቶ ደበበ፣ የዓለም አቀፍ ገበያው ሲረጋጋ ችግሩ እንደሚቀረፍ አመልክተዋል።
በመጨረሻም በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ወደ ዘርፉ የሚገቡ አምራቾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በምርት ሂደት ላይ የሚታዩ የዋጋ፣ የጥራት እና መሰል ችግሮች እንዲፈቱ ተቋሙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
seledadotio

7 months ago
ባለ 20 ሊትሩ የታሸገ የ“ጃር” ውሃን ጥራት ለመለካት የሚያግዝ ጥናት ሊካሄድ ነው
በተለምዶ “ጃር” እየተባለ በሚጠራውና በ20 ሊትር መያዣ ታሽጎ ለገበያ በሚቀርበው የመጠጥ ውሃ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሱ የጥራት መጓደል ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያግዝ አገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው።
ባለሥልጣኑ ለአሐዱ እንደገለጸው፣ ጥናቱ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እና የሕብረተሰቡን ጤና መጠበቅን ዓላማ ያደረገ ነው።
“ከሕብረተሰብ ጤና እና ደህንነት የሚበልጥ ምንም ዓይነት ነገር የለም” ያሉት የባለሥልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈጸም ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ፣ ከተገልጋዮች በየጊዜው የሚደርሱ ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ተቋሙ በጃር ውሃ ጥራት ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ሥራ አስፈጻሚው በማብራሪያቸው የጥራት ችግሩ የዜጎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ከተገኘ ምርቱ ሙሉ በሙሉ ሊታገድ እንደሚችል ጠቁመዋል።በተጨማሪም “ባለ 20 ሊትሩ የታሸገ ውሃ መያዣ (ጃሩ) ተደጋግሞ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ፣ በጽዳት እና ሥርጭት ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄን ይፈልጋል።” ብለዋል።
ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት ከአመራረት እስከ ገበያ ያለውን ሂደት በመከታተል እና ናሙና በመውሰድ ምርመራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በማከፋፈያ ቦታዎች ላይ ጭምር ክትትል እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ የተፈጠረውን የጥራት ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት የሚካሄደው አገር አቀፍ ጥናት እንደተጠናቀቀም፣ የምርቱን ደህንነት የሚያረጋግጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል።
#አሐዱ

‘ፋይን’ (Fine) የታሸገ ውሃ ጥንቃቄ ይደረግበት ተባለ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በገበያ ላይ በስፋት የሚገኘው ‘ፋይን’ (Fine) የታሸገ ውሃ ምርት ላይ የጥራት ጉድለት በመገኘቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰበ።
በተለይም የመለያ ቁጥር (Batch number) 620 የሆነው ምርት ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
እገዳው ለምን ተላለፈ?
ባለስልጣኑ ከባለድረሻ አካላት በደረሰው ጥቆማ መሰረት በፌደራል ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አማካኝነት የላብራቶሪ ምርመራ እንዲደረግ አድርጓል።
በምርመራውም የሚከተሉት ግኝቶች ተመዝግበዋል፦
* ባዕድ ነገር፦ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር (Slime/Biofilm formation) ተገኝቶበታል
* የአመራረት ጉድለት፦ የማምረት ሂደቱ የመልካም አመራረት ሥርዓትን (GMP) ያልተከተለ መሆኑ ተረጋግጧል።
* የጤና ስጋት፦ ምርቱ በውስጡ በያዘው ባዕድ ነገር ምክንያት ለሰው ልጅ ጤና እጅግ አደገኛ መሆኑ ተገልጿል።
የተወሰኑ እርምጃዎች
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአምራች ድርጅቱ ላይ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፦
* የምርት ዕገዳ፦ ድርጅቱ የችግሩን መንስኤ ለይቶ አውቆ ማስተካከያ ማድረጉ እስካልተረጋገጠ ድረስ፣ ከየካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን ማምረትና ማሰራጨት እንዳይችል ታግዷል።
* ምርትን የመሰብሰብ ትዕዛዝ፦ በገበያ ላይ የዋለውና ችግር ያለበት Batch number 620 ምርት በአምስት ቀናት ውስጥ ከገበያ ተሰብስቦ እንዲያልቅ ተወስኗል።
ለህብረተሰቡ የቀረበ ጥሪ
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ማህበረሰቡ የተጠቀሰውን መለያ ቁጥር ያለው ውሃ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስቧል። በተጨማሪም ይህ ምርት በገበያ ላይ ሲሸጥ ካጋጠመዎት፦
* በአቅራቢያዎ ለሚገኝ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ቅርንጫፍ ቢሮ ጥቆማ ይስጡ።
* ወይም በነጻ የጥቆማ መስመር 8864 በመደወል ያሳውቁ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የጤና_ጥንቃቄ #ታሸገ_ውሃ #ፋይን_ውሃ #አዲስ_አበባ #የምግብና_መድኃኒት_ባለስልጣን #ethiopia #healthalert #finewater

⚠️ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ፦ "ፋይን" (Fine) የታሸገ ውሃ ከገበያ ታገደ!
የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን "ፋይን" (Fine) በተሰኘው የታሸገ ውሃ ላይ ባደረገው ምርመራ፣ የምርት ቁጥር 620 ጥራትና ደህንነቱን ያልጠበቀ መሆኑን አረጋግጧል። ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በተደረገው ፍተሻ፣ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር የተገኘ ሲሆን የማምረት ሂደቱም የጤና መስፈርቶችን ያልተከተለ መሆኑ ተረጋግጧል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን የምርት ቁጥር ያለውን ውሃ ለጤናው ሲባል እንዳይጠቀም ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ባለስልጣኑ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት፣ ድርጅቱ ችግሩን በቋሚነት ማስተካከሉ ተረጋግጦ በጽሁፍ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ከየካቲት 24 ጀምሮ ወደ ገበያ ምርት እንዳያሰራጭ ታግዷል። በተጨማሪም በገበያ ላይ የሚገኘው የምርት ቁጥር 620 ውሃ በ5 ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ ለባለስልጣኑ ሪፖርት እንዲደረግ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ይህም እርምጃ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና የተበከለው ምርት ስርጭትን ለመግታት ያለመ ነው።
የባለስልጣኑ ዳይሬክተር እስጢፋኖስ ጌታቸው እንደገለጹት፣ ህብረተሰቡ ይህንን የታገደ ምርት በገበያ ላይ ሲያገኝ በነፃ ስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል። ጤናዎን ለመጠበቅ ሲሉ የታሸጉ ውሃዎችን ሲገዙ የምርት ቁጥሩን በጥንቃቄ እንዲያዩና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከቱ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የበኩልዎን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

9 months ago
ለትግራይ ክልል ከተመደበው በጀት ውስጥ እየተላከ ያለው አንድ ሶስተኛው ብቻ ነው ተባለ‼️
በክልሉ ያለውን የበጀት እጥረት ለመቅረፍ በሲሚንቶ፣ በመጠጦችና በታሸጉ ውሃዎች ላይ አዲስ የዋጋ ጭማሪ ተጥሏል
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እያጋጠመው ያለውን የበጀት እጥረት ለመቅረፍ እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ሲል በተለያዩ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ሀብት ለማሰባሰብ መወሰኑን አስታወቀ።
የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር አብርሀም ተከስተ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ ከፌዴራል መንግስት የሚላከው በጀት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ገልጸዋል።
እንደ ሰብሳቢው ገለፃ፣ ከጥቅምት ወር ወዲህ ለክልሉ ከተመደበው በጀት ውስጥ እየተላከ ያለው አንድ ሶስተኛው ብቻ በመሆኑ፣ አስተዳደሩ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመርዳትና የመንግስት ስራዎችን ለማስኬድ በገንዘብ እጥረት ተፈትኗል።
ይህንን ችግር ለመፍታት የወጣው አዲስ ደንብ በንግድ ምርቶች ላይ የሚከተሉትን የዋጋ ጭማሪዎች ደንግጓል፦
* በመጠጦች ላይ፦ በአንድ ቢራ ላይ 3 ብር፣ በአንድ ጠርሙስ አረቄ ላይ 10 ብር፣ በወይን ላይ 20 ብር እንዲሁም በአንድ ጠርሙስ ውስኪ ላይ 200 ብር ጭማሪ ተደርጓል።
* በውሃ እና ለስላሳ፦ በአንድ ደርዘን የታሸገ ውሃ ላይ 12 ብር፣ በለስላሳና አምቦ ውሃ ላይ ደግሞ 1 ብር ተጨምሯል።
* በግንባታ ዕቃዎች፦ በአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ላይ 100 ብር ጭማሪ ተደርጓል።
ይህ የሀብት ማሰባሰብ ሂደት በ13 ባንኮች በተከፈተ ሂሳብ እና በሰባት ንዑስ ኮሚቴዎች አማካኝነት የሚመራ ሲሆን፣ አሰባሰቡም ኮሚቴው በሚያሳትመው ልዩ ደረሰኝ ብቻ እንደሚከናወን ተገልጿል።
የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ምህረት በየነ እንደተናገሩት፣ ከዚህ የሚገኘው ገቢ ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ፣ ለፍትህና ፀጥታ አካላት ስራ ማስኬጃ እንዲሁም ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚውል ይሆናል ተብሏል።

ዓለም ላይ ከሚሸጡ የታሸጉ ውሃዎች ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ከቧንቧ የተቀዳ ውሃ መሆናቸውን ያውቃሉ?
ብዙዎቻችን የታሸጉ ውሃዎች የሚመጡት ከንፁህ የተፈጥሮ ምንጮች ወይም ከተራራዎች እንደሆነ ብናስብም፣ እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። የታሸጉ ውሃ አምራቾች ከተራ የቧንቧ ውሃ ላይ ማጣሪያ በማድረግና አንዳንድ ማዕድናትን በመጨመር መልሰው ያሽጉታል።
በአሜሪካ ውስጥ ደግሞ ወደ 64% የሚጠጋ የታሸገ ውሃ የቧንቧ ውሃ ብቻ መሆኑን አንድ ጥናት አመልክቷል።

"የታሸገ የፕላስቲክ ውሃ በየቀኑ የሚጠጡ ሰዎች ተጨማሪ 90,000 የማይክሮፕላስቲክ ቅንጣቶችን ወደ ሰውነታቸው ያስገባሉ"- ጥናት
በየቀኑ የታሸገ ውሃ የሚጠጡ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በተጨማሪ 90,000 የማይክሮፕላስቲክ ቅንጣቶችን ወደ ሰውነታቸው እንደሚያስገቡ በካናዳው ኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ አዲስ ጥናት አመላከተ።
በአማካይ ሰዎች በአመት ከ39,000-52,000 መጠናቸው ከ5 ሚሊሜትር በታች የሆኑ እነዚህን የፕላስቲክ ቅንጣቶችን ወደ ሰውነታቸው ያስገባሉ ተብሏል።
የፕላስቲክ ምርቶቹ ከምርት ጀምሮ በሚጓጓዙበት ጊዜ እና በሌሎችም ጊዜያት እነዚህን የፕላስቲክ ቅንጣቶች በፀሐይ እና የአየር መፈራረቅ ሲያመነጩ ወደ ሰውነታችን ገብተው የመተንፈሻ ችግርና የሆርሞን መዛባትንም ያስከትላሉ።
የተለመደውን የቧንቧ ውሃ የሚጠጡ ሰዎች በአመት 4000 የማይክሮፕላስቲክ ቅንጣቶችን ወደ ሰውነታቸው ሲያስገቡ በየቀኑ የታሸገ ውሃ የሚጠቀሙ ሰዎች ከእነዚህ ሰዎች በተጨማሪ 90,000 ቅንጣቶችን ያስገባሉ ተብሏል።
ተመራማሪዎች የፕላስቲክ እሽግ ውሃን ለአስቸኳይ ጊዜ መጠቀም ተገቢ ቢሆንም በየቀኑ ልንጠቀመው የተገባ ነገር ግን አይደለም ብለዋል።

11 months ago
የውሃ እጥረትን ተከትሎ ኢራን ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ድርቅ ገጠማት
#ethopia | ኢራን በተለይም ዋና ከተማዋ ቴህራን በዚህ መኸር ወቅት ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ገጥሟታል፣ የዝናብ መጠን እጅግ ዝቅተኛ ሲሆን የውሃ ማጠራቀሚያዎችም ባዶ ሆነዋል። የመንግስት ባለሥልጣናቱ ቀውሱ እየሰፋ በመሄዱ ዜጎች ውሃን እንዲቆጥቡ ተማጽነዋል።
ፕሬዝደንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በቅርቡ በቂ ዝናብ ካልጣለ የቴህራን የውሃ አቅርቦት በፈረቃ ሊከፋፈል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ነገር ግን አደጋን ለመከላከል በፈረቃ ለማዳረስ እንኳን በቂ ላይሆን ይችላል ብለዋል።
ፔዝሽኪያን "የራሽን አሰጣጥ ካልሰራ ቴህራን ከተማን ለቀን መውጣት ሊኖርብን ይችላል" ሲሉ ተደምጠዋል። የፕሬዝዳንቱ አስተያየት ግን በኢራን ጋዜጦች እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ትችት ፈጥረዋል ።
የቀድሞው የቴህራን ከንቲባ ጎላምሆሴን ካርባሺ ሀሳቡን “ቀልድ” ሲሉ “ከቴህራንን ሙውጣት ምንም ትርጉም የለውም” ሲሉ ተናግረዋል።የኢራን የሚቲዎሮሎጂ ባለስልጣናት በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ምንም ዝናብ እንደማይጠበቅ አስታውቋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የውሃ ችግሩ በዋና ከተማው የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። በቴህራን የምትኖር አንዲት ሴት ለመጸዳጃ ቤት እና ለሌሎች አስፈላጊ ነገሮች የሚያገለግሉ የውሃ ታንከሮችን ለመግዛት አቅጃለሁ ብላለች። ኢራናዊው ራፐር ቫፋ አህመድፑር ምንም አይነት ውሃ የሌለበት የኩሽና ቧንቧ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርቷል። ውሃ የለም ወደ መጸዳጃ ቤት ለመሄድ የታሸገ ውሃ ገዝቻለሁ ሲል ተደምጧል።
ከቴህራን ዋና የውሃ ምንጮች አንዱ የሆነው የላቲን ግድብ ስራ አስኪያጅ ግድቡ አሁን ካለው አቅም ከ10 በመቶ በታች ይዟል። በአቅራቢያው ያለው የካራጅ ግድብ ለቴህራን እና አልቦርዝ ግዛቶች ውሃ የሚያቀርበው ነው።
ሁለቱም ግዛቶች በተመሳሳይ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኘሉ። "ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ግድብ ባዶ ሆኖ አይቼው አላውቅም" ሲሉ አንድ አዛውንት የአካባቢው ነዋሪ ለኢራን መንግስታዊ ቲቪ ተናግረዋል።
የካራጅ ግድብ ስራ አስኪያጅ መሀመድ አሊ ሙአለም እንዳሉት የዝናብ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። "የዝናብ መጠን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ92 በመቶ ቀንሷል" ብለዋል።
"በእኛ ማጠራቀሚያ ውስጥ ያለን ስምንት በመቶው ውሃ ብቻ ነው እና አብዛኛው ጥቅም ላይ ሊውል የማይችል እና 'የሞተ ውሃ' ተብሎ የሚታሰብ ነው።" ሲሉ አስከፊነቱን ገልፀዋል ያለው ዳጉ ጆርናል ነው።

Sponsored by
Surafel
11 months ago
የኢራን ፕሬዝዳንት አገሪቱ ያጋጠማትን ድርቅ ተከትሎ "ቴህራንን ለቀን መውጣት" ሳይኖርብን አይቀርም አሉ
ኢራን፣ በተለይም ዋና ከተማዋ ቴህራን ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ማጋጠሙን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ "ቴህራንን ለቀን መውጣት" ሳይኖርብን አይቀርም አሉ።
በኢራን የጣለው ዝናብ መጠንም እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ የውሃ ማጠራቀሚያዎችም ባዶ ናቸው ተብሏል። ባለሥልጣናቱ ቀውሱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ዜጎች ውሃ እንዲቆጥቡ ተማጽነዋል።
ፕሬዝደንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በቅርቡ በቂ ዝናብ ካልጣለ በቴህራን ውሃ ማከፋፈል እንደሚጀመር ተናግረው ነበር።
ነገር ግን የውሃ እጥረቱን ለመቅረፍ በተራ ማከፋፈል ብቻ በቂ ላይሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ፔዝሽኪያን "ማከፋፈሉ ካልሰራ ቴህራንን መልቀቅ ሊኖርብን ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል።
የፕሬዚዳንቱ አስተያየቶች በኢራን ጋዜጦች እና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ትችትን አስተናግደዋል። የቀድሞው የቴህራን ከንቲባ ጎላምሆሴን ካርባሺ ሀሳቡን "ቀልድ" ሲሉ አጣጥለው "ቴህራንን ለቅቆ መሄድ ምንም ትርጉም የለውም" ብለዋል።
የኢራን የሚቲዎሮሎጂ ባለስልጣናት በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ምንም ዝናብ እንደማይጠበቅ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የውሃ ችግር በዋና ከተማው የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው።
በቴህራን የምትኖር አንዲት ሴት ለቢቢሲ ፐርዢያ "ለመጸዳጃ ቤት እና ለሌሎች አስፈላጊ ነገሮች የሚያገለግል የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ለመግዛት አቅጃለሁ።
ኢራናዊው ራፐር ቫፋ አህመድፑር ደግሞ በማብሰያ ክፍል ውስጥ የሚገኝ ቧንቧን በማሳየት ምንም ዓይነት ውሃ እንደሌለ የሚገልጽ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርቷል።
"አራት ወይም አምስት ሰዓት አልፏል" በማለት " ወደ መጸዳጃ ቤት ለመሄድ የታሸገ ውሃ ገዝቻለሁ።"
ከቴህራን ዋና የውሃ ምንጮች አንዱ የሆነው የላቲያን ግድብ ሥራ አስኪያጅ ግድቡ ካለው ውሃ የመያዝ አቅም ከ10 በመቶ በታች መያዙን ተናግረዋል።
በአቅራቢያው ያለው የካራጅ ግድብ ለቴህራን እና አልቦርዝ ከተሞች ውሃ የሚያቀርብ ሲሆን በተመሳሳይ አነስተኛ ውሃ ብቻ መያዙ ተነግሯል።
"ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ግድብ ባዶ ሆኖ አይቼው አላውቅም" ሲሉ አንድ አዛውንት የአካባቢው ነዋሪ ለኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የካራጅ ግድብ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መሀመድ አሊ ሞአለም እንዳሉት የዝናብ መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።
"የዝናብ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ92 በመቶ ቀንሷል" ብለዋል።
"በግድቡ ውስጥ ያለን ስምንት በመቶው ውሃ ብቻ ነው። እና አብዛኛው ጥቅም ላይ ሊውል የማይችል እና 'የሞተ ውሃ' ተብሎ የሚታሰብ ነው።"
መንግሥት አሁን ተስፋውን በበልግ መገባደጃ ላይ ዝናብ ሊጥል ይችላል የሚል ነው።
ነገር ግን የሚትዎሮሎጂ ትንበያዎች ያንን አያሳዩም።
የኢራን የኢነርጂ ሚኒስትር አባስ አሊ አባዲ ሁኔታው በቅርቡ የውሃ አቅርቦትን እንዲቋረጥ ሊያስገድድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
"አንዳንድ ምሽቶች የውሃውን ፍሰት ወደ ዜሮ ልንቀንስ እንችላለን" ብለዋል።
ባለሥልጣናቱ ከመጠን በላይ ውሃን የሚጠቀሙ ቤተሰቦችን እና ንግድ ቤቶችን ለመቅጣት ማቀዱን አስታውቀዋል።
የኢራን የኢነርጂ ሚኒስትር አሊ አባዲ የቴህራን የውሃ ችግር በዝናብ እጥረት ብቻ የተከሰተ አይደለም ይላሉ። በመዲናዋ ለዘመናት በቆየው የውሃ መሠረተ ልማት ምክንያት የተከሰተውን የውሃ ፍሰትን እና በቅርቡ ከእስራኤል ጋር ለ12 ቀናት የዘለቀው ጦርነትን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
በዚያ ግጭት ወቅት፣ እስራኤል ሰኔ 15 ቀን በሰሜናዊ ቴህራን የታጅሪሽ ሰፈር ላይ ዒላማ አድርጋለች። ከዚያ በኋላ በአካባቢው ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ መከሰታቸውን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ወጥተዋል።
በጥቃቱ ማግስት የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራንን ጦር "ማዘዣ ማዕከላት" ላይ ማነጣጠሩን አስታውቋል።
ነገር ግን ይህ የውሃ እጥረት ቀውስ ከዋና ከተማው የሰፋ ነው።
የኢራን ብሔራዊ የአየር ንብረት እና ድርቅ ቀውስ አስተዳደር ማዕከል ኃላፊ አህመድ ቫዚፈህ ከቴህራን በተጨማሪ በሌሎች በርካታ ግዛቶች ውስጥ ያሉ ግድቦች "አስጊ ሁኔታ" ውስጥ እንደሚገኙ አስጠንቅቀዋል።
በግድቦቹ ውስጥ ያለው የውሃ መጠን በመቶኛ ሲሰላ በነጠላ አሃዝ የሚቀመጥ ነው።
በኢራን ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ማሽሃድ ባለስልጣናትም እጥረት መከሰቱን እየገለፁ ነው።
BBC

1 year ago
ኤርትራ‼️
The Economist ባወጣዉ መረጃ መሰረት ኤርትራ በአፍሪካ የበርካታ ኢንዱስትሪ ባለቤት ነበረች፣አሁን ላይ ግን የታሸገ ውሃና ሳሙና እንኳን ከውጭ ለማስገባት የተገደደች ሀገር መሆኗን ገልጿል።
ኤርትራ የውስጥ ችግሯ እንዳለ ሆኖ ከኢትዮጵያ ጋር በአሰብ ወደብ ምክንያት ውጥረት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ የኤርትራ ሉዓላዊነት አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ ጠቅሷል።(አዩ)

መፀዳጃ ቤት በሌላቸውና ንፁህ የመጠጥ ውሃ በማያቀርቡ ምግብ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | ደረጃቸውን ያልጠበቁ በተለይ መፀዳጃ ቤት በሌላቸው እና ከታሸገ ውሃ ውጪ ያለ ክፍያ ከምግብ ጋር ንፁህ የመጠጥ ውሃ በማያቀርቡ ምግብ ቤቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።
በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት እስጢፋኖስ ጌታቸው ለአሐዱ እንደገለጹት፤ ማንኛውም ተቋምም ሆነ ግለሰብ ፍቃድ ተሰጥቶት ሥራ ከጀመረ በኋላ በምግብ ቤቶች ውስጥ ማሟላት ያለበትን ደረጃ እንዲያሟላ ይገደዳል።
አክለውም፤ ደረጃውን በማያሟሉ ምግብ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ወደ ተቋሙ የሚመጡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎች መሠረት በማድረግ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በምግብ ቤቶች የፅዳትና ንፅህና ጉድለት፣ መፀዳጃ ቤት አለመኖር እና የቧንቧ ውሀ አለማቅረብ ለተቋሙ ቅሬታ ከሚቀርቡ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸው፤ እነዚህን መሠረታዊ መስፈርቶች በማያሟሉ ምግብ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።
"እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንደተቋሙ ይለያያል" ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "ከቁርስ ቤቶች እስከ ባር ቤቶች ድረስ ከሚወሰዱ እርምጃዎች በተጨማሪ፣ ጤናማ ምርት በማያቀርቡ የምርት ማከፋፈያ ቤቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
አሐዱ እንደገለጸው መስሪያ ቤቱ በ11 ቅርንጫፍ እና 36 ክላስተር እየሰራ ሲሆን፤ ሕብረተሰቡ ደረጃቸውን ያላሟሉ ምግብ ቤቶች 8864 ላይ ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ ማድረግ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ጉዞ ወደ እንሳሮ
V I P ቻሌጅ ትሪፕ
📆የጉዞ ቀን: ቅዳሜ እና እሁድ ነሀሴ 24 እና 25
⌚️ የቆይታ ጊዜ: _ አንድ ቀን አዳር
🛣 የቦታ ርቀት፡ 130 ኪ.ሜ
💵 ጥቅል ዋጋ በሰው፦ 8600 ብር
🦶መነሻ ቦታ፡ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን
⏰መገኛ ሰዓት 12 : 00 ሰዓት መነሻ ሰዓት 12:10
የጉዞ ወጪ የሚያካትተው
🚌ትራንስፖርት ቱሪስት ስታንዳርድ
🍕🥘🍱ቁርስ ፣ ምሳ ፣ እራት : ቁርስ :ምሳ :💧የታሸገ ውሃ ፣ ሻይ ቡና
🧾 የመግቢያ
🚶የአስጎብኚ
👮♂👨✈️የፓርክ ጠባቂ
📸የፎቶግራፍ
የሚጎበኙ ስፍራዎች
👉 2 የተለያዩ ረጃጅም ዋሻዎች
👉 እንሳሮ ፊልም የተሰራበት የተለያዩ መልክአ ምድሮች
👉 ውብ የቋጥኝ ስፍራዎች እና ረጃጅም ፏፏቴዎች
👉 ግዙፉን የለሚ ናሽናል ሲቢቶን መጎብኘት
አሁኑኑ ይመዝገቡ
BOOK NOW
📞0989798919 or fetan9
~Account for deposit
1000294086815 - የኔነህ እንግዳወርቅ - ንግድ ባንክ
33325886 - የኔነህ እንግዳወርቅ - አብሲኒያ
የቴሌግራም ጉሩፓቻችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/fetanbroker
👉 ያሉን ቦታዎች ጥቂት ብቻ ስለሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ
~ማሳሰቢያ
👉ለመመዝገብ ከላይ በተገለፁት የባንክ ቁጥሮች ገቢ በማድረግ በቴሌግራም ደረሰኙን መላክ ይኖርባችሗል

🍕🥘🍱ቁርስ ፣ ምሳ ፣ እራት : ማረፊያ(መኝታ) ቁርስ :ምሳ :💧የታሸገ ውሃ ፣ ሻይ ቡና
🧾 የመግቢያ
🚶የአስጎብኚ
👮♂👨✈️የፓርክ ጠባቂ
📸የፎቶግራፍ
👉 አልኮል መጠጦችን እና ከላይ ከተፃፉት ውጭ ፓኬጁ አያካትትም

አዘጋጅ
የኔነህ ፊልም ፕሮዳክሽን

በሰውነታችን ላይ ስለ ማይክሮፕላስቲክስ አሉታዊ ተፅእኖዎች እየጨመረ የመጣ ስጋት አለ።
ከሁለት ሳምንት በፊት እንዳመለከትኩት፣ ሁሉም ሰው በአማካይ 7 ግራም የሚጠጋ ማይክሮፕላስቲክ በአንጎሉ ውስጥ አለው፤ ይህ ደግሞ የአንድ የፕላስቲክ ማንኪያ መጠን ያህላል። ማይክሮፕላስቲክስ በሰውነት ውስጥ ባሉ የተለያዩ አካላት ውስጥም ይገኛል። ምርምር ገና እየተካሄደ ቢሆንም፣ ማይክሮፕላስቲክስ ለስኳር በሽታ ዓይነት 2፣ ለከፍተኛ የደም ግፊት፣ ለልብ ድካም፣ ለስትሮክ፣ ለታይሮይድ ሕመሞች እና ለአልዛይመር በሽታ መጨመር መንስኤ ተብሎ ይታሰባል። ማይክሮፕላስቲክስ በፍራፍሬዎችና በአትክልቶች ውስጥ፣ በአየር ውስጥ፣ በታሸገ ውሃ ውስጥ፣ እና በፕላስቲክ መያዣዎች፣ በፕላስቲክ ከረጢቶች፣ በፕላስቲክ መጠቅለያዎች እና በመስታወት ጠርሙሶች/ማሰሮዎች ውስጥ እንኳ በብረታ ብረት ክዳን ሊገኙ ይችላሉ። ከፕላስቲክ የተሠሩ ነገሮችን ከመጠቀም ይልቅ ሴራሚክስ፣ መስታወት እና አይዝጌ ብረት መጠቀም ጊዜው አሁን ነው።
በሀኪም ፊሊፕ ኤስ.ቹዋ የተፃፈ

ስለ ጂያርዲያ (Giardiasis) በሽታ ማወቅ ያሉብን ቁልፍ ነጥቦች 🦠
#ethiopia | ስለ ጂያርዲያ በሽታ ምን ያህል ያውቃሉ?
ሰላም ጤና ይስጥልን! ዛሬ በብዙዎቻችን ዘንድ በውኃ አማካኝነት (ውኃ ወለድ) ስለሚተላለፈው እና የአንጀት ኢንፌክሽን ስለሚያስከትለው ጂያርዲያ በሽታ ጠቃሚ መረጃ ይዘንላችሁ ቀርበናል።
ጂያርዲያ (Giardia) በአይን በማይታይ ጥገኛ ተህዋሲ ወይም ፓራሳይት (Parasite) የሚመጣ በሽታ ሲሆን፤ በዋናነት በተበከለ ውኃ አማካኝነት ይተላለፋል።
እስኪ የበሽታውን መንስኤ፣ ምልክቶች፣ ምርመራ፣ ህክምና እና የመከላከያ መንገዶችን በዝርዝር እንመልከት።
✅ መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው? 🧐
――――――――――――――――
የጂያርዲያ በሽታ የሚከሰተው የጀርሙን እንቁላል/እጭ (cyst) ስንውጥ ወይም ወደ ውስጣችን ስናስገባ ነው።
ይህ እጭ "ሲስት" (cyst) ተብሎ የሚጠራ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን፤ ከሰውነት ውጪ በአፈርና ውሃ ውስጥ ለሳምንታት እና ለወራት በህይወት እንዲቆይ ያስችለዋል።
✅ የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች
――――――――――――――――
💧 የተበከለ ውኃ መጠጣት:-
ይህ ዋነኛው የመተላለፊያ መንገድ ነው። ጀርሙ (ፓራሳይቱ) በወንዞች፣ በሀይቆች፣ በምንጮች፣ በህዝብ የውሃ አቅርቦቶች፣ በጉድጓድ ውሃ፣ በመዋኛ ገንዳዎች እና በወተር ፓርኮች ውስጥ ሊገኝ ይችላል።
ይህም በዋናነት ከግብርና ፍሳሾች፣ ከፋብሪካዎች ውጋጅ ቆሻሻ እና ከእንስሳት እዳሪ ጋር በተያያዘ ይከሰታል።
🍲 የተበከለ ምግብ መመገብ:-
➔ በበሽታው የተያዘ ሰው እጁን በደንብ ሳይታጠብ ምግብ ከነካካ።
➔ ጥሬ አታክልቶችን በተበከለ ውሃ ካጠብን ወይም ለመስኖ ከተጠቀምን።
🤝 ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ:-
✦ በተለይ ህጻናት በሚውሉባቸው ቦታዎች (እንደ ዴይኬር) ዳይፐር በሚቀየርበት ጊዜ ከሰገራ ጋር ንክኪ ሲኖር በቀላሉ ይተላለፋል።
✦ በግብረ-ስጋ ግንኙነት ወቅት (በተለይ በፊንጢጣ ወሲብ) ሊተላለፍ ይችላል።
🐾 ከእንስሳት ጋር ንክኪ:-
ምንም እንኳን ከቤት እንስሳት ወደ ሰው የመተላለፍ እድሉ አነስተኛ ቢሆንም፤ በበሽታው ከተያዙ እንስሳት ሰገራ ጋር ንክኪ ሲኖር ሊተላለፍ ይችላል።
✅ የበሽታው ምልክቶች 🤒
――――――――――――
ምልክቶቹ ጀርሙ ወደ ሰውነት ከገባ ከ 1 እስከ 2 ሳምንታት ውስጥ መታየት ይጀምራሉ፤ አብዛኛውን ጊዜ ከ 2 እስከ 6 ሳምንታት ሊቆዩ ይችላሉ።
አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ፤ ነገር ግን በሽታውን ለሌሎች ማስተላለፍ ይችላሉ።
👉👉 ዋና ዋና የአጭር ጊዜ ምልክቶች:-
➔ ተቅማጥ (ብዙውን ጊዜ ውኃ የመሰለ፣ መጥፎ ሽታ ያለው፣ ቅባታማ እና በውሃ ላይ የሚንሳፈፍ)
➔ የሆድ ቁርጠት ወይም ህመም
➔ የሆድ መነፋት
➔ የሆድ ጋዝ (አየር ማስወጣት)
➔ ማቅለሽለሽ ወይም የሆድ መረበሽ
➔ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
➔ ድካም
➔ የሰውነት ፈሳሽ እጥረት (Dehydration)
👉👉 የረጅም ጊዜ ምልክቶች እና ጉዳቶች:-
✦ ትኩሳት
✦ የቆዳ ማሳከክ፣ ሽፍታ፣ የአይን ወይም የመገጣጠሚያ እብጠት (ብዙም አይታይም)
✦ የሰውነት ክብደት መቀነስ
✦ የምግብ እጥረት (በተለይ በህጻናት ላይ የእድገት መቀጨጭን ያስከትላል)
✦ የላክቶስ አለመስማማት (የወተት ተዋፅኦዎችን መፍጨት መቸገር)
✦ የአንጀት መቆጣት ሲንድሮም (IBS)
✅ የበሽታው ምርመራ 🔬
―――――――――――
የጂያርዲያ በሽታን ለማወቅ ሐኪምዎ የሰገራ ናሙና ምርመራ እንዲያደርጉ ይጠይቅዎታል።
ምክንያቱም ጀርሙ በሁሉም የሰገራ ናሙና ውስጥ ላይገኝ ስለሚችል፤ በተለያዩ ቀናት የተወሰዱ ከአንድ በላይ የሰገራ ናሙናዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ።
✅ የህክምና አማራጮች 💊
―――――――――――――
ብዙ ሰዎች ህክምና ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ጊዜ ይድናሉ። ነገር ግን ምልክቶቹ ከባድ ከሆኑ ወይም ለረጅም ጊዜ ከቆዩ ሀኪምዎ መድሃኒት ሊያዝልዎ ይችላል።
👉👉 የተለመዱ መድሃኒቶች:-
➔ ሜትሮኒዳዞል (Metronidazole):- በኢትዮጵያ በስፋት የሚታወቀው ፍላጂል (Flagyl) በሚለው ስሙ ነው።
➔ ቲኒዳዞል (Tinidazole)
➔ ኒታዞክሳናይድ (Nitazoxanide)
ማሳሰቢያ:- በተለይ ተቅማጥ ካለብዎ በቂ ፈሳሽ በመውሰድ ሰውነትዎ እንዳይደርቅ ማድረግ (የሰውነት ድርቀትን መከላከል) በጣም አስፈላጊ ነው።
✅ የመከላከያ መንገዶች 🧼
――――――――――――
ጂያርዲያን መከላከል በዋናነት ጥሩ የግል ንጽህናን በመጠበቅ እና የተበከሉ ምግቦችን እና ውሃን በማስወገድ ላይ ያተኩራል።
✴️ እጅን በደንብ መታጠብ:-
በሚከተሉት ጊዜያት እጅዎን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይታጠቡ:-
✦ ምግብ ከማዘጋጀትዎ ወይም ከመመገብዎ በፊት
✦ ከመጸዳጃ ቤት ከተመለሱ በኋላ
✦ የህጻናትን ዳይፐር ከቀየሩ በኋላ
✦ እንስሳትን ወይም አካባቢያቸውን ከነኩ በኋላ
✴️ የውሃ ጥንቃቄ:-
➔ ከወንዞች፣ ከሀይቆች፣ ከምንጮች እና ጥልቀት ከሌላቸው ጉድጓዶች የሚገኝ ያልተጣራ ውሃ አይጠጡ።
➔ የውሃ ጥራት ወደማይረጋግጡባቸው ቦታዎች ሲጓዙ የታሸገ ውሃ ይጠቀሙ ወይም ውሃውን በማፍላት (ቢያንስ ለ1 ደቂቃ)፣ በማጣራት (cyst/oocyst ማጣራት የሚችል ማጣሪያ በመጠቀም) ያጽዱ።
➔ በመዋኛ ገንዳዎች እና በሀይቆች ውስጥ ሲዋኙ ውሃ አይውጡ።
✴️ የምግብ ደህንነት:-
✦ ምግቦችን በደንብ አብስለው ይመገቡ።
✦ ጥሬ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በንጹህ ውሃ በደንብ አጥበው ይጠቀሙ።
✴️ የግል ንጽህና:-
➔ እርስዎ ወይም ልጅዎ ተቅማጥ ካለበት፤ ተቅማጡ ሙሉ በሙሉ እስኪቆም ድረስ ከትምህርት ቤት፣ ከስራ ወይም ከህጻናት ማቆያ ቦታ ያርቋቸው።
➔ ምልክቶቹ እያሉብዎ ለሌሎች ምግብ አያዘጋጁ።
✴️ ደህንነቱ የተጠበቀ የግብረ-ስጋ ግንኙነት:-
ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት በፊት እና በኋላ እጅን እና ብልትን በደንብ መታጠብ እንዲሁም ኮንዶም መጠቀም ከሰገራ ጋር ንክኪን ይቀንሳል።
ጤናዎትን ይጠብቁ! ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ።
ጤና ይስጥልን!❤️

Comments