6 months ago
“መሸነፍ አይገባንም ነበር” - ሚኬል አርቴታ
#ethiopia | ቡድናቸው በኤፌ ካፕ (FA Cup) ከሳውዝሀምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ የደረሰበት ሽንፈት የሚገባው እንዳልነበር በቁጭት ገለጹ።
አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ ጨዋታውን ለሁለት ጊዜያት ደግመው መመልከታቸውንና ቡድኑ በሜዳ ላይ ካሳየው እንቅስቃሴ አንፃር ሽንፈት የማይገባው እንደነበር አፅንዖት ሰጥተዋል።
አርቴታ አክለውም “ይህ እግርኳስ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ከእኛ ማንነት ጋር በተያያዙ ስህተቶች እንቀጣለን” በማለት፣ ምንም እንኳን ውጤቱ ባይሳካም ሽንፈቱ ከጨዋታው ይዘት ይልቅ በትንንሽ ስህተቶች የመጣ መሆኑን አመልክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvah #አርሰናል #ሚኬልአርቴታ #ኤፌካፕ #እግርኳስ #የስፖርትዜና #ሳውዝሀምፕተን #arsenal #arteta #facup #footballnews

አርሰናል በሳውዝሀምፕተን ተሸንፈ
* የካራባዎና የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎቾ አመለጡት
#ethiopia | መድፈኞቹ ሌላኛውን የዋንጫ ዕድላቸውን አጥተዋል። በኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አርሰናል በሻምፒዮንሺፑ ክለብ ሳውዝሀምፕተን ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።
የአርሰናል የዋንጫ መንገድ ...
🏆 ካራባዎ ዋንጫ
በፍጻሜው በማንችስተር ሲቲ ተሸንፈው ዋንጫውን አጥተዋል።
🏆 ኤፍ ኤ ካፕ
ዛሬ በሩብ ፍጻሜው በሳውዝሀምፕተን ተሸንፈው ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
በመጋቢት ወር ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ሁሉ አሸንፎ የነበረው አርሰናል፣ ዛሬ በሳውዝሀምፕተን የታየበት ድክመትና ከውድድር መውጣቱ ለደጋፊዎቹ የማይዋጥ ውጤት ሆኗል።
ሲቲ እና ቼልሲ በሰፊ ውጤት አልፈው አርሰናል መውደቁ የለንደኑን ክለብ በቀጣይ በሊጉ ላይ ያለውን ትኩረት አሳሳቢ ያደርገዋል።
#getu #arsenalout #facup #southamptonfc #arsenalfans #footballheartbreak #gunners #premierleague #አርሰናል #ኤፍኤካፕ #ሽንፈት #እግርኳስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ቼልሲ ፖርት ቫልን 7 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜ ገባ
#ethiopia | በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት የሊግ አንዱን ፖርት ቫልን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። በዚህም ከማንችስተር ሲቲ በመቀጠል ለግማሽ ፍጻሜው የደረሰ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።
በወጣቱ አሰልጣኝ ሊያም ሮሰኒየር የሚመራው ቼልሲ በየተራ ግቦችን አከታትሏል፦
ጆርል ሃቶ
ጃኦ ፔድሮ
ቶሲን አዳራቢዮ
አንድሬ ሳንቶስ
ኤስቲቫኦ ዊሊያን
አሌሃንድሮ ጋርናቾ
ጋብርኤል (በራሱ መረብ ላይ)
በሊግ አንድ የሚሳተፈው ፖርት ቫል ጠንካራ ተቃውሞ ለማሳየት ቢሞክርም፣ በቼልሲ የፊት መስመር ተጫዋቾች ብቃት ተሸንፎ ጉዞው በሩብ ፍጻሜው ሊገታ ችሏል።
አሁን የሁላችንም ዓይን ወደ ምሽቱ 4:00 ጨዋታ ዞሯል፦
🔴 አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን (መድፈኞቹ ሶስተኛው የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን ወደ ሜዳ ይገባሉ)።
#getu #facup #chelseafc #portvale #stamfordbridge #goalfest #londonisblue #footballethiopia #mancity #arsenal #ቼልሲ #ኤፍኤካፕ #እግርኳስ #ድል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 4 ለ 0 በመርታት ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለ!
#ethiopia | ዛሬ በኢትሀድ ስታዲየም የተደረገው የኤፍ ኤ ካፕ (FA Cup) የሩብ ፍጻሜ ፍልሚያ፣ በማንችስተር ሲቲ ፍጹም የበላይነት ተጠናቋል።
የካራባዎ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ሲቲዎች፣ የየርገን ክሎፕን ሊቨርፑል ያለምንም ምህረት 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል።
አስፈሪው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ በጨዋታ ሁለት ጎሎችን፣ በአንድ የፍጹም ቅጣት ምት ደግሞ ሦስተኛ ጎሉን በማስቆጠር ድንቅ ሃትሪክ ሰርቷል።
ሌላኛዋን አራተኛ ግብ ሴሚኒዮ ከመረብ ጋር በማገናኘት የሲቲን ድል አረጋግጧል።
ሊቨርፑሎች በጨዋታው ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት መሀመድ ሳላህ ሳይጠቀምበት በመቅረቱ፣ የመርሲሳይዱ ክለብ ባዶ እጁን እንዲወጣ ሆኗል።
የኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ፍልሚያዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ፦
ምሽት 1:15፦ ቼልሲ ከ ፖርት ቫል (በስታምፎርድ ብሪጅ)
ምሽት 4:00፦ አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን (ከሜዳው ውጪ)
#getu #facup #mancity #liverpool #haaland #guardiola #arsenal #chelsea #footballnews #ethiopiasports #ማንችስተርሲቲ #ሊቨርፑል #ሃላንድ #ኤፍኤካፕ #እግርኳስ #ድል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ማንችስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል (ቀን 8፡45)
ቼልሲ ከ ፖርት ቫል (ምሽት 1፡15)
አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን (ምሽት 4፡00)
#ethiopia | የቢግ ፋይቭ ፍልሚያ በኤፍ ኤ ካፕ፦ የዘመን መለወጫ ወይንስ የበላይነት ማረጋገጫ?
ዛሬ በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍጻሜ፣ የዓለም እግር ኳስ ዓይኖች ወደ ኢትሀድ ስታዲየም ያርፋሉ። ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ከግማሽ ፍጻሜ መድረስ በላይ ትርጉም አለው።
🔥 ማንችስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል (ቀኑ 8፡45)
ከ2017/18 ጀምሮ ሊጉን በበላይነት የተቆጣጠሩት የሁለቱ ቡድኖች የ8 ዓመት ፉክክር መጋረጃው እየተዘጋ ይመስላል። የሳላህ መልቀቅና የዴ ብሮይን መሄድ የዚህ ማሳያ ነው።
ጋርዲዮላ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ብዙ የተሸነፈው በሊቨርፑል ነው (10 ጊዜ)። ዛሬ ካሸነፈ ግን የሽንፈትና ድል ታሪኩን እኩል (9-9) የማድረግ ዕድል አለው።
ሳላህ በ23 ጨዋታዎች ለ19 ግቦች ምክንያት በመሆን ሲቲን ሲያስጨንቅ ቆይቷል። ዛሬም በቋሚነት እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።
አሊሰን ቤከር (ሊቨርፑል) እና ጆስኮ ግቫርዲዮል (ሲቲ) በጉዳት አይሰለፉም።
🔴 አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን (ምሽት 4፡00)
የካራባዎ ዋንጫን በሲቲ የተነጠቀው አርሰናል፣ በኤፍ ኤ ካፕ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት ከሻምፒዮንሺፑ ክለብ ሳውዝሀምፕተን ጋር ይገናኛል።
በመጋቢት ወር ሁሉንም ጨዋታዎች ያሸነፈው አርሰናል በጥሩ ግስጋሴ ላይ ይገኛል። ሆኖም የኤዜ፣ የቲምበርና የኦዴጋርድ ጉዳት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው።
🔵 ቼልሲ ከ ፖርት ቫል (ምሽት 1፡15)
አሰልጣኝ ሊያም ሮሰኒየር ኢንዞ ፈርናንዴዝን በሥነ-ምግባር ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ማድረጋቸው በመልበሻ ክፍል አለመረጋጋት ፈጥሯል። ቼልሲ ከ96 ዓመት በኋላ ከፖርት ቫል ጋር ይገናኛል።
#ጌጡተመስገን
#getu #facup #mancity #liverpool #arsenal #chelsea #salah #guardiola #footballethiopia #premierleague #ማንችስተርሲቲ #ሊቨርፑል #አርሰናል #ቼልሲ #ኤፍኤካፕ #እግርኳስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
1 year ago
ያሳዘንኳቸውን ሰዎች ሁሉ ለመካስ ቆርጬ ተነስቻለው
✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#ethiopia | በማንችስተር ዩናይትድ ፓትሪስ ኤቭራን ለመተካት ተስፋ ተጥሎበት ከሳውዝሀምፕተን ከመጣ ጀምሮ ደጋግሞ በደረሰበት ጉዳት ተስፋውን መኖር ያለቻለውን ሉክ ሾውን ተክቶልናል በሚል በቀድሞው የክለቡ ሥራ አስፈጻሚ ኤድ ውድዋርድ አድናቆት ደርሶለት የነበረውና በካፌዋ ፈጣን ጥብሳጥብስ ምግቦችን በመሸጥ የምትተዳደረውን የእናቱን ሕይወት ይቀይር ዘንድ ተስፋ የተጣለበት ብራንደን ዊሊያምስ፤ ተስፋውን ሁሉ መኖር ተስኖት በእንግሊዝ እግር ኳስ ስኬታማ ከሆኑት ክለቦች አንዱ በሆነው በማንችሰተር ዩናይትድ የተሰጠውን ወርቃማ የእግር ኳስ ህይወት እድል ባለመብሰልና፤ ከእድሜው ቀድሞ ያገኛቸውን የገንዘብና የእውቅና ጫና መቋቋም አቅቶት ሩቅ አልሞ ቅርብ አዳሪ፤ ተስፋ አግኝቶ ከንቱ ቀሪ የሆነው ብራንደን ዊሊያምስ ወደ እግር ኳስ ተመለሷል፡፡
ከሰባት አመቱ ጀምሮ ባደገበት ማንችስተር ዩናይትድ አካዳሚ ወደዋናው ቡድን በፍጥነት በማደግ በሉክ ሾው ተደጋጋሚ መጎዳት የተሰላፊነት እድል እንዲሁም የአራት አመት ውልን ዳጎስ ካለ አመታዊ የ3.4 ሚሊየን ዶላር ክፍያ ጋር ቢያገኝም ያገኘውን ገንዘብና ዝና መቋቋም ከብዶት በዩናይትድ ቤት የተጣለበትን ተስፋ መኖር ስላልቻለ በውሰት ኖርዊችና ኢፕስዊች ታውን ተሰጥቶ ውሉ ሲጠናቀቅ ከክለቡ ተሰናብቷል፡፡ በውሰት በመሄድ የኢፕስዊች ታውን ተጫዋች በነበረበት ግዜ ህይወቱ ወዳልተፈለገ መስመር እንደዲያመራ ያደረገው ክስተት የተፈጠረው፡፡ የሚያሽከረክራትን Audi A3 መኪና ከተፈቀደለት ፍጥነት ወሰን በማሳለፍ በሰአት100 ኪሎ ሜትር በመንዳትና ከፎርድ መኪና ጋር በማጋጨቱ ለ3 አመታት የመንጃ ፈቃዱን በመነጠቅ እንዲሁም በሁለት አመት ውስጥ በሌላ ወንጀል ተሳታፊ የማይሆን ከሆነ በገደብ የተያዘ የ14 ወር እስርና የ180 ቀናት የማህበራዊ አገልግሎት የተፈረደበት መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለምዶ የሚያስቅ ጋዝ ተብሎ የሚጠራውን ናይትረስ ጋዝ በመኪና ውጥ የነበረችውን ፍቅረኛውን ሲያስጠቀም ተስተውሏል ፡፡(በታላቋ ብሪታንያ ከነሐሴ 2023 በኃላ ይህን ጋዝ መጠቀም በወንጀል ያስጠይቃል)፡፡
ከዚህ ሁሉ ነገር በኃላ በመጨረሻም ክለብ አልባ ይሆናል ተብሎ የተገመተው ብራንደን ዊሊያምስ በክረምቱ ቅድመ ውድድር ወቅት በሻምፒየንሺፕ በሚወዳደረው ሁል ሲቲ የሙከራ ልምምድ ካደረገ በኃላ በአንድ አመት ውል ስምምነት ላይ ደርሶ ቡድኑ አባል ሆኗል፡፡ በሻምፒየንሺፑም ባለፈው ሳምንት በብላክበርን ሶስት ለዜሮ በተሸነፉበት ጨዋታ ከአንድ አመት ከስድስት ወር በኃላ በ85ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ወደ እግር ኳስ ተመልሷል፡፡ ለሁል ሲቲ በፈረመበት ግዜ በጸጸት «ያሳዘንኳቸውን ሰዎች ሁሉ ለመካስ ቆርጬ ተነስቻለው:: ለታዳጊዎቹ ምሳሌ መሆን አለብኝ፡» በማለት ሲናገር ተሰምቷል፡፡

Comments