20 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አንድ ከፍተኛ የእስራኤል የደህንነት ባለስልጣን ከጥቂት ጊዜ በፊት በጋዛ ከተማ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የሐማሱ መሪ ኢዝ አል-ዲን አል-ሐዳድ መገደላቸውን የሚያመላክቱ "የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች" መኖራቸውን ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል። የፍልስጤም መገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት፣ ጥቃቱ በጋዛ ከተማ 'ሪማል' በተባለው ሰፈር የሚገኝን የመኖሪያ ሕንፃ ኢላማ ያደረገ ነበር።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ስለ ጥቃቱ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ ባያወጣም፤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ አል-ሐዳድን እንዲገድል ለእስራኤል አየር ኃይል ቀጥተኛ ትእዛዝ መስጠታቸውን በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የእስራኤሉ 'ቻናል 12' ቴሌቪዥን ምንጮቹን ሳይጠቅስ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው፣ ኔታንያሁ እና ካትዝ ይህንን የግድያ ትእዛዝ የሰጡት ሐማስ ትጥቁን እንዲፈታ በሚደረገው ጥረት ላይ አል-ሐዳድ ዋነኛ እንቅፋት መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።
ይህ ጥቃት በእስራኤል በኩል የተፈጸመ የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰት ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም፣ እስካሁን አል-ሐዳድ በእርግጠኝነት ስለመገደላቸው በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። እስራኤል ከዚህ ቀደም መሰል ጥቃቶችን ስትፈጽም፣ ኢላማ የተደረጉት ግለሰቦች በወታደሮቿ ላይ አደገኛ ስጋት ደቅነዋል በሚል ምክንያት ማቅረቧ ይታወቃል።
ኔታንያሁ እና ካትዝ በመግለጫቸው፣ አል-ሐዳድ የቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ እና "የጥቅምት 7ቱ ጭፍጨፋ ፊታውራሪዎች አንዱ" መሆኑን ገልጸዋል። "አል-ሐዳድ በሺዎች ለሚቆጠሩ የእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች እና የጦር ሠራዊት አባላት መገደል፣ መታገት እና መጎዳት ተጠያቂ ነው፤ ታጋቾቻችንን በጭካኔ አስሮ አቆይቷል፤ በኃይሎቻችን ላይ የሽብር ጥቃቶችን መርቷል፤ እንዲሁም በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሪነት ሐማስ ትጥቅ እንዲፈታ እና የጋዛ ሰርጥ ከጦር መሣሪያ ነጻ እንድትሆን የወጣውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም" ሲሉ መሪዎቹ ከሰዋል።
መግለጫው አክሎም የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና የደህንነት ተቋሙ (ሺን ቤክ) ስጋቶችን አምቆ ከመያዝ ይልቅ ጠላቶችን አስቀድሞ የማምከን የመንግሥትን ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ እየተገበሩ መሆናቸውን አስታውቋል። "ይህ ሕይወታችንን ለማጥፋት ለሚሹ ነፍሰ ገዳዮች በሙሉ የተላለፈ ግልጽ መልእክት ነው፤ ዛሬም ሆነ ነገ፣ እስራኤል እናንተ ዘንድ መድረሷ አይቀርም" በማለት መሪዎቹ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ የሆኑት የባህር ኃይል አድሚራል ብራድ ኩፐር፣ አሜሪካ በየካቲት ወር መገባደጃ ላይ የጀመረችው "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ" የተሰኘው ወታደራዊ ዘመቻ የኢራንን ወታደራዊ አቅም እና በቀጠናው ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ሙሉ በሙሉ ማዳከሙን አስታወቁ። አዛዡ ይህንን የተናገሩት በዋሽንግተን ዲሲ ለሴኔቱ የጦር ኃይሎች ኮሚቴ ስለ 2027 የበጀት ዓመት ጥያቄ እና በቀጠናው ስላለው ወታደራዊ አሰላለፍ ምስክርነት በሰጡበት ወቅት ነው።
አዛዡ በምስክርነታቸው እንዳብራሩት፣ የአሜሪካ ኃይሎች ከ40 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወታደራዊ ግባቸውን በማሳካት የኢራንን የመከላከል አቅም ክፉኛ መትተዋል። በተለይም ባለፈው ዓመት ሚያዝያ እና ጥቅምት ወራት በእስራኤል ላይ ታይቶ የማያውቅ የጅምላ ሚሳኤል ጥቃት የፈጸመችው ኢራን፣ አሁን ላይ ይህን መሰል ጥቃት የመፈጸም አቅሟ በአሜሪካ ኃይሎች ተወግዷል። አድሚራል ኩፐር አክለውም፣ የኢራን የድሮን፣ የሚሳኤል እና የባህር ኃይል መከላከያ ኢንዱስትሪ በ90 በመቶ መውደሙን እና ቀሪ አቅሟ 10 በመቶ ብቻ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኢራን የባህር ኃይል ይህንን ከባድ ውድመት ተቋቁሞ አቅሙን መልሶ ለመገንባት ከ5 እስከ 10 ዓመታት ሊወስድበት እንደሚችልም ወታደራዊ ግምገማቸውን አቅርበዋል።
ይህ ወታደራዊ እርምጃ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን መቼም ቢሆን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ያስቀመጡትን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ከዚህም ባሻገር ኢራን በቀጠናው ለሚገኙ አሸባሪ ቡድኖች ስታደርግ የነበረው ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ ክፉኛ ተመቷል። ለዓመታት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እና የጦር መሣሪያ ሲቀርብላቸው የነበሩት እንደ ሐማስ፣ ሕዝቦላህ እና ሁቲ ያሉ የተኪ ተዋጊ (Proxy) ቡድኖች፣ በዘመቻው ምክንያት ከኢራን የሚያገኙት ማንኛውም ዓይነት ትጥቅም ሆነ ሃብት መቋረጡን አዛዡ አብራርተዋል። ይህ ድል በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ለወራት የተደረገ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ እና የዓመታት ልምድ ውጤት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
"ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ" የአሜሪካን ወታደራዊ የበላይነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ካሉ አጋር አገራት ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩ ተገልጿል። አድሚራል ኩፐር እንደገለጹት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ባህሬን፣ ኩዌት፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር ጎን ለጎን በመቆም ራሳቸውንም ሆነ አሜሪካውያንን በመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በተጨማሪም ይህ ግዙፍ ወታደራዊ ስኬት ያለ ዮርዳኖስ እና እስራኤል የጠበቀ አጋርነት ሊሳካ እንደማይችል በመግለጽ፣ ዘመቻው በቀጠናው ያለውን የጸጥታ ትብብር ምን ያህል እንዳጠናከረው መስክረዋል።

3 months ago
ሐማስ ጋዛን በድጋሚ እየተቆጣጠረ መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | ከእስራኤል ጋር በነበረው መጠነ ሰፊ ጦርነት ከፍተኛ ወታደራዊ ምት የደረሰበትና ቁልፍ አዛዦቹን ያጣው ሐማስ፣ በአሁኑ ወቅት በጋዛ ሰርጥ ያለውን አስተዳደራዊ እና ጸጥታ ነክ ቁጥጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያጠናከረ መሆኑ ተሰማ።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ቡድኑ በአሜሪካ አደራዳሪነት ከተደረሰው የተኩስ አቁም በኋላ ከተደበቀበት በመውጣት አብዛኞቹን የጋዛ አካባቢዎች መልሶ መቆጣጠር ጀምሯል።
ቁልፍ መረጃዎች፡-
* አስተዳደራዊ ቁጥጥር፦ ሐማስ የመንግሥት አገልግሎቶችን መስጠት፣ ግብር መሰብሰብ እና የጸጥታ ጥበቃ ሥራዎችን ዳግም ማከናወን ጀምሯል።
* የይዞታ ስፋት፦ በአሁኑ ወቅት ከጋዛ ሰርጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ግዛት በቡድኑ ቁጥጥር ስር መሆኑ ይነገራል።
* የነዋሪዎች ቅሬታ፦ ቡድኑ ቁጥጥሩን ቢያጠናክርም፣ ነዋሪዎች ግን ለጥበቃና ለግብር የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን ከበፊቱ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን በመግለጽ ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው።
ሐማስ በበኩሉ ጋዛ በአሁኑ ወቅት በ"አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ" ስር እንደምትገኝ በመጥቀስ፣ አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም እና መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ለመጀመር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።
ምንም እንኳ የእስራኤል ጦር የሐማስን ወታደራዊ ክንፍ በእጅጉ አዳክሜያለሁ ቢልም፣ በሲቪል አስተዳደሩ በኩል ቡድኑ ያለው ተጽዕኖ ግን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ወቅታዊ ሁኔታዎች ያሳያሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #gazaupdate #hamas #middleeastnews #gazaceasefire #የጋዛዜና #ሐማስ

4 months ago
የሐማስ የምስራቅ ረፋህ ሻለቃ አዛዥ በቁጥጥር ስር ዋለ
የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት (IDF) ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በደቡባዊ ጋዛ በረፋህ አካባቢ ከሚገኝ የመሬት ስር መተላለፊያ (tunnel) ለማምለጥ ሲሞክር የነበረውን የሐማስ የምስራቅ ረፋህ ሻለቃ ቁልፍ አዛዥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
የታሰረበት ሁኔታ፦ ትላንት ሌሊት ስምንት የሚሆኑ የሐማስ ታጣቂዎች ከመሬት ስር መተላለፊያ ሲወጡ በእስራኤል የአየር ድብደባ የተፈጸመባቸው ሲሆን፣ ሦስቱ ወዲያውኑ ተገድለዋል። አዛዡ ግን ለማምለጥና ለመደበቅ ሲሞክር መያዙን ሰራዊቱ ገልጿል።
ልዩ መረጃ፦ ምንም እንኳን የእስራኤል ጦር "እኛ ነን የያዝነው" ቢልም፣ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ግን አዛዡ የተያዘው በረፋህ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው እና ሐማስን በሚቃወመው "አቡ ሻባብ" (Abu Shabab) በተሰኘ ሚሊሻ እንደሆነ ያሳያሉ። ሚሊሻው አዛዡን ከያዘ በኋላ ለIDF አሳልፎ እንደሰጠው እየተነገረ ነው።
ቀጣይ እርምጃ፦ የእስራኤል ሰራዊት እና የሺን ቤት (Shin Bet) የደህንነት ተቋም በአካባቢው የቀሩ ሌሎች ታጣቂዎችን "ለማግኘትና ለመደምሰስ" ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የጋዛ ዕጣ ፈንታ በካይሮ፡ የሐማስ ከፍተኛ ልዑክ ለወሳኝ ድርድር ግብፅ ገባ
በጋዛ ለወራት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማቆም የሚደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማፋጠን፣ ከፍተኛ የሐማስ ልዑክ ትናንት ምሽት ግብፅ ካይሮ ገብቷል።
በካሊል አል-ሀያ የሚመራው ይህ የድርድር ቡድን፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱን የመጀመሪያ ምዕራፍ ለማጠናቀቅና እጅግ ወሳኝ የተባለውን የራፋህ ድንበር በሁለቱም አቅጣጫዎች ዳግም ለማስከፈት ከግብፅ ባለሥልጣናት ጋር ምክክር ይጀምራል።
የዚህ ጉብኝት ዋነኛ ትኩረት የእስራኤል ወታደር ከጋዛ እንዲወጣ የሚሰራውን ስራ ማቀላጠፍ እና አካባቢውን የሚያስተዳድር የቴክኖክራት ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ሁለተኛው የሰላም ምዕራፍ በፍጥነት መሸጋገር እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የፀደቀውንና በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ባለ 20 ነጥብ የሰላም ፍኖተ-ካርታ መሠረት ያደረገ ነው።
እቅዱ በፈረንጆቹ እስከ 2027 ድረስ የሚቆይ ዓለም አቀፍ የማረጋጊያ ኃይል ማሰማራትን፣ የታገቱ እስራኤላውያን እንዲፈቱ እና ሐማስ ትጥቅ እንዲፈታ የሚሉ ነጥቦችን የያዘ ሲሆን፣ የልዑካን ቡድኑ በካይሮ ቆይታው ከሌሎች የፍልስጤም ቡድኖች ጋር በመምከር በጋዛና በዌስት ባንክ ስላለው የወደፊት የፖለቲካ ዕጣ ፈንታ የጋራ አቋም ለመያዝ ይጥራል።

እስራኤል ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድንን እና ኦክስፋምን ጨምሮ የበርካታ የእርዳታ ድርጅቶችን የሥራ ፈቃድ ሰረዘች
ተቃውሞዎች ቢኖሩም እስራኤል የበርካታ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችን የሥራ ፈቃድ ሰርዛለች። የእስራኤል ባለሥልጣናት ድርጅቶቹ ሥራቸውን ለመቀጠል ከዛሬ ጀምሮ ምዝገባ እንዲያካሂዱ የጠየቁ ሲሆን፣ በርካታ ድርጅቶች ግን ይህ መስፈርት ሕገ-ወጥ ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል።
እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ገለጻ ከሆነ፣ እነዚህ ድርጅቶች እስከ መጋቢት ወር ድረስ ሥራቸውን በቋሚነት ማቆም አለባቸው፤ ይህም በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረገው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት በደረሰባት በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችንም ይጨምራል።
በውሳኔው “ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን እና “ኦክስፋም”ን ጨምሮ 37 ድርጅቶች ተጎጂ ሆነዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ የእስራኤልን ድርጊት "አስነዋሪ" ሲሉ ገልጸውታል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ምዝገባው ያስፈለገው "የሽብርተኝነት አካላት ተሳትፎን ለመከላከል እና የሰብዓዊ ሥራውን ታማኝነት ለመጠበቅ ነው" ብሏል።
በቤልጂየም የእስራኤል አምባሳደር ኢዲት ሮዘንዝዌግ-አቡ በኤክስ (X) ማህበራዊ ገጽ ባሰፈሩት ጽሁፍ እርምጃውን ተከላክለዋል።
ከመቶ በላይ ድርጅቶች እንደተጠየቀው የምዝገባ ማመልከቻ ማቅረባቸውን እና ውድቅ የተደረገው የዘጠኙ ብቻ መሆኑን ጽፈዋል።
የተጠቀሱት 37 ድርጅቶች ሂደቱን ያላጠናቀቁት የአካባቢው ተቀጣሪ ሰራተኞቻቸውን ዝርዝር ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
እስራኤል “ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድንን ” በሽብርተኝነት ተግባር ላይ የተሳተፈ ሰራተኛ አለው ስትል ትከስሳለች።
ሮዘንዝዌግ-አቡ "እነዚህ 37 ድርጅቶች እንደሌሎቹ ድርጅቶች ሁሉ የምዝገባ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ አሁንም ጥሪ ይቀርብላቸዋል" ሲሉ ጽፈዋል።
ድርጅቶቹ በተኩስ አቁም ወቅት ወደ ጋዛ ሰርጥ ምንም ዓይነት እርዳታ አላደረሱም፣ ከዚያ በፊትም ቢሆን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከጠቅላላው የእርዳታ መጠን አንድ በመቶ ብቻ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ተቺዎች የእስራኤልን የምዝገባ መስፈርት ለዘፈቀደ ውሳኔዎች መንገድ የሚከፍቱ ግልጽ ያልሆኑ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው ብለውታል።
እንደ ተቺዎቹ ገለጻ፣ ድርጅቶቹ ስለ ፍልስጤማውያን ሰራተኞቻቸው ምስጢራዊ መረጃ እንዲያሳውቁ እና ሲጠየቁም ያለምንም ምክንያት ሰራተኞችን እንዲያሰናብቱ ይገደዳሉ።
በአንድ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆነ አካል በሰራተኞች የማጣራት ሂደት ውስጥ ጣልቃ መግባቱ እንደ ገለልተኝነት እና ነፃነት ያሉ መሰረታዊ የሰብዓዊ መርሆዎችን መጣስ ተደርጎ ይወሰዳል።
በገለልተኛ አካላት በኩል ይደረግ የቀረበው የማጣራት ጥያቄ እስካሁን ውድቅ ተደርጓል።

የጣሊያን ፖሊስ ዛሬ እንዳስታወቀው በሰብአዊ ድርጅቶች በኩል ቢያንስ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ለሐማስ ሰብስበዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰባት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
6 months ago
እስራኤል የሀማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆኑትን ራኢድ ሳአድን መግደሏን አስታወቀች
ሳአድ በሐማስ የታጠቀው ክንፍ ውስጥ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በጋዛ ከተማ የቃሳም ብርጌድ የጦር መሳሪያ ምርት ኃላፊ ነበር።
ሀማስ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ሲቪል ተሽከርካሪን ኢላማ ማድረጋቸውን በመግለጽ ሌላኛውን ወገን የተኩስ አቁሙን በግልጽ በመጣስ ወንጅሏል።
በሌላ በኩል እስራኤል የሳአድን የጦር መሳሪያ ምርት ተግባራት የተኩስ አቁም ስምምነት መጣስ እንደሆነ ገልጻለች።
እንደ እስራኤል አባባል ራኢድ ሳአድ ጥቅምት 14 ቀን 2023 በእስራኤል ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የማቀድ ሥራ ውስጥ ተሳትፏል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት የዳረገው ይህ ጥቃት የጋዛ ጦርነትን የጀመረ ሲሆን በእስራኤል እና ፍልስጤም መካከል ያለውን ግጭትም አባብሶታል።
እንደ ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ ከሆነ ሳአድ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በጋዛ በደረሰ የእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድሏል።
የፍልስጤም የዜና ወኪል ዋፋ በጋዛ ውስጥ ቅዳሜ ዕለት በተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የእስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ዘግቧል።
ይሁን እንጂ ጥቃቱ የሐማስ አዛዥ እንደተገደሉበት ከተነገረው ጥቃት ጋር አንድ አይነት ስለመሆኑ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
ስለ ራኢድ ሳአድ የሚወጣው ዜና እውነት ከሆነ፣ አል-ጀዚራ እንደገመተው፣ ጊዜያዊው የተኩስ አቁም ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ የተፈጸመ የመጀመሪያው ከፍተኛ መገለጫ ያለው ግድያ ይሆናል።
እስራኤል ሳአድን ለመግደል ለረጅም ጊዜ ስትሞክር ቆይታለች።
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ20-ነጥብ የሰላም ዕቅድ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ቀጣዩ እንዲሸጋገር ማድረግ አስቸጋሪ ሆኗል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሁለተኛው ምዕራፍ ድርድር ተቃርቧል አሉ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም በዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት ወደሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር ለመግባት መቃረባቸውን ገለፁ።
ነገር ግን ቁልፍ ጉዳዮች አሁንም ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።
በሁለተኛው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዕቅድ መሠረት በጋዛ የሽግግር አስተዳደር ተቋቁሞ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ኃይል ሲሰማራ እስራኤል ወታደሮቿን ከጋዛ ማስወጣት አለባት።
ከዚህም በተጨማሪ ሐማስ ትጥቁን ፈትቶ ጋዛን መልሶ መገንባት መጀመር ይኖርበታል።
የሐማስ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ቡድኑ የቀረውን የጦር መሣሪያ "ላለመጠቀም ወይም ለማከማቸት" ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች አደራዳሪዎች ወደ ቀጣዩ የትራምፕ ዕቅድ መሄድ እንዲቻል በሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ላይ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የአረብ መገናኛ ብዙኃን የቀይ መስቀል ቡድን እና የሐማስ ታጣቂ ክንፍ አባላት በጋዛ ከተማ ዜይቱን አካባቢ የቀረውን የእስራኤላዊ ታጋች አስከሬን ፍለጋ መቀጠላቸውን ዘግበዋል።
ይህ እስራኤላዊ ፖሊስ የነበረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሙሉ ስሙ ሳጅን ራን ጊቪሊ እንደሚባል ይፋ ተደርጓል። ሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በፈጸመበት መስከረም 26፣2016 ዓ.ም. ጊቪሊ የተገደለ ሲሆን አስከሬኑ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረገው የመጀመሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት መመለስ አለበት።
ኔታንያሁ እሁድ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ "እናመጣዋለን" ሲሉ ቃል ገብተዋል።
የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ሁለት ወራት የሞላው ሲሆን ሁለቱም ወገኖች በየቀኑ አንዳቸው ሌላኛቸውን ስምምነቱን በመጣስ እርስ በርስ መወነጃጀላቸውን ቀጥለዋል።
የእስራኤል ጦር ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የጋዛ ሰርጥ ይቆጣጠራል። ሐማስ ደግሞ በተቀረው የግዛቱ ክፍል ውስጥ ዳግም ራሱን አደራጅቷል።
ኔታንያሁ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ በወሩ መጨረሻ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር የዕቅዱን ሁለተኛ ምዕራፍ ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጠቃሚ ውይይት እንደሚያካሂዱ ተናግረዋል።
የእስራኤል መንግሥት ቃል አቀባይ ስብሰባው እአአ ታኅሳስ 29 እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
ኔታንያሁ እሁድ ዕለት ከጀርመን መራሄ መንግሥት ፍሬድሪክ መርዝ ጋር በእየሩሳሌም ከተገናኙ በኋላ ሐማስ ጋዛን የሚያስተዳድርበት ዘመን ማብቃት እንዳለበት እና ቡድኑ የታጠቀውን መሳሪያ ለመፍታት እና አካባቢውን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ለማድረግ "በቁርጠኝነት" እንዲወጣ በድጋሚ ተናግረዋል።
የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ባሴም ናኢም ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ቡድናቸው የጦር መሣሪያ መፍታትን አስመልክቶ "ላለመጠቀም ወይም በመጋዘን እንዲቀመጥ ማድረግ" ላይ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ አባል የሆኑት ናኢም አብዛኛው የቡድኑ አመራር በሚገኝባት በኳታር በሰጡት ቃለ ምልልስ "ከዚህ የበለጠ ግጭቱ እንዳይቀጥል ወይም ተጨማሪ ግጭቶችን እና ፍንዳታዎችን ለማስቀረት አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ዝግጁ ነን" ብለዋል።
ሐማስ ከዚህ ቀደም ነፃ የፍልስጤም መንግሥት ሳይፈጠር የጦር መሳሪያዎቹን ለመፍታት ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲናገር ነበር።
ናኢም እስራኤል ቁልፍ የተኩስ አቁም ቃል ኪዳኖችን ሳትፈጽም ቀርታለች በማለት የከሰሱ ሲሆን ወደ ጋዛ በቂ እርዳታ እየገባ አለመሆኑን እና ከግብፅ ጋር ያለው የራፋህ ድንበርም እንደገና እንዳልተከፈተ ተናግረዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች ወደ ሰርጡ የሚገቡት እርዳታዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን፤ ነገር ግን አሁንም በፀጥታ እጦት እና በእስራኤል ጦር እገዳ ምክንያት እግር እየገጠማቸው መሆኑን ይናገራሉ።
በሰላም ዕቅዱ የመጀመሪያ ምዕራፍ መሠረት በሕይወት ያሉ 20 ታጋቾች እንዲሁም 28 የታጋቾች አስከሬኖች እንዲመለሱ ይጠበቃል።
እስራኤል በሕይወት ያሉ ታጋቾችን ለማስፈታት ወደ 2,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቅቃለች።
ሐማስ በሕይወት ያሉትን ታጋቾች በሙሉ የለቀቀ ሲሆን፣ ከሟቾች የቀረው የአንድ ፖሊስ አስከሬን ብቻ ነው።
እስራኤል ሐማስን የሟቾችን አስከሬን ለመመለስ ሆን ብሎ ያዘገያል ስትል ትከስሳለች።
BBC

ጋዛ ፈገግታዋ ታዬ ታላቁ የህብረት ጋብቻ ተፈፀመ !
ጠባቧ የጋዛ ሰርጥ ከፈገግታና ከሳቅ ከፍስሐና ደስታ ጋር የተለያየችዉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 2023 ነበር ።
የሐማስ ታጣቂዎች ጥቅምት 7፣ 2023 ደቡባዊ እስራኤልን አጥቅተዉ- 1200 ሰዎችን ገደሉ፤ ከ200 በላይ አገቱ ።
ይህን ተከትሎ እስራኤል የአጸፋ ርምጃውን ከጀመረች ጀምሮ ወደ ጋዛ ሰርጥ ምግብ ውኃና መድኃኒትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች እንዳይገቡ በመከልከል በጀመረችው ዘመቻ የዚያች ትንሽ፣ ጠባብ፣ ደሐ ሰርጥ ቦምብ-ሚሳዬል እየተዘራባት ፣ፍርስራሽ እየተከመረባት ፣የቦምብ-ሚሳዬል ወዠብ ይወርድ ገባ ።
ዲፕሎማቶች በየመገናኛ ዘዴ-ጉባኤ-ስብሰባዉ የኃይማኖት መሪዎች በየፀሎት፣ ሶላታቸዉ ወቅት፣ከሳንቲያጎ ደ ቼሌ እስከ ኦታዋ፣ ከሲድኒ እስከ ሰነዓ የሚገኘዉ ሕዝብ በየአደባባይ ሰላም እንዲሰፍን የቀረቡ ሀሳቦች በሁለቱም ተፋላሚዎች ጀሮ ዳባ ልበስ ተብለዉ ከሁለት አመታት በላይ መአት ወረደባት ።
ጎስቋሎች ሕፃን-ካዋቂ፣ ወንድ ከሴት ሳይለይ ሽዎችን ህይወት የነጠቀው ጦርነት ሰርክ በባሩድ ጭስ ስለማይለያት አይደለምና ወግ ማዕረግ ለማየት ለመኖር ስጋት ሁና ከርማለች ።
እልፎች አልፈዉ ብዙዎች አልቀው የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከጥይት ኳኳታ ከመድፍ ድምድምታ ተንፈስ ያለችው በደቡባዊ ጋዛ የምትገኘው የካን ዩኒስ ከተማ በአቡ ዳቢ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ድጋፍ የተደረገለት በጦርነት የፈራረሱ ህንጻዎች መሃል 54 ጥንዶች የተሞሸሩበት የጅምላ ሰርግ አድርጋለች ።
በእለተ ማክሰኞ ነጭ፣ ቀይ እና አረንጓዴ ባህላዊ ቀሚስ የተዋቡ ጥንዶችኝ የያዙ መኪኖች ሰልፍ በፈረሱ ሕንፃዎች ውስጥ እየተንሸራሸሩ አለምህ ዛሬ ነዉ ሲጨፈር ዉሏል ።
ወትሮም ለፍልስጤማውያን፣ ሰርጎች ብዙውን ጊዜ ለቀናት የሚቆዩ የተንቆጠቆጡ ክብረ በዓላት ናቸዉና የፍልስጤምን ባንዲራ በዙሪያቸው ያሉ ቤተሰቦች በሙዚቃ ሲጨፍሩ
ጥንዶቹ እና የሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸዉ አስደሳች ጭፈራዎችን እና ሰልፎች ሀይሎጋን ሲጨፍሩ ታይተዋል ።
ይህ በሃማድ መኖሪያ አካባቢ በፈረሱ ሕንፃዎች ፍርስራሽ ውስጥ የተካሄደው ሥነ ሥርዓት የተካሄደው በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ "ጋላንት ናይት 3" የሰብአዊነት ዘመቻ ስር ነው ሲል የአናዶሉ ዘጋቢ ዘግቧል።
ሀጫ በረዶ የመሰለ ቬሎና ሱፍ የለበሱት ተጋቢዎች መካከል የሆኑት ላውዋ እና ኢማን፣ ሠርጉ ለዓመታት ከመከራ በኋላ ትንሽ እፎይታ እንደሰጣቸው ተናግረዋል።
ኤማን በጦርነቱ ወቅት የተገደሉትን አባቷን፣ እናቷን እና ሌሎች የቤተሰቧን አባላት በማጣታቸው ዉስጧ ሀዘን ቢኖም ሞትና ሰርግ የህይወት ኡደት በመሆናቸው ተመስገን ስትል ተደምጣለች ።
"እንዲህ ካለው ሀዘን በኋላ ደስታን ማግኘት ከባድ ነው" አለች እንባዋ እየፈሰሰ። "እግዚአብሔር ቢፈቅድ፣ ጡብ በጡብ እንገነባለን" ብላለች።
ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ መሪዎች አዲስ ተጋቢዎችን በሰልፍ ሲመለከቱ የፍልስጤም ባንዲራዎች፣ አበቦች እና ባህላዊ ዘፈኖች ታጅበዉ ወልደው እንዲከብዱ ምኞታቸውን ገልፀዋል ሲሉ ያስነበቡት አናዶሉ አረብያ ኒዉስ ዘጋርዲያን ናቸዉ ።

የእስራኤል ድሮን ጥቃት የፎቶ ጋዜጠኛውን ሞሐመድ ዋዲ ገድሎ ሌላ ጋዜጠኛ አቆሰለ
ይህ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት በጥቅምት 2 ከጀመረ በኋላ የተገደለው ሁለተኛው የሚዲያ ሰራተኛ ነው።
ሞሐመድ ዋዲ ህዳር 23 ቀን ጠዋት ላይ በመካከለኛው የጋዛ ሰርጥ ውስጥ ከሚገኘው የአል-ቡሬጅ የስደተኞች ካምፕ በስተምስራቅ በእስራኤል በድሮን ጥቃት የተገደለ ፎቶ ጋዜጠኛ ሲል አረብ ኒውስ የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።
በዚሁ ጥቃት ደግሞ ሌላኛው ጋዜጠኛ ሞሐመድ አብደል ፈታህ አስሊህ—በግንቦት ወር በእስራኤል ጥቃት በናስር ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ውስጥ የተገደለው የሪፖርተር ሀሰን አስሊህ ወንድም—ቆስሏል።
በሳዑዲ ሚዲያዎች የተዘገቡት የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ዋዲ ስቱዲዮው በእስራኤል የቦምብ ጥቃት እስኪወድም ድረስ በኻን ዩኒስ ውስጥ የታወቀ የሰርግ ፎቶግራፍ አንሺ የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን በጋዛ ጦርነት ላይ መዘገብ ጀምሯል።
እሱ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት በጥቅምት 2ከጀመረ በኋላ የተገደለው ሁለተኛው የሚዲያ ሰራተኛ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትላንት እንደተናገሩት “የጦርነት ህጎች ግልፅ ናቸው፡ ሲቪሎች እና የሲቪል መሠረተ ልማቶች ኢላማ አይደሉም። ጋዜጠኞች ያለ ጣልቃ ገብነት፣ ማስፈራራት ወይም ጉዳት አስፈላጊ ስራቸውን ማከናወን መቻል አለባቸው። ይህም ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ የተጣለው ተቀባይነት የሌለው እገዳን ይጨምራል” ብለዋል።

እስራኤል ከወራት በኋላ በቤይሩት በፈፀመችው አዲስ ጥቃት ከፍተኛ የሔዝቦላህ ባለሥልጣንን ገደለች
የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በፈጸመው ጥቃት የሔዝቦላህ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ገደለች።
የተገደሉት ባለሥልጣን የሔዝቦላህ ዋና ኢታማዦር ሹም ሀይታም አሊ አል ታታባይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ቡድኑን በተለያዩ ከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ላይ ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር፤ በዳሂ ዲስትሪክት የመኖሪያ ህንጻ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን እና 28 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።
ሔዝቦላህ የታታባይን ሞት አረጋግጦ፣ እስራኤል ጥቃቱን በመፈጸም "ቀይ መስመር" አልፋለች ብሏል።
የእስራኤል ጦር ከወራት በኋላ በደቡባዊ ቤይሩት ጥቃት ሲፈጽም ይህ የመጀመርያው ነው።
ባለፈው ኅዳር ወር በዩናይትድ ስቴትስ እና በፈረንሳይ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም እስራኤል በኢራን ከሚደገፈው ሔዝቦላህ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ሰዎች እና ተቋማት ማጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች።
የእስራኤል ባለሥልጣናት ሔዝቦላህ ወታደራዊ አቅሙን ዳግም ለማጠናከር እየሞከረ ነው በማለት ይከስሳሉ።
አክለውም የጦር መሣሪያ ወደ ሊባኖስ እያስገባ እና በሮኬቶች እና ሚሳዔሎች ምትክ የሚፈነዱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እያመረተ መሆኑን በመጥቀስ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ይገልጻሉ።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከጥቃቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ "በእኔ መሪነት የእስራኤል መንግሥት ሔዝቦላህ አቅሙን መልሶ እንዲያጠናክር፤ በእስራኤል መንግሥት ላይም ስጋት እንዲፈጥር አንፈቅድም" ብለዋል።
የሊባኖስ መንግሥት "ሔዝቦላን ትጥቅ ለማስፈታት የገባውን ግዴታ ይፈጽማል" ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን በደቡባዊ ሊባኖስ ቢያንስ አምስት ቦታዎችን በቁጥጥሯ ሥር አድርጋ የምትገኘው እስራኤል፤ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም እና ከአገሪቱ ለቅቃ እንድትወጣ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የእስራኤል ድርጊት ለ13 ወራት ግጭት ያስቆመውን ስምምነት የጣሰ ነው ሲሉም ኮንነዋል።
የሊባኖስ መንግሥት ሔዝቦላህን ትጥቅ ለማስፈታት ቃል ገብቷል።
ነገር ግን ቡድኑ እስራኤል ጥቃቷን ሳታቆም፣ ከሊባኖስ ሙሉ በሙሉ ለቅቃ ሳትወጣ እና ሊባኖሳዊያን እስረኞችን ሳትለቅ ስለ ትጥቅ መፍታት እንደማይወያይ አስታውቋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የምዕራባውያን አገር ዲፕሎማት ለቢቢሲ እንደተናገሩት የሊባኖስ ባለሥልጣናት በትራምፕ አስተዳደር ግፊት እየደረሰባቸው ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይትድ ኪንግደም እንደ አሸባሪ ድርጅት በሚቆጠሩት ሔዝቦላህ ላይ እየታየ ያለው አዝጋሚ ለውጥ የትራምፕ አስተዳደርን ትዕግሥት እያሟጠጠው መሆኑን ዲፕሎማቱ ጠቅሰዋል።
በእስራኤል እና በሔዝቦላህ መካከል በድጋሚ ግጭት የተቀሰቀሰው ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ አማጺ ቡድኑ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን ማስወንጨፍ በመጀመሩ ነው።
ሔዝቦላህ ከጥቃቱ በኋላ በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጎን መቆሙን ተናግሯል።
ከዚያ ወዲህ እስራኤል በአገሪቱ ላይ በፈጸመችው መጠነ ሰፊ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ 4,000 የሚጠጉ ሰዎችን መገደላቸውን እና ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የሊባኖስ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
እስራኤል በበኩሏ በጦርነቱ ከ80 በላይ ወታደሮቿ እና 47 ንፁኃን ዜጎቿ መገደላቸውን አስታውቃለች።
የአሜሪካ መንግሥት በታታባይ ላይ እአአ በ2016 ማዕቀብ ጥሎ በአሸባሪነት ፈርጇቸዋል። ስለ ግለሰቡ መረጃ ለሚሰጠው ማንኛውም ግለሰብ የ5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አቅርቦ ነበር።
አሜሪካ ታታባይ በአንድ ወቅት በሶሪያ እና በየመን የቡድኑን ልዩ ኃይል ሲያዙ የነበሩ እና የሔዝቦላህ ቁልፍ ወታደራዊ መሪ መሆናቸውን ገልጻ፣ በእነዚህ አገራት ያከናወኗቸው ተግባራት ሔዝቦላህ "ቀጠናውን ለማመስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አካል ናቸው" ብላ ነበር።

7 months ago
በሁለት ዓመት ውስጥ ቢያንስ 94 ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች መሞታቸውን የሰብአዊ መብት ተቋም ገለጸ
ከሁለት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 94 ፍልስጤማውያን እስረኞች እና ታጋቾች በእስራኤል እስር ቤቶች መሞታቸውን የሰብአዊ መብት ተቋም አስታወቀ።
'ፊዚሽያንስ ፎር ሂውማን ራይትስ እስራኤል' የተባለው ታዋቂ የእስራኤል የሰብአዊ መብት ተቋም እንደገለጸው፤ ፍልስጤማውያኑ የሞቱት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግላቸው እስር ቤቶች ውስጥ ነው።
"ስልታዊ የሆነ ግድያ እና ግድያዎችን መሸፈን ተፈጽሟል" በማለት ተቋሙ ገልጿል።
ሪፖርቱ የሚሸፍነው ሐማስ ጥቃት ካደረሰበት ወቅት ማለትም ከጥቅምት 7/2023 እስከ ነሐሴ 7/2025 ያለውን ጊዜ ነው።
ባለፉት 10 ዓመታት ወደ 30 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ይዞታ ሥር ሳሉ መሞታቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል።
የእስራኤል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር "ቁጥጥር በሚያደርጉ አመራሮች ክትትል መሠረት እና ሕግን ተከትሎ ይሠራል" ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል።
"ሁሉም ታራሚዎች የሚያዙት ሕግን በተከተለ መንገድ ነው። ሕክምና የማግኘት፣ ንጹህ ቦታ የመቆየት እና ተስማሚ የኑሮ ሁኔታ የማግኘት መብታቸው ሥልጠና በወሰዱ ባለሙያዎች አማካኝነት ይጠበቃል" በማለትም አክሏል።
ሆኖም ግን ከውጭ አካላት በተሰነዘሩ ክሶች እና ቁጥሮች ላይ አስተያየት እንደማይሰጥ አስታውቋል።
ከሐማስ ጥቃት በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የተለያየ ውንጀላ ቀርቦባቸው በጋዛ እና በዌስት ባንክ በእስራኤል ተይዘዋል። አብዛኞቹ በይፋ አልተከሰሱም።
የሰብአዊ መብት ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት ስልታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን አጋልጧል።
እስራኤል "የደኅንነት እስረኞች" በምትላቸው ፍልስጤማውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥሰቶችን ያጋለጠው ተቋሙ፤ እየደረሰ ያለው አስጊ የሆነ ስልታዊ የመብት ጥሰት ነው ብሏል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እየተፈጸመ ያለው ይፋዊ የሆነ ፖሊሲን በመከተል እንደሆነም ጠቅሷል።
እስራኤል በይዞታዋ ሥር ስላሉ ፍልስጤማውያን ለቀይ መስቀል መረጃ መስጠት እንዲሁም እስረኞችን ማስጎብኘት አቁማለች።
የእስራኤሉ የሰብአዊ መብት ተቋም ያወጣው ሪፖርት ይፋዊ መረጃ ላይ የተመረኮዘ እንደሆነ ጠቅሷል።
መረጃውንም ከፎረንሲክ ምርመራ ውጤት፣ ከእረኞች፣ ከቤተሰቦቻቸው እና ከጠበቆቻቸው እንዲሁም ከሌሎች ሰብአዊ መብት ተቋማት ሪፖርት ጋር አመሳክሯል።
በሪፖርቱ መሠረት፤ 52 ፍልስጤማውያን የሞቱት በእስራኤል ወታደራዊ እስር ቤት ውስጥ ሳሉ ሲሆን፤ 42 የሚሆኑት ፍልስጤማውያን የሞቱት በእስራኤል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሥር በሚገኙ ሲቪል እስር ቤቶች ነው።
የእስራኤል ቀኝ ዘመም ብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር እና የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፓርቲ ቁልፍ አባል ኢታማር ቤን-ጊር ፖሊሲዎች በዋነኛነት በሪፖርቱ ተጠቅሰዋል።
በሚኒስትሩ አስተዳደር ሥር ያሉ የግዳጅ ማቆያዎች "ወደ ስቃይ እና ብዝበዛ ማዕከልነት" መለወጣቸውን ይገልጻል።
በየዕለቱ አካላዊ ጥቃት እና ስልታዊ ስቅይት እንደሚፈጸም፤ በዚህም ምክንያት በርካታ ፍልስጤማውያን ለሞት እንደተዳረጉ ሪፖርቱ ያሳያል።
በብዛት የፍልስጤማውያን ሞት የተመዘገበው በጋዛ አቅራቢያ በደቡባዊ እስራኤል በሚገኘው በስዴ ታሚን ወታደራዊ እስር ቤት ነው።
በዚህ እስር ቤት አንድ ፍልስጤማዊ ተደብድቦ፣ በፊንጢጣው ስለት መከተቱ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ፤አምስት የእስራኤል ተጠባባቂ ወታደሮች በብዝበዛ እና የከፋ አካላዊ ጉዳት በማድረስ ተከስሰዋል።
ወታደሮቹ ፍልስጤማዊውን በፖሊስ ሺልድ ከበው ጥቃት ሲያደርሱበት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ወጥቷል። ተጠባባቂ ወታደሮቹ ክሱን አስተባብለዋል።
ፍልስጤማዊው ላይ የደረሰው ጥቃት አገሪቱን ለሁለት ከፍሏል። አንዳንድ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ወታደሮቹን አውግዘው ድርጊቱ ላይ ምርመራ እንዲደረገግ ሲጠይቁ፤ ሌሎች በተቃራኒው በእስር ቤቶች አካባቢ ባደረጉት ሰልፍ "የመድፈር መብትን" ደግፈዋል።
የሰብአዊ መብት ተቋሙ እንዳለው የእስራኤል ባለሥልጣናት የደረሱት ጥቃቶች እና ሞቶች እንዳይመረመሩ "ለመሸፈን" ሞክረዋል።
የፍልስጤማውያኑ ሞት ለቤተሰቦቻቸው እንዳልተነገረ እና አስከሬናቸውም እንዳልተሰጣቸው ሪፖርቱ ያሳያል።
እስራኤላውያን የእስር ቤት ጠባቂዎች እና ወታደሮች ላይ ክስ አልተመሠረተም።
እስራኤል በፖሊሲ ደረጃ "የግዳጅ ስወራ" እንደምትፈጽም እና በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ያለ ቤተሰቦቻቸው ዕውቅና እንደታገቱ በሪፖርቱ ተካትቷል።
ቤተሰቦቻቸው፤ ፍልስጤማውያኑ የት እንደሚገኙ መረጃ አይሰጣቸውም።
በዚህ "ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት" እስራኤል የፈጸመችው ድርጊት በትክክል እንዳልታወቀ እና የፍልስጤማውያኑ እጣ ፈንታ የከፋ እንደሆነ ጠቁሟል።
የሞቱት ፍልስጤማውያን ቁጥር በሪፖርቱ ከተጠቀሰውም በላይ እንደሚሆን ተገልጿል።
የእስራኤል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር "እነዚህ ክሶች የእስራኤል እስር ቤትን ድርጊት አይወክሉም" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
በእስራኤል እስር ቤት "የሚከሰት ሁሉም ሞት በተቀመጠው አሠራር መሠረት ምርመራ ይደረግበታል" ሲልም ገልጿል።
"ግላዊ መረጃን ለመጠበቅ፣ ደኅንነት እና ሕግን ለማክበር ሲባል የእስራኤል የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስለ እስረኞች ሁኔታ መረጃ አይሰጥም" በማለትም አክሏል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ኦፕሬሽኖቹ "ዓለም አቀፍ ሕግን የሚከተሉ እና በሽብር በተጠረጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸሙ" እንደሆኑም ገልጿል።
በአንዳንድ ሁኔታዎች "የእስራኤል ሕግን እና የጄኔቫ ስምምነትን በመከተል ለቅድመ ጥንቃቄ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ" አክሏል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እንዳለው፤ በእስር ቤት ሳሉ የሞቱ ሰዎች እንዲሁም የአካል ጉዳት እና ሕመም የገጠማቸው እንዳሉ መረጃ ደርሶታል።

እስራዔል በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 አለፈ
#ethiopia | እስራዔል በጋዛ ወታደር ተገድሎብኛል በሚል በፈጸመችው ጥቃት የሟቾቹ ቁጥር104 መድረሱን በሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታወቋል።
ጥቃቱ ሐማስ በአሜሪካ አደራዳሪነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ሥምምነት ጥሷል በሚል የተፈጸመ መሆኑን እስራዔል አስታውቃለች።
በዚህም “በርካታ የሽብር ኢላማዎችን እና አሸባሪዎችን” መምታት መቻሉን ነው የእስራዔል ጦር የገለጸው።
የእስራዔል መከላከያ መስሪያ ቤት ሐማስ በትናንትናው እለት ከሥምምነቱ ውጭ አንድ ወታደር ገድሎብኛል፤ የታጋች እስራዔላውያን አስከሬንንም አልመለሰም ሲል ኮንኗል።
ሐማስ በበኩሉ ተፈጽሟል ከተባለው ግድያ ጋር “ግንኙነት የለኝም” ለተኩስ አቁም ሥምምነቱ ተፈጻሚነትም እሰራለሁ ብሏል።
የእስራዔል ጥቃት በሰሜናዊ፣ ደቡባዊ እና ማዕከላዊ ጋዛ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፥ መኖሪያ ህንጻዎች፣ ቤቶች እና ትምህርትቤቶች ማውደሙን ቢቢሲ እና ሬውተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርገው አስነብበዋል።
የተኩስ አቁም ሥምምነቱን “ምንም ነገር” አያስተጓጉለውም ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ እስራዔል ወታደሮቿ ከተመቱባት አፀፋ መመለስ ይገባታል ሲሉ ተደምጠዋል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

8 months ago
እስራኤል በጋዛ አውቶቡስ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 11 ሰዎች ተገደሉ
በሰሜን ጋዛ ከእስራኤል ታንክ በተተኮሰ ጥይት በአንድ አውቶቡስ ተሳፍረው የነበሩ 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የሲቪል መከላከያ አስታወቀ።
የአቡ ሻባን ቤተሰብ አባላት ናቸው የተባሉት ሟቾች አርብ ምሽት ላይ በጋዛ ከተማ ዜይቱን ሰፈር የሚገኝ ቤታቸውን ለማየት እየሄዱ ነበር ተብሏል።
ይህ ከስምንት ቀናት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት ከተጀመረ ወዲህ በጋዛ በእስራኤል ጦር የተፈጸመ እጅግ አስከፊው ክስተት ነው።
የእስራኤል ጦር ወታደሮቹ በጋዛ የእስራኤል ጦር የሚገኝበትን እና ቢጫ መስመር በሚል የተከለለውን አካባቢ ያለፈ "አጠራጣሪ መኪና" ላይ መተኮሳቸውን ገልጿል።
በመጀመሪያው የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት የእስራኤል ወታደሮች ከግማሽ በላይ በሚሆነው የጋዛ ሰርጥ እንደተቆጣጠሩ ይቆያሉ።
የሲቪል መከላከያ ቃል አቀባይ ማህሙድ ባሳል ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ግለሰቦቹ የተገደሉት በአካባቢው የሚገኘውን ቤታቸውን ለማየት ሲሞክሩ ነው።
ከሟቾቹ መካከል ሴቶች እና ሕጻናት እንደሚገኙበት የሲቪል መከላከያው አስታውቋል።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል አርብ ዕለት "አጠራጣሪ መኪና የእስራኤል ወታደሮች በሚንሳቀሱበት በሰሜን ጋዛ ሰርጥ ቢጫውን መስመር አቋርጦ እየቀረበ እንደነበር ተለይቷል" በማለት በተሽከርካሪው ላይ "የማስጠንቀቂያ ጥይቶችን" መተኮሱን ተናግሯል።
ተሽከርካሪው "ወደ ወታደሮቹ ተጨባጭ ስጋት በሚፈጥር መልኩ መጠጋቱን በመቀጠሉ" እና "በተደረሰው መግባባት መሠረት ወታደሮች ጥቃቱን ለማስወገድ ተኩስ ከፍተዋል" ብሏል።
ሐማስ ቤተሰቡ ያለምክንያት ዒላማ እንደተደረገ ተናግሯል።
የእስራኤል መከላከያ ፍልስጤማውያን በጋዛ በቁጥጥሩ ስር ባሉ አካባቢዎች እንዳይገቡ አስጠንቅቋል።
የኢንተርኔት አገልግሎት ውስን በመሆኑ ብዙ ፍልስጤማውያን የእስራኤል ወታደሮች ያሉበት እና ቢጫ መስመር የተባለው የቱ እነደሆነ አያውቁም።
ይህ መስመር በመሬት ላይ ባለመካለሉ አውቶብሱ የቱ ጋር መስመሩን አንዳቋረጠ ግልጽ አይደለም።
ቢቢሲ አደጋው የተፈጸመበትን ስፍራ የሚያመለክት ኮኦርዲኔትስ እንዲሰጠው የእስራኤል ጦርን ጠይቋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ አርብ ዕለት ሠራዊቱ የመስመሩን ቦታ የሚጠቁሙ የሚታዩ ምልክቶችን እንደሚያስቀምጥ ተናግረዋል ።
በዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት እስራኤል 250 ፍልስጤማውያን እስረኞችን እና 1,718 ከጋዛ በመውሰድ ያጎረቻቸውን ሰዎች ለቅቃለች።
ሐማስ በበኩሉ በሕይወት ያሉ 20 ታጋቾችን በሙሉ ወደ ለእስራኤል አስረክቧል።
መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ በደቡባዊ እስራኤል በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት 1,200 ሰዎቸን ሲገድል 251 ግቶ ወስዷል።
የእስራኤል ጦር ይህንን ተከትሎ በከፈተው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ ቢያንስ 67,900 ሰዎች መገደላቸውን የሐማስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የእስራኤል የቀድሞ ታጋቾች ምስክርነት
"በዋሻው ውስጥ የገዛ መቃብሬን መቆፈር ነበረብኝ።"
"በጨለማ ውስጥ በሰንሰለት ታስሬ ነበር።"
"የእጅ ቀዶ ሕክምና ያለ ማደንዘዣ አድርጌያለው ።"
ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ዓመት ውስጥ፣ በሐማስ እጅ ሕይወት ያላቸው እስራኤላውያን ታጋቾች የሉም፡ የታገቱት እስራኤላውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተው ሆስፒታል ገብተዋል።
በቦምብ በተመታችው ጋዛ ዋሻዎች ውስጥ፣ ከእንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ወንዶችና ሴቶች የሉም። በሕይወት ያሉት ተመልሰዋል። አሁን መመለስ ያልቻሉትን ታጋቾች አስከሬን ይጠባበቃሉ፣ ነገር ግን እዚህ፣ "ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት ዓመት ውስጥ፣" መተንፈስ ተችሏል። የመጨረሻዎቹ ሃያ እስረኞች—ሁሉም ወንዶች፣ አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው።
የህክምና ምርመራ እየተደረገላቸው ሲሆን፣ ለ738 ቀናት ሲጠብቋቸው ከነበሩት ወዳጆቻቸው አሁን መገናኘት ይችላሉ።
ከመፈታታቸው ከ48 ሰዓታት በኋላ፣ እነዚህ ወጣቶች በአካልም ሆነ በመንፈስ የደረሰባቸውን መናገር ጀምረዋል። ስቃዩን፣ ጠባሳዎቹን፣ እንዲሁም ተስፋቸውን ይናገራሉ።
ረሃቡን፣ ብቸኝነቱን እና ቤታቸው ምንም እንዳልቀረ፣ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ወድማ ሊሆን እንደሚችል የነበረውን ፍርሃት ይገልጻሉ። በእግራቸው ላይ የነበሩትን ሰንሰለቶች፣ ከባልደረቦቻቸው ጋር የተጋሩትን ዳቦ ያስታውሳሉ።
ኤልካና ቦህቦት
ኤልካና ቦህቦት የሆድ ሕመም አለበት። ሐኪሞች እንደሚሉት ይህ የሆነው የሐማስ ታጣቂዎች ከመፍታታቸው በፊት በምግብ ስለሞሉት ነው፤ ወደ ውጭ ሲወጣ የተመጣጠነ ምግብ የጎደለው (የሰሳ) መስሎ እንዲታይ አልፈለጉም። በምትኩ፣ በኖቫ ፌስቲቫል የተጠለፈው የ36 ዓመቱ ኤልካና፣ ከሞላ ጎደል 738 ቀናት በሰንሰለት ታስሮ፣ በዋሻ ስር፣ ያለ ብርሃንና አየር ያሳለፈ ሲሆን፣ የበላውም ጥቂት የፒታ ዳቦ ብቻ ነበር።
ከሆስፒታል ክፍሉ እንዲህ ብሏል፡ "እዚያ ስር፣ የጊዜና የቦታ ግንዛቤ ጠፋብኝ።" ለእሱ ልዩ የሆነ አንድ ወቅት ያስታውሳል፡ የሠርጋቸው ዓመታዊ ክብረ በዓል ነበር። ሚስቱ ሪቭካ ትባላለች። ያንን ቀን ለማክበር ፈልጎ ገላውን እንዲታጠብ ጠባቂውን ጠየቀ። ከዚያ በፊት ተጣጥቦ አያውቅም ነበር። ታጣቂው "ዝም በል" ሲል መለሰለት። ኤልካና ግን ለመጠየቅ ድፍረት አግኝቶ አሳመነው። አሳሪውም ከሰንሰለቱ ፈትቶት፣ ራሱን ተላጭቶ እንዲታጠብ አደረገው።
ዛሬ፣ ኤልካና በእግሩና በጀርባው ላይ በከባድ ሥቃይ ይሰቃያል። የቀድሞው እስረኛ ከትዳር አጋሩ እና ከአምስት ዓመቱ ልጁ ራም ጋር ሊገናኝ ችሏል። ትንሽየው ልጅ በመዋዕለ ሕጻናት ውስጥ አጉሊ መነጽር ሠራ፡ "አባቱ በሄሊኮፕተር እንደሚመለስ ስለተማረ፣ ለወራት ያህል ወደ ሰማይ እየተመለከተ ሲፈልገው ቆይቷል።"
ቤተሰቡ ለመጨረሻ ጊዜ በሕይወት ሲያዩት፣ ሐማስ ባወጣው ቪዲዮ ላይ ነበር። እያለቀሰ፣ ጎንበስ ብሎ፣ እንዲህ ሲል ተማጸነ፡ "እየታፈንኩ ነው። መውጣት እፈልጋለሁ። እባካችሁ እርዱኝ። ቤተሰቦቼ ናፍቀውኛል።"
ማታን አንግረስት
ማታን አንግረስት ያለፉትን አራት ወራት ያህል ያሳለፈው በጣም ጠባብ እና ጨለማ በሆነ ዋሻ ውስጥ ነው። በጋዛ ድንበር በታንክ ታፍኖ የተወሰደው ወታደር እንደ ጋዛ ውስጥ እንዳሉት ብዙዎች ያለ ማደንዘዣ በእጁ ላይ ቀዶ ጥገና እንደተደረገለት ተናግሯል። እናቱ ልጇ ላለፉት 738 ቀናት ስላሳለፋቸው የጨለማ ጊዜያት አንዳንድ ዝርዝሮችን አካፍላለች፡- "ለረጅም ጊዜ ብቻውን ነበር፤ የሰራዊቱ አባል ስለነበር በልዩ ክትትል ስር ነበር።" በአካባቢው ስለሚሆነው ነገር ምንም ዓይነት መረጃ አልነበረውም። "
እስራኤል እንደተወቻቸው፣ አገሪቱን ድል እንደሚያደርጉ እና ቀጣዩን የጥቅምት 7 እቅድ እያወጡ መሆናቸውን ነገሩት። የእስራኤል ጦር ከባድ ቦምቦች ሲጥል፣ አውሮፕላኖች ከላይ ሲበሩ፣ ግድግዳዎች ከጎኑ ሲናዱ እና ከፍርስራሹ የሚወጣውን አቧራ" ያስታውሳል። ከመለቀቁ በፊት በነበሩት ቀናት " ብዙ ምግብ ሰጥተውታል" ብላለች እናቱ።
ማታን ስለ ታፈነበት ዝርዝር ጉዳዮች ቢረሳም፣ ቀድሞ ስለነበረው ውጊያ እና ስለተገደሉት ጓደኞቹ ግን አልረሳም። " የእሳት ብልጭታዎች ይታወሱታል። እጆቹን እንዳቃጠለ እና የአእምሮ ስሜቱን እንዳጣ ያስታውሳል።" ወደ እስራኤል ከተመለሰ በኋላ ታጋቾቹ ስለ ቤተሰቡም እንደዋሹት አወቀ፡ የሆሎኮስት ሰለባ የሆኑት አያቶቹ እንደሞቱ ነግረውት ነበር። በህይወት ማየቱ ከታላላቅ ደስታዎቹ አንዱ ነበር። እናቱ "ከሁሉም ነገር በላይ" ማታን በተለይም በስነ-ልቦናው ረገድ በጣም ደህና ያለ ይመስላል" ብላለች።
ኒምሮድ ኮሄን
አሁን የተናገሩትን መናገር መቻሉ የኒምሮድ ኮሄን ወላጆች ህልም ነበር። አባቱ: "ኒምሮድ አሁንም ኒምሮድ ነው።" የሁለት ዓመት ምርኮ ቀጭንና የገረጣ ቢያደርገውም፣ "የልጄ አነጋገር ተመሳሳይ ነው፣ ስሜቱ ጥሩ ነው። ኒምሮድ ቀደም ሲል የነበረው ልጅ ነው" ይላል የሁዳ ኮሄን። ወጣቱ የቀድሞ ታጋች በሚሊሻው ዋሻዎች ውስጥ ያሳለፋቸውን 738 ቀናት መናገር ጀምሯል። ባለፈው መጋቢት፣ ሁለተኛው የእርቅ ጊዜ ካበቃ በኋላ፣ እስራኤል ሰብአዊ እርዳታን በማገድ ምክንያት፣ ለታራሚዎቹ የሚቀርበው ምግብም በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ኒምሮድ በታሰረበት ጊዜ፣ ከአጋቾቹ ንግግሮች እና ከሬዲዮ ጥቂት የዜና ቁርጥራጮችን ለመስማት ችሏል። እሱ እና ሌሎች ቤተሰቦች ታጋቾቹን ወደ ቤታቸው ለመመለስ "ለሱ እየተዋጋን እንደሆነ ያውቅ ነበር።" የእስራኤል ህዝብ ታራሚዎቹን እንዳልረሳ ያውቅ ነበር። አቶ ኮሄን እጅግ በጣም ደስተኛ ናቸው፤ የልጃቸው መመለስ ቅድሚያ የሚሰጡት ነገር ነበር፣ አሁን ግን ኒምሮድ ቤት ስለገባ የሚያስቡትን በመጨረሻ መናገር ችለዋል፡- "ጦርነቱ በሀገር ደረጃ አላበቃም። የዚህ ጉዳይ ተጠያቂዎች፣ ከሁሉም አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ እንዲለቁ ማረጋገጥ አለብን።" በጥቅምት 7 ቀን 2023 ኒምሮድ በጋዛ ድንበር ላይ በታንክ ተመታ። አራት የጦር ጓዶቹ ከእሱ ጋር ነበሩ፡ ሁሉም በጥቃቱ ሞተዋል።
አቪናታን ኦር
አቪናታን ኦር እንደ ነጻ ሰው ለመጨረሻ ጊዜ ያየው የሴት ጓደኛው በሁለት ሚሊሻዎች አካል ተይዛ በሞተር ሳይክል እየተወሰደች ነበር። ኖአ አርጋማኒ ልቀቀኝ ብላ በመለመን እጆቿን ወደ እሱ ዘረጋች። እስከ ጥቂት ሰዓታት በፊት ሁለቱ በኖቫ ፌስቲቫል በደስታ እየጨፈሩ ነበር። ከዚያም አቪናታን ኖአ ላይ ምን እንደደረሰባት ሳያውቅ ወደ ጋዛ ተወሰደ።
በማዕከላዊ ክፍል ውስጥ ተደብቆ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሁለት ዓመታትን ሙሉ በሙሉ ብቻውን ያሳለፈው ከጥቂቶቹ የቀድሞ ታጋቾች አንዱ ነው። ስልታዊ በሆነ መንገድ እንደተራበ እና ከመጀመሪያው የህክምና ሪፖርት መሠረት ከክብደቱ ከ30% እስከ 40% እንደቀነሰ ተናግሯል። ከተለቀቁት ሃያ ሰዎች መካከል አቪናታን በጣም እየተሰቃየ ይመስል ነበር። ሆኖም ወደ ቤቱ መመለሱን ለማክበር ችሏል። ከዋሻው ውጭ፣ ከእስር ቤቱ ውጭ ምን እየተከናወነ እንዳለ ምንም አያውቅም ነበር። ኖአ በእስራኤል ጦር ወረራ እንደተለቀቀች ምንም ሀሳብ አልነበረውም። "የህይወቴ ፍቅር የሆነውን አቪናታንን ለመጨረሻ ጊዜ ካየሁት ሁለት ዓመታት አልፈዋል። በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ አሸባሪዎች እኔን ጠልፈውኝ፣ ሞተር ሳይክል ላይ አስቀምጠውኝ፣ እና በዓለም ሁሉ ዓይን ፊት ከአቪናታን ለዩኝ" ብላ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፅፋ ነበር።
"እያንዳንዳችን ስፍር ቁጥር የሌለው ጊዜ ሞትን ተጋፍጠናል፣ ሆኖም ከ738 ቀናት መለያየት በኋላ፣ በመጨረሻ በእስራኤል ግዛት ውስጥ እንደገና አብረን ተገናኘን "ብላለች።

የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር በመተባበር የተከሰሱ ሰባት ሰዎችን ገደሉ
ሰኞ እለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለ ቪዲዮ እንደሚያሳየው የሐማስ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር ተባብረዋል የተባሉ ሰባት ሰዎችን በጋዛ እየጎተቱ ሲወስዷቸው ያሳያል።
ከዚያም እንዲንበረከኩ ከተደረጉ በኋላ ከኋላቸው በጥይት ተመተው ተገድለዋል። ቪዲዮው በሮይተርስ የተረጋገጠ ሲሆን ኤጀንሲው ስለ ትክክለኛነቱም ከሐማስ ምንጮች ማረጋገጫ አግኝቷል።
የዜና ምንጩ ግድያው ሰኞ ጥቅምት3 እንደተፈጸመም አረጋግጧል።
በርካታ ምስክሮች (እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚገኙ ቪዲዮዎች) የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚጭኑ መንገዶችን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ የታጠቁ የሐማስ ታጣቂዎችን ያሳያሉ።
የፍልስጤም የጸጥታ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ በቅርብ ቀናት በሐማስ ታጣቂዎች እና በተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት ውስጥ ደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል።

በተራዘመዉ ጦርነት የፍልስጤም ክርስትያኖች 800 ብቻ ቀርተዋል !
ግብፅ በፍልስጤም የወደሙ መሳጂዶችን ዳግም ለመገንባት አዲስ አረብ ሀገራት የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብያ ለማዘጋጀት ቃል መግባቷ ተሰምቷል አብያተክርስቲያናቱን ግን እስካሁን ዳግም ለመስራት አልተገኘም ።
በአንድ ወቅት አለምአቀፋዊው ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን በዓለማች 38 አገሮች ውስጥ ክርስቲያኖች ስቃይና በደል እንዲሁም መገለል እንደሚደርስባቸው ከሰባቱ መካከል አንዱ ስቃይ መከራና ስደት እንደሚዳረግ
በጥናት አረጋግጧል ። ጥናቱ እንደገለፀው ከሆነ ደግሞ ክርስቲያኖች የሚገፉት የእምነቱ መፍለቂያ ከተባለው መካከለኛው ምስራቅ ነዉ ከቀዳሚዎቹ ደግሞ ፍልስጤም ትጠቀሳለች ።
እስኪ ለዛሬው እንደሌሉ ተቆጥረው ልሳን ቸግሯቸዉ በሁለት ጉልበተኞች መሃል ተገኝተው ህልዉናቸዉ አደጋ ላይ ስለሚገኘው የፍልስጤም ክርስትያኖችና አብያተክርስቲያናት ጥቂት ልበል ።
ፍልስጤም በጥንታዊ እና በዘመናዊው የመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሚና ያለው አንድ አነስተኛ ክልል ነው። ለበርካታ የዓለማችን ዋና ዋና እምነቶች ካለው ጠቀሜታ እና በአፍሪካ እና እስያ መካከል ጠቃሚ የሆነ አገናኝ ድልድይ የሆነ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው በመሆኑ የፍልስጤም ታሪክ ተደጋጋሚ በሆነ ፖለቲካዊ ግጭት እና በአደገኛ የመሬት ወረራ የተሞላ ነው።
ይህ ሰርጥ ከግጭቱ በፊት በነበረ ቁጥራዊ መረጃ ከሆነ ሰፊውን ቁጥር የሚይዙት አረቦች ከዚህም ውስጥ በአብዛኛው የሱኒ ሙስሊም ሀይማኖት ተከታይ ቢሆንም ቅሉ ቀላል የማይባል አናሳ ክርስቲያኖች ይገኙበት ነበር።
የጋዛ ክርስቲያኖች ቁጥራቸው እምብዛም ባይሆንም እኒህ የጋዛ ክርስቲያኖች በቤተ-ክርስቲያኑ ዙሪያ ካለው መሬት ጋር ትልቅ ቁርኝት ስላላቸው ከጥንት እስከዛሬ እምነታቸው አስጠብቀው መዝለቅ ችለዉ ነበር ። ነገር ግን ከሁለት አመት በፊት አይ.ሁ..ዳዊ መሰረት ባላት እስራኤልና ከስሙ መነሻ ጀምሮ ለእስልምና እንደሚታገል የሚገልጸው ሃማስ ጦርነቱ ተቀሰቀሰ ።
በሀማስና እስራኤል በተራዘመ ጦርነት ምክንያት በ365 ስኩዌር ኪሎሜትር በ40 ኪሎሜትር የባህር እርዝማኔ ክልል ዉስጥ የምትገኘውን 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይኖሩባታል የተባለችዉን ጋዛ ሰርጥ የምድር ገሀነም ሆነች ሁለቱም ፅንፍ በመያዝ አፀፋ በሚመላለሱበት ወቅት በሁለቱም ዘንድ በሰላይነት የተፈረጁ እነዚህን ክርስትያኖች እና የእምነት ተቋማት ከቁብ የሚቆጥር ጠፋ ።
እስራኤል " የሐማስን መሪዎች ላይ ያነጣጠረ " እያለች በምትፈፅማቸዉ ንፁሃንን ከታጣቂዎች ያለየ ጥቃትና በሰማይ የቦንብ ዶፍም ሆነ ሃማስ ሰላይ ናችሁ በማለት በሚያደርስባቸዉ ማህበራዊ መገለል መፈጠራቸውን እስኪጠሉ መከራ ገጠማቸው ።
በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ እንደሆነ የሚታመነዉ በ400 ዓ.ም አካባቢ በቅዱስ ፖርፊየስ እራሱ ባሰራው ቤተክርስትያን መሰረት ላይ እንደታነፀ የሚነገርለት በአለም ላይ ካሉ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት አንዱ የሆነዉ በአለም ሶስተኛው ጥንታዊ ቤተክርስትያን ወደመ ።
የክርስቶስ የልደት ስፍራ በሆነችው የፍልስጥኤም ግዛት የዌስት ባንክ ከተማ ቤቴልሄም እና በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ክርስቲያኖች የልደቱን በዓል እንዲያከብሩ ተከለከሉ ሌሎችም አብያተክርስቲያናት እንዳልነበሩ ሆኑ ።
ምንድነው ማስረጃዎችህ ከተባልኩ አለምአቀፋዊ ሚዲያዎችን መጥቀስና ዘገባዎችን ማስታወስ ይቻላል ።
ለአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት (ICC) የወንጀል ምርመራ ሪፖርት እንደገለፁት ከአምስት በላይ አብያተ ክርስቲያናት የ150 ዓመታት ታሪክን መዛግብትን ጨምሮ ተጎድተዋል ወይም ወድመዋል። ሲል ገልፆታል ።
በጋዛ የባህል ዘርፍ መጥፋት፣ ቤተመጻሕፍት እና የባህል ቅርሶች በመውደማቸው እንዳስደነገጣቸው ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። "የፍልስጤም ማህበረሰብ መሰረቱ ወደ ፍርስራሽነት እየተቀየረ ነው፣ እናም ታሪካቸው እየጠፋ ነው።" ብለዉታል ።
በአለፉት ሁለት ዓመታት የጋዛ አነስተኛ ክርስቲያኖች መካከል 550 የሚጠጉ ሰዎች ከቤታቸዉ ከቤተክርስቲያን ተፈናቅለው
የመቃብር ሥፍራዎች ለመኖር ተገደዋል. ሲል ፎክስ ኒዉስ ዘግቧል ።
በጋዛ የሚኖሩ ክርስቲያኖች እስራኤል የምትፈፅመው ሞትና ውድመት እንዲያበቃ በመጸለይ የገናን በዓል አክብረዋል። በዌስት ባንክ ከተማ ቤተልሔም የኢየሱስ የትውልድ ቦታ በርካቶች ጸሎታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በእስራኤል “የዘር ማጥፋት” ሰለባዎችን በማስታወስ ፀሎት አድርገዋል። የሚለው ዘገባ የ ዋሽንግተን ፖስት ነዉ ።
በ2024 እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ከሚገኙት ሶስት አብያተ ክርስቲያናትን ሙሉ በሙሉ አፍርሳለች ሲል የግዛቱ ኢንዶውመንት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለአናዶሉ ተናግሯል።
ኢክራሚ አል ሙዳላል እንዳሉት የእስራኤል ጦር ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን 255 የሀይማኖት አባቶች እና መግደሉን እና ሌሎች 26 ሰዎችን ማሰሩን ተናግረዋል። ብሏል የአናዶሉ ዘገባ
" የአምልኮ ቦታዎች ላይ በፀጥታ ሃይሎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ሁሉንም ቅድስናዎች፣አለም አቀፍ ህጎች እና የሰብአዊ መብት ህጎችን መጣስ ነው"ብለዋል።
በአውሮፓውያኑ 2024 ጥቅምት 19 አመሻሽ ገደማ ከእስራኤል የተወነጨፈ ሚሳዔል አንዱን የቤተ-ክርስቲያኑን ሕንፃ መታው። በጥቃቱ 18 ሰዎች ተገደሉ፤ በርካቶች ቆሰሉ።
ማሪያን እንደምትለው የ34 ዓመቱ የባሏ ወንድም ሶሊማን ልጆቹን ከሕንፃው ፍርስራሽ ሲከላከል ሕይወቱ አልፏል።
“በጣም አስፈሪ ነው። የሞተ ሰው አይቼ አላውቅም። ምን ማለት እንዳለበኝ አላውቅም። በጣም ፈጣን ሞት ነበር።”
ራሚ ታራዚ ደግሞ ሕንፃው በሚሳዔል ሲመታ በሥፍራው የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውስ “ከባድ ሚሳዔል ነው። በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በሌላኛው ሕንፃ ውስጥ የነበሩ ሰዎች አቧሯ ለብሰው ነው የወጡት” ይላል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቤተ-ክርስቲያኑ በአቅራቢያው በነበረ የሐማስ ይዞታ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት እንደተጎዳ አምኗል። የቢቢሲ ዘገባ ነበር ።
በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ የተለጠፈ ቪድዮ፣ አንድ የእስራኤል ወታደር የወደቀ ሃይማኖታዊ ሕንፃን በእብራይስጥ ቋንቋ ሲያቆሽሽ አስመልክቷል።
ቢቢሲ ለእስራኤል መከላከያ ይህን ቪድዮ ልኮ አስተያየት ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም።
የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የአርኪዮሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑት ጆርጂያ አንድሪው፣ በጋዛ ሰርጥ ጉዳት የደረሰባቸውን ሕንፃዎች ሲያጠኑ ቆይተዋል።
ፕሮፌሰሯ እኒህ ሃይማኖታዊ ሥፍራዎች በጣም ትልቅ ታሪካዊ ጠቀሜታ አላቸው ይላሉ።
“[ጥቃቱ] ሰዎች ከእነዚህ ሕንፃዎች ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለማጥፋት እንደተደረገ ሙከራ ነው መታየት ያለበት” የሚሉት ምሑሯ መሰል ውድመት አይተው እንደማያውቁ ይናገራሉ።
በአለም ሶስተኛው ጥንታዊ ቤተክርስትያን ነው ተብሎ የሚታሰበው በዉስጡ የያዛቸውን ታሪኮቹ ቅርስና መዛግብቶችን እንደያዘ ወደ አመድነት መቀየሩን ተከትሎም ።
የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችም ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ ያወጡ ሲሆን “የጋዛ ሕዝብ፣ በአያቶቻቸው ምድር ለትውልድ የኖሩ ቤተሰቦች፣ በግዞት መገደድ የለባቸውም፣ የተረፈውን ቤታቸውን፣ ቅርሶቻቸውን፣ እና የማንነታቸው መገለጫ በሆነው ምድር ላይ የመቆየት መብታቸውን ሊነጠቁ አይገባም” ሲሉ መናገራቸውን አልጀዚራ ዘገባ ያሳያል ።
የኢየሩሳሌም አብያተ ክርስቲያናት እንደ ክርስቲያን በጋዛ ሕዝብ ለሚደርስባቸው መከራ ግድየለሾች ሊሆኑ እንደማይችሉ "ወንጌል የሰውን ልጅ ሁሉ ክብር እንድንጠብቅ ያዘናልና።"
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በጋዛ ያለውን ሰብአዊ አደጋ ለመግታት አፋጣኝ እና ቆራጥ እርምጃ እንዲወስዱ ያሳስባሉ።
የሰው ልጅ ሕይወት ቅድስና እና መከላከያ የሌላቸውን የመጠበቅ የሞራል ግዴታ ከጥፋት እና ተስፋ መቁረጥ ይበልጡ። ተስፋ የቆረጡ ሰዎች አፋጣኝ ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ እንጠይቃለን።"ያሉት ኩስቶስ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ፓተን
"ልመናቸውን በእምነት እና በተስፋ መልእክት ሲያጠቃልሉ፣ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሐዘን መጽናናት፣ ለቆሰሉት ፈውስ እና መከራ ቢደርስባቸውም በአገራቸው ለሚቀሩት ጽናትን ለማግኘት እንደሚፀልዩ ተናግረዋል ። በማለት የዘገበው ጀሩሳሌም ፖስት ነበር ።
እነዚህና ምናልባት በዝርዝር ብፅፋቸዉ አንባቢያን እንዳይሰለቹ የተዉኳቸዉ በሁለቱም ወገኖች በሀማስና እስራኤል በተራዘመ ጦርነት ምክንያት በ365 ስኩዌር ኪሎሜትር በ40 ኪሎሜትር የባህር እርዝማኔ ክልል ዉስጥ የምትገኘውን ጋዛ ሰርጥ ይኖሩ በነበሩ ክርስትያኖች ላይ የደረሱ ግፎች ናቸው ። ከዚህ ምስቅልቅል በኋላ ለወትሮው ጥቂት የነበረው የፍልስጤማውያን ክርስትያኖች ቁጥር አሽቆልቁሎ 800 ብቻ ቀርቷል ። እነዚህም የማምለኪያ ስፍራዎች ስለወደሙባቸዉ መቀጠላቸው ያጠራጥራል ሲል ያስነበበው ደግሞ አለምአቀፋዊ የክርስቲያን ህብረት ነዉ ።
( ታዴ የማመይ ልጅ በየኔታ ትዩብ )

ትራምፕ በክኔሴት (የእስራኤል ፓርላማ) የምስጋና ጭብጭባ ተደረገላቸው
ትራምፕ "ለመካከለኛው ምስራቅ ታሪካዊ ጎህ ነው።"
ኔታንያሁ: "ለሰላም ያለኝን ቁርጠኝነት አሳያለሁ ።"
ሐማስ ታጋቾችን በሙሉ ለቋል። ሁለት የክኔሴት አባላት “ፍልስጤምን እውቁ” የሚል ምልክቶችን ይዘው በመነሳታቸው ከክኔሴት አዳራሽ ተባረሩ።
ከ738 ቀናት በኋላ፣ በሐማስ እጅ ውስጥ ምንም በሕይወት ያሉ ታጋቾች የሉም። የመጀመሪያዎቹ ሰባት ሰዎች ዛሬ ጠዋት አንድ ሰዓት ሲለቀቁ፣ ሁለተኛው የ13 ሰዎች ቡድን ከሁለት ሰዓታት በኋላ ነጻ ወጥቷል።
ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ጠዋት በአየር ኃይል አውሮፕላን በታጋቾች አደባባይ ("Hostage ላይ ከበረሩ በኋላ ቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ አርፈዋል። ከዚያም ባለጸጋው ረጅም ንግግራቸውን ለማቅረብ ወደ ክኔሴት አመሩ።
ፕሬዝዳንቱ ተጋቾች ወደ ቤታቸው በመመለስ እና ሰላም በማስፈን ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋና ቀረበላቸው።

የፍልስጤም ፕሬዚዳንት የጋዛን ጦርነት ለማስቆም በግብጽ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ሊካፈሉ ነው
የፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማሃሙድ አባስ ዛሬ ሰኞ፣ በግብጽ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ከዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች የዓለም መሪዎች ጋር በመሆን ሊካፈሉ ነው።
ስብሰባው በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የተግባቡበትን ስምምነት ከፍጻሜ ለማድረስ ያለመ መሆኑን ጽሕፈት ቤታቸው ገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ በስብሰባው ላይ የተጋበዙት በሻራም ኤል ሼክ ከትራምፕ ጋር በመሆን ጉባዔውን የሚመሩት የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ናቸው።
በስብሰባው ላይ የዩኬውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ጨምሮ ከ20 አገራት በላይ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ትራምፕ በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም ያቀረቡት ዕቅድ በአባስ የሚመራው የፍልስጤም አስተዳደር፣ ሪፎርሞች ከተካሄዱ በኋላ ጋዛን በማስተዳደር ሚና ሊኖረው እንደሚችል ይገልጻል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን ይህንን ሃሳብ አይቀበሉትም።
የፍልስጤም አስተዳደር የሐማስ ተቀናቃኝ በሆነው ፋታህ የሚመራ ሲሆን በእስራኤል ወረራ ስር የሚገኘውን ዌስት ባንክ ያስተዳድራል።
የ89 ዓመቱ አባስ ባለፈው ወር ለመንግሥታቱ ድርጅት ስብሰባ ወደ ኒው ዮርክ እንዳይገቡ የእርሳቸው እና የ80 ልዑካን ቡድኖቻቸው ቪዛ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሰረዙ ይታወሳል።
በወቅቱ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት በእስራኤል እና ፍልስጤማውያን መካከል ተግባራዊ በሚሆን የሰላም ዕቅድ ላይ ከዓለም መሪዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረው ነበር።
ሐማስ በወደፊቷ ጋዛ ላይ የሚኖረውን ሚና ውድቅ ያደረጉት አባስ ትጥቁን እንዲፈታ በንግግራቸው ላይ ጠይቀዋል።
የትራምፕ ባለ 20 ነጥብ የሰላም ዕቅድ የመጀመርያ ምዕራፍ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ረቡዕ ዕለት ስምምነት የተደረሰበት ሲሆን ከአርብ ዕለት ጀምሮ የተኩስ አቁም ተጀምሯል፥።
ዛሬ ሰኞ የፍልስጤማውያን እስረኞችን እና እስራኤላውያን ታጋቾች ልውውጥ ይደረጋል።
በሰላም ዕቅዱ ቀጣይ ዙሮች ላይ፣ ጋዛን ማን ያስተዳድራታል፣ የሐማስ ትጥቅ መፍታት እና የእስራኤል ጦር መውጣትን የሚሉትን ጨምሮ ድርድሮች መካሄድ ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እስራኤል እና ሐማስ በግብፁ ስብሰባ ላይ ባለሥልጣኖቻቸው እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል።
በትራምፕ ዕቅድ መሠረት የጋዛ አስተዳደርን ይቆጣጠራል የተባለውን "የሰላም ቦርድ" ይመራሉ ተበሎ የሚጠበቁትን የቀድሞው የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ቶኒ ብሌር እሁድ ዕለት የፍልስጤምን አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሁሴን አል ሼክ አግኝተው አነጋግረዋል።
የሲሲ ቢሮ የሰኞው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ዓላማ "በጋዛ ሰርጥ የሚካሄደውን ጦርነት ማስቆም፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ማጠናከር " መሆኑን ተናግሯል።
የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "በጋዛ ሰርጥ የሚካሄደው ጦርነት እንዲያበቃ የሚቀርበውን ሰነድ" ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
በስብሰባው ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማርኮን፣ የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ 2ኛ፣ የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ጠይብ ኤርዶዋን ይገኛሉ።
የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ስብሰባው ላይ ከሚገኙት መካከል ናቸው።

ሐማስ በሕይወት ያሉ እስራኤላውያን ታጋቾችን በሙሉ ለቀቀ
የእስራኤል መከላከያ በሕይወት ያሉ ታጋቾች በሙሉ መለቀቃቸውን አስታዉቋል።
የእስራኤል ጦር ዛሬ ማለዳ የመጀመርያዎቹን ሰባት ታጋቾች ተረክቦ ቤተሰቦቻቸውን ወደሚያገኙበት ስፍራ እየወሰደ መሆኑን ገልጾ ነበር።
ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተጨማሪ 13 ታጋቾችን ከቀይ መስከል ተረክቦ ወደ እስራኤል እየወሰደ መሆኑን ገልጿል።
ጦሩ ባወጣው መግለጫ ላይ "የእስራኤል ጦር እና ደህንነት ኤጀንሲዎች ተመላሾቹን ወደ እስራኤል አጅበው እያመጧቸው ነው" ብሏል።
ወደ እስራኤል ከተመለሱ በኋላ "የመጀመርያ የሕክምና ምርምራ ይደረግላቸዋል" ያለው መግለጫው፤ በኋላ ላይ ለቀይ መስቀል ተላልፈው የሚሰጡ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመረከብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ሐማስ በበኩሉ በሕይወት ያሉ ሁሉንም ታጋቾች ማስረከቡን የገለፀ ሲሆን፤ የ28 ታጋቾች አስከሬንን በዛሬው ዕለት እንደሚያስረክብ አስታውቋል።
የእስራኤላውያኑ ታጋቾች ቤተሰቦች ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ላይ ናቸው።
የታጋቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች የተሰባሰቡበት 'ሆስቴስ ኤንድ ሚሲንግ ፋሚሊስ ፎረም' በማኅበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ "ወደ አገራችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ" ሲል ለጥፏል።
ETHIO FM

ሐማስ 7,000 የሚጠጉ የጸጥታ ኃይሉን በቅርቡ በእስራኤል ወታደሮች የተለቀቁትን የጋዛ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር በድጋሚ መጥራቱን ከአገር ውስጥ የተገኘ መረጃ አመለከተ።
ቡድኑ ወታደራዊ ልምድ ያላቸውን አምስት አዳዲስ ገዥዎችን ሾሟል። አንዳንዶቹ ቀደም ሲል በታጠቂ ክንፉ ውስጥ ብርጌዶችን ይመሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።
ሀማስ እነዚህን ታጣቂዎች የጠራው የስልክ መልዕክት በመሊክ ሲሆን አንዳንዶቹ ሚሊተሪ የለበሱ ሲሆን ግማሾቹ የሰቪል ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በእስራኤል እና በሀማስ መካከል የተደረሰው ስምምነት እንዳይጣስ ለመቆጣጠር አሜሪካ 200 ወታደሮችን ወደ እስራኤል ልካለች።
seledadotio

ሶማሊያ እና ጅቡቲ የፍልስጤም ነጻ መንግሥት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ
#ethiopia | ሶማሊያ እና ጅቡቲ የጋዛን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የተደረሰውን የተኩስ ማቆም፣ የሰብአዊ አገልግሎት አቅርቦትን እና እስረኞችን ለመፍታት አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ጥረቶችን አድንቀዋል።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አርብ ባወጣው መግለጫ ሉፍልስጤም መብቶች፣ ነፃ ሉዓላዊ ሀገር መመስረት ላይ ያለውን ድጋፉን አረጋግጧል።
ሶማሊያ ይህ ስምምነት የፍልስጤም ህዝቦችን ስቃይ የሚያቆም እና በአካባቢው ፀጥታን እና መረጋጋትን የሚያጠናክር ፍትሃዊ እና ሁሉን አቀፍ ሰላም ለማምጣት እውነተኛ እርምጃ እንደሚሆን ተስፋ ታደርጋለች ብሏል።
የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ በመግለጫቸው የአሜሪካ፣ኳታር፣ግብፅ እና ቱርኪ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል።
በመግለጫቸው "ሰላምን ለማስጠበቅ፣ ሰብአዊ ተደራሽነት እና የሁለት ሀገራት መፍትሄ ለማምጣት ተዓማኒነት ያለው መንገድ እንዲመጣ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር እናሳስባለን" ብለዋል።
የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ሀሙስ ማለዳ በግብፅ ቀይ ባህር ከተማ ሻርም ኤል ሼክ ፣ በኳታር ፣ በግብፅ ፣ በአሜሪካ እና በቱርኪ ሸምጋይነት ተፈርሟል ።
በሴፕቴምበር 29 ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው ባለ 20 ነጥብ የተኩስ አቁም እቅድ የፍልስጤም እስረኞች እንዲፉቱ በአፀፋው ሀሜስ ሁሉንም የእስራኤል ምርኮኞች እንዲለቅ ይጠበቃል። ስምምነቱ የተኩስ አቁምን፣ የሃማስን ትጥቅ ማስፈታት እና ጋዛን እንደገና መገንባትን ያጠቃልላል ያለው ዳጉ ነው።

የእስራኤል መንግሥት የጋዛን የተኩስ አቁም እና የታጋቾች ስምምነትን አጸደቀ
የእስራኤል መንግሥት የተኩስ ማቆም እና ታጋቾችን እና እስረኞችን ወደ መፍታት የሚያመራውን የጋዛ ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ አጽድቋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኤክስ ገጻቸው ላይ "መንግሥት አሁን ሁሉንም ታጋቾች (በሕይወት ያሉትን እና የሞቱትን) የሚፈቱበትን ማዕቀፍ አጽድቋል" ሲሉ ጽፈዋል።
የእስራኤል ጦር 53 በመቶ ጋዛን ወደ ሚቆጣጠርበት መስመር ይወጣል።
ሐማስ በሕይወት ያሉ 20 ታጋቾችን በ72 ሰዓታት ውስጥ መልቀቅ አለበት። በመቀጠልም የሞቱትን የ28 ታጋቾች አስከሬን መመለስ ይጠበቅበታል።
እስራኤል በበኩሏ 2መቶ50 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን የዕድሜ ልክ እስረኞችን እና ከጋዛ የተያዙ አንድ ሺህ 7መቶ እስረኞችን እንደምትለቅ የፍልስጤም ምንጭ ለቢቢሲ ተናግሯል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ የእርዳታ መኪናዎች ምግብ፣ መድኃኒት እና ነዳጅ ይዘው ወደ ጋዛ በመግባት ለሁለት ሚሊዮን ነዋሪዎች እንደሚያደርሱ የመንግሥታቱ ድርጅት ገልጿል። አብዛኛዎቹ በድንኳን ወይም በፍርስራሾች ስር ተጠልለው የሚገኙ ናቸው።
እስራኤል በመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ በየቀኑ 400 የእርዳታ መኪኖች ወደ ጋዛ እንዲገቡ ትፈቅዳለች። ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚሄድ የፍልስጤም ከፍተኛ ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ ጦር ስር የሚመራ እና ወደ 200 የሚጠጉ ኃይሎችን የያዘ ቡድን የጋዛን የተኩስ አቁም ሁኔታ ይቆጣጠራል ሲሉ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
ኃይሉ ከግብጽ፣ ከኳታር፣ ከቱርክ እና ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የተውጣጡ ወታደሮችን እንደሚያካትትም ታውቋል።

እስራኤልና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሲደረግ የቆየው ድርድር በስምምነት ተጠናቋል።
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በተካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ሸምጋዮች ሁለቱ ወገኖች በጋዛ ሰርጥ ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሐሙስ ማለዳ ላይ አስታውቀዋል ሲል ሪወተርስ ዘግቧል።
የተኩስ አቁሙ ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን፤ በ72 ሰዓታት ውስጥ የእስረኞች ልውውጥ እንደሚደረግም ታውቋል።
በስምምነቱ የመጀመርያ ምዕራፍ ከሁለቱም ወገን እስረኞች ይለቀቃሉ ሲሉ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ሃማስ በህይወት ያሉ የእስራኤል 20 እስረኞች በአንድ ጊዜ ይፈታሉ፤ በአምስት አቅጣጫ ወደ ጋዛ ሰርጥ ሰብዓዊ እርዳታን የጫኑ መኪኖች መግባት ይጀምራሉ ተብሏል በስምምነቱ ላይ።
ሃማስን ትጥቅ ማስፈታትና የጋዛ ሰርጥን ማን ያስተዳድር የሚለው ጉዳይ ሁለተኛው የድርድር ምዕራፍ ተደርጓል።
ሁለተኛው ምዕራፍ ድርድር ከመጀመርያው አፈፃፀም በኋላ እንደሚቀጥል አል አረቢያ ዘግቧል።
የሐማስ ተጨማሪ የልዑካን ቡድን ማምሻውን በምክትል ዋና ጸሃፊው እየተመራ ግብፅ ገብቷል።
ልዑካኑ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም በሚደረገው ድርድር ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ

የአሜሪካ ሸምጋዮች የጋዛ ጦርነትን ለማስቆም በግብፅ የሚደረገውን ውይይት መቀላቀላቸዉ ተገለጸ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ዕቅድ ማዉጣታቸዉ ይታወሳል፡፡
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም አላማውን አድርጎ በግብፅ እየተካሔደ በሚገኘው እና ሶስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት ላይ የአሜሪካ ከፍተኛ ልዑካን እና ባለስልጣናት መቀላቀላቸዉ ተገልጿል፡፡
ስቲቭ ዊትኮፍ እና የትራምፕ አማች ያሬድ ኩሽነር፤ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቱርክ የስለላ ሃላፊ ጋር በመሆን ሻርም ኤል ሼክ ይገኛሉ፤ ይህም ዉይይቱ ለዉጥ ማምጣት ይችል እንደሆነ የሚያመላክት ቁልፍ ቀን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
አንድ የሐማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ለቢቢሲ በውይይቱ አስፈላጊው አዎንታዊነት መታየቱን ተናግረው፤ እስራኤል በጋዛ ለተያዙ ታጋቾች ምትክ መፍታት የምትፈልገውን የፍልስጤም እስረኞች ዝርዝር ቀርቧል ብለዋል፡፡
የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣኖቹን ጠቅሰው፤ ጥንቃቄ የተሞላበት ብሩህ ተስፋ አለ ሲሉ ዘግበዋል።
ትራምፕ በበኩላቸው ፤አንድ ነገር ማድረግ የምንችልበት እውነተኛ ዕድል አለ ሲሉ መናገራቸዉን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡
የኳታሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱል ራህማን አልታኒ እና የቱርክ የስለላ ሃላፊ ኢብራሂም ካሊንም ውይይቱን መቀላቀላቸው ነዉ የተገለጸዉ፡፡
የሼክ መሀመድ የመገኘት አላማ፤ የጋዛን የተኩስ አቁም ዕቅድ እና ታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነትን ወደፊት ለማራመድ ነው ሲሉ አንድ ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በበኩላቸው ፤ ትራምፕ፤ ሃማስ ዕቅዳቸውን እንዲቀበል ለማሳመን በቅርቡ በስልክ ባደረጉት ንግግር ጠይቀውት ነበር ማለታቸዉ ተዘግቧል፡፡#ሀና

የአሜሪካ ሸምጋዮች የጋዛ ጦርነትን ለማስቆም በግብፅ የሚደረገውን ውይይት ተቀላቀሉ

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በበኩላቸው ፤ ትራምፕ፤ ሃማስ ዕቅዳቸውን እንዲቀበል ለማሳመን በቅርቡ በስልክ ባደረጉት ንግግር ጠይቀውት ነበር ማለታቸዉ ተዘግቧል፡፡

"ያንን ቀን ማሰብ አንፈልግም" ፍልስጤማዊያን
#ethiopia | መላው አለም ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተው ጦርነት እነሆ ሁለት አመቱን ዛሬ ደፍኗል።
በዛ ቀን ማንም ወደ ፊት ምን ሊመጣ ይችላል ብሎ በቀላሉ የገመተ አንድም ሰው አልነበረም።
የጦርነቱ ትኩሳት ይብዛም ይነስ የሁሉንም ቤት አንኳኩቷል።
በጦርነቱ እሳቱን በለኮሱትም ሆነ በተለኮሰባቸው ወገን ያተረፈም በርካታ ነው።
ግን እንደ ፍልስጤማዊያን እናቶችና ህጻናት በጦርነቱ የተለበለበ አንደም አካል ማግኘት ያዳግታል።
በእስራኤል በኩልም በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ውድ ህይወታቸውን መገበራቸውም ሳይረሳ ማለት ነው።
አነሆ አንደ ቀልድ በአንድ ጀምበር የተጀመረው የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ሁለተኛ አመቱን ትላንት ደፍኗል።
በዚያች ቀን መስከረም 26 2016 ዓ.ም. ሀማስ በከፈተው ጥቃት ከእስር ራኤል በኩል 1ሺህ 200 የሚጠጉ ሰዎች እንዲሞቱ እንዲሁም 251 ያህሉ ደግሞ እንዲታገቱ ምክንያት ሆነ።
ዛሬም ድረስ ወደ ቤታቸው ያልተመለሱ 20 ታጋቾች በሕይወት እንዳሉ እሰራኤላዊያን የሚያምኑ ሲሆን የቀሪዎቹ 28 ሰዎች ደግሞ አስከሬናቸውን መረከብ ይፈልጋሉ።
ሁለት አመት በዘለቀው የሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች ጦርነት ከ66 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ተገለዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 18 ሺህ የሚሆኑት ህጻናት ናቸው።
የተቀሩትም ቢሆኑ የጦርነቱ አላማና የመጨረሻ ግብ የማያውቁ ንጹሀን ዜጎች ናቸው።
አሁን እስራኤልን በአውዳሚ ኃይል ማጥቃት የቻለው ሐማስ ከሁለት ዓመት የማያባራ ወታደራዊ ዘመቻ በኋላ ተሰብሯል።
በፍርስራሾች መካከል የደፈጣ ውጊያ የሚያካሂድ የከተማ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል ሆኗል።
ጦርነቱ በድርድር ለመቋጨት በርካታ ስምምነቶችና ድርድሮች ቢደረጉም አንዳቸውም ውጤት አላመጡ።
ከሁለት አመት በኋላም ቢሆን ውጤታማ ድርድር ለማድረግ አሸማጋዮች ግብጽ ተሰይመዋል።
ካይሮ ሰላም ለናፈቃቸው ዜጎች ጥሩ ዜና ታሰማን ይሆን?
ብዙዎች ተስፋ ሰንቀዋል ፍልስጤማዊያንም የሰላም አየር የሚተነፍሱበት ቀን ናፍቋቸዋል።
ሰላም ለአለማችን ይሁን
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ከስምምነት ለመድረስ 'ጥሩ ዕድል' መኖሩን ትራምፕ ገለጹ
የጋዛን ጦርነት ለማስቆም አሜሪካ ያረቀቀችው የሰላም ዕቅድ በግብፅ ሻርም ኤል-ሸይክ ውይይት እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ቀጥተኛ ያልሆነው ውይይት የሰላም ዕቅዱ የመጨረሻ ስምምነት ላይ እንዲደረስበት ያስችላል ተብሏል።
የግብፅ እና ፍልስጤም አመራሮች ለቢቢሲ እንደገለጹት ውይይቱ እየተካሄደ ያለው እስራኤላውያን ታጋቾች እና ፍልስጤማውያን እስረኞች የሚለቀቁበትን "መንገድ ለማመቻቸት" ነው።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "በቀጣይ ቀናት" ታጋቾች እንደሚለቀቁ ተስፋ አለኝ ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሀውስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ስምምነት ላይ የመድረስ ዕድላችን ሰፊ ነው። ዘላቂ ስምምነትም ይሆናል" ብለዋል።
ሐማስ የሰላም ዕቅዱን በከፊል እንደሚስማማበት ቢገልጽም፤ ትጥቅ መፍታትና በቀጣይ ጋዛን የማስተዳደር ነጥቦች ላይ ከስምምነት አልተደረሰም።
በውይይቱ ሁለተኛ ቀን የግብፅና የካታር አመራሮች ከእስራኤልና ሐማስ ጋር ይወያያሉ።
ትራምፕ እና ኔታንያሁ የተስማሙበት የሰላም ዕቅድ 48 እስራኤላውያን ታጋቾች እንዲለቀቁና ግጭት እንዲቆም ያስችላል። ከታጋቾቹ መካከል 20 የሚሆኑን በሕይወት እንዳሉ ይታመናል።
እስራኤላውያን ታጋቾች ሲለቀቁ እስራኤል በምላሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትለቅ ተገልጿል።
ሁለቱም ወገኖች በሰላም ዕቅዱ ከተስማሙ "በአፋጣኝ ወደ ጋዛ ሰርጥ ሰብአዊ እርዳታ ይገባል" ተብሏል።
ሐማስ ጋዛን በማስተዳደር ሚና እንደማይኖረው የሚገልጸው የሰላም ዕቅዱ፤ በቀጣይ ፍልስጤም እንደ አገር የምትተዳደርበትን በር ይከፍታል።
ኔታንያሁ ግን የፍልስጤምን አገርነት ተቃውመዋል።
ሐማስ የሰላም ዕቅዱ ቅድመ ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ ሁሉንም ታጋቾች እንደሚለቅ አስታውቋል።
የጋዛ ሰርጥ "በገለልተኛ ፖለቲከኞች እንዲመራ" የሚያስችል ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ይህ አስተዳደር በፍልስጤማውያን ብሔራዊ ስምምነት ያለው እና በአረብ አገራት የሚደገፍ መሆኑ ተገልጿል።
ሐማስ የሰላም ዕቅዱን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ትጥቅ ማውረድን በተመለከተ በቀጥታ ያለው ነገር የለም።
ጋዛን ለወደፊት ማን ያስተዳድራታል የሚለውን በሚመለከት "የፍልስጤማውያንን መብት ባስጠበቀ ሁኔታ ብሔራዊ ውይይት እየተካሄደ" እንደሚገኝና ሐማስም የውይይቱ አካል እንደሆነ ገልጿል።
ሐማስ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው በሰላም ዕቅዱ ላይ "ቀይ መስመሮች" በሚል የማይቀበላቸው ነጥቦች በግልጽ አለማስቀመጡ የውጭ ጫና እንደበረታበት ያሳያል ተብሏል።
የአውሮፓና መካከለኛው ምሥራቅ መሪዎች የሰላም ዕቅዱን ይደግፋሉ።
እስራኤል በይዞታ ሥር ያደረገችውን ዌስት ባንክ የሚያስተዳድረው የፍልስጤም አመራር የትራምፕን የሰላም ዕቅድ "እውነተኛና ቆራጥ" ብሎታል።
ሐማስን በዋናነት የምትደግፈው ኢራንም ለሰላም ዕቅዱ ድጋፍ እንዳላት ጠቁማለች።
እስራኤል አሁንም በጋዛ ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው።
የጋዛ ሲቪል መከላከያ ቃል አቀባይ ማሕሙድ ባሲል ለቢቢሲ "ከአራት ሳምንታት ወዲህ እርዳታ የጫኑ መኪኖች ጋዛ እንዳይገቡ ተከልክሏል" ብለዋል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ለመፈናቀል ተገደዋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 21 ፍልስጤማውያን እንደተገደሉና 96 የሚደርሱ እንደተጎዱ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ኖቤል ይገባቸዋል !/ ቴላቪቭ /
የሐማስ ታጣቂዎች በደቡባዊ እስራኤል በኩል ዘልቀው ገብተው ባደረሱት ጥቃት
ቡድኑ አግቶ ወደ ጋዛ የወሰዳቸው 251 እስራኤላውያን ታጋቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች ለኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተከበረውን የኖቤል የሰላም የክብር ሽልማት እንዲሰጥ ደብዳቤ መላካቸው ተሰማ ።
የታጋች ቤተሰቦች ይህን ደብዳቤ የላኩት ትራምፕ በጋዛ ሰብአዊና ቁሳዊ ዉድመት ያስከተለዉን ጦርነት ለማቆም ታጋቾችን ለማስፈታት በአዲስ መልክ የተደረገውን ድርድርና አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ተነሳሽነትን ማሳየታችን ተከትሎ የመጣ ነው።
በደብዳቤው ላይ የትራምፕ የሰላም ሀሳብ የዕለት ተዕለት ጭንቀታቸውንና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን የመመለሳቸው ቀጣይነት ያለውን ተስፋ ያጫረ መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦች ።
በጦርነቱ ወቅት የታፈኑ የእስራኤላውያን ቤተሰቦችን እና የውጭ ሀገር ዜጎችን ለማስፈታት ትራምፕ “ሰላም ለማምጣት ያሳዩትን ቁርጠኝነት” አድንቆ እና አመራሩ “ብዙዎች ፈጽሞ ሊደረጉ የማይችሉትን” እንዲቻል አድርጓል ብሏል።
ደብዳቤው "በመግለጽ ሊገለጽ የማይችል ጨለማን የታገስን ቤተሰቦች የምንወዳቸው በምርኮ ከተያዙት ወገኖቻችን ተለያይተው በየቀኑ በሰቀቀን ስቃይ ሁለት አመታት አሳልፈን ስለዚህ ይህን ደብዳቤ እንጽፍላችኋለን - " ዛሬ፣ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንድትሰጡ ለመማፀን ስንነሳ በጥልቅ አክብሮት እና ባሳለፍናቸው ስሜት በመነሳት ነዉ።
የትራምፕ አስተዳደር 39 ታጋቾች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ በማመቻቸት እና ቤተሰቦች እንዲያገግሙ እና በምርኮ የተገደሉ ዘመዶቻቸውን እንዲቀብሩ በማድረጉ ያመሰገነዉ ደብዳቤዉ። “በማያወላውል ቁርጠኝነት እና ያልተለመደ አመራር ብቃት፣ 39 የቤተሰባችን አባላት ወደ ቤት ተመልሰዋል ” ሲሉ ጽፈው ጥረታቸው የኖቤል ሽልማት እንደሚገባው ጠቁሟል ።
ቤተሰቦቹ በተጨማሪም የትራምፕ ተጽእኖ "ከቤተሰቦቻችን እጅግ የላቀ" መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል, ሽምግልናውን በመጥቀስ. "ከጥር ወር ጀምሮ በአለም ዙሪያ በተከሰቱት በርካታ ግጭቶች ላይ የትራምፕ ውሳኔዎች በተሳካ ሁኔታ አስታራቂ አድርጓል።ሌሎች ብጥብጥ እና የሞት ፍፃሜ ብቻ ባዩበት ጊዜ የሰላም እድሎችን አሳይቷል ። ዲፕሎማቶች የማይቻል ነገር ባዩበት ጊዜ ውጤቱን አስመዝግቧል" ሲል ደብዳቤው ተናግሯል።
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከትራምፕ በላይ “ለአለም አቀፍ ሰላም የበለጠ አስተዋፅዖ ያበረከተ” መሪም ሆነ ድርጅት እንደሌለ ተከራክሯል። “ሌሎች ስለ ሰላም ሲናገሩ እርሱ አደረሰን” ሲሉ ጽፈዋል። "ሌሎች ባዶ ቃል ሲገቡ፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ህይወት የሚታደጉ ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቧል።"
የኖቤል ኮሚቴ መስራች አላማን በመጥቀስ በሀገሮች መካከል ወንድማማችነትን ያዳበሩ እና ሰላምን ያጎናፀፉ እንደ ትራምፕ ያሉ ሰዎችን ማክበር "የተቋሙን ራዕይ ማሳካት " ብለዋል ። ሲል ያስነበበው ጀሩሳሌም ፖስት ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ