19 days ago
በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የተቀናጀ የህፃናት እድገት ማዕከል ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ ።
ኔክሰስ ፎር ኢምፖወርመንት ኤንድ ዴቨሎፕመንት - N4ED ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ያስገነባውን የተቀናጀ የህፃናት ዕድገት ማዕከል ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች እና አጋር ድርጅቶች በተገኙበት በደማቁ አስመርቋል።
የቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮግራም በከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን ይህንኑ ለማጠናከር N4ED ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ማዕከሉን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነ መልኩ ለአገልግሎት ክፍት ያደረገ ሲሆን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚተገበረውን የተቀናጀ የህፃናት ልማት ፕሮግራም በይፋ አስጀምሯል።
ኔክሰስ ፎር ኢምፖወርመንት ኤንድ ዴቨሎፕመንት -N4ED የቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮግራም እና ሴቶችን በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለማብቃት በአዲስ አበባ ፣ በድሬዳዋ ፣ በሀረር እና በመቀሌ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እየሰራ ያለ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡
በምርቃት እና የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የቢሮው ሃላፊ ፣ የሴቶች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ፣ የህጻናት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ፣ የቀዳማዊ ልጅነት ዕድገት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ፣ የህጻናት መብት ደህንነት ድጋፍና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር፣ የፕሮጀክት ዝግጅት እና ሀብት ማሰባሰብ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት መረሀግብሩ ተከናውኗል።

29 days ago
የዋዜማ ኮንሰርት በሀዋሳ
በግዙፉ ግራንድ ያማረች ሪዞርት ላይ ሊካሄድ ነው።
ምሽቱን እና የዓመት መሸጋገሪያው
- ዳዊት ፅጌ
- ሀይሉ አመርጋ
- ዘቢባ ግርማ
- ወንድሙ ጅራ
- ኢትዮጵያ በቀለች
- እና ሌሎችም
ተጣምረው ከፍ ያደርጉታል። ሀዋሳ ውበቷን አጉልታ ታሳያለች።
በሄንከን ሀረር ቢራ አዘጋጅነት የሚዘጋጀው የዋዜማ ኮንሰርት ሀዋሳ ለሀገራች የሙዙቃ ኮንሰርት ኢንዱስትሪ ትልቅ ደረጃ የሚያደርስ እንደሆነ ይጠበቃል ተብሏል።
ለሀዋሳ ሌላ ውበት።

1 month ago
ማስታወቂያ
የምትወዱኝ ላይክም ኮመንትም በጣም ከቻላቹ ሼርም አድርጉልኝ
ገነት ክትፎ በአዲስ መልክ ሀረር ላይ
ቀድሞ ከነበረበት ቦታ በአዲሱ አድራሻ
ቦቴ ከደሳለኝ ሆቴል በታች ወደ ፖሊስ ሆስፒታል መውረጃው ኮብልስቶን መንገድ ላይ እራሷ ባሰራችው ዘመናዊ ህንፃ ላይ ፏ ብልጭ ብሎ አዳዲስ መስተንግዶዎችን ጨምረው ብቅ ብለዋል
ያው ስለክትፎ ጣእም ባዲስ አናወራም
ጥሬው ጥብሱ ... ሁሉ እጃሻቹ ከተሟላ መስተንግዶ ጋር 😍

2 months ago
ዕዳ ቁጭትና እውነት
#ethiopia | ቴአትር ቤቶች በሚጨናነቁበት በዚያ ሰሞን አንድ እለት ብሩክ ግቢ ውስጥ ሆኖ ወደ ውጭ ሲመለከት በአጥር አጮልቀው፣ ተንጠላጥለው ወይም ተንጠራርተው ወደ ውስጥ የሚመለከቱ ሰዎችን ይመለከታል፡፡ ከእነዚህ ሰዎች አንዷ ልታዋራው እንደፈለገች አይነውሃዋን አይቶ የተረዳው ብሩክ ጠጋ ይላል
‹‹ደህና ነሽ! እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››
‹‹ሥራ ፍለጋ መጥቼ ነው ጋሼ!››
‹‹ነይስኪ በበሩ ዙሪና ግቢ፡፡ ሰሞኑን ለትኬት ቆራጭ መደብ ማስታወቂያ እንደወጣ አውቃለሁ፤ ነይ ግቢ እስኪ በበር ዙረሽ›› ይላታል፡፡
ይህች ሰው በተፈቀደላት መሰረት በበር ገብታ ብሩክን ታገኘዋለች፡፡ ወደ መዝናኛ ክበብ ወስዷት ጭውውታቸውን ይቀጥላሉ፡፡
‹‹እና የትኬት ቆራጭነት መደብ ይሆንሻል?››
‹‹እንደ እሱ አይደለም ጋሼ››
‹‹ሥራ ፈላጊ ነኝ አላልሽም እንዴ?››
‹‹አዎ ሥራ እፈልጋለሁ፤ ግን ድምጻዊ መሆን ነው የምፈልገው››
‹‹እውነት?››
‹‹እውነቴን ነው፤ ጥሩ ድምጽ አለኝ፤ አገሬ እያለሁም እዘፍን ነበር››
‹‹የት ነው ሀገርሽ?››
‹‹የሀረር ልጅ ነኝ››
‹‹ስምሽን ማን ልበል?››
‹‹ሀመልማል - ሀመልማል አባተ››
‹‹በጣም ጥሩ ነዋ፡፡ እስኪ ነገ በጠዋት ነይና በመሳሪያ አጅቤ ድምጽሽን እሞክረዋለሁ፡፡ እና እንደሚሆን እናደርጋለን፤ ለማንኛውም ነገ በጠዋት ነይ›› ብሎ ያሰናብታታል፡፡
ብሩክ በነጋታው ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሲያቀና ሀመልማል ገና በማለዳ ደርሳ ኖሮ በር ላይ ቁጭ ብላ ያገኛታል፡፡ ጥበቃው እንዲያስገባት ነግሮ ይዟት ወደ መለማመጃ ክፍል ይሄዳሉ፡፡ በኪቦርድ አጅቧት እንድትዘፍን ያደርጋል፡፡ ጥሩ ድምጽ እንዳላት ተረዳ፡፡
(ዕዳ ቁጭትና እውነት ከሚለው አዲሱ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡ በጃዕፈር መጻሕፍት (ለገሀር) እና በጦቢያ መጻሕፍት (ካዛንችስ) ያገኙታል)

Sponsored by
Surafel
2 months ago
በኢትዮጵያ ካሉ የቱሪስት መስዕቦች ውስጥ የትኛውን ቢጎበኙ ነው ነፍሰና መንፈስዎትን የሚያድሱት ?
- ላሊበላ
- አክሱም
- የጎንደር የፋሲል ግቢ
- ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት
- የሀረር ጀጎል ግንብ
- የጢስ አባይ ፏፏቴ
- የሶፍ ኡመር ዋሻ
ባሕር ዳር በጣና ሀይቅ ዙሪያ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት
-ኡራ ኪዳነምህረት :
-ዳጋ እሰቲፋኖስ :
-ጣና ቂርቆስ
-ናርጋ ስላሴ
ተፈጥሯዊና ብሔራዊ ፓርኮች
ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ
ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ
የኦሞና ማጎ ብሔራዊ ፓርኮች
ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት
አርባ ምንጭ ፖርክ
በአዲስ አበባ ያሉ ሰዉ ሰራሽ ፓርኮች
እንጦጦ ፓርክ፡
አንድነት :ፓርክ
ወዳጁነት : ፓርክ እንዲሁም ከፓርክ ወጭ እንደ ቱሪስት መስዕብ የሚቆጠረው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ናቸው ።
ምርጫዎን በኮመንት ያስቀምጡልን

ለእርስዎ ምቹ ከተማ የቱ ነው ?
ጅማ
ደብረ ብርሃን
ደሴ
ሀረር
አክሱም
ሻሸመኔ
ጎንደር
አሳይታ
ደብረማርቆስ
አርባ ምንጭ
ወላይታ ሰዶ
አሶሳ
እንጅባራ
መቱ
ወልድያ
ሽሬ
አሰላ
ቢሸፍቱ
ሰመራ
ሎግያ
ነቀምት
አስተያየትዎን በኮመንት ይፃፍልን
ጅማ
ደብረ ብርሃን
ደሴ
ሀረር
አክሱም
ሻሸመኔ
ጎንደር
አሳይታ
ደብረማርቆስ
አርባ ምንጭ
ወላይታ ሰዶ
አሶሳ
እንጅባራ
መቱ
ወልድያ
ሽሬ
አሰላ
ቢሸፍቱ
ሰመራ
ሎግያ
ነቀምት
አስተያየትዎን በኮመንት ይፃፍልን
3 months ago
ዛሬ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉሥ የልደት ቀን ነው
#ethiopia | ቁመታቸው ከ1 ሜትር ከ 60 ሴንቲ ሜትር አይበልጥም፣ክብደታቸውም ከ50 ኪግ የሚዘል አይደለም፡፡በጣም አጭር እና ቀጭን ነበሩ፡፡
ግን ግርማ ሞገሳቸው ልዮ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸው 8 ጊዜ ወልደው ከእርሳቸው በስተቀር አላደገላቸውም፡፡በእርግጥ እናታቸው ወይዘሮ የሺእመቤትም በልጅነታቸው ስለሞቱባቸው ያለ እናት፣በአባት ብቻ አድገዋል፡፡
አባታቸው ራስ መኮንን በባዶ እግራቸው በሮም አደባባይ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን የሸመገሉ መሪ ነበሩ።ግርማዊነታቸው ከአባታቸው ዲፕሎማሲን ተምረዋል፡፡በዓለም ላይ ከ 160 በላይ ሀገራትን የጎበኙ እሳቸው ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ አሸናፊነት ሲያከተም፣የሂትለር ባድማ ጀርመን ዓለም ፊቱን አዞረባት፡፡ጀርመን እንደ ሲኦል መንደር ተቆጠረች፡፡ጃንሆይ ግን የተዘጋ በር ከፍተው ጀርመንን ጎብኝተዋል፡፡አስታርቀዋል፡፡አሜሪካ ከጆርጅ ዋሽንግተን እስከ ትራምፕ ድረስ 45 ፕሬዝዳንቶችን ሹማለች፡፡
እነዚህ ፕሬዝዳንቶች በሙሉ አየር ማረፊያ ድረስ ሂደው የሀገር መሪ አይቀበሉም፡፡ጃንሆይን ግን ፕሬዝዳንት ኬኔዲ መንገድ ወጥተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ለጥቁር የነፃነት አውጭ ናቸው፡፡
ኤርትራን ከኢትዮጵያ አዋህደዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከግብፅ ጣልቃገብነት ነፃ አውጥተዋል፡፡የፊውዳሊዝም ሥርዓትን አሻሽለዋል፡፡ስነፁሁፍ እንዲያድግ ነፃነትን ሰጥተዋል፡፡1960 ዎቹ ወርቃማው የስነፁሁፍ ዘመን ነበር፡።
የተፃፈ ህግን፣ ህገመንግስትን ጨምሮ አሰንደዋል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት እስከ ተመድ ድረስ እንዲመሰረት ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
የኒወክርክ ታይምስ ጋዜጣ ጃንሆይን የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ንጉስ አድርጎ ከማውጣቱም ባለፈ፣የኖቤል ሽልማት ሊሸለሙ እያለ በ 1953 ዓም በተነሳው አለመረጋጋት ምክንያት ሽልማቱ አልፏቸዋል ፡፡
የአፍሪካ መስራች ቢሆኑም፣ሀውልት ለጃንሆይ ሳይገነባ ለጋናዊው ክዋሜ ንኩርማህ ብቻ ተገንብቶ ቆይተዋል፡፡በሗላ ከመሸምቢሆን የአፍሪካ ህብረት የጃን ሀውልት በግቢው አቁሟል።
ለነባር ዕውቀት ዕድገት ተግተዋል፡፡
ጃንሆይ ለፈረንጅ የማያጎበድዱ ይልቁንም ጃንሆይ ና ህዝቦቻቸው ለነጭ ንቀት ያላቸው ብቸኛ የዓለማችን ሰዎች ናቸው ይላሉ ፈረንጀች፡፡እንዳውም ፈረንጆች አማርኛ ቋንቋ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፡፡የኢትዮጲያን ባህል እንዲላበሱ ይወተወታሉ።
በእርግጥም ጃንሆይ፣ሀገር በቀል እውቀት እንዲለማ ከጣና ገዳማት እስከ አክሱም ፅዮን ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲታደሱ እና ለታሪክ ምርምር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡
የዓለም ስልጣኔ መነሻው ውሃ እንደሆነ በመረዳት አባይን ከመገደብ ጀምረው ጣናን እስከ ማልማት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ግን በነሩሲያ የፖለቲካ ጫና እና በነጣሊያን ውስጣዊ ሴራ መክኗል፡፡
ለሙስሊም ህብረተሰብ የሀይማኖቱን ምሁራንን ከየአካባቢው በመሰብሰብ ቁርዐንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ታላቅ ድጋፍ እና አስተዋፅዎ አድርገዋል።
ጃንሆይ ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓም በሀረርጌ ኤጀርሳ ጎሮ ተወለዱ፡፡ ሐምሌ 16 የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የልደት በዓላቸው ነው፡፡ራስታዎችም( ጃይማካዎች) የጃንን ልደት ይዘክራሉ።
ደጋፊና ነቃፊዎቻቸው መሳ ለመሳ ቢሄዱም ሟች አይወቀስምና ምንዳው ምንዳው ብቻ ተጻፈ
📸 ተስፋዬ ወልደሚካሄል
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ማዕድ ከማድመቅ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እስከመሆን የዘለቀው ቡናችን
******************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር እና መለያችን የሆነው አረንጓዴው ወርቅ ዛሬ ላይ ከሀገር ውስጥ የፍጆታ ገበያ አልፎ የሀገራችንን ማክሮ ኢኮኖሚ በውጭ ምንዛሬ በመደገፍ ረገድ ታሪካዊ የተባለለትን ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።
ኢትዮጵያ የቡና መገኛ እንደመሆኗ ምርቱ በባሕላችን ውስጥ ጥልቅ ሥር አለው። ሀገራችን በዓመት ከምታመርተው አጠቃላይ የቡና ምርት ውስጥ ግማሽ ያህሉን ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ታውላለች።
ይህን ከፍተኛ የሕዝብ ፍላጎት እያሟላችም በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ በመሆን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ችላለች።
በተለይም በ2018 በጀት ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ ከ600 ሺህ ቶን በላይ ምርት ለዓለም ገበያ በማቅረብ 3.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማስገኘት መቻሏ ታሪካዊ ክንውን ሆኗል።
ይህ የገቢ መጠን በ2014 ዓ.ም ተመዝግቦ ከነበረው 1.4 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ማደጉን ያሳያል።
የዚህ አስደናቂ ስኬት መሠረት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ የፖሊሲ ትኩረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደጋግመው ገልጸዋል።
ሀገራዊ የሪፎርም ሥራው ከመጀመሩ በፊት ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ በዓመት ታገኝ የነበረው ገቢ 700 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ብቻ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት የሰጠው ልዩ ትኩረት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የ'አረቢካ' ቡና ወደ ውጭ በመላክ ሦስተኛዋ ሀገር እንድትሆን እንዳስቻላት አስገንዝበዋል።
አክለውም እያደገ የመጣው የሕዝብ ቁጥር እና የቡና ፍጆታ ምርቱ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዳለው እንደሚያሳይ እና ይህም በዘርፉ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣቱን አስረድተዋል።
ይህ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ስኬት በተከታታይ በተተገበሩ ስር ነቀል መዋቅራዊ ማሻሻያዎች የመጣ ውጤት ነው።
ከእነዚህም ውስጥ ዋነኛው የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር፣ በመሀል ከ40 በመቶ በላይ የቡና ዋጋ ይወስዱ የነበሩ ደላሎችን በማስወገድ አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ወደ ውጭ የሚልክበት "የቀጥታ ግብይት ትስስር" መፈጠሩ ነው።
በዚህም ምክንያት የአርሶ አደሩ የትርፍ ድርሻ ከ40 በመቶ ወደ 80 እና 90 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል።
በተጨማሪም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን በመትከል፣ ያረጁ ዛፎችን በመጎንደል እንዲሁም ከቀረጥ ነፃ በገቡ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት የምርት መጠኑን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል።
በዚህም የይርጋጨፌ፣ የሲዳማ፣ የሀረር፣ የጂማ እና የሌሎችም አካባቢዎች መለያ የሆነው አረንጓዴው ወርቃችን ታሪካዊውን የውጭ ምንዛሬ ግብ ማሳካት ችሏል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ይህንን ስኬት ያስመዘገበችው ተፈጥሮን ሳይጎዳ፣ ከደን ጋር በተዋሃደ የጥላ ሥር የቡና እርሻ ሥርዓት (Shade-grown coffee) መሆኑ፣ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ለአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪነቷን በማሳየት ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ አኩሪ ገጽታዋ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #ethiopiancoffee #macroeconomy #coffeeexport #greenlegacy

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ያወጣው አዲስ የምርመራ ሪፖርት፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አስተዳደር እና በጀት አጠቃቀም ላይ የፈጸመውን ከባድ ኃላፊነት የጎደለው አሰራር እርቃኑን አውጥቶታል። ሚኒስቴሩ ሀገራዊ የኮንትራት አስተዳደር ማንዋል ማዘጋጀት ባለመቻሉ፣ የሀገሪቱ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃን እንዳያሟሉ እና ለከፍተኛ ብልሽት እንዲዳረጉ ማድረጉ በኦዲት ግኝቱ ተጋልጧል።
የሪፖርቱ አንኳር እና አሳሳቢ ግኝት የሚያተኩረው በእግር ኳስ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ነው። በሀገሪቱ ውስጥ ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ እና ከፊፋ እውቅና ያገኙት አደይ አበባ እና ሀላባ ስታዲየሞች ብቻ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የክልል ስታዲየሞች ግን ዝቅተኛውን የካፍ እና የፊፋ ቴክኒካል መስፈርት እንኳ ማሟላት አልቻሉም። በአንጻሩ እንደ ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያሉት ነባር እና ግዙፍ መሰረተ ልማቶች በደካማ የጥገና ስርዓት ምክንያት በውሃ እና በአፈር መሸርሸር እየፈረሱ ይገኛሉ። የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ላለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት አንድም ጊዜ ስብሰባ አለማድረጉ ደግሞ፣ የተቋሙን አስተዳደራዊ ሞት እና የስፖርት ፖሊሲው ከጥቅም ውጪ መሆን በግልጽ ያሳያል።
የሚኒስቴሩን ድክመት ይበልጥ አሳሳቢየሚያደርገው ደግሞ አስገራሚው የበጀት አጠቃቀም ቅራኔ ነው። ተቋሙ በበጀት እጥረት እና በዋጋ ግሽበት ምክንያት በባህር ዳር፣ ሀረር፣ ሰመራ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚገኙ የስታዲየም ግንባታዎች መጓተታቸውን እንደ ምክንያት ሲያቀርብ ቢቆይም፤ በተግባር ግን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከተመደበለት የካፒታል በጀት ውስጥ 3.08 ቢሊዮን ብር (44.3 በመቶውን) ስራ ላይ ሳያውል በካዝና አስቀምጦት ተገኝቷል። በቢሊዮን የሚቆጠር በጀት እያለው ስታዲየሞች እንዲፈርሱ እና ግንባታዎች እንዲጓተቱ መፍቀዱ፣ ተቋሙ በሀገሪቱ የስፖርት ዕድገት ላይ የፈጸመውን ታሪካዊ በደል የሚያረጋግጥ ነው ሲል ሪፖርቱ አጥብቆ ኮንኖታል።

የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-
✅ ከጠዋቱ 4፡00-ቀኑ 9፡30
👉 ሜክስኮ፣ ብሔራዊ ፣ ሰንጋተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ ኩባ ፓርክ፣ ተ/ሃይማኖት፣ በርበሬ በረንዳ፣ ዲአፍሪካ እና አካባቢያቸው ፣
✅ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡00
👉ጎፋ ካምፕ፣ ጀርመን አደባባይ፣መከኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ላፍቶ፣ ቄራ፣ቆሼ፣ ዘነበወርቅ፣ጎፋ እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00-10፡30
👉ሸገር ዳቦ፣ ኤሞሌስ ፋብሪካ፣ ለገ ጣፎ ከተማ ፣ የካሰዴ፣የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም፣ወሰን ግሮሰሪ፣ ሲኤምሲ ሚካኤል፣ ካራሎ፣ለገጣፎ፣ ሲዲሲ ፣ ኮሰሮ፣ ለገዳዲ፣ ሰንዳፋ፣ 44 ማዞሪያ፣ ሲሬ ጎዩ፣ የካ ሰዴ፣ድሬ ሰኩር እና አካባቢያቸው፣
👉 ጁኒፐር ግላስ፣ ደጋ ውሃ፣ ቻንግልዶንግራን፣ ፊበላ፣ ቦልት ማልት፣ ሃዋ ትሬዲንግ፣ ብራውን ፉድ ፣ ማማ ዱኬት ፋብሪካዎች እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከለሊቱ 6፡00-ቀኑ 6፡00
👉 ድሬደዋ ውሃ፣ ፓይነር ሲሚንቶ፣ ቱሬ ሲሚንቶ፣ ሀረር ውሃ፣ ማረሚያ፣ ኩርቱ፣ በለዋ፣ ቃልቻ፣ ቢሻን በሄ፣ ሃሎብሳ፣ ለጎዳ፣ አሳሊሶ፣ ኢንዱስትሪ ኮንዶሚኒየም፣ ሻሎም ኢንጂነሪንግ፣ መልካ፣የኢንዱስትሪ እና አካባቢያቸው፣
✅ ከጠዋቱ 1፡30-5፡00
👉አዳማ ከወንጂ ቀበሌ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋት 12፡00-12፡00
👉በአሰላ፣ አዳሚቱሉ፣ ቡታጅራ፣ ወራቤ እና አካባቢው
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ውድ ደንበኞቻችን፤ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Seledadotio

5 months ago
በምዕራብ ሀረርጌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ
#fastmereja I በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጡሎ ወረዳ "ቀራ ፋርሾ" ተብሎ በሚጠራው ልዩ ቦታ ዛሬ ረፋድ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።
አደጋው የተከሰተው ከባጃጅ ጋር በተጋጨ የጭነት መኪና (ኮንቴይነር) ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የጭነት መኪናው ከባጃጇ ጋር በፈጠረው ግጭት፣ በሰው ህይወት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት መድረሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሀረር አንዲት እናት አምስት ልጆችን ተገላገሉ
በሐረሪ ክልል በሐረር ከተማ አንዲት የ35 ዓመት እናት አራት ወንድ እና አንድ ሴት በድምሩ አምስት ሕፃናትን (Quintuplets) በሰላም መገላገሏ ተገለጸ።
ወይዘሮ በድሪያ አደም የተባሉት እነዚህ እናት፣ ዛሬ ምሽት 3፡30 አካባቢ በሐረር ሕይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች በሰጡት ድጋፍ ሕፃናቱን በሰላም ሊያገኙ ችለዋል።
እናትየው በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቂሌ ቀበሌ "ገንደ አህመድ" ተብሎ በሚጠራው መንደር ነዋሪ ሲሆኑ፤ ትዳር መሥርተው በቆዩባቸው 12 ዓመታት ውስጥ ልጅ የመውለድ ፍላጎታቸው ሳይሳካ መቆየቱ ተገልጿል።
ይሁንና አሁን ላይ በአንድ ጊዜ የአምስት ሕፃናት እናት ለመሆን በቅተዋል።
የሕክምና ባለሙያዎቹ እንደገለጹት ከሆነ፣ በአሁኑ ወቅት አምስቱም ሕፃናት (4 ወንድ እና 1 ሴት) በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
ሕፃናቱ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በማሞቂያ ክፍል (Incubator) ውስጥ እንደሚገኙም ታውቋል።
ይህ ልዩ ክስተት በሆስፒታሉ ባለሙያዎችና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ሲሆን፣ እናትየውም በሰላም መገላገላቸው ተረጋግጧል።
seledadotio

የሀረሩ ጃፓን!
የአገር ኩራት!
ያንዳንድ ሰው እድል ደሞ ይገርማል፡፡
የሀረሩ ጃፓን እንድል አሰኝቶኛል፡፡
ይህ የእውቁ ቢሊየነር የሮክፌለር መነሻ፤ መናገሻ ነው ኢስት ክሊቭላንድ ከተማ።
ሰውየው ደግሞ እስኪገርመኝ የነካኸው ይስፋ የተባለለት አይነት ነው።
“የአንዳንድ ሰው እድል ደግሞ ጉደኛ ነው፣” ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል።
ግራ ቢገባኝ ነው የሀረሩ #ጃፓን ማለቴ።
በአሜሪካ አገር ከፊት ከሚቆሙ በጣት የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ባለሃብቶች አንዱ ነው፡፡
የአለም ቀን መጀመሪያ የምስራቁ ክፍል መነሻ አገር ጥንቁቅ ወግ እና ባህል ለሚረዱ ነገሩ ይገባል፡፡
የጃፓኖች አመጋገብ ሆነ የምግብ ዝግጅት የተለየ ግምት የሚወስድ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።
ለዚህም ነው በጃፓን ምግብ ስራ ለመሰማራት እንኳን ሌላ ጃፓናዊ እራሱ ሁለት ሶስቴ ማሰብ ይጠበቅበታል የሚባለው፡፡
ቢዝነስ እና ድፍረት ግን ያወጣል! እንዲል መርሁ
በምስራቅ አፍሪካ ከምስራቋ ታሪካዊ ከተማ ሀረር የፈለቀው ሰው ወደዚህ ቢዝነስ ሲገባ ውሳኔው የቢዝነስ ድፍረት ነበር፡፡
ጀመረው፤ እናም ብዙዎች ይሆንልኛል ብለው የማያስቡትን የጃፓን ጣእም አመጣው!
ተሳካለት!
የምወደውን ምግብ ለመመገብ ከባልደረቦቼ ጋር ጃፓን ሬስቶራንት ሄድኩኝ አለ ጨዋታው ሲነሳ፡፡
በምኖርበት ክሊቭላንድ ከተማ ወደሚገኝ የጃፓን ቴርያኪ ሬስቶራንት አቀናሁ የተመኘሁትን ለማግኘት ግን እንዳሰብኩት አልቀናኝም ይላል ለማ ጌታቸው፡፡
“ምግብ ልበላ ሄጄ ወረፋ አላስደርስ አለኝ፡፡ ያኔ ወሰንኩ።” የሚለው የተለያዩ ግዙፍ ቢዝነሶች ባለቤት፤ አስቦት በማያውቀው ነገር ግን ገንዘብ እንደሚያመጣ ቀልቡ በነገረው የምግብ ቢዝነስ ለዛውም ትልቅ ግምት በሚሰጠው የጃፓን ማእድ ስራ ሊሰማራ ወሰነ፡፡
እውነቱን ነው!
የሞላ ገበያ መገለጫዋ በሆነችው አገረ አሜሪካ ‘የምን ወረፋ ነው? የምን እጥረት?’
ቀልቡ ነገረው፡፡ እሱም አመነው፡፡ “ቢዝነሱ ተጨማሪ ዘዋሪ ይፈልጋል፣” ሲል ወሰነ በቀዝቃዛማዋ ኦሃዮ ግዛት የሞቀ የንግድ ህይወት የሚዘውረው ለማ፡፡
ቀልጣፋው የሃረር ልጅ ዘየደ። አንድ ወዳጁ ጋር ደወለ።
“ስማ ወዳጄ የፈጀውን ይፍጅ እስቲ ሁነኛ የጃፓን ሼፍ ፈልግልኝ፣” አለ፡፡ ተገኘ፡፡
መኖር ደጉ ጨላውን አወጣ! በሮክፌለር የቢዝነስ መነሻ ሰፈር፤ ኢስት ክሊቭላንድ ሬስቶራንቱ የሚከፈትበትን ቦታ ገዛው፡፡
አቦ ይመቸው!
ቢዝነሱ ተጀመረ። ተከፈተ፡፡ ተሳካ! መሳካት ብቻ አይደለም ሞቀ። በቅርንጫፎች ሰፋ፤ ደመቀ።
እንደ መደበኛ ተመጋቢ ምናልባት በወራት አንዴ ይሄድ እንደሆን እንጂ ዛሬ ቢዝነሱ እሱን አይፈልግም፡፡ ጥሩ ገንዘብ ግን ያመጣል፡፡
“ተመጋቢዎች ለምን እንዳማረን ይቅር?” በሚል የተጀመረው ቢዝነስ ዛሬ የካናዳ ድንበር በምትጋራው የኦሃዮ ክሊቭ ላንድ እና ኮሎምበስ ከተሞች ስራው ሞቋል፡፡
በሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጫና፤ የራስ ሰው በማጣት እና በአንዳንድ አካባቢዎች የስራ ቦታ አመቺነት ችግር ቢዝነሱ እጅግ ማደግ የሚችልበትን እድል አልተጠቀምም እንጂ በጣም ሊሰፋ ይችል ነበር ይላል ለማ፡፡
ስለ እትዮጵያ ዲያስፖራ እንዲህ አለ፡፡ “እኛ ትንሽ ነን፡፡ የሆነ 10 ሺ ኢትዮጵያዊ ባለበት ከተማ ለምን መቶ የሀበሻ ምግብ ቤት ትከፍታለህ? ሁሉም ላይሰሩ ነው፡፡ ማን ውጤታማ ሊሆን ነው? ስንት ሰው በአንድ የሀበሻ ምግብ ቤት ሊመገብ ነው?” ሲል ይጠይቃል ለማ፡፡
“ሀበሾች መንቃት አለባቸው እርስ በእር ከመነጣጠቅ ይልቅ በርካታ ተመጋቢ ባለባቸው የሌላ አገር የሬስቶራንት ቢዝነሶች ጭምር ስለመሰማራት ማሰብ ይኖርባቸዋል፣” ሲል ሃሳቡን ያጋራል፡፡
ይህ ከለማ በርካታ ተስፈንጣሪ የቢዝነስ መገለጫዎጭ መካከል አንዱ ብቻ ነው፡፡
በርግጥ ሰውየው ብዙ ስራ አለው፡፡ ይህ የጃፓን ቴርያኪ ምግብ አቅራቢ እሱ ከደረሰበት የሀብት ማማ አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው፡፡ የትርፍ ጊዜ ስራ (ሆቢ እንደማለት)፡፡
የብዙ ክህሎት ባለቤት!
በግዛቱ አለ የተባለ የሪል እስቴት ኢንቨስተር ነው ለማ፡፡
በኦሀዮ ክሊቭላንድ እና ኮሎምበስ ከተሞች የሚያከራያቸው በርከታ የንግድ ህንፃ እና ቦታዎች አሉት፡፡
የተለያዩ ቢዝነሶች ጀምሮ ያሳካ፡፡
ለስደተኛ አይታለፍ የሚባሉ መከራዎችን የተሻገረ ጀግና፡፡
አይደለም ተወልዶ ላደገባት ኢትዮጵያ የህዝብ ወገን እና ደራሽ ነው ለማ በሰሜን አሜሪካ፡፡
ሀረር ከተማ አደሬ ጢቆ ነው ተወልዶ ያደገው፡፡
ጨዋታ አዋቂ፣ ወሬ የሚያምርለት፣ ተዝናንቶ የሚያዝናና ነው ይሉታል፡፡
ያደገበትን ያካባቢውን ወግ አልረሳም፡፡ ወደ አገሩ ሲመጣ አብሮ አደግ የሀረር ልጆችን ይዞ ይዞራል፡፡
ወርቃማ የህይወቱን ክፍል ውጭ ነው ያሳለፈው ከማለት ይልቅ እዛው ሀረር ነው የሚኖረው ያስብላል ነገረ ስራው፡፡
ቸርነቱስ ቢባል አሉ። ሰውየው በዚህ ጉዳይ ብዙ መናገር ባይፈቅድም እጁ የደረሰበት ልቡ ያውቀዋል።
መጪው ትውልድ ላይ ደግሞ ወጥሮ መስራት ነው መርሁ፡፡ ትምህርት ላይ ያምናል፡፡
የአገር ኩራት!
ኢትዮጵያውያኖች በደረሳችሁበት ይሁንላችሁ!
መሉቀን የወንደወሰን
ከአሜሪካ
#harar #ጃፓን #ሀረር #teriyaki #clevelandohio #cleveland #teriyaki_express #lemmagetachew #lemma_getachew #ohio #japanesefood #ጃፓን #ethiopianfood #ethiopia #realestate #addisababarealestate #clevelandclinic #clevelandclinicabudhabi #clevelandsddisview #addisview #harar #japan #teriyaki #cleveland #ohio #success #business #diaspora #realestate #entrepreneur #ethiopian #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
1.9 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ኃይሌ ሆቴል በደብረብርሃን ከተማ ተመርቆ ስራ ጀመረ
የሀይሌ ሆቴሎች ከ16 ዓመታት በፊት ጅማሮውን ያረገ ሲሆን 11ኛ ሪዞርቱን በደብረብርሃን በዛሬው እለት አስመርቋል።
ከአዲስ አበባ በ130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የአማራ ብሔራዊ ክልል ውስጥ በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ላይ የተገነባው ይህ ሆቴል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አቶ መካሻ አለማየሁ እና የከተማዋ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ተገኝተዋል።
ደብረ ብርሃን ከተማ በታሪክ የምትታወቅ እና አዲስ የኢኮኖሚ ማዕከል እየሆነች የመጣች ከተማ መሆናን የተናገረው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ከተማዋ ኢንዱስትሪን ተገን በማድረግ ኢንቨስትመንትን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሻገረች ትገኛለች ሲል ገልጿል።
ኃይሌ ሆቴል ደብረብርሃን 123 አልጋዎች ያሉት ሲሆን ከ200 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ተወላጆች የስራ እድል ፈጥራል።
ኃይሌ ሆቴሎች ባለፉት ሁለት ዓመታት በወላይታ ሶዶ እና ጅማ ከተሞች ያስገነባቸውን አዳዲስ ሆቴሎች አስመርቆ ወደስራ ያስገባ ሲሆን በሻሸመኔም ጉዳት የደረሰበትን ሪዞርት ዳግም ወደስራ አስገብቷል።
ቀጣይም የሀይሌ ሆቴሎች በድሬደዋ ፣ ሀረር እና ወደሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እንደሚሻገርም ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ምስረታውን አካሄደ
#ethiopia |የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽ ላለፉት ስድስት አመታት በተለያዩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በአሶሴሽን ደረጃ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ በምስረታው ወቅት ተነግሯል።
በዚህም አሁን ላይ ፌዴሬሽን ለመሆን የሚያስችል ሙሉ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
ግሎባል ቴኳንዶ በአለም አቀፍ ደረጃ ከኢንተርናሽናል ቴኳንዶ እና ወርልድ ቴኳንዶ ጋር በእኩል ደረጃ ተቀባይነት ያለው እንደሆነ ይታወቃል።
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ጊዜያት የሴቶችን የግሎባል ቴኳንዶ ስፖርታዊ ተሳትፎ የማስፋፋት ስራዎችን እንደሚሰራ ታውቋል።
በዚህም ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን እንዲመሩ፦
1. ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሐመድ መኪ-ፕሬዚዳንት
2. አቶ ፉዓድ አብደላ- ም/ፕሬዚዳንት
3. ወ/ሪት ፂዮን ግርማ- አቃቢንዋይ፣
4. አቶ ካሳሁን ድሪባ- የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ
5. ወ/ሮ ዝናሽ ገ/መስቀል-የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ
6. ወ/ሮ ፎዚያ አወል- የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ እና
7. አቶ ጀማል ንጉስ-የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተመርጧል።
እንዲሁም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በጉባዔው የክብር አባል በመሆን መመረጥ ችለዋል።
በፕሮግራሙ ፌዴሽኑ ያደራጁ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የምስጋና ሽልማት አበርክቷል።
ፌዴሬሽኑ የምስረታ ጠቅላላ ጉባዔውን ያደረገው በሀረር ከተማ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በዛሬው እለት በይፋ ተመስርቷል።
የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽ ላለፉት ስድስት አመታት በተለያዩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በአሶሴሽን ደረጃ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ በምስረታው ወቅት ተነግሯል።
በዚህም አሁን ላይ ፌዴሬሽን ለመሆን የሚያስችል ሙሉ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
ግሎባል ቴኳንዶ በአለም አቀፍ ደረጃ ከኢንተርናሽናል ቴኳንዶ እና ወርልድ ቴኳንዶ ጋር በእኩል ደረጃ ተቀባይነት ያለው እንደሆነ ይታወቃል።
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ጊዜያት የሴቶችን የግሎባል ቴኳንዶ ስፖርታዊ ተሳትፎ የማስፋፋት ስራዎችን እንደሚሰራ ታውቋል።
ፌዴሬሽኑ የምስረታ ጠቅላላ ጉባዔውን ያደረገው በሀረር ከተማ ነው።
በዚህም ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን እንዲመሩ፦
1. ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሐመድ መኪ-ፕሬዚዳንትንት
2. አቶ ፉዓድ አብደላ- ም/ፕሬዚዳንት
3. ወ/ሪት ፂዮን ግርማ- አቃቢንዋይ፣
4. አቶ ካሳሁን ድሪባ- የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ
5. ወ/ሮ ዝናሽ ገ/መስቀል-የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ
6. ወ/ሮ ፎዚያ አወል- የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ እና
7. አቶ ጀማል ንጉስ-የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ በመሆን ተመርጧል።
በዛሬው መርሀግብር ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በጉባዔው የክብር አባል በመሆን መመረጥ ችለዋል።

የሹዋሊድ በዓል
በፍቅር ከተማ ሐረር
#ethiopia | ለዘመናት በኩራት ለዘለቀውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የሹዋሊድ በዓል ተከብሯል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እንደተናገሩት የሐረሪ ሕዝብ ካሉት በርካታ ድንቅ ባህላዊ እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል።
ሹዋሊድ ከረመዳን ጾም መጠናቀቅ በኋላ የሚከበር የደስታ፣ የፍቅር እና የማኅበራዊ ትስስር መገለጫ ነው።
ሚኒስትሯ በዓሉ ኢትዮጵያ ያላትን ጥንታዊ ሥልጣኔና ለዓለም ያበረከተችውን ድንቅ የባህል ሀብት በኩራት ያስታወሰ ነውም ሲሉ ተናግረዋል።
የሹዋሊድ በዓል ለቱሪዝም ዘርፋችን ትልቅ አቅም ይዞ የመጣ ብርቅዬ ሀብታችን ነው።
በታሪካዊቷ የሐረር ጀጎል ግንብ ውስጥ የተከበረው ይህ ደማቅ በዓል፣ በባህላዊ ጭፈራዎች፣ ውብ በሆኑ አልባሳትና የሐረሪ ሕዝብ የእንግዳ ተቀባይነት ሥነ-ሥርዓቶች የታጀበ በመሆኑ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ የሳበ ነበር።
የቱሪዝም ሚኒስትር ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ ቅርስ ለዓለም በማስተዋወቅ፣ ሐረርን ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
በመጨረሻም፣ ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ ታላቅ ቅርስ የመጠበቅ፣ የመንከባከብና ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት የሁላችንም ነው።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በኩላቸው
የሸዋሊድ በአል ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ የኢትዮዽያዊነትና የጋራ ማንነታችንን በሚያጎላ መልኩ በታላቅ ድምቀት እንዲከበር አድርገናል ብለዋል።
ይህ በመሆኑም በርካቶች የሚታደሙበት የሰላም የፍቅርና የአብሮነት አውድማ እየሆነ መጥቷል።
ሁለቱም ስራዎቻችን በቱሪዝም ዘርፉ የተሰናሰሉ እና በሀረሪ ክልል ፈጣን የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ ሀረርን ወደ ቀድሞው ክብሯና ገናና ታሪኳ መልሰናል ሲሉም ገልጸዋል።
የዘንድሮ የሹዋሊድ በዓል የጎዳና ላይ ሩጫ በማድረግ ተጠናቋል።
በዚህም የ'ቪዚት ሐረር' የጎዳና ላይ ሩጫ በታሪካዊቷ ፈረስ መጋላ ተደርጓል"::
የሹዋሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ "ቪዚት ሐረር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና መነሻና መድረሻውን ታሪካዊው ፈረስ መጋላ ላይ ያደረገው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ፌስቲቫል፤ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ አትሌቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#getutemesgen

7 months ago
ምንልክ ያችን ሰዓት
(ጋሻው ደበበ አለሙ)
▫️መነሻ ሀሳብ -ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ
▫️አርትኦት- አሰግደው ሽመልስ
የካቲት 23/ 1888 ማለዳ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምዬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ያረጉት ፀሎት
ስብሐት ለእግዚአብሔር- ኅያው በመንበሩ
ሰላም ለዛቲ -ሃገሪትነ ቅድስት
ወሰላም ለህዝብየ- ዘይሔሉ ለምድሩ
ዘይመውት -ለክብሩ ፡፡
ምስጋና ለሕያው አግዚአብሔር
ሰላም ለዚህች -አንድ ቅድስት አገር
ሰላም ለደጉ ህዝቤ-አፈሬን ብሎ ለሚኖር
ክብር ላንተ-ሰማዕቱ የእናት የአባቴ ታቦት
ጊዮርጊስ መመኪያዬ-እንግዴህ ከፊቴ ዝመት
መንገድ ጥረግ ፈረሰኛው -ቀዳማዊው ሰራዊት
ተማርኩ ያለ አገር ሊዘርፍ-ውል አዛንፎ በለበጣ
የነገር ፈሩን ስንጨብጥ -ለሴራው ብልሐት ሲያጣ
ለጦር ልቡ ሸፍቶ -ዳር ድንበር ጥሶ ከመጣ
ፈርሐ-እግዜር የሌለው ጣሊያን -ህዝቤን በጅምላ ሲወር
በህዝቤ ተደምስሶ -አደዋ አረህ ውስጥ ሲቀር
በሟጥሽ ስር ተበትኖ -በአጋም ስራስር ሲሰባበር
እለቱ በደም ታፍኖ-ሰልስቱን በአሞራ ሲያከብር
ኪደነ-ምህረት ገሰሶ-ምንድብድብ ሸዊቶ ሜዳ
እማርክ ብሎ የመጣ -ሞቱ በአፍታ ቢረዳ
እኔ ክፉ እማይደለሁ -ልቤን ቅር እንዳይለው ነገር
መቼም ነፍሰ-እግዚሃር ነውና…
ክብር ለሃያሉ አምላክ -ቃሌን ቀድሜ ልናገር ፡፡
ቴወድሮስ ይሙት! ቃሌ ነው!!
እኔ ምኒልህ …
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
መልህቅ ቢያነሳ ብዬ እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡
እንዴት አይነት ጥጋብ ነው ? እንዴት አይነት መወፍነን?
ምኒልክን ለባርነት- ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት
አሳብ ጠንስሶ መጅመንመን?
እንዴት አይነት ንቀት ነው -ምን የሚሉት ሰማይ ማከክ?
ጣሊያን ሱሪ የለበሰው ሐበሻን ለማንበርከክ?
......
አዬ ያገሬ ጀግና
አንጀተ ፅኑው ገበሬ
በማርያም መማፀኔን -ያገር አዋጄን ሰምቶ
ከመናገሻ እስከ ሀረር በጌምድር ተጠራርቶ
የአራት ማዕዘን -ጀግና ድፍን ኢትዮጵያ ተነስቶ
በሮቹን ባለህ ባይ ሳይኖር -ዝሪቱን ለተባይ ትቶ
ወንጭፉን ከማማ ሰቅሎ -ጦርና ጋሻ አንግቶ
ምኒልህ ጠራኝ ብሎ -በጭብጦ ተሸኝቶ
በእፍኝ ጥሬ-ከቤት ወጥቶ
ላመል ታህል በኮዳ ውሃ-ከምንጭ በቅል ጠጥቶ
ለእግሩ ከለላ ሳይኖረው -አሜኮላውን ጥሶ
ጫካውን በግር በፈረስ -ዥው አርጎት እንደኮሶ
ላገር ሟቹ ቃል ጠባቂው ይሔው አደዋ ከተመ
ለነፃነቱ እልፍ ሆኖ -ለክብሩ በአንድ ተመመ
የአብሮነት ቃልኪዳኑን -በባንዲራው ስም አተመ፡፡
እና ከዚህ በላይ -ምን ደስታ አለ?
ከህዝብና ከክብሩ- ሰው ካገሩ ከዋለ
እምነትና ጀብዱን ታጥቆ -አገሩን ብሎ ለመጣ ሰው
እስከ አፅናፍ የሚነገር -ድል ነው ፀዲቅ የሚቆርሰው፡፡
እንደ ቤተ-መቅደሱ -እንደ ሞገሩ ሽታ
እንደ ነጋሪቱ ድምፅ -መለከትና እምቢልታ
ተመስገን ያባቴ አምላክ -ልቤ ሃሴት ተሞልቷል
ሰማዕቱ በእለተ ቀንህ -ክንዴ እልፍ ጦር አንግቷል
ህዝቤ -አፎቱን ከፍቷል
ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ- አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው- ክንዴን ገበየሁን አደራ::
ክብር ለአያቶቼ
ኢትዮጵያን ከነ-ስሟ -ከነ ክብሯ ላኖሯት
ጣሊያን ጉድጓዱ ይገባል -ዛሬም ማንም አይደፍራት።
የካሳ እልፍኝ ይታዘበኝ -ጦር ሰልጥኜ ያደኩበት
ልበ-ባህሩ ሸዋ -አባ መቻል-አባ መስጠት
ስም አልጠራም አባባ ብዬ -አይወልደኝም ሀይለመለኮት
እኔ ዳኘው ምኒልህ -ወገኔን ካሳፈርኩት !!
በቀዳማዊ ምኒልክ -በሳህለ ሥላሴ መንፈስ
በአያቴ ወንበር ዘውድ ስጭን -በጥንቶቹ አልጋ ስነግስ
እንዴት ተብሎ ቃል ቢዛነፍ-ጫፏ ይነካል አገሬ
አፍር ይሆናል እንጂ-ጠላት ይገባል መረሬ!!
እውነት ኪዳነ-ምህረት -በቀንሽ ቅጠል ሳልበጥስ
ዳዊት ከደጅሽ ደግሜ -ፀበል ጠጥቼ ሳልሰልስ
ቆመ-ብዕሴሽን ታሽቼ-ገራገራሽን ተሳልሜ
የኖርኩት የከበርኩት -ባንች እማዶለ አለሜ !
ፈገግተዋ የሚያጠግበኝ-የመኖር ውሃ ሙላቴ
እንግዲህ አንቺ ከልያት-ከፊት ቀድማለች ጣይቴ ፡፡
አሔሔ!
ኢትዮጵያዊነት ሥሙ -ሀይሉ ካድማስ የሚርቀው
የወገኔ እንኳን ጦሩ-ድምጡ ጠላት የሚንደው
ከወረይሉ እስከ ሶሎዳ - እየፎከረ የተመመው
እምቢ ብሎ እንደመጣ -የድል ጀንበር ሊያሳልፍ ነው፡፡
እንግዴህ ይህ ነው ፀሎቴ ...
ይህ ቀን -ታላቅ ነውና -
የኢትዮጵያ ሐያልነት በአደባባይ ይወሳ
ወራሪ አጥንቱ ደቆ- ከደሃ ላይ እጁን ያንሳ
አንበሳ አንበሳ ነውና- እንደትላንቱ ዛሬም ያግሳ
ጥቁርና የጥቁር ምድር- አንገቱ ቀና ይበል
የሐበሻን ጠንካራ ክንድ -አውሮጳም አምኖ ይቀበል ።
እኔ ምኒልህ
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
ልቦና ቢገዛ ብየ-እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡
ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ -አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው ክንዴን ገበየሁን አደራ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ሳባዊያን ፣ መቼቱን በአዲስ አበባ እና በሀረር ከተማ ላይ ያደረገው በታሪክ አወቃቀር እና በተዋንያን ብቃት የታጀበ በከፍተኛ ወጪ የተሰራው በሄኖክ ረዳኢ ( የአልማዝ ልጅ ) እና በቢንያም ጆን ኦቶ ተፅፎ በሳዶፍ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ የቀረበው > የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከየካቲት 30 ጀምሮ ዘውትር ሰኞ ምሽት 3 ሰዓት ላይ በETV ENTERTAINMENT ቻናል መተላለፍ ይጀምራል ።
ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ
በ 0912082673 ወይም በ 091 197 1964 ይደውሉልን።
>
ሳዶፍ ፊልም ፕሮዳክሽን
ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ
በ 0912082673 ወይም በ 091 197 1964 ይደውሉልን።
>
ሳዶፍ ፊልም ፕሮዳክሽን
8 months ago
በሂርና ከተማ በጅብ ላይ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ የህክምና ወጪውን እንዲሸፍን ተደረገ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሂርና ከተማ አስተዳደር ሀዬታ ቀበሌ ውስጥ ከጫካ የወጣ ጅብ በሰው ተመቶ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን የፖሊስ ፅ/ቤት አስታውቋል።ጉዳት የደረሰበት ጅብ የህክምና እርዳታ አግኝቶ ወደጫካው መመለሱ ተገልጿል።
የሂርና ከተማ መደሀዮታ ቀበሌ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ሬድዋን ኢብራሂም ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ጅቡ ከጫካ የወጣው ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ሲሆን አንድ ግለሰብ ቤት አካባቢ ሲጮህ የቤቱ ባለቤት ጅቡን ለማባረር በወረወረው ድንጋይ ጅቡ በሁለት እግሮቹ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል ።
ጅቡ ጉዳት ሲደርስበት በአካባቢው ፖሊስ እና ባህላዊ ፍርድቤት ግቢ ገብቶ ጥቅልል ብሎ በመተኛት የደረሰበትን ጉዳት በጩኸት ሲገልጽ እንደነበረ ተጠቁሟል ።የጅቡን ጩኸት የተመለከቱ የፖሊስ አባላትም ግቢያቸው የገባውን የጫካ ጅብ ከማባረር እና ከመጉዳት ይልቅ ምግብ እና ውሃ በመስጠት አሳድረውታል።
በነጋታውም ለጅቡ የሚያስፈልገውን በመስጠት ጉዳቱን እንዲታከም የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሞያ እና ሀኪም አፈላልገው በማሳከም ለሶስት ቀናት ካሳከሙት በኋላ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መጣበት ጫካ በሰላም ሸኝተውታል።
ፖሊስ ከጫካ የወጣውን ጅብ ላይ ጉዳት ያደረሰውን ግለሰብ ተከታትሎ በመያዝ የህክምናውን ወጭ እንዲሸፍን ያደረጉ ሲሆን የሶስት ቀን የምግብ ወጭውንም ፖሊሶች ስጋ በመግዛት አገግሞ ወደ ጫካው እንዲመለስ ማድረጋቸውን ኢንስፔክተር ሬድዋን ኢብራሄም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

በዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ የተጻፈው "ፍካሬ ትኩረት" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | በዲጂታል ዘመን የሰው ልጅ ትኩረትና ማንነት ላይ የሚያጠነጥነው የዶክተር አብዲበሺር ሰኢድ "ፍካሬ ትኩረት " የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አንጋፋው አርቲስት ሥዩም ተፈራ፣ የኢትዮጵያ ሠዓሊያን እና ቀራፂያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አርቲስት አክሊሉ መንግሥቱን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ምሁራንና የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል።
"ፍካሬ ትኩረት" የዲጂታል ዘመን ልማት፣ማንነት፣ እና ኃያልነት መበየኛ መጽሐፍ በአሁኑ ዘመን እንደ ትልቅ የገቢ ምንጭ የሚቆጠር ሀብት መሆኑን መጽሐፉ ከዓለም አቀፍ እውነታ ጋር እያመሳከረ ይተነትናል።
መጽሐፉ በዲጂታል መሣሪያዎችና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት የሚሰረቀውን የሰው ልጅ አእምሯዊ ንቃት እንዴት መመለስ እንደሚቻል የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያመላክታል።
✅ በዲጂታል ዘመን ውስጥ የማንነትን ጥያቄ በጥልቀት የሚዳስስ
✅ ለሀገራዊ ልማት አዳዲስ አቀራረቦችን የሚያቀርብ
✅ በትምህርት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያለውን ልምድ የሚያንጸባርቅ
✅ ለወጣቱ ትውልድ መሪ ሐሳብና ተግባራዊ መንገድ የሚያበረታታ መሆኑን ሒሳዊ ዳሰሳ ያቀረቡ ምሁራን እና ተወያዮች ገልጸዋል።
ዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ እና ጂኦግራፊ ትምህርት፤ የመጀመረያ ድግሪ የማስተርስ ድግሪ፤ በቱሪዝም እና ልማት ጥናት ከታላቁና አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በተጨማሪም ፣ ከሕንዱ ሀገር አቀፍ የኢንተርፔነርሺፕ ልማት ተቋም የድሕረ-ማስተርስ የዓለም አቀፍ የኢንተርፕሬነር የአሰልጣኞች ስልጠና አግኝተዋል።
በተጨማሪም ከኬኒያው ሞይ ዩኒቨርሲቲ በድሕረ ማስተርስ የቱሪዝም አስተዳደር ስልጠና ፣ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ ምረቃ ዲፕሎማ በከፍተኛ ትምህርት የማስተማር ሥነ ዘዴ ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን ፣
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ፣የቱሪዝም፣ የእንተርፕሬነርሺፕ እና የድኅነት ቅነሳ ተመራማሪ ፣በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊና ሰብዓዊ ልማት ጥናቶች ኃላፊ ፣በታላቁ የአል-ነጃሺ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት የቅርስና ቱሪዝም አመራር ጥናቶችን ሠርቷል።
በቱሪዝም፣ በኢንተርፕሬነርሺፕ፣ በምጣኔ ሀብት ዘርፎች የተለያዩ ጥናቶችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተመ
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሕንድ እና ሌሎች ሀገሮች ውስጥ የጥናት ምርምሮችንና የስልጠና ፕሮግራሞችን ያቀረበ ነው።
ከዚህ ቀደም ሲል የሴቶችን ትውልድ የማነጽ ሚና የሚዳስሰውንና በሦስት ቋንቋዎች(በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ) የታተመውን "Architects of The Ummah" የተሰኘ መጽሐፍ ከጓደኞቹ ጋር ለንባብ አብቅቷል።
በ7 ምዕራፎች ተቀንብቦ በ107 ገጾች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፣ በአሁኑ ወቅት በ320 ብር ለገበያ ቀርቧል። መጽሐፉ በተለይ በቴክኖሎጂ ተጽዕኖ ውስጥ ለሚገኘው ወጣት ትውልድና ለምሁራን ትልቅ ግንዛቤን እንደሚሰጥ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ከረመዳን ጾም በኃላ በሀረር የመጽሐፍ ምረቃና የፊርማ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።
#ethiopia #fikretukret #digitalage #identity #newbook #focus #mentalawareness #drabdibeshir #literature #addisababa #booklaunch #attentioneconomy

ምንነቱ ካልታወቀ ግብዓት ጋር ተቀላቅሎ የተዘጋጀ እንጀራ ለገበያ ሊያውሉ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ቃሉ
በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ጂኔላ ወረዳ በልዩ ስሙ ሚካኤል ሰፈር በተባለ አካባቢ ምንነቱ ካልታወቀ ግብዓት ጋር በመቀላቀል ለመጋገር የተዘጋጀ ሊጥ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ምክትል ዳሬክተር ኮማንደር አብዲ ቶፊቅ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ከማህበረሰቡ ለፖሊስ በደረሰዉ ጥቆማ መሰረት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ወደ ቦታዉ በማምራት ለመጋገር የተዘጋጁ ሊጦች እጅ ከፍንጅ መያዝ መቻሉን ሀላፊው ገልፀዋል።
ምንነቱ ያልታወቀ ባእድ ጋር ተቀላቅሎ በቁጥጥር ስር የዋለው የእንጀራ ሊጥ ናሙና ምርመራ ወደ ኢትዮጵያ የምግብ እና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ተልኳል። የእንጀራ ሊጡ የሚዘጋጅበት ቦታ እጅግ ንፅህና የጎደለው እና ለጤና አደገኛ በሆነ ቦታ በመሆኑ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ባገኘው ጥቆማ ወዲያው በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።
ማህበረሰቡ ለፖሊስ የሰጠዉን ጥቆማ ምስጋና አቅርበዉ ድርጊቱን በፈፀሙ 2 ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደር አብዲ ቶፊክ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

9 months ago
ይድረስ የጎንደርን ጥምቀት ለተቻችኹ ኹሉ!
============================
ሃይማኖት ባህል እንዲሆን እንሥራ
ባህል ግን ሃይማኖት እንዳይኾን እንጠንቀቅ
አድፋጭኢዝም የዘመናችን ፈተና!!!
ጎንደር ላይ ተጨፈረ ብላችኹ እርግማን ቀረሽ ጥራዝ ነጠቅ ሂስ ስታስወነጭፉ ተመለከትን። ወቀሳውን በሁለት ከፍለን እንመልከተው። አንደኛው ወገን ከመልካም ዕሳቤ፣ ከበጎነት፣ ለሃይማኖት ከመቆርቆር ይመነጫል። መነሻ እውነት አላቸው። መዳረሻቸውን ግን ጎጠኞች፣ ጨለምተኞች፣ ቂመኞች ጠልፈውታል ብዬ አምናለሁ። ሁለተኛው ወገን ጎንደርን እና የጎንደርን ምእመናን ለማሸማቀቅ፣ ሊቃውንት የሏትም ለማሰኘት፣ ወንጌል አልተሰበከም ለማስባል፣ በሃይማኖት እና በሀገር ጭምብል ውስጥ ተወሽቀው ጎንደርን እና ኦርቶዶክሳውያንን ለማርከስ ምቹ ጊዜ ሲያደቡ የነበሩ አድፋጭ ጎጠኞች እና ወለፈንዲዎች ናቸው።
ከአሁን በፊት በዕውቀት ማነስ ምክንያት "ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያ አይባልም" ብለው ለጎንደር ሊቃውንት ስልጠና ሲሰጡ የተተቹ፣ ከመድረክ ተዋርደው የወረዱ ሰበብ ፈልገው ቂም መወጣጫ ሲያደርጉ ሳይ አፈርኩ። ምክንያቱም እነሱ ተወልደንበታል ያሉበትን ቀዬ አንድም ቀን ባህላዊ ክዋኔውን ተችተው የማያውቁ ለጎንደር ሲኾን ብዕራቸውን ከአፎቱ መዘዙ፤ አፍረናል፤ ስህተት ጎጥ፣ ቀለም፣ ውፍረት እና እጥረት የላትም። የትም ቦታ ትሠራለች። በሚዛን ትከረከማለች፤ ኑረው ኑረው ከስካሩ እንደ ነቃ ሠካራም የጎንደር ሲኾን መንጋጋን ማላቀቅ ምን ይባላል? ቅናት ነው መልሱ።
ነገረ ጉዳዩን ከጎንደር እናውጣውም..... አናውጣውም
1. ቤተክርስቲያኗ ይኽ ድርጊት ዶግማዬ ነው አላለችም። ቀኖናዬ ነው ብላ አልተናገረችም። ትውፊቴ ነው ብላም አላወጀችም። ጉዳዩ የተፈጸመውም ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አይደለም። እናማ ቤተክርስቲያኗን እና ሊቃውንቷን፤ መምህራኖቿን እና ምእመናን በዚኽ ልክ መቀጥቀጥ የፍትሕ ሚዛኑን ያጎድለዋል።
2. ይኽ ነገር ጎንደር ላይ ሲደረግ የመጀመሪያ ነው ወይስ የመጨረሻ? ክንውኑ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል። በዘመናዊውም በባህላዊውም። እየጠበበም እየሠፋም እዚኽ ደርሷል። ቦታውን እየቀያየረ አንዴ በቁምጣ፣ አንዴ በካሽሚር፣ ሌላ ጊዜ በጅንስ፣ እልፍ ሲል በዱላ፣ ዘለል ሲል በጎፈሬ ብቻ ዘመን ተቆጥሯል። ይኽ ከኾነ ጉዳዩ የዘንድሮውን ወቀሳ ምን አመጣው ሲባል፣ የመጀመሪያው የሕዝቡ መብዛት፣ ሲቀጥል የሚዲያ ሽፋን በማግኘቱ፣ ሢሰልስ መሐል ከተማ ላይ መኾኑ፣ አራተኛ የጎንደርን ማበብ፣ መድመቅ፣ መፍካት፣ መጉላት፣ መግነን የማይወዱ ቀን ጠባቂዎች አንዱ ጅል በለኮሰላቸው መረባረባቸው፤ ይኼ ነው ምክንያታቸው። እንጅማ በዚህ ሁለት ዓመት የጀመረ ይመስል ጎንደርን እና ኦርቶዶክሳውያንን መቀጥቀጥ ተገቢ አልነበረም።
3. ጎንደርን እና ኦርቶዶክሳውያንን እንደ መስዋዕት በግ
ፖለቲካውን መተቸት መብትህ ነው። ከፖለቲከኞች ጋርም መወቃቀስ ትችላለህ። አይመለከተኝም። በሀገር እና በሃይማኖት ስም ተደብቀህ ግን የጎንደሬዎችን እና የኦርቶዶክሳውያንን በዘመን የሸመገለ ስብእና እና ማንነት ግን ማንቆሸሽ አትችልም። ሁሉንም በሜዳው ግጠም። ለይተህ ተከራከር፣ ነጥለህ ሞግት፤ እደግመዋለሁ እኔ ፖለቲከኛ ስላልኾንኩ አይመለከተኝም። ያንን ጨዋ ሕዝብ ርኩስ፣ ራስኽን ቅዱስ አድርገኽ
ለተቀሪው ዓለም ልታሳይ ስትሞክር ግን በሰለጠነ መንገድ በገባኝ መጠን በቃል እና በመጣፍ እሞግትሃለው።
4. መርጦ ማልቀስ፤ ምን ማለት መሰለህ ኹሉም ቤት የተከሠተው ኅዘን እኩል ኾኖ ፊት እና ወንፊት እያዬህ እንባን ማንዠርዠር ማለት ነው። ወሎ ሻደይ፣ ትግራይ አሸንዳ፣ ጎጃም ጭፈራ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ኦሮሚያ፣ ሀረር፣ ድሬ፣ ቤንሻንጉል የትኛው የኢትዮጵያ ክልል ነው ጎንደር ላይ የኾነው አይነት የሌለው? ወይም ያልተደረገው? ንገረኛ? የጎንደሩ ከሌላው የሚለዬው የሊቃውንት ሐገር መኾኑ እንዳትለኝ?! ሊቃውንቱኮ አልጨፈሩም ወዳጄ፤ ጎንደር የሃይማኖት ሀገር ስለኾነ ነው? ሌሎቹ ሃይማኖት የላቸውም እያልከኝ ነው? እንዳትሳሳት፤ ኦርቶዶክሳውያን የሌሉበት የኢትዮጵያ ክልል የለም። የቁጥር መብዛት እና ማነስ ብቻ ነው። ጎንደር ላይ ግን በኢጎ የሚሰቃዬው እና ፀረ ኦርቶዶክሱ እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ ዘመቱ። ደስ የሚለው አልተሳካም አይሳካም።
በመጨረሻም እኘዚኽ ሰዎች ቁስል ባለበት አሉ። ነገረ ሥራቸው የዝንብ ነው። ወደ አበባ አይመለከቱም። ወደ ስብራት ነው የሚሮጡት። የጎንደርን ጥምቀት መልካም ጎን ለመጻፍ ብዕራቸው ደልዱም ነው። አንደበታቸው ዲዳ ነው። ምክንያቱም እነሱ ከእውነት ጋር ሳይኾን ያሉት። ከመምረጥ ጋር ነው። በተለይ ጀግና ናቸው የሚያስብላቸው ከኾነ፤ እነርሱ ኮ አይፈሩም ከተባለላቸው፤ እነሱ ኮ የቤተክርስቲያን ጠበቃ ናቸው ከተባሉ ኹሌም የሚታያቸው ስህተት ነው። 99% ደጉን ነገር ገደል ከትተው፣ በ1% ሲያላዝኑ፣ ሲወቅሱ፣ ሲከስሡ፣ ሲሳደቡ፣ ሲያንቋሽሹ ይውላሉ። ትችት፣ ስድብ፣ ማንቋሸሽ፣ ማሳነስ፣ ማራከሥ መተዳደሪያቸው ነው። ሌላ content (ይዘት ) የላቸውም። መተዳደሪያቸው ነው - አብዛኞቹ።
5. ለቅን ኦርቶዶክሳውያን ብቻ ይኽን እላለኹ፤
እናንተ ከቅንነት ነው። ለሃይማኖታችኹ ካላችኹ ቀናኢነት ነው። ለቤተክርስቲያናችኹ ከመቆርቆር የተነሣ ነው። ይኽንን እረዳለኹ። ነገር ግን እናንተ በቅንነት የጀመራችኹትን ዐሳብ እና አስተያዬት ኦርቶዶክሳውያንን፣ ጎንደርን እና የጎንደር ምእመናን ለመሳደብ ክፋታቸውን በልባቸው አዝለው ቀን ሲጠብቁ ለነበሩ መጠቀሚያ ኾናችኋል። የእናንተን ቅንነት ቅንቅን ኾነው በጥልቀት እየሠሩ ነውና፤ ኹሌም ለመተቸት እና ለመውቀስ ስንነሣ ከእኛ አስተያዬት ጀርባ እነማን ሊጠቀሙበት ይችላሉ ብላችኹ ጠይቁ፤
intension፣attention and tension የሚሉት ነገሮች ኹሌም ወቀሳ፣ ትችት፣ ሂስ፣ ስድብ ወዘተረፈ ከመስጠታችን በፊት ልናስብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።
በዚያ ጉዳይ ላይ ዐሳብ የሚሰጡ ሰዎችን ማንነት መመርመር መልካም ነው። የጀርባ ፍላጎት፣ በነገረ ጉዳዩ ላይ ያለቸውን ዕውቀት፣ ተገቢ ልምድ፣ የኋላ ታሪክ መፈተሽ ተገቢ ነው። ከዚያ እኛ ከሠርገኛ ጤፍ መሳይ ዐሳቦች መሐል የሚጠቅመንን መርጠን መውሰድ ያስፈልጋል።
6. በነገረ ጉዳዩ ላይ ግን እንደ ጎንደር ብቻ ሳይኾን እንደ ሀገር መነጋገር፣ መወያዬት፣ መከራከር ዐሳብ መለዋወጥ ይቻላል። ባዕዱን እያረምን፣ ማዕዱን ማቅናት ይቻላል። እኔ የምጠላው ነጥሎ መጣልን ነው፤ እኔ የምንቀው ለይቶ ማጥቃትን ነው፣ እኔ የምጸየፈው በዕውቀት የሚደረግን ፍጥጫን ሳይኾን የጩኽት ስድብን ነው። እኔ የማልወደው ዝንቡን እመታለኹ ብለኽ ግንባሩን ገንድሶ መጣልን ነው።በጨዋ ቅጥ እንወያይበት። እንደ ሀገር መፍትሔ እንፈልግበት። አለቀ። አንድን ሃይማኖት፣ አንድ ሕዝብ፣ ምእመናን ለማዋረድ የሚደረገውን ዘመቻ ግን ማንም ቆሞ አያይም።
7. እነደ ሀገር አንተ፣ አንች፣እኔ፣ እኛ ከሃይማኖታዊ ክዋኔዎች ጎን ለጎን የሚደረገውን እንደጎንደሩ ዐይነት ድርጊት እንዳይፈጸም የሠራነውን አዎንታዊ ተግባር እንጥቀስ እስቲ አለ? ቤተክርስቲያን እና ክርስቲያኖች ባሉበት በሁሉም ማኅበረሰብ ዘንድ የተቃወምነው፤ ተቃውመነው ያስተካከልነው፣ ጀምረን የጨረስነው አለ? በተነሣው ርእሰ ጉዳይ ላይ እኔ ይኽን ሠርቼ ይኽን አሳክቻለሁ እንበል እስቲ? ካለ ጻፉ። ከሌለ እንደ ሀገር ይሠራበት እንጅ ጎንደርን እና የጎንደርን ምእመናን እንዲኹም እንግዶቿን ለይቶ ማጥቃት ዋጋ እንደሚያስከፍል እንወቅ
ስንጠቀልለው ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ከባህል፣ በዓልን ከትውፊት፣ ዶግማን ከቀኖና እየለየን እና ጠንቅቀን እያወቅን ስህተቶች ሲታዩ ማሳጣት፣ ማጋነን ልታይ ልታይ በሌለበት መንፈስ፤ በሚያጸና እና በሚያቀና ፍኖት እየተጓዝን ወደ ፊት እንድንጓዝ እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን።
ሃይማኖት ባህል እንዲሆን እንሥራ
ባህል ግን ሃይማኖት እንዳይኾን እንጠንቀቅ!!!
የማርያምወርቅ ተሻገር (መ/ር)

በምስራቅ ሀረርጌ የባሏን ገዳይ በምህረት ከእስር በመውጣቱ ምክንያት ከቤተሰቦቿ ጋር በመተባበር ያስገደለችው ግለሰብ እና ግብረ አበሮቿ በጽኑ እስራት ተቀጡ
በ2014 ዓ.ም ያዩ ሀሰን እና አልዩ ሀሰን የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች (የአይሻ አጎት ልጆች) የአይሻን ባለቤት በስለት ወግተው ገድለውት ነበር። በወቅቱ በነበረው የፍርድ ሂደት ያዩ ሀሰን ጥፋተኛ ተብሎ ሲታሰር፣ ወንድሙ አልዩ ሀሰን ግን በነጻ ተለቆ ነበር።
ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ቀዳሚው ገዳይ ያዩ ሀሰን በምህረት ከእስር ይፈታል። በዚህ የተበሳጨችው የሟች ሚስት አይሻ አህመድ፣ ከቤተሰቦቿ (አህመድ እዩ፣ አፈንዲ ጀማል እና መሃመድ አልዩ) ጋር በመሆን ሴራ ጎነጎነች።
ግለሰቦቹ እንደ ገጀራ እና ሜንጫ ያሉ ስለታም መሳሪያዎችን በመያዝ፣ ከእስር የተፈታውን ያዩ ሀሰንን እና ቀድሞ በነጻ ተለቆ የነበረውን ወንድሙን አልዩ ሀሰንን በመደብደብ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል።
የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አህመድ አዪ እና አፈንዲ ጀማልን
በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣አይሻ አህመድ (አስተባባሪ) እና መሀመድ አልዩን እያንዳንዳቸው በ20 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጥቷል።

አዋሽ ባንክ ታሪካዊ የሆነውን 1000ኛ ቅርንጫፉን አስመረቀ
===========
በግል ባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ በመሆን በአምስት ቅርንጫፎች ስራ የጀመረው አዋሽባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሰ ጎሮ ከተማ1000ኛ ቅርንጫፉን የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራውን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና እንግዶችበተገኙበት በይፋ አስመርቋል።አዋሽ
ባንክ በመላ አገሪቱ ቅርንጫፎቹን በማስፋፋት ህብረተሰቡ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችንበአቅራቢያው እንዲያገኝ በማስቻል በአሁን ወቅት የደንበኞቹን ብዛት ከ16.3 ሚሊዮን በላይ አድርሷል፡፡ በተጨማሪም ለአገሪቱ የኢኮኖሚዕድገት እና ለሕብረተሰቡ የኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው የበኩሉን አስተዋፅኦ በመወጣት ላይእንደሚገኝ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡ ባንኩ ከመ
ደኛው የባንክ አገልግሎት ሰጪ ቅርንጫፎች በተጨማሪ ደንበኞችን ማዕከልባደረጉ ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎትና በዲጂታል ቅርንጫፎች (e-Branch) በመታገዝ ዘመኑን የዋጁ ቀልጣፋ አገልግሎቶችን እየሰጠይገኛል።
አዋሽ ባንክ የጃርሶ ቅርንጫፍን ከመክፈት በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሀገር ብዙ ውለታ የዋሉ የሀገር ባለውለታዎች ላፈራው ለጃርሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግምታቸው በብር አንድሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ዋጋ የሚያወጡ ብዛታቸው 25 የሆኑ ኮምፒዩተሮችን አበርክቷል።
ከዚህም በተጨማሪ የኤጀርሳ ጎሮ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ አናየአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የከርሰ ምድር የውሃ ቁፋሮ ፕሮጀክት ለማከናወን ባንኩ በጀት የመደበ ሲሆን የፕሮጀክቱማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይም በዛሬው እለት ተቀምጧል።

#fastmereja I በግል ባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ በመሆን በአምስት ቅርንጫፎች ስራ የጀመረው አዋሽ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሰ ጎሮ ከተማ 1000ኛ ቅርንጫፉን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራውን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና እንግዶች በተገኙበት በይፋ አስመርቋል።
አዋሽ ባንክ በመላ አገሪቱ ቅርንጫፎቹን በማስፋፋት ህብረተሰቡ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችንበአቅራቢያው እንዲያገኝ በማስቻል በአሁን ወቅት የደንበኞቹን ብዛት ከ16.3 ሚሊዮን በላይ አድርሷል፡፡
በተጨማሪም ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሕብረተሰቡ የኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው የበኩሉን አስተዋፅኦ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡
ባንኩ ከመደኛው የባንክ አገልግሎት ሰጪ ቅርንጫፎች በተጨማሪ ደንበኞችን ማዕከል ባደረጉ ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎትና በዲጂታል ቅርንጫፎች (e-Branch) በመታገዝ ዘመኑን የዋጁ ቀልጣፋ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።
አዋሽ ባንክ የጃርሶ ቅርንጫፍን ከመክፈት በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሀገር ብዙ ውለታ የዋሉ የሀገር ባለውለታዎች ላፈራው ለጃርሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግምታቸው በብር አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ዋጋ የሚያወጡ ብዛታቸው 25 የሆኑ ኮምፒዩተሮችን አበርክቷል።
ከዚህም በተጨማሪ የኤጀርሳ ጎሮ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ አና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የከርሰ ምድር የውሃ ቁፋሮ ፕሮጀክት ለማከናወን ባንኩ በጀት የመደበ ሲሆን የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይም በዛሬው እለት ተቀምጧል።

“ሸንተም ሹቢሳ”- ትዝተኛው አንበሳ
------
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
-----------
#ethiopia | ከአንጋፋ አርቲስቶቻችን መካከል አንዱ ሙሐመድ ኢብራሂም ወዳይ ነው፡፡ ሆኖም ሰውዬውን በዚህ ስም የሚያውቀው ሰው ብዙም አይደለም፡፡ እኔም ይህንን ስም የጠቀስኩት እናትና አባቱ ያወጡለት መጠሪያው መሆኑን ልነግራችሁ በመፈለጌ ነው እንጂ እናንተ በምታውቁት ስም “ሸንተም ሹቢሳ” ብዬ ልጠራው እችል ነበር፡፡
አዎን! ሸንተም ሹቢሳ አንጋፋ አርቲስት ነው፡፡ ይህ ኮከብ የተወለደው በድሬ ዳዋ ከተማ ነው፡፡ የወጣትነት ዕድሜውንም እዚያው ነው ያሳለፈው፡፡ ቀልቡ በሙዚቃ የተሳበው ገና ወጣት ሳለ በ1940ዎቹ ነው።
የአፍረን ቀሎ ቡድን አንጋፋ አባልም ነበር፡፡ ሸንተም ሹቢሳ ገጣሚ፣ ዜማ ቀማሪና የስነ-ቃል ሊቅም ነው፡፡ አርቲስት ሸንተም ከሌሎች አርቲስቶች የሚለየው ከዘፈኖቹ መካከል ለሚበዙት ዜማና ግጥም የደረሰው እርሱ ራሱ በመሆኑ ነው፡፡ ሌሎች ዘፋኞችም የርሱን ዘፈኖች እየወሰዱ ተጫውተዋቸዋል፡፡
ለምሳሌ ሐመልማል አባተ የሸንተምን ዘፈኖች በመዝፈን ትታወቃለች፡፡ ከነርሱም መካከል በጣም ዝነኛው “ኪያ ኪያ” የተሰኘው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ “ቦና ሀረርጌ” የተሰኘው ነው፡፡ እስቲ “ቦና ሀረርጌ”ን ላስታውሳችሁ (ዘፈኑን ሸንተም የተወጫተው “ቦንቱ ሀረርጌ” በማለት ነበር፤ በመሆኑም “ቦንቱ ሀረርጌ” ወደሚለው ቀይሬዋለሁ)፡፡
Gamnomni khee ajabaa
Arjoomni khee jaalalaa
Miidhagni keetis daran dhaabbatni khee waatola
Khabajaa fi arjoomummaa hundaatu sirrati wal-gaha
----
Miidhagni kee honga hinqabu
Boontuun Harargee naaf lubbuu
Bareedni kee hammanaa hammasi
Je’ee himuu hindandayu
----
በአማርኛ ለመፍታት ብንሞክረው እንዲህ ሊሆን ይችላል (ቃል በቃል አልተረጎምኩትም)፡፡
አርቆ ማሰብሽ አጃዒብ ነው፤ ችሮታሽም ፍቅር ነው
ውበትሽ ከዚያም ይበልጣል፣ ቁመናሽማ ልዩ ነው
ክብርና ለጋስነት ሁሌ ባንቺ ላይ ነው የሚሰባሰበው፡፡
---
ውበትሽ እንከን የለውም
የሀረርጌ ጉብል ነፍሴ ናት
ቁንጅናሽ እንዲያ ነው እንዲህ ነው
ብሎ መናገር ለምላሴ ተሳናት
---
በ1960 ገደማ ሸንተም ሹቢሳ ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተሰደደ፡፡ በኋላም ከጓደኞቹ ጋር የኃይለ ሥላሴን መንግሥት በትጥቅ ትግል የመጣል እቅድ ወጥኖ በሰሜን ሶማሊያ በኩል ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ላይ ሳለ በሶማሊያ ወታደሮች ተያዘ፡፡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ዚያድ ባሬ በነበረው የመስፋፋት ምኞት የሀረርጌ ኦሮሞ “ሶማሌ አቦ” ነው በማለት ሲያካሄደው የነበረውን ፕሮፓጋንዳ እንዲቀበሉና በሶማሊያ ስም እንዲታገሉ ጠየቃቸው፡፡ ሸንተም ሹቢሳ እና ጓደኞቹ ግን ተቃውሞአቸውን ፊት ለፊት ገለጹለት፡፡ በዚህም ምክንያት ሸንተምና ጓደኞቹ ለአምስት ዓመታት በስመ-መጥፎው የማንዼራ እስር ቤት ታስረዋል (ይህ እስር ቤት በአሁኑ የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ውስጥ ነው የሚገኘው)፡፡
ሸንተም ሹቢሳ ከእስር ከወጣ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ የዚያድ ባሬን ፕሮፓጋንዳ “ገዋን ሂንዸለቲን” በተሰኘው ዘፈኑ አምርሮ ተችቶታል፡፡ ይሁንና በሀገር ቤትም በሰላም ለመኖር አልታደለም፡፡ የደርግ የአፈና አገዛዝ የፈጠራ ስራውን በነጻነት እንዲሰራ ስላልፈቀደለት በቅድሚያ ወደ ጅቡቲ ተሰደደ፡፡ በ1980ዎቹ ደግሞ ወደ አውስትራሊያ ተሻገረ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሀገረ አውስትራሊያ ነው የሚኖረው።
------
ከሸንተም ሹቢሳ ዘፈኖች መካከል ዘወትር የማልረሳው አንድ ዘፈን አለ፡፡ ይህ ዘፈን በዜማና ግጥሙ ውህደት በጣም ውብ የሚባል ነው፡፡ እስቲ ግጥሙን አንዴ ልጻፍላችሁ!
Naaf si uume siif na uume nu lachuu wal-duraa
Hamdi gooytaa nu ciqqaawe Rabbi foon tokkorraa
-----
Ani aaree dallansuudhaan yoon dufee gama khee
Kokofleetin of wallaala agarraan fuula khee
-----
Ani si qofan jiruu tiyyaaf filadhe
Ani simalee ani simalee
Ani simalee je’ee durin khakhade
---
የዚህ ማራኪ ጣዕመ ዜማ ደራሲ በሸንተም ሹቢሳ ራሱ፡፡ ትርጉሙም እንዲህ ነው፡፡
---
ለኔ ነው የፈጠረሽ ላንቺው ነው የፈጠረኝ
ሁለታችንም አንድ አምሳያ፡፡
ካንድ ስጋ ቆርሶ የሰራን አንድዬ ይመስገን
የሌለው እኩያ፡፡
---
በጣም ተናድጄ ወዳንቺ ብመጣ መልኬን አጠልሽቼ
ወዲያው ስቄ እረሳዋለሁ ፊትሽን አይቼ
---
አንቺን ብቻ ነው ለህይወቴ የመረጥኩት
ድሮ ነው “ካንቺ በቀር” ካላንቺ በቀር
ብዬ የማልኩት፡፡
---
ይህንን ዜማ በጣም ነው የምወደው። በጣም ነው የማስታውሰው። ለለምን መሰላችሁ? የልጅነት ትዝታ አለኝ፡፡ የደጉ ዘመን ማስታወሻ!!
የከተማችን (ገለምሶ) ዋነኛ የገበያ ቀን ማክሰኞ ነው፡፡ በዚህ ቀን በመላው የሀብሮ አውራጃ የሚኖሩ ገበያተኞች ለግብይት ይመጣሉ፡፡ እቃ የሚሸጠው፣ ቡና የሚገዛው፣ ከብት የሚሸጠው ወዘተ.. ሁሉም ይመጣል፡፡ ከዚህ ለየት የሚሉ ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡ የስፌት መኪናቸውን በመኪና አስጭነው የሚመጡ! እነዚህ ልብስ ሰፊዎች የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑ ሌሎች ልብስ ሰፊዎች የሚለዩት ለዚያች አንድ ቀን ብቻ ወደ ገለምሶ የሚመጡ በመሆናቸው ነው፡፡ በማክሰኞ ቀን በጠዋቱ ላይ የስፌት መኪናቸውን አስጭነው ከች ይላሉ፡፡ ከገጠር አካባቢዎች የሚመጡት ወገኖቻችንን ልብሶች ሲሰፉ ይውላሉ፡፡ በአስራ ሁለት ሰዓት ሰዓት ገደማ ያገኙትን ሲሳይ ይቋጥሩና ወደ መጡበት ይመለሳሉ፡፡
ከነዚያ ልብስ ሰፊዎች አንዱ “አደሜ” ይባላል፡፡ አደሜ ወደ ገለምሶ የሚመጣው ከመቻራ ከተማ ነው፡፡ ጧት የስፌት መኪናውን ያስጭንና ከች ይላል፡፡ በከተማችን መሀል ላይ ከሚገኘው የአቶ ማማ ዩሱፌ መደብር ስር ገበያተኞችን ይጠብቃል፡፡ ገበያተኞቹ ሲመጡለት የተለያዩ ብትን ጨርቆችን ይቀበላቸውና ሲሰፋላቸው ይውላል፡፡ ምሽት ላይ ስራውን አጠናቅቆ ወደ መቻራ ይመለሳል፡፡
ታዲያ አደሜ ልብሱን ሲሰፋ በአፉ ዝም አይልም፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲዘፍን ነው የሚውለው፡፡ ዘፈኑ ደግሞ አንድ ብቻ ነው፡፡ እርሱኑ ነው የሚደጋግመው፡፡ ደግሞም በከፍተኛ ተመስጦ እየጮኸ ነው የሚዘፍነው፡፡ ሆኖም እኛ ታዳጊዎቹ የዘፈኑን ግጥም ስለማናውቀው “ወጀላቴ….ወጀላቴ…” የሚል ቃል የሚደጋግም ይመስለን ነበር፡፡ በመሆኑም “ወጀላቴ” የሚል ቅጽል አወጣንለት፡፡
በዚያ ወርቃማ ዘመናችን ማክሰኞ ዕለት በጣም ነበር የሚናፍቀን፡፡ ማክሰኞ እንዲናፍቀን ከሚያደርጉት ምክንያቶችም አንዱ ማራኪው የአደሜ “ወጀላቴ” ጨዋታ ነው፡፡ እናም በማክሰኞ ዕለት ከእኩለ ቀን በኋላ የአንድ ሰፈር ልጆች ተሳበስበን ወደ ማማ ዩሱፌ መደብር መሄድ የዘወትር ተግባራችን ነበር፡፡ በመጀመሪያው ላይ የአደሜን ዘፈን ከመስማት በስተቀር ሌላ ተንኮል አልነበረብንም፡፡ በሂደት ግን ተንኮል ለመድን፡፡ ከአደሜ ፊት እንቆምና ከፍ ባለ ድምጽ
“ወጀላቴ… ወጀላቴ…
ወጀላን… ወለጃቴ…
አለለ ለላ!…አለለ..ለላ”
እያልን እንዘፍናለን፡፡ አደሜ ይናደድና ስፌቱን ትቶ እኛን ያባርራል፡፡ ከዚያም የስፌት መኪናው ወደ ተቀመጠበት ይመለሳል፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን እንደገና ተሰባስበን እንመጣና ከፊቱ ቆመን “ወጀላቴ… ወጀላቴ…” እያልን እንዘፍናለን፡፡ አደሜም እንደፈረደበት ከመቀመጫው ተነስቶ ያባርረናል፡፡ እንዲህ እያደረግን ቀኑን ሙሉ በንዴት እንዲቃጠል እናደርገዋለን (አላህ ይቅር ይበለን መቼስ!… ልጅነት የማያደርገው ነገር የለም!)፡፡
በኋላ ጎረመስኩ፡፡ በ1989 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆንኩ፡፡ በዚያው ዓመት ሻፊ አብዱላሂ በዳሶ የሚባል አማቻችን (የአክስቴ ባል) ከሳዑዲ ዐረቢያ መጣ፡፡ እናም አንድ ቀን ከርሱ ጋር ቁጭ ብለን ሳለ ያንን የአደሜን ዘፈን ከነሙሉ ግጥሙ ለቀቀው፡፡ “አጃዒብ!” ብዬ አደመጥኩት፡፡ “ይህ አሁን የዘፈንከው የእውነት ዘፈን ነው? ወይንስ አንተ ራስህ ፈጥረኸው ነው?” ብዬ ጠየቅኩት፡፡ የሸንተም ሹቢሳ ዘፈን መሆኑን ነገረኝና ሙሉ ግጥሙን አስጨበጠኝ፡፡ በዚያች ቅጽበት አደሜ ትውስ አለኝ፡፡ ልጅነታችን በከንቱ እንደሸወደን ተገለጸልኝ፡፡
አንዳንዴ ትንንሽ ነገሮች ያስገርሟችኋል አይደል? እኔን ካስገረሙኝ ትንሽዬ ነገሮች መካከል አንዱ ያ አደሜን “እንደውክበት” የነበረው የልጅነት ጨዋታችን ነው፡፡ ለኛ የአደሜ የግል ፈጠራ ይመስለን የነበረው ዘፈን የታላቅ ሰው ውድ ስራ በመሆኑ በጣም ነበር የተደነቅኩት፡፡ ሸንተም ሹቢሳን ከልጅነቴ ጀምሮ ባውቀውም ሻፊ እስኪያስረዳኝ ድረስ ያ ዘፈን የአደሜ የግል ጨዋታ ይመስለኝ ነበር፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ቀመር ዩሱፍ ዘፈኑን ባማረ ሁኔታ ተጫውቶት ሰማሁት፡፡ በ1997 ደግሞ ሸንተም ሹቢሳ ራሱ በድጋሚ ተጫወተው፡፡
እንግዲህ ይህንን የልጅነት ትዝታ ጥሎብኝ ያለፈ ስራ የሰራልን ሸንተም ሹቢሳ ነው፡፡ ሸንተም ሹቢሳን ያስገኘችው ደግሞ ውዲቷ ድሬ ዳዋ ናት፡፡ ከዋክብት መፍጠር የማያልቅባት ቀሽቲ ከተማ!
----
አፈንዲ ሙተቂ
ኡመተ ፈናን ኡመተ ቀሽቲ ዲሬዳዋ ከተሰኘው መጽሐፌ የተወሰደ

ጋስትሪክ አሲድ ብሎ የቅጽል ስም አውጥቶ መቀለጃ አደረገኝ በሚል የአጎቱን ልጅ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት አመዲን ቃሲም ሙሜ እና በኸር ሙክታር ሙሜ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ ገራ ወዳጆ የተባለ ስፍራ የተወለዱና እድሜያቸው በሃያዎቹ አጋማሽ የሚገኙ የወንድማማች ልጆች ናቸው።
ሁለቱ ወጣቶች ከስጋ ዝምድና ባሻገር በአንድ አካባቢ በማደጋቸው እና የእድሜ እኩያዎች በመሆናቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱና ሲመጡም ሆነ ሲጫወቱ አብረው እንደነበረ ተነግሯል። በሁለቱ ወጣቶች ጣልቃ የሚገባ ሰው ሳይኖር የወጣትነት እድሜ ላይ ሲደርሱ አመዲን ቃሲም የሚያናድደው እና የሚያበሽቀው ድርጊቶች ሲፈፅም እሱም በንዴት ድርጊትህ ጨጓራዬን ልጦ ለጋስትሪክ አሲድ ዳረገኝ እንዳለውና ከዚያን ግዜ ጀምሮ በአካባቢ ሰዎች ጋስትሪክ የሚል ቅፅል ስም ለአህመዲን እንደተሰጠው ተገልጿል ።
ሀምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ላይ አመዲን ቃሲም ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር እየተጫወተ አንዱ ጋስትሪክ ብሎ በቅፅል ስሙ ሲጠራው በንዴት ከመሃላቸው ተነስቶ እንደወጣ ነው የተነገረው። አህመዲን በንዴት ከጓደኞቹ መሃል በመውጣት በቀጥታ ወደ አጎቱ ቤት በመሄድ የአጎቱን ልጅ ከብት ወድቆ ስለተሰበረ እናንሳው በማለት እንዲያግዘው ጠይቆት ተያይዘው ወደጫካ እንደሄደ ተነግሯል።
ጫካ ውስጥ የደበቀውን ሜንጫ የተባለ ሰዎች ለተለያዩ ስራ የሚጠቀሙበት ስለታም ብረት በማውጣት አንተ ባወጣህልኝ ቅፅል ስም ሰው ሁሉ ያንጓጥጠኛል በማለት በስለታሙ ሜንጫው ሰባት የተለያዩ ሰውነት ክፍሎቹ ላይ በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጎል። አህመዲን ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ የተሸሸገ ሲሆን ጫካ ውስጥ የወደቀ የሰው አስክሬን የተመለከቱ የአካባቢ ሰዎች ጉዳዩን ለፖሊስ በመጠቆማቸው ፖሊስ ወዲያው በስፍራው በመድረስ የሟች አስክሬንን በማንሳት ወደ ሆስፒታል ልኳል።
የድርጊቱ ፈፃሚ እና ከቤት ጠርቶት የሄደው የአጎቱ ልጅ መሆኑ ከቤተሰብ በተሰጠ መረጃ መሰረት በክትትል ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር ይውላል። ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን ሲያጣራ ተከሳሽ የአጎቱን ልጅ የገደለው ጋስትሪክ የሚለው ቅፅል ስም አቃጣይ የሚል ስያሜ ስላሰጠው በዚያ ቂም ይዞ ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ ወንጀል የፈፀመበትን ስለታም ሜንጫ ብረት በማስረጃነት ከሸሸገበት ቦታ አውጥቶ ለፖሊስ ያስረክባል።
ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን ሙሉ ማስረጃ አጠናክሮ ለአቃቢ ህግ የላከ ሲሆን አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ይመሰርታል። በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አህመዲን ቃሲም ሰው ለመግደል አስቦ፣ አቅዶ እና ተዘጋጅቶ ድምፅ አልባ በሆነ ስለታም መሳሪያ በአሰቃቂ ሁኔታ የአጐቱን ልጅ መግደሉ ጨካኝ፣ ነውረኛ እና አደገኛ መሆኑን የሚያመለክት በመሆኑ በ22 ዓመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።

10 months ago
ዓመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል በዓልን ለማክበር የሚያስችል የፀጥታ ግብረ ሃይል ተቋቋመ
#ethiopia | በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ አቡነ ሰላማ ቀበሌ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የቁልቢ ገብርኤል ክብረ በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የተቀናጀ ጥምር ግብረሀይል መቋቋሙን ፖሊስ አስታወቀ።የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ ረዳት ኮሚሽነር ናስር መሀመድ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረውን ዓመታዊ የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ ለማክበር ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።
ጥምር የጋራ ግብረ ሀይሉ ከሀገር ፣ከፌደራል ፣ከኦሮሚያ፣ ከሀረሪ፣ ከድሬደዋ ፖሊስ፣ ከሀገር መከላከያ፣ ከብሔራዊ ደህንነት እና መረጃ አገልግሎት የተውጣጣ መሆኑን ኮሚሽነሩ ለብስራት ሬዲዮ ተናግርዋል።የበዓሉ አከባበር በተመለከተ በተዘጋጀው የጸጥታ እቅድ ላይ ውይይት ተደርጎ ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቶች መጠናነቃቸው ገልፀዋል።
በበዓሉ ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት እና የማጭበርበር ድርጊቶችን በፈጣን ችሎት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በአቃቢ ህግ እና በፍርድ ቤት በኩልም ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ከበአሉ ቀደም ብሎ ወደ ስፍራው በመሄድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተገልጿል።ወደ በአሉ ስፍራ የሚጓዙ የተሽከርካሪ ፍሰቱን ሰላማዊ ለማድረግ ከፍተኛ ጠመዝማዛና ቁልቁለታም ስፍራዎች ላይ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የትራፊክ ፖሊሶች ተመድበው እንደሚሰሩ ተነግሯል።
አሽከርካሪዎች የአካባቢውን መልካ ምድር ተረድተው በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ ረዳት ኮሚሽነር ናስር መሀመድ ጨምረው ለብስራት ገልፀዋል።

Comments