Logo
FIDEL POST NEWS
በቺሊ የምትኖር እናት ከ45 ዓመታት በኋላ ከተሰረቁባት መንትያ ልጆቿ ጋር ተገናኘች

የሲኤንኤን ዘገባ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ በ1979 የ10 ወር እድሜያቸው የሆኑ
መንትያ ሴት ልጆቿን ሶቶ የተባለችው. እናት ክልኒክ ወስዳቸው ማሳደግ አትችይም ተብላ ልጆቿ ተሰርቀው በማደጎ ለማደግ ጣልያን ተወስደው ነበር።

ባለፈው ዓመት መጋቢት ላይ የአንደኛዋ መንትያ ሴት ወንድ ልጅ ዲኤንኤ ምርመራ አድርጎ አያቱን አገኛት።

ዴል ሪዮ እንደተናገረው፣ ሶቶን በፌስቡክ ለማግኘት ሞከረ፣ ከ20 ደቂቃ ሙከራ በኋላም የልጅ ልጆቹ እርስ በርስ መነጋገር ጀመሩ።

ሶቶ ሴት ልጆቿን መልሳ የማግኘት ተስፋ ፈጽሞ አልተወችም ነበር። ነገር ግን እነርሱን መልሳ ለማግኘት 45 ዓመታት እንደሚፈጅባት አላወቀችም ነበር። ጷግሜ 4 ሁለቱ ልጆች ከጣሊያን ወደ ቺሊ በረሩ።

በእናትና በሁለት ሴት ልጆች መካከል በእንባ በተሞላው የመገናኘት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ ሶቶ ልጆቹን አቅፋ "እናታቹ ሁልጊዜም ትፈልጋችሁ ነበር" አለች።
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.