እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏
#ዕንቍ ዕጣ ወጣሽልኝ
የጥበብ ቤት፣ በክርስቶስ ደም የተመሰረተች፣ በሐዋርያት ትምህርት የጸናችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ምጡቅ የሆነውን የዘመን ቀመር ፈጥራ ለዓለም አስረክባለች፡፡ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት በዓለማችን ልዩና ጥንታዊ ከሚባሉት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ መስከረም 1 የአዲስ ዘመን ብስራት የብሩህ ተስፋ መጀመሪያ ነው፡፡ እለቱ እንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ ይጠራል፡፡ እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ መነሻው ኖኅና ልጆቹ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሰማዩ በደመና በመክበዱ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንም ይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፣ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችና በዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተ ብርሃን ጥንተ ዓመት ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል።
ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፣ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕት ይሠውበት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት ካቀረቡ በኋላ እርስ በርስም የአበባ ስጦታ በመለዋወጥ ነበር። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነተኛ መልካም ምኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። በሌላ በኩል ዕንቍጣጣሽ ማለት ተንቈጠቈጠ፣ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል የተወሰደ ምድር በአበባ አጌጠች፣ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ፣ ሰማይን በከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው፡፡ ሁለተኛም ጥንታዊያን አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና “ዕንቍ ዕጣ ወጣሽልኝ” ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸው መታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል።
በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቆሞ ምድር ጸንታ፣ አበባ ቋጥራ፣ ፍሬ ለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። የኖኅ መርከብ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ በአራራት ተራራ አናት ላይ ዐርፋለች። ከዘመን ብዛት በኋላ «ቀ» ወደ «ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፣ ወይም መርከቧ ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩ ስያሜ ነው። ዐውደ ዓመት መባሉም፣ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታት ኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል።
ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፣ የደቂቃ፣ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ 365ኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ስለዚህም ዕለቲቱ ዙሪያ፣ ክብ መግጠሚያ ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ የምንተላለፍባት ናት ማለት ነው። ዕለት አዕዋዲት፣ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላ ትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺ ቀን ዕለተ ሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለችና። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎ የሚመጣው ቀን የዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖች በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 year ago