ግብፅ ክስ መሠረተች‼️
በኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የደስታና የፌሽታ ቀን ግብፅ ለተመድ ፀጥታው ምክር ቤት የክስ ደብዳቤ ይዛ ሄዳለች።
ደብዳቤው ምንም የተለየ ነገር የሌለው ሲሆን " ግድቡ ለብቻ በተወሰደ እርምጃ የተሰራና ዓለም አቀፍ ህጉን የጣሰ ነው " የሚል የተለመደ ክሷን የያዘ ነው።
" የግድቡ ምርቃት ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የፈፀመቻቸው ጥሰቶች ላይ የተጨመረ አዲስ ጥሰት ነው " የሚል አስቅኝ ክስም አቅርባለች።
" እኛ እና ሱዳንን የመኖር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ተግባርን አልቀበልም። እራሴን አቅቤ ተመድን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመስራት ስሞክር ቆይቻለሁ በዲፕሎማሲ ላይ መተማመን የመኖር ስጋቴን ለመከላከል አለመቻል አይደለም " የሚል የተለመደ ፉከራዋን አሰምታለች።
" ኢትዮጵያ በብቸኝነት የጋራ የውሃ አካላትን እንድታስተዳድር አልፈቅድም ጥቅሜን ለማስጠበቅ በዓለም አቀፍ ህግ ስር ያሉ ሁሉንም እርምጃዎች እወስዳለሁ " ስትልም ሌላ ፉከራ አሰምታለች።
ግብፅ ከግድቡ መጀመር አንስቶ ባለፉት 14 ዓመታት ተመሳሳይ ክስ ስታሰማና ስትፎክር ነው የኖረችው ነገር ግን ግድቡ ተጠናቆ እንዳይመረቅ ማድረግ አልቻለችም። ሀገሪቱ በይፋ በአደባባይ ግድቡ ዳር እንዳይደርስ ስትሰራ ኖራለች ግን ምንም አላመጣችም።
ኢትዮጵያ ግድቡ ማንንም እንደማይጎዳ ስትገልፅ ቆይታለች።
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግድቡ ለጎረቤቶችም ሆነ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በረከት እንደሆነ አንድም ቀን ኢትዮጵያ ሌሎችን ለመጉዳት አስባ እንደማታውቅ አስረግጠው ተናግረዋል።
በግድቡ ስራ የተሳተፈው የዊ ቢዩልድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒትሮ ሳሊኒ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሞልቶ በሚፈስበት ጊዜ የአስዋን ግድብ ውሃ አለመቀነሱ ሲወሩ የነበሩ ወሬዎች ሁሉ ውሸት መሆናቸውን ያሳየ እንደሆነ ዛሬ በምርቃቱ ላይ ተናግረዋል።
seledadotio

1 year ago