Logo
Getu Temesgen
የክብር ካባ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተበረከተ
#ethiooia | መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ያሰናዳው አምስተኛ ዙር የስነ-ጽሁፍ ምሽት ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ቃሊቲ በሚገኘው ካፍደም ሲኒማ ቤት የተካሄደ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በመሸለም የክብር ካባ አልብሷቸዋል።

መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነ-ጥበባዊ ፋይዳ ለመስጠት ከመንግስት እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በተለይ በኪነ-ጥበቡ መስክ ለሀገራችን እና ለወገኖቻችን ታላቅ ስራ የሰሩ ባለሙያዎችን ሲዘክር ቆይቷል።

በዛሬው እለት በተከናወነው ለአምስተኛ ጊዜ በተሰናዳው የኪነጥበብ መርሐግብር ላይ

🙏 ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ
🙏 ጸሐፌ ተውኔቱና ገጣሚው ጋሽ አያልነህ ሙላቱ
🙏 ዶክተር ተሻለ አሰፋ (ረ/ኘ)
🙏 አርቲስት ራሄል ተሾመ

በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ላበረከቱት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተግባር የክብር ካባ እና የእውቅና
ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

በሌላ በኩል
🙏 ወይዘሮ አንጋቱ ኃይሌ በኢንቨስትመንት ዘርፍ
🙏 አርቲስት ግርማ ተሾመ በኪነጥበብ ዘርፍ
🙏 አትሌት ዮሐንስ ቢፋ (መኩ)በስፖርት ልማት ዘርፍ
🙏 ለአቃቂ ልጆች ህብረት በበጎ አድራጎት ዘርፍ

በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ ላከናወኑ ተቋማት እና ግለሰቦች የክብር ካባ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገው የኪነጥበብ እና የእውቅና መርሐግብር ላይ በርካታ አርቲስቶች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ኮሜዲያኖችና በሀገራችን ታዋቂ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪዎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.