9 months ago
ወንድሜን ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅን ታዘብኩት !!!
#ethiooia | አሁን ካለሁበት ዉጥረት አንፃር ሶሻል ሚዲያ ላይም ሆነ የፕሮግራም አዘጋጅነቴን ከተዉኩት ሁለት ዓመት ሞላኝ።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እነ ግብፅን አሳብዶ የሚይዙ የሚጨብጡትን ባሳጣቸዉ ጊዜ "የዐረቡ ዓለም ሚዲያ ስለ ህዳሴ ግድባችን እና ስለ ኢትዮጵያ ምን ይላሉ" የሚለዉን ወቅታዊና አሳሳቢ ርእሰ ጉዳይ በስፋት ለመዳሰስ እንዲቻልና መንግስትም ሆነ ህዝብ በዚህ ዙሪያ አስፈላጊዉን መረጃ ያገኝ ዘንድ ምን ይደረግ በሚለዉ ዙሪያ እኔና ወንድሜ ዶር ኢብራሒም ሙሉ ሸዋ አስበን ተጨንቀን አንድ ፕሮጄክት ይዘን ወደ አዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ሔድን።
ከዛም በጊዜዉ የአዋሽ 90.7 ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረዉ አቶ በሽር በሐሳቡ ከተስማማ በኋላ የፕሮግራሙን ስያሜ እንድናመጣና ፕሮግራሙ እንዲጀመር ታዘዘ።
ከዛም አዉጥቼ አዉርጄ የፕሮግራሙ ስያሜ "ከአባይ ጓዳ" ቢሆን የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ በኋላ ዶር ኢብራሒምን አሳየሁት በጣም ወደደዉ እንዲሁም ሌሎች ያማከርኳቸዉ ወንድሞችም በስያሜዉ ተደመሙበት።
በወቅቱ በአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም የፕሮግራም ሓላፊ የነበረዉ ጋዜጠኛ በቀለ አመነ ስያሜዉንም ፐሮፖዛሉንም እጅጉን በመዉደዱ ፕሮግራሙም እንዲጀመር ተደረገ። (ልብ በሉ እዚህ ላይ ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ የለም)
ከአባይ ጓዳን ለማዘጋጀት አሁን ያለነዉ እኔና ዶክተር ኢብራሒም ሙሉሸዋ ነን።
ወንድሜ ዶር ኢብራሒም ታሪካዊ ትንታኔዎችን በመስጠት እኔ ደግሞ በዐረብኛ ስለ ህዳሴዉ እና በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ የተፃፉትን መረጃዎች በማምጣት ፕሮግራሙን አሳምረን በአድማጭ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ አድርገን አስቀጠልነዉ። (ልብ በሉ አሁንም ወንድሜ ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ የለም)
ከዛ በኋላ ወንድሜ ዶር ኢብራሒም ሙሉሸዋ በራሱ ጉዳይ ቢዚ እየሆነ ሲመጣ ፕሮግራሙን ብቻዬን በማዘጋጀት እንግዳም እየጋበዝኩ በብቃት አስቀጠልኩት።
ከዛ በኋላ ነዉ እንግዲህ ጋዜጠኛ በቀለ አመነ ስራዉን ሲለቅ ወንድሜ ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ እሱን ተክቶ ወደ አዋሽ 90.7 የመጣዉ ከዛም "ከአባይ ጓዳ" ስያሜዉን እኔ ባመጣሁት መሰረት እንዲቀጥል ሆኖ እሱም እንደአዘጋጅ አብሮኝ እንዲቀጥል የተደረገዉ።
በእርግጥ ከጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ ጋርም ቢሆን እጅግ በጣም ያማሩ ፕሮግራሞችን በመስራት በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፍን ቢሆንም እሱም እንደ ዶር ኢብራሒም ሙሉሸዋ አብሮኝ መቀጠል ስላልቻለ እነሆ አሁንም "ከአባይ ጓዳን" ለብቻዬ በማዘጋጀት ፕሮግራሙ ከዳር እስከ ዳር የተወደደ ፣ የዉሓ ጉዳዮች በሚመለከታቸዉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዘንድም እጅጉን የተወደደ፣ ግብፃዊያን ሳይቀሩ በፍርሓት የሚከታተሉት በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሱዳናዊያን ሳይቀሩ ጣቢያችን ድረስ እየመጡ ድጋፋቸዉን የሚገልፁበት፣ አዋሽ 90.7 በኔ ፕርግራም የተነሳ የተሸለመበት..... ፕሮግራም በመስራት ለትምህርት ወደ ዉጭ እስከወጣሁበት አስከ ጁን 2023 አካባቢ ድረስ ከአባይ ጓዳን በብቃት መርቸዋለሁ ለዚህም በመላዉ ኢትዮጵያ ያሉ አድማጮቼ ምስክር ናቸዉ።
- አሁን ዋናዉ ነገር ወንድሜ ሙሐመድ ሲራጅ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ "መቻል" የሚል መፅሐፍ ለምን ፃፈ ሳይሆን ቢያንስ እዉነቱን ቢናገር ምን ይሆናል ነዉ ጥያቄዬ????
- መረጃዎች በሙሉ የኔ መሆናቸዉን እያወቀ አይን ያወጣ ዉሸት ለምን ይዋሻል ነዉ ጥያቄዬ ???
- ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ ከእኔ ጋር እንጅ ብቻዉን "የአባይ ጓዳ" አዘጋጅ የሆነበት አንድም ጊዜ እንደሌለ ልቦናዉ እያወቀ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሆኖ የነበረዉም ለተወሰነ ጊዜ ከኔ ጋር በጥምረት ይሰራ በነበረበት ጊዜ ብቻ መሆኑን እያወቀ "የአባይ ጓዳ አዘጋጅ" በነበርኩበት ጊዜ ብሎ ለመናገር ያደፋፈረዉ ነገርስ ምንድነዉ???
- ዐረቦች በተለይም ግብፃዊያን ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚጽፉት በዐረብኛ ነዉ የዐረብኛዉ ባለሙያ ደግሞ እኔ እንጅ ወንድሜ ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ አልነበረም ታዲያ ይኸንን ድፍረትስ ከየት አመጣዉ???
- በነገራችን ላይ "ከአባይ ጓዳ" አሁንም በአዋሽ 90.7 በመተላለፍ ላይ ይገኛል አዘጋጁ ጌታሁን አማረ ሲሆን እኔ ለትምህርት ወደ ዉጭ ስሄድ በእኔ እንዲተካ ያደረኩት ስለ ተፋሰስ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ ጂኦግራፊ የተሻለ እዉቀት ስላለዉ ነዉ። (ልብ በሉ አሁንም ወንድሜ ጋዜጠኛ ሙሐመድ ሲራጅ የለም)
- በእርግጥ "መቻል" ን አላየሁትም አላነበብኩትምም በመጽሐፉ የተካተቱት ርእሰ ጉዳዮች ብሎ በራሱ የፌስ ቡክ ገፅና በሌሎች ገፆች ያነሳቸዉ ነጥቦች ግን ሁሉም በእኔ ፕሮግራም የተነሱ መሆናቸዉን ልብ ይሏል።
- ሌላዉ በአዋሽ የትንታኔ ገፅ ላይም ስለ "አፍሪካ ቀንድና አዲሱ ጂኦፕለቲከስ" በሚል ርእስ ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ ወቅታዊ ስትራቴጂካዊ ሐገራዊ የሆኑ ጉዳዮችን ዳስሻለሁ ከነዚህም መካከል "ኢትዮጵያ ያለ ባህር በርና ወደብ መኖር እንደማትችል" አስቀድሜ ጠቁሚያለሁ በፕሮግራሞቼ ላይም ከአድማጮቼ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቸበታለሁ ምናልባት እነኝህንም ነጥቦች የራሱ አስመስሎ አንስቷቸዉ ከሆነ ገርሞ ገርሞ ይገርመኛል።
- እንዳልኳችሁ ያለሁት ዉጭ በመሆኑ"መቻልን" አላየሁትም ግን ቢያንስ ቢያንስ በመጽሐፉ መግቢያ ወይም መዉጫ ላይ ወይም የሆነ ቦታ ላይ እኔን ሳይጠቅሰኝ ቀርቶ ከሆነ ትልቅ ትዝብትን ያተርፋል።
- ለማንኛዉም የ "መቻል" ን ታትሞ መዉጣት እችለዋለሁ ደስ ከሚላቸዉ ወንድሞቹ መካከል አንዱ ነኝ አልቻልህ ያለኝ ግን ነገ ከነገ ወዲያ ሊጋለጡ የሚችሉ ነገሮችን ሽምጥጥ አድርጎ መካዱ ነዉ።
በእርግጥ እኔም ነገ ከነገ ወዲያ በ "መቻል" ሳይሆን " የ _____ሴራ ____. " በሚል መጽሐፍ ብቅ ልል እችላለሁ የኔንም መጽሐፍ በመቻል እንድታነቡልኝ ለማለት ነዉ።
ፅሑፌ ረዝሟል ግን በመቻል አንብቡልኝ
መልካም ጊዜ
ዑመር መኮንን ዑስማን
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
የአረብኛ ቋንቋ መምህርና የህዳሴ ግድብ ተሟጋች
- ለትምህርት ወደ ዉጭ አስከሄደበት ድረስ ማለትም እስከ ጁን 2023 ድረስ በአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም የ ከአባይ ጎዳ አዘጋጅ የነበረ
- እንዲሁም በዚሁ ጣቢያ የሚዲያ ዳሰሳ አዘጋጅ
- በፋና በዋልታ በአዲስ ሚዲያ ኔት ወርክ በየኛ በባላገሩ ቲቪዎች ስለ ህዳሴ ግድብ መረጃ የሰጠ

“በሕይወት እያለሁ የግድቡን መጠናቀቅ የማየት ህልሜ እውን በመሆኑ ደስተኛ ነኝ”
- መሐመድ አልአሩሲ
#ethiooia | በሕይወት እያለሁ የግድቡን መጠናቀቅ የማየት ህልሜ እውን በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ሲሉ መሐመድ አልአሩሲ ተናገሩ።
ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጥብቅና በመቆም በአረብኛ ሲሟገቱ የሚታወቁት እና የምክር ቤት አባል የሆኑት ብሎም የውሀና ኢነርጂ ሚንስቴር አማካሪ መሐመድ አልአሩሲ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የዓባይ ግድብ ተጠናቆ ማየት ትልቁ ሕልማቸው እንደነበር ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች ያልተንበረከከች በተባበረ ክንድ አድዋ ላይ የጥቁሮች ኩራት የሆነውን ደማቅ ድል የተቀዳጀች ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሕዳሴውንም አጠናቅቃ ሪቫን ለመቁረጥ በመዘጋጀቷ ደስተኛ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቁጭት የጀመረችውን የሕዳሴ ግድብ በራሷ ፋይናንስ ምንጭነት ታሪክ በመስራቷ ዳግማዊ የዓድዋ ድል ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሐብቷ እንዳትጠቀም ብዙ ዘመቻዎች ሲደረጉ እንደነበር የገለፁት አቶ መሐመድ፤ በሁሉም መስክ ቁርጠኝነቷን በመሳየት የባንዳዎችን ምኞት ከንቱ ማድረግ እንደቻለች ጠቁመዋል።
የውጪና የውስጥ ጫናን በመቋቋም ግድቡን ለመመረቅ ጥቂት ቀናት የቀሯት ኢትዮጵያ ቀድሞውንም የሌሎች የዓባይ ተፋሰስ አገሮችን ጥቅም የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በይፋ ስትገለፅ መቆየቷን አንስተዋል።
በዚሁ መሰረት የተፋሰሱ ሀገራት ብዥታ እንዲስተካከል የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ስራ እንዲሁም በአረብኛ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ በመሟገትና ገለፃ በማድረግ ለምርቃት መብቃታችን ታላቅ ድል ነው ብለዋል።
የድል ብስራቱን ቀን ለማዬት ትልቅ ጉጉት ነበረኝ ያሉት አቶ መሐመድ፤ በሕይዎት እያለሁ በማየቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ ገልጸዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሳይሰስቱ ግድቡ የእኔ ነው በማለት ያላቸውን አበርክተው የአንድነት አሻራቸውን አሳርፈው ደማቅ ድል ስላሰመዘገቡ ደስታቸው የላቀ መሆኑን በመግለጽ፤ በዚህም ኢትዮጵያ አሸንፋለች ሲሉ ገልጸዋል።
ይህን ደማቅ ድል በባሕር በርም መድገም ግድ ነው ያሉት አቶ መሐመድ፤ እሳቸውም በማንኛውም የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዳይ የማይደራደሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድበን የአገራችንን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የተለመደው አብሮነታችንን ማስቀጠል አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
በዋስሁን ተክሌ #ኢትዮጵያ #ዓባይ #አባይ #ህዳሴ #ግድብ #ግብጽ #መሐመድ_አልአሩሲ

ባለመግባባታችን ባለን አኩሪ ታሪክ ልክ መራመድ አልቻልንም- ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ
ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም (ቶሮንቶ)
#ethiooia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ ተጀምሯል።
መድረኩ በሀይማኖት አባቶች ፀሎት ነው የተጀመረው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ መድረኩን በከፈቱበት ንግግራቸው "እኛ ኢትዮጵያዊያን ታሪክ የማይዘነጋቸው ድሎች ያስመዘገብን ነን" ብለዋል።
ከበርካታ 10 ዓመታት ወዲህ ግን የማንግባባና ግጭት የማያጣን መሆን መታወቂያችን ሆኗል ሲሉም አክለዋል።
በዚህ ምክንያት ካለን አኩሪ ታሪክ አንፃር በሚገባን ልክ ወደ ፊት መራመድ አልቻልንም ሲሉም ተደምጠዋል።
አለመግባባታችን በየጊዜው እየሰፋ አሁንም ድረስ የዘለቀ የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ነን ያሉት ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ፣ ይህ ሁኔታ እንደ ሀገር የመቀጠላችንን ጉዳይ አጠራጣሪ አድርጎታል ሲሉም ገልፀዋል።
አለመግባባቶቻችንን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ ሙከራዎቹ በሀይል አማራጮች ላይ የተወሰኑ ስለነበሩ ከኪሳራ የዘለለ ፋይዳ አልነበራቸውም ብለዋል።
የሀይል አማራጮች አንዱን አሸናፊ፣ ሌላውን ተሸናፊ ከማድረግ የዘለለ ሁሉንም አሸናፊ ማድረግ የማይችሉ ስለሆኑ ዘላቂ መፍትሄ ሳይገኝ እዚህ ደርሰናል ሲሉም አክለዋል።
አሁን ግን ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ የምክክር መንገድ ተጀምሯል፤ ይህንንም ለማሳካት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል ሲሉም ገልፀዋል።
ኮሚሽኑ አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ ያለመግባባት መንስኤ የሆኑ እጅግ መሰረታዊ ጉዳዮችን በህዝባዊ ውይይት በመለየት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
እንደ ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ገለፃ ይህ ሂደት ህብረተሰቡ በሀገሩ ጉዳይ ላይ እንዲወስን ያስቻለ ነው።
ይህንንም ለማጠናከር በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተወካዮቻቸው አማካኝት በምክክሩ እየተሳተፉ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህ ሂደት በርካታ ውጤቶች እየተገኙ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ዳያስፓራው በሀገሩ ጉዳይ የሚወስንበት እድል እንዲያገኝ ኮሚሽኑ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህ በካናዳ እየተካሄደ ያለው መድረክም የዚህ ጥረት አካል መሆኑንም ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ በንግግራቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

የክብር ካባ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተበረከተ
#ethiooia | መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ያሰናዳው አምስተኛ ዙር የስነ-ጽሁፍ ምሽት ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ቃሊቲ በሚገኘው ካፍደም ሲኒማ ቤት የተካሄደ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በመሸለም የክብር ካባ አልብሷቸዋል።
መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነ-ጥበባዊ ፋይዳ ለመስጠት ከመንግስት እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በተለይ በኪነ-ጥበቡ መስክ ለሀገራችን እና ለወገኖቻችን ታላቅ ስራ የሰሩ ባለሙያዎችን ሲዘክር ቆይቷል።
በዛሬው እለት በተከናወነው ለአምስተኛ ጊዜ በተሰናዳው የኪነጥበብ መርሐግብር ላይ
🙏 ጸሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ
🙏 ጸሐፌ ተውኔቱና ገጣሚው ጋሽ አያልነህ ሙላቱ
🙏 ዶክተር ተሻለ አሰፋ (ረ/ኘ)
🙏 አርቲስት ራሄል ተሾመ
በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ላበረከቱት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተግባር የክብር ካባ እና የእውቅና
ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
በሌላ በኩል
🙏 ወይዘሮ አንጋቱ ኃይሌ በኢንቨስትመንት ዘርፍ
🙏 አርቲስት ግርማ ተሾመ በኪነጥበብ ዘርፍ
🙏 አትሌት ዮሐንስ ቢፋ (መኩ)በስፖርት ልማት ዘርፍ
🙏 ለአቃቂ ልጆች ህብረት በበጎ አድራጎት ዘርፍ
በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ ላከናወኑ ተቋማት እና ግለሰቦች የክብር ካባ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
ለአምስተኛ ጊዜ በተደረገው የኪነጥበብ እና የእውቅና መርሐግብር ላይ በርካታ አርቲስቶች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ኮሜዲያኖችና በሀገራችን ታዋቂ እንዲሁም ተጽኖ ፈጣሪዎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል።