Logo
Getu Temesgen
ሞተረኛ ትራንስፖርት ወደ ስራ ገባ
#ethiopia | ሞተረኛ ትራንስፖርት በመዲናዋ በነዳጅ የሚሰሩትን ሞተሮች በኤሌክትሪክ ለመተካት ማሰቡን ገልጿል።

የሞተረኛ ትራንስፖርት የቦርድ ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ንጉሴ ባደረጉት ንግግር፣ የሞተረኛ ትራንስፖርት በአዲስ አበባ የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ሞተሮችን በኤሌክትሪክ ሞተሮች ለመተካት ማቀዱን ገልጸዋል።

ይህ ፕሮጀክት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በንግግራቸው፣ አቶ ሮቤል በ2024 ዓ.ም. በተደረገ ጥናት መሰረት፣ በአዲስ አበባ ብቻ 23 ሺህ 854 የነዳጅ ሞተሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ሞተሮች በዓመት 34 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ይህም 4.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ያስወጣል ሲሉ ገልጸዋል።

በነዳጅ የሚሰሩ ሞተሮችን ወደ ኤሌክትሪክ ሞተር በመቀየር በዓመት
48 ሺህ6 44 ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን መከላከል እንደሚቻልም አብራርተዋል።

ኩባንያው ሞተረኞችን ለመደገፍ፣ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር የኤሌክትሪክ ሞተር መግዣ ዋጋን 50 በመቶ የሚሸፍን የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ ለኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ሞተሮችን ለማቅረብ ከቻይና አጋር ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተደርጓል።

አቶ ሮቤል አክለው እንደተናገሩት የሞተረኛ ትራንስፖርት አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ የሎጅስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

የድርጅቱ ስራዎች በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎች በዝርዝር እንደሚገለጹም አስታውቀዋል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.