Logo
Getu Temesgen
ግብጽ 2 ፡ 0 ኢትዮጵያ
#ethiopia | በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከግብጽ እያደረጉት የሚገኝው ጨዋታ የመጀመርያው 45 ደቂቃ በግብጽ 2 ለ 0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

በካይሮ ስቴዲየም እየተደረገ በሚገኝው ጨዋታ ሙሀመድ ሳላ እና ማርሙሽ ሁለቱንም በፍጹም ቅጣት ምት የግብጽን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

በመጀመርያው 45 በኳስ ቁጥጥሩም ይሁን የግብ ዕድሎችን በመፍጠር የግብፅ ብሔራዊ ቡድን የተሻለ ሆኖ አሳልፏል፡፡

የዋልያዎቹ የተከላካይ ክፍል ስራ በበዛበት የመጀመርያው ግማሽ ግብ ጠባቂው አቡበክር ኑራ ያለቀላቸውን ኳሶች አድኗል፡፡

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.